Fano Media 24

Description
የፋኖ ሚዲያ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያጋሩት:-

ቴሌግራማችን:-
https://t.me/FanoMedia24
ትዊተራችን:-
https://twitter.com/FanoMedia24?s=35
ግሩፓችን:-
https://t.me/FanoAmahara
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 месяц назад

ጃዋር እንዲህ ብሏል ታራሚዎችን በቀዶ ህክምና በወሰዱበት ቀን ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ማድረግ ጨካኝ እና ኢሰብአዊ ድርጊት ነው።

ሁለቱ ታዋቂ የአማራ መሪዎች የፓርላማ አባል ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው በምትኩ ተፈትተው ለበለጠ እንግልት ሊዳረጉ አይገባም። የእነርሱ ቀጣይ እስራት ምንም አይነት ዓላማ የለውም እና የህብረተሰቡን ፖላራይዜሽን ከማስፋፋት ውጪ ነው።👇🏿👇🏿👇🏿
Sending detainees back to a prison cell on the same day they underwent surgery is cruel and inhumane treatment.

The two prominent Amhara leaders, MP Christian Tadele and Yohannes Buayalew, should be released instead and not subjected to further mistreatment. Their continued incarceration serves no purpose and has only deepened societal polarization. https://x.com/fanomedia27/status/1868610638458827204?s=52

1 месяц назад

#Amhara

#ጎንደር_ቋራ #ሸኸዲ

በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ጠላት የወንዶች አገር ቋራን እይዛለሁ ብሎ በአለፋ እና በሸኸዲ በኩል ሞክሮ በሁለቱም ግንባር ቢመጣም በወንዶቹ የመልስ ምት በመመታቱ ከ450 በላይ ኃይሉን አስደምስሶ ዙ-23 ፥ ኦራሎችን አስቃጥሎ የቡድን መሣሪያዎችን አስረክቦ ፤ ሙት እና ቍስለኛውን በሂሊኮፍተር ጭኖ ባሕርዳር ሆስፒታል ሲያመላልስ ሰነባብቷል! የሚገርመው ደግሞ በግዳጅ የወሰዳቸውን የግል ሹፌሮቹን ሳይቀር ሙሉ ለሙሉ ሁሉንም አስደምስሷል!

ድል ለዐማራ ፋኖ ፤ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ፣ ኮማንዶ ሳሚ ባለዕድል እና ሌሎች የጎንደር አማራ አርበኞች ትችላላችሁ!!

@FanoMedia24

1 месяц назад

የብልጽግናው አፋኝ ቡድን በመዲናዋ

ብልጽግና በአዲስ አበባ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት የተባለ አፋኝ ቡድን ማቋቋሙ ተገለጸ

ብልጽግና በአዲስ አበባ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት በሚል  አፋኝና ገዳይ ቡድን መቋቋሙ ተዘግቧል፡፡ ይህ ኮማንድ ፖስት ተጠሪነቱ ለአዳነች አቤቤ ሲሆን ፣ ከመከላከያ ፣ ከኢንሳ ፣ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ከመረጃና ደህንነት መረብ አገልግሎት እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅርበት እንዲሰራ ተደርጎ የተዋቀረ ነው ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ሊዲያ ግርማ ደግሞ ይህን አፋኝ ቡድን እንድትመራ መደረጉም ነው የተነገረው፡፡
እነ አዳነች በአዲስ አበባ መዋቅሩን መዘርጋቱን ደርሰንበታል ያሉትን የፋኖ ሃይል ለማጽዳት በሚል መጠነ ሲፊ አፈሳና አፈና ለማካሄድ እንቅስቃሴ ጨርሰው ወደ ስራ መግባታቸውም ነው የተነገረው፡፡
ይህን ተከትሎም በሃና ማሪያም ፣ በፉሪና በሌሎች አካባቢዎች እስርና አፈናው ተሰምቷል፡፡
በመዲናዋ መውጪያና መግቢያ በሮች በሙሉ ከፍተኛ የሆነ ፍተሻና ብርበራ እየተካሄደ ነው ሲል የዘገበው አንከር ሚዲያ ነው፡፡ እነ ሽመልስ ከጫካ ያስገቡት የኦነግ ሸኔ ቡድንም በዚህ አፈና ላይ እንደሚሳተፍ ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባና አካባቢው አራት ካምፖች የሰፈረው የሸኔ ታጣቂም በዚህ አፈና ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠው መሆኑም ተሰምቷል፡፡
አንድ የአገዛዙ ክፍለጦርም የከተማ ውጊያ ስለጠና እየወሰደ ነው ተብሏል፡፡ ይህም በአዲስ አበባ የገጠማቸውን ስጋት ለመቋቋም ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ታሕሳስ 06/04/2017 ዓ.ም

@FanoMedia24

1 месяц назад

"በአንድነታችን ጥንካሬ የጠላትን አከርካሪ እንሰብራለን"

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ ለጎንደር ህዝብ ፣ለመላው የአማራ ፋኖ እና ለትግሉ ደጋፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

በጥቃቅን ክፍተቶቻችን ገብተው እንደ አክርማ ሊሰነጣጥቁን የሚፈልጉትን የጠላት ሰይጣናዊ ምኞት ሰብረን ፣የአንድነታችንን ሻማ ስንለኩስ የጠላት ቅስም ተሰብሮ የትግላችን ብርቱ ክንድ እንደ ብረት የጠነከረ እንደ አለት የፀና ይሆናል ።የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ  ያበሰሩንን የአንድነት ብስራት በሰበር ዜና  ስንሰማ ደስታችን ወደር የለሽ ፣ወኔያችን ልብ የሚያሞቅ የምስራች ነው ።

አንድነታችን ብርታታችን፣አብሮነታችን ጌጣችን፣ትብብራችን ጉልበታችን ስለሆነ ጎንደር ላይ የተለኮሰው የአንድነት ሻማ በቅርቡ ሸዋ ላይ እንደሚለኮስ ባለሙሉ ተስፋ ነን። ጠላት በውጊያ ያልተሳካለትን ድል በጥቃቅን ልዩነቶቻችን በተከፈተ ጊዜያዊ መስኮት በመግባት ሰፊ  በር ለመክፈት ቢሞክርም እንደ አማራ አትግደሉን ብለን የጀመርነው ፖለቲካዊ  የትጥቅ ትግል እንደ አማራ አንድ ሆኖ መደራጀት አማራጭ የሌለው ምርጫ በመሆኑ የአንድነት ሻማ መለኮስ ግዴታችንም ህልውናችንም ነው።

አይደለም የጎንደር አንድ መሆን ይቅርና ሸዋ፣ ጎጃም፣ጎንደር እና ወሎ አንድ ሆነን ጠላትን በአንድ የዉጊያ አውድማ የምንወቃበት ታሪካዊ ክስተት በቅርቡ እንደሚሆን አንጠራጠርም። በሸዋ ምድር የምንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እንደ ሸዋ ብቻ ሳይሆን እንደ አማራ አንድ ድርጅት ፈጥሮ ጠላትን መውጫና መግቢያ ለማሳጣት እና አገዛዙን ገርስሶ ለመጣል መጠነ ሰፊ ውይይቶች ፣ፍሬያማ ንግግሮች እየተደረጉ ስለሆነ ጎንደር ላይ የወጣችው የአንድነት ጮራ በቅርቡ ሸዋ ላይም እንደምትወጣ በልበ ሙሉነት በመተማመን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ ለጎንደር ህዝብ፣ ለመላው የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎች በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን!!

ድል ለአማራ ፋኖ !
    ድል ለአማራ ህዝብ!
   ክብር ለተሰውት!
   የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
    ህዳር 30/2017 ዓ.ም

@FanoMedia24

1 месяц назад

ልዩ መረጃ!

ይህ ግለሰብ አሊ አደም ይባላል ከአንድ ዓመት በፊት በሳውዲ ዓርቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚሊተሪ አታሼ ሆኖ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልገሎት የተመደበ ሰው ነው፡፡

ይህ ሰው በኢንሳ የቴክኒካል መረጃ ትንተና ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን በዓባይ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን ወክሎ ከግብፅ አክቲቪስቶች ጋር ሲከራከር፣ ሲሞግት እና ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መረጃዎችን ሲያቀርብ የነበረውን አክቲቪስት ሱሌማን አብደላ ላበረከተው የሀገር ውለታ ኢትዮጵያ ልታመሰግነው ሲገባ አፓርታይዳዊ መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት ተከትሎ ፋሽስቱ መንግስትን በይፋ መቃወም ጀምሮ የነበረ በመሆኑ አክቲቪስቱ ካለው አቅም እና በዓለም አቀፍ የውጭ ሚዲያዎች ካለው ግንኙነትና ተሰሚነት አንጣር የአገዛዙን አምባገነናዊነትና የአብይ መንግስት በአማራን ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጠፋት ወንጀል ለዓለም ሚዲያዎች ያጋልጥብናል በሚል ስጋት ከፍተኛ ክትትል ሲደረግ ነበር።

ይህንንም ስራ እንዲሰራ በአብይ አህመድና በሲሳይ ቶላ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተመርጦ ኃላፊነት የተሰጠው አሊ አደም የሚባል የኦሮሞ ምዕራብ ሀረርጌ መሰላ ተወላጅ የሆነ በአማራ ጠል ትርክት የሰከረና የናወዘ ጽንፈኛ ኦሮሞ ነው፡

አሊ በኢንሳ የመረጃ ትንተና ኃላፊ እያለ ጀምሮ እስማኤልን በሳውዲ መንግስት ወንጀል እንደፈፀመ ተደርጎ እንዲታሰር፣ በታቀደ ሴራ የተቀናጀ ሴትአፕ ተሰርቶ በሐሰት ክስ እንዲታሰር ያስደረገው ይህ ሰው ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ደግሞ ይህ ሰው ጉዳዩን በቅርበት ከሳውዲ መንግስት ጋር እንዲሰራ እና በምንም ምክንያት እንዳይፈታ እንዲሁም ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ የሳውዲን መንግስት በኤምባሲው በኩል እንዲያግባባ በልዩ ሁኔታ ተልዕኮ ተሰጥቶት በሳውዲ የኢትዮጵያ ቆንስላ በሚሊታሪ አታሼነት ተመድቦ በዋናነት ይህን ስራ ሲሰራ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የሳውዲ ምንጮቻችን ለኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጠውልናል፡፡

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት አክቲቪስት ሱሌማን አብደላ በዚህ አሊ አደም የተባለ አማራ ጠል ጽንፈኛ ኦሮሞ እና በአለቃው ሲሳይ ቶላ የረጅም ጊዜ የሳውዲ መንግስት ጋር ድርድርና ማግባባት በኋላ ለፋሽስቱ የኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ ተሰጧል፡፡

ምንጫችን - ኢትዮ 251 ሚዲያ ነው።

@FanoMedia24

1 месяц назад

መረጃ(ለፋኖ የሚደርስ)
ዛሬ(30/3/2027 ዓ.ም)በአባዱላ ሬሽን በፓትሮል በሸራ የተሸፈነ ከባድ መሳሪያ ጭነው በኦራልና በኦባማ እያጀቡ ከቢቸና ወደ ደ/ወርቅ ጉዞ ጀምረዋል::ፋኖዎቻችን አቀባበል አድርጉላቸው።

1 месяц, 1 неделя назад

ተቀበል ፬
ወሎን ያህል ግዛት የአሳምንን ሀገር
ደፍረው የረገጡት፥
የእምብርክክ ሲነዱ እንዴት ነው የሚወጡት?😂🤐

1 месяц, 1 неделя назад

ተቀበል ፫

#ጎጃም
የኮስትር አሽከር ብሎ ቢፎክር
አብይ ሸሼ ክምር ለክምር
በተክለሀይማኖት ብሎ ቢደግመው
ብርሃኑ ጁላ የት ነው መገኛው?😂

1 месяц, 1 неделя назад

ተቀበል ፪

#ሸዋ
የአስማረ ዳኘ ሀገር
የነ እሸቴ ሞገስ የነ ፕሮፍ አስራት
አይወድም ሲነኩት ይፋጃል እንደ እሳት

1 месяц, 2 недели назад
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana