Asfaw abreha

Description
News
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
ህዳር 2 / 2013 ዓም ጧት …

ህዳር 2 / 2013 ዓም ጧት ላይ እድሪስ ውስጥ እጆቻቸውን የፊጥኝ ታስረው በጥይት የተደበደቡ ሰማዕታት

3 weeks, 2 days ago

ሰማዕታት ሲዘከሩ
(አቶ አማረ ጥሩነህን እንደማሳያ)

በ2009 ዓ.ም አጋማሽ ላይ አቶ አማረ ጥሩነህ አንዳንድ "የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ናችሁ" ተብለው በእስር ሲሰቃዩ የቆዩ ወገኖች እንዲፈቱ በተደረገ ጥረት ታሳሪዎቹ ለተጠየቁት የዋስትና ብር ለሁሉም ብርና የቤታቸውን ካርታ በማስያዝ ወንድሞቻቸውን (ለጊዜውም ቢሆን) ያስፈቱ ሰው ነበሩ።ቀድሞዉኑም በወያኔ ጥርስ ከተነከሰባቸው ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት አቶ አማረ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ለሞት እንደታጩ መረዳታቸውን ለቀርብ ጓደኞቻቸው ይናገሩ ነበር። በየስብሰባውና በየመድረኩ ስማቸው እየተነሳ ይወነጀላሉ - በግምገማ ስም ለሰዓታት እየቆሙ በስድብና በወቀሳ ሰውነታቸው ደክሞና ዝሎ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።
ከእነዚህ የግምገማ መድረኮች መካከል በ2010 ዓ.ም የሆነው ተጠቃሽ ነው።በወቅቱ በጎንደርና አካባቢውም ተመሳሳይ የ"አይደገምም" መድረኮች ይደረጉ የነበረበት ጊዜ ነው።እናም ከሌሎች የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ጋር በመሆን ከህዝብ ፊት የቀረቡት እነ አቶ አማረ ጥሩነህ በአገዛዙ ካድሬዎች አማካኝነት " የአስመላሽ ኮሚቴውን በብር ትደግፋላችሁ .... ለኮሚቴው መረጃ ታቀብላላችሁ ...በየእርሻ ካምፖቻችሁ ወታደራዊ ስልጠና ትሰጣላችሁ " የሚሉ ጠንካራ ውንጀላዎች ቢሰነዘርባቸውም ውንጀላው መሠረት የሌለውና ሀሰት መሆኑን በድፍረት ሞግተዋል።ከጥርጣሬ ውጪ መረጃና ማስረጃ ያልነበራቸው ከሳሾቹ አማራጭ በማጣታቸው ብቻ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲሸኟቸው ቢገደዱም ሰዎቹን ለማጥፋት አመቺ ጊዜንና ቦታን ከመጠበቅ ግን አልቦዘኑም ነበር።

ከሶስት አመታት በኋላ ወያኔ ሲጠብቅ የነበረውን አመቺ ጊዜ አገኘ ።

ከመንግስት ጋር ጦርነት የገቡት የወያኔ ወታደሮች በመጨረሻዎቹ የሽንፈት ቀናቶች ጥቅምት 30 , 2013 ዓ.ም ማይካድራን በደም አበላ አጥበው ከጨረሱ በኋላ አመሻሹ ላይ ወደ ሁመራ በመምጣት በየቤቱ እየዞሩ በቀጠሮ ያቆዩዋቸውን የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ "ሟቾችን" ለቀሟቸው።
ከእነዚህ መካከል አቶ አማረ ጥሩነህ አንዱ ነበሩ። ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ገና ከሻወር እንደወጡ ነበር ወደ ቤታቸው ቅጥር ጊቢ ከገቡ ገዳዮቻቸው ጋር ፊት ለፊት የተያዩት። "ትፈለጋለህ" ብለውም ወሰዷቸው።
ከሁለት ቀናት በኋላ ህዳር 2/ 2013 ዓ.ም ከሁመራ ከተማ 35 ኪሜ ገደማ በምትርቀው "እድሪስ በተባለች ከተማ ዙሪያ ላይ የአቶ አማረ ጥሩነህን ጨምሮ የሌሎቹ "ሟቾች" "አስከሬኖች ተገኙ።
ነብስ ይማር !!
(ዛሬ የአቶ አማረ ጥሩነህ አራተኛ አመት የመታሰቢያና የፍትሃት ስነስርዓትን ከፈፀሙ የቤተሰብ አባላት ጋር ከነበረኝ አጭር ቆይታ በኋላ የተፃፈ )

3 weeks, 3 days ago

ከድራማ ወደ አክሽን

የደብረፂዮን አንጃ የቀን ተቀን ስራዎቼን ከማደናቀፍ አልፎ አሁን ላይ ግልፅ ወደሆነ የመንግስት ግልበጣ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል//

--ከዛሬው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት መግለጫ ላይ የተወሰደ

4 weeks ago
እግረ መንገድ ......

እግረ መንገድ ......
እኔ በበኩሌ አጀንዳ እየሰጠሁ አይደለም።የእግረ መንገድ ወሬዬ ነው።
ምናልባት አጀንዳችሁ ሆኖ ከተናጠሳችሁም ያው እንደፍጥርጥራችሁ።👇
===============+=========

በአፍሪካ ህብረት አወያይነት የወያኔን ህጋዊ ሰውነት በመመለስና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመንግስትና በወያኔ መካከል ይደረጋል የተባለው የሁለትዮሽ ውይይት ለህዳር 2017 ዓ.ም ተቀጥሮ ነበር ። ቀኑ የተቆረጠው ግንቦት ወር ላይ በ2016 ዓ.ም ነው።
ለነገሩ አሁን ወያኔ እርስበርሱ እየተናጠሰ ስለሆነ ይህ ውይይት እውን ይሆናል ብዬ አላምንም።

👉ለማንኛውም ግን ....
የአሜሪካው ምርጫ ተጠናቆ ትራምፕ በተመረጠ ማግስት ውይይቱ እንዲካሄድ በመፈለግ ይሄንን ቀን የመረጠው አካል በእውነቱ ወያኔን ጠንቅቆ የተረዳ ምጡቅ ፖለቲከኛ መሆን አለበት ‼️
😎

4 weeks ago

Kammala 1
&
Kammala 2

😂

1 month ago
ትናንትና ቮድካው ይቺን ገፁ ላይ ለጠፈ።የወያኔ …

ትናንትና ቮድካው ይቺን ገፁ ላይ ለጠፈ።የወያኔ ማቲ ታርቀዋል ብሎ ከበሮ ደለቀ። Ethioforum ከደላቂ ወያኔዎች አንዱ ነው።
መገናኘቱን ተገናኝተዋል ።መሃከል ላይ ያለው ቅቤ ነው ለማስታረቅ የሞከረው። ሳይስማሙ ነው የተለያዩት።
ግንኙነቱን ከጓዶቹ ተደብቆ በምስጢር ያደረገው ደብረፂዮን ስለግንኙነቱ ሲጠየቅ "ውሸት ነው አልተገናኘንም" ብሎ ጓዶቹን ስለካደ ነው ቮድካው ይቺን የለጠፈው - ያው 'ሲያሳጣው' መሆኑ ነው።

1 month ago
Asfaw abreha
1 month ago
DDR 'ን ሲሳለቁበት

DDR 'ን ሲሳለቁበት
👇

ማሳሰቢያ
የDDR ፎርም ሞልታችሁ ስታበቁ በፍቃድም ይሁን ያለፈቃድ ከግቢው የወጣችሁ የጦር ጉዳተኞች በሙሉ እስከ 18/2/2017 ዓ.ም ድረስ ህክምናችሁን በተከታተላችሁባቸው ተቋማት ውስጥ ትገኙ ዘንድ እናሳስባለን

1 month, 1 week ago

እግረ መንገድ ......

መዘክር አባዲ ዘሙ ወያኔንና ገመናዎቿን በተመለከተ የዩቲዩበሮች ተመራጭ የመረጃ ምንጭ ነው።እውነቱን ለመናገር በተለይ በጦርነቱ ወቅት በወያኔ በኩል የነበረውን የቀን ተቀን ኹነት በቅርብ ይከታተል የነበረ ሰው በመሆኑ መረጃዎቹ እንከን የላቸውም ።
ነገር ግን ....
በጦርነቱ ወቅት ወደ ጎንደር ፣ ወደ ባህርዳርና ወደ አስመራ ይተኩስ የነበረውን የወያኔውን የሚሳኤል ክፍል በበላይነት ይመሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል መዘክር አባዲ ዘሙ አንዱ እንደነበረ እነዚህ ዩቲዩበሮች ያውቃሉን ?
የወያኔውን የሚሳኤል አሃዱ በበላይነት ከሚመራው
'ወዲ ፀሃዬ' ቀጥሎ የነበረው ሁነኛ ሰው መዘክር አባዲ ነበር።

(ሃይለ ታደለ (ሃይለ መጋል) በጊዜው ሚሳኤሉን ጭኖ ከቦታ ቦታ ያንቀሳቅስ የነበረውን መኪና ይዘውር የነበረ ሹፌር ነው። ይህ ሹፌር ከወዲ ፀሃዬ ቀጥሎ መመሪያዎችን ይሰጥ የነበረው መዘከር አባዲ እንደነበረ በአንድ ወቅት ለአንድ ሚዲያ መናገሩን አስታውሳለሁ)

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago