ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
✥የዓብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት✥
✥ቅድስት✥
በመባል የታወቃል ።
በዚህ ቀን እግዚያአብሔር አምላክ ቅዱስ ነውና እኛም ቅዱስ እንድንሆን ይፈልጋል ሁሉም የተቀደሰ ህይወት እንዲኖረው ይሻል። እኛም እርሱን መስለን በሮሜ 8÷28 የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቅድሞ ወሰነ ይላልና። እግዚያአብሔር አምላክ በቅድስና እንዲመራን የርሱ መልካም ፍቃድ ይህውንልን።
ሌላው ግን በዚህ ጊዜ ቅድስት ተብሎ በሚታወቀው ሳምንት ውስጥ የምናስበው ምንድነው? ስንል ሰንበትን ነው። እግዚያአብሔር አምላክ ሰንበትን እንደቀደሳት ሰንበትን ቀድሶ ለኛ ቅድስት አድርጎ እንደሰጠን የሚያሳይ ነው።
ሰንበት ስናከብር ሁለት ሰንበት እናከብራለን።
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።
1ኛ ቀዳሚ ሰንበት
2ኛ ሰንበተ ክርስቲያን
የክርስቲያን ሰንበት ቀዳሚ ሰንበት የተባለቺው #ቅዳሜ ነው። ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም በንደግምበት ሰዓት ውዳሴሃ ለእግዝተነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ። ይላል።
የቀደመች ሰንበት የአይውድ ሰንበት ወይም በብሉይ ዘመን የምትከበር ሰንበት ሁሉም ሰው ሊያከብራት የምትገባ ሰንበት። ዘፍጥረት 2÷3 እግዚያአብሔር አምላክ ሁሉን በስድስት ቀን ከፈጠረ በዋላ በሰባተኛው ቀን አረፈ የሰባተኛው ቀንም ቀደሰው።
አከበረው ሰንበት አለው። ዘጸአት 20 ላይ ስንመለከት ከአስርቱ ትዛዛት አንዱ ሰንበቴን አክብር ነው። ወይም ሰንበትን አክብር ነው።
እዚህ ሰንበት ቅዳሜ ላይ ጌታ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ አረፈ ። ለምን አረፈ?
ደክሞት በፍፁም አይስማማውም።
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባው።
ከምንሰራው ስራ አርፈን እግዚያአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ ነው።
ስለዚህ ቅዳሜ የስጋ እረፍት ነው።
2ኛ ሰንበት እውድ ነው።
እውድን ሰንበት እንደውም የቀኖች ሁሉ ንግስት ነው የሚላት አትናቲዮስ ሲጠራት ። የእለታት ሁሉ ንግስት አባይ ታላቅ እለት ይላታል።
ለምን ?
በዚህ ቀን ደሞ ነብሳችን አርፋለች።
እንዴት ? አለምን በስድስተኛው ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ያረፈው የሁሉ ፈጣሪ እግዚያአብሔር አለምን ለማዳን በጀመሪያውስንመለከት ትምህርት ዘወረደ እንደተመለከትነው ወርዶ ወደዚህ መቶ ነብሳችን በህለተ ሰንበት እውድ አሳረፋት። ማቴ 28÷1 ዮሐ 20÷1 በመቃብሩ ስፍራ በህለተ ሰንበት ወይም ደግሞ የሰንበቱ መጨረሻ በመጀመሪያው የሰንበት ቀንእነሆ ወደ መቃብሩ ስፍራ ኤዶ መቃብሩ ግን ባዶ ነበር። ነብሳችን ያረፈችበት ሰንበት እለተ ሰንበት እውድ ነበር ። እውድ ደግሞ ሰንበት ተብሎ ይጠራል።
1 ቀዳሚት ሰንበት ።
2 እውድ ሰንበት ።
ይኤንን እነሆ ሰንበታቴን አክብሩ ብሎ እንደተናገረ እነዚህን እናከብራለን ።
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በፍጥሞ ደሴት ሳለው ይላል ። ራይ 1÷10 ላይ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኹ አለ። የጌታ ቀን የሚላት እውድነው። ሐዋሪያት የጌታ ቀን ብለው ይጠርዋታል ።
ቅዳሜ ሥጋችን ያረፈበት የሚያርፍበት
እውድ ደግሞ ነፍሳችን የሚያርፍበት ልዩ ቀን ነው። ቅድስት ሲል እግዚያአብሔር ቅዳሜን እግዚያአብሔር እውድን ለውላችን ቅድሶ ሰጠን ።
በዚህ ቀን አርፈን የታመመን እንድንጠይቅ ድውያን እድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይፈልጋል።
ለስጋ ብቻ መሮጥ አይደለም ወገኖቼ ለዓለማዊ ነገር ብቻ መክነፍ አይደለም።
እግዚያአብሔር ዛሬ ይጠይቀናል ።
በዚህ ቀን ችግረኞችን እንድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይሻል።
✥
የህለተ ሰንበ በረከት እረድኤት ከኛጋር ይኑር።
ሼር በማድረግ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ።
???????
╔═✟✞════?? ════✟✞═╗
@dmse_tewado @orthodoxswi_eywet
╚═✟✞════?? ════✟✞═╝
የእረኝነታቸውን ብኩርናቸውን በምስር ያልሸጡ አባት..
አሸርጋጅ አጎብዳጅ በበዛበት በእዚህ በእሾህ ዘመን ያለአንዳች አባት ያልተወን ቅድስት ሥላሴ የተመሰገነ ይሁን።
እረኛ ያልነው አካል አስብቶ ለአራጅ የሚሰጥ ሻጫ አጋፋሪ ሆኖ በተገለጠበት በእዚህ ትውልድ እንደ አብርሐም አባትነትን ያልናቀ እረኛ መኖሩ ተመስገን ያስብላል።
ብጹዕ አቡነ አብርሐም
በረከትዎ ትድረሰን !!!
ውበቱን አድንቀን የማንጨርሰውን ዓለማት በፈጠረ አምላክ ፊት እንኳ ፥ ቅዱሳን ሲናገሩ የሰማነው “በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” ሲሉ እንጂ ፥ እፁብ ድንቅ ስለሆነው ውብ ዓለማት ከሚፈሰው ደም በፊት የአድናቆት መዝሙር ሲዘምሩ አይደለም።(ዮሐ ራዕ 6፥10)።
በደም በጨቀየ ሀገር ውስጥ ፥ ንጹሐን እንደ በግ ከሚታረዱበት የተሰበሰቡ አባቶች ስለአንድ ሙዚየም በሀገር መሪ ፊት እንዲህ መናገር ምንኛ ያሳፍራል! ለመንጋው ጠባቂ የተባሉት እረኞች ፥ የልጆቻቸው ስቃይ ሳይሆን በከተማ መኃል ስላዩት ውበት ተናግሮ ዝም ማለት እንደምን አስቻላቸው?! ለመሪውስ መስማት የሚወደውን የሚነግሩት ወይስ እውነትን የሚያጋፍጡት እንደ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የበለጠ ወዳጆቹ ናቸው?
©ሙሉዓለም ጌታቸው
ዘወረደ /ዘመነ አዳም/
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ዘወረደ ማለት፣ ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም የአምላካችን ሰው መሆን ያመለክታል፡፡ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሳት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ “ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ” በማለት በጾመ ድጓው መጀመሪያ ላይ ገልጾት ይገኛል፡፡
አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፣ የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ፣ /መሐትው/ ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፡፡ ይዘመራል፡፡ ይመሰገናል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የሳምንቱ ስያሜ ከዚህ የተወሰደ ነው፡፡ እንዲሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን የጀመረው፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሰው በመሆን ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቆ በማስተማር እንደሆነ ሁሉ የመጀሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
በዚህ ሳምንት በተለይም እሑድና ሰኞ የሚነገሩት ውዳሴያት ከመጻሕፍተ ኦሪትና ነቢያት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሁለተኛም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ለማዳን ከሰማይ መውረዱንና በመስቀል መሰቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ታሉቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፣ በዘወረደ ጾመ ድጓው ሰንበት ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን፣ ሕይወት ላለው ነገር ሁሉ ጸጥታና ሰላም የሰፈነባት የዕረፍት ቀን ስለመሆኗ “አዘዞ እግዚአብሔር ለሙሴ ወይቤሎ ሰብዕከ ወላህምከ ወኲሉ ቤትከ ያዕርፍ በሰንበት” ዘፀ.20፥10፣23፣12፣ ጾመ ድጓ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝብህ የከብትህ መንጋህ ቤተሰብህ ሀሉ በሰንበት ቀን ከድካማቸው ይረፉ በማለት አዘዘው ይላል፡፡ በዚህም ዘመነ ጾም፣ ወይም ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡
በጾመ ድጓው ዘወረደ እየተባለ የሚታወቀው፣ በጾመ አርባው ወቅት በተለይም በመጀመሪያው ሳምንት የሚገኘው ያሬዳዊ ድርሰት በነግህ በሠለስት፣ በቀትርና በሠርክ እንዲሁም ቅዳሜና እሑድ በሌሊት የሚዘመር ነው፡፡ በውስጡም የያዘው ፍሬ አሳብ፣ የጾምን፣ የጸሎትን፣ የምጽዋትንና የፍቅርን ጠቃሚነት አጉልቶ የሚያስተምር ነው፡፡
በዚህ በጾም ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት በአብዛኛው ከቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ውስጥ የሚዘመረው ምዕራፍ የተባለው ነው፡፡ ምዕራፍ የተባለበት ምክንያትም በየመዝሙራቱ መሀል ሃሌታና ድጓ እያስገባ ለመዝሙሩ ማረፊያ ስላበጀለት በዚህ ምክንያት ምዕራፍ የሚል ስያሜ ሊያገኝ ችሏል፡፡ ይህ የዜማ መጽሐፍ በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ይኸውም የዘወትር ምዕራፍና የጾም ምዕራፍ በመባል ይታወቃል፡፡የዘውትር ምዕራፍ የሚባለው በዓመቱ ውስጥ ባሉት ቀናት ውስጥ ሳምንታትና በዓላት ሁልጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን፣ የጾም ምዕራፍ የሚባለው ደግሞ በጾመ አርባ ብቻ ለአገልግሎት የሚውል ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዐሥሩ ምህላት አርዕስተ ምህላ በዚሁ ክፍል ይካተታል፡፡ የምዕራፍ ቅንብር ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከድጓና ከጾመ ድጓ ጋር የተቀናጀ ነው፡፡ የትምህርት አሰጣጡም እንደ ድጓው ወይም እንደ ዝማሬ መዋሥዕቱ መጽሐፍ ተዘርግቶ ሳይሆን በቃል የሚጠናና የሚወሰን ነው፡፡ ስለሆነም ምዕራፍን ለመማር 150 መዝሙረ ዳዊትን፣ ከነቢያት 15 ምዕራፎችንና 5 መኃልያተ ሰሎሞንን በቃል ሸምድዶ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ወይም ግድ ነው፡፡
ጾምን መጾም የፈቃድ ብቻ ሳይሆን የትእዛዝም ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ ነቢዩ ኢዩኤል “ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ” ጾምን ያዙ አጽኑ ምሕላንም ዐውጁ ሸማግሌዎቹን ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ሁናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩሁ /ለምኑ/ ብሏል፡፡ ኢዮ.ምዕ.1፥11፣ 2፣12፣15-16 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ወኲኑ ላዕካነ፣ ለእግዚአብሔር በጾም ወበንጽሕ፡፡ በጾም፣ በንጽሐና ተወስናችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ ብሏል 2ቆሮ.6፥4-6፡፡
ጾም ከሌለ ወይም ተገቢ ካልሆነ ጌታችን በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ ስለ ጽድቅ የሚራቡ የሚጠሙ ንዑዳን ክብራን ናቸው ለምን አለ? ማቴ.5፥፣6፣16፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ሰውነቴን በጾም አሳመምኳት በቀጠና፣ በሰልት አደከምኳት ለምን አለ መዝ.34፥68፣ ት.ዳን. 9፥3-4፣ 14፥5
ነብዩ ሚኪያስ ሐዋርያት ሙሸራውን ከነሱ ለይተው የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ ያለውን የጌታን ቃል መሠረት በማድረግ ክርስቶስ በሞት ከተለያቸው በኋላ ጾመዋል፡፡ ጾምንም ሠርተዋል የሐዋ.ሥራ 13፥3፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ሐዋርያት የጾሙትንና እንዲጾም የወሰኑትን መጾም ይገባል ብለው ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸውን አጽዋማት እንዲጾሙ መወሰናቸው ይህን የጌታ ቃል መሠረት በማድረግ ስለሆነ፣ የትእዛዝ መሆኑን ተገንዝበን መጾም አለብን፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠራዔ ሕግ እንደመሆኑ አርባ ቀን አርቦ ሌሊት ጾመ እንጂ እርሱ ሳይጾም ጾሙ አላለንም ማቴ.4፥2፡፡
ሠናይ መዋዕለ ጾም፡፡
የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
✍ ✔
❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️
ለመቀላቀል ?
https://t.me/natanimube
https://t.me/dmse_tewado
https://t.me/maetebe_kbrenew
https://t.me/orthodoxswi_eywet
https://t.me/ortodoksawzmare
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
"#ጾምን ውደደው " #ማር ይስሐቅ
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
#ጾም ማለት መተው ፣ መከልከል፣ መጠበቅ ፣ በታወቀ ጊዜ ከምግብ መከልከል ማለት ነው።
ሌላው በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ እንዲህ ይላል
" ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው ፤ ሰው በደሉን ለማስተስረይ ዋጋውን ለማብዛት የፈቲሁን ኃይል ( በምኞትና ባምሮት መያዝ) ለማድከም የሚጠቀምበት ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ የምታደርግ ናት"።
? ስለዚህ ሰው በደሉን ለማስተስረይ ዋጋውን ክብሩን ለማብዛት የፈቲሁን ( በምኞትና ባምሮት መያዝ) ኀይል ለማድከም እና ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ለማስገዛት በታወቀ ጊዜ ውስጥ ከምግብ መከልከል ነው::
? ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው ፤ ጾም ለሥጋ መንፈሳዊ ልጓም ነው ማለትም ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የሚበቃበት ለወዲያኛው ዓለም ረብሕ ያለው ስንቅ የሚይዝበት ነው ፤ (።)
? ጾም የነፍስን ጠላት ለማድከም የምታግዝ መሆኗን ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ሲናገር "የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ የእህሉንም መግቢያ ሁሉ ይዘጋል ፤ ያን ጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ፣ ይጠማሉ በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ ይሰጣሉ ምርኮኛም ይሆናሉ ፤ የነፍስን ጾር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ተገቢ ነው ፤ የሥጋን ፈቃድ የሚያበዛው ድሎት ምቾት ነው ስለዚህ የነፍስን ጾር ለማሸነፍ ትክክለኛው መንገድ ጾም ነው፤ አንድ ሰው በጾም ከጸና የነፍሱ ጠላቶች ይደክማሉ። "
? ማር ይስሐቅም ጾም ገንዘብ ያደረጓትን መንፈሳዊ ሥራ የምታሠራቸው መሆኗን ሲገልጥ
" ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፣ ( ፤ ) ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፣ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፣ የወንጌልን ሥራ መጀመሪያ ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፣ የንጽሕና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት ፣ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፣ አርምሞን የምታስተምር ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ና ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።"
በዚህም ጾም የበጎ ነገር ሁሉ መገኛ መከማቻ ናት ማለት ነው።
? ሰው የሚጾመው ምግብ ባለ መብላቱ እግዚአብሔር የሚደሰት ስለሆነ አይደለም ፤ ዲያቢሎስ በልቶ አያውቅም ፤ ስለዚህ ሰው የሚጾመው ፈቃዳተ ነፍሱን ለመፈጸም ፤ከሞት ያዳነውን አምላኩን በተገቢው መልኩ ለማገልገል ፤ንጽሕናን ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ ይጾማል።
ጾም ከሰይጣን ሥራዎች ሁሉ ርቆ ስለ ራስና ስለ ሕዝብ ስርየተ አበሳ ፤ ሰላምንና በረከትን ለመለመን ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት ነው።
? ጾም ከእኅቶቿ ከጸሎት እና ከምጽዋት ጋር የተጋመደችና በአግባቡ የተፈጸመች እንደ ሆነ ወደ ጽድቅ መንገድ ትመራለች፤ ጾም የምግባራት ሁሉ ንግሥት ነች። ይህን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲናገር "የመልካም ሕይወት ምግባር ሁሉ እናት የማስተዋልና የሌሎች ምግባራት ሁሉ ንግሥት የምትሆን ጾም ናት"
ይህች የምግባራት ሁሉ በር የሆነችው ጾምን ልንቀበላት የሚገባው የልቡናችንን በር ከፍተን ራሳችንን ለንስሓ አዘጋጅተን በቀናው መንገድ ለመጓዝ ቆርጠን መሆን አለበት።
? የጾም ዓላም ዓላማ ለተወሰኑ ጊዜያት ከምግብ መከልከል አይደለም ፤ በመንፈሳዊ ሕይወታችን አንድ ወይም ሁለት ደረጃዎችን ለመውጣት የተዘጋጀልን ነው ።ጾም በሕይወታችን ለውጥ የሚያመጣ የበረከት በር ነው። ጾም የማንጸልይ ከነበረ እንድንጸልይ ፤ የማንመጸዉት ከነበረ እንድንመጸውት ፤ የማናስቀድስ ) ከነበረ እንድናስቀድስ ፤ የማንቆርብ ከነበር እንድንቆርብ የሚያበረታን የሕይወት በር ነው።
በተለይ በጾም ወቅት ርቀነው የነበረውን መቅደስ በይበልጥ የምንቀርብበት ነው ። አንድ ኦርቶዶክሳዊ አምልኮትን መፈጸም ( ማስቀደስ) ( ማስቀደስ አምልኮትን መፈጸም ተብሎ መተርጎም ይችላል? )ግዴታው ( ምን ለማለት ነው ? ) ነው ፤ ስለዚህ በዚህ ጾም ብንችል የዘውትር ( የዘወትር ) ቀናትን እና የሰንበትን ቅዳሴን ለመሳተፍ ( ዘወትር ማለት ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉትን ቀናቶች ስለሚያካትት እና ብሎ መጨመሩ አስፈላጊ አይደለም። ) መሞከር ካልቻልን ግን በሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ) ቅዳሴን መሳተፍ ይገባናል።
? ሌላው በጾም መቃረብያ ጊዜ የምናደርገውን የቅበላ ሥርዓታችንን መመልከት ይኖርብናል ። ቅበላ በክርስትና ውስጥ ያገኘነውን ምግብ መመገብ ፤ ያገኘነውን መጠጥ መጠጣት አይደለም ፤ ቅበላ ራስን ለጾም ማዘጋጀት ሲሆን ይህም በቅዳሴ ፣ በተመስጦ ፣ በምስጋና እና ከንስሐ አባት ጋር ተነጋግሮ መንፈሳዊ ሥራዎች በመሥራት ነው። የቀደሙ አባቶች ጾምን በመጾም ይቀበሉ ነበር ። እኛስ?
ስለዚህ ጾምን በመንፈሳዊነት ተቀብለን በመንፈሳዊነት ጾመን መዳረሻችን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል መሆን አለበት።
? ጾም አያደክምም ንቁ ያደርጋል እንጂ። በጾም የሚደክም ፍትወተ ሥጋ ነው። በጾም ወቅት የመግደፊያ ሰዓቱ ሳይደርስ የሚርበን ከሆነ ቆም ብለን ራሳችንን መመርምር ይገባናል። ነፍሳችን ካልተራበች የሆድ ባዶ መሆን ሊያስጨንቀን አይችልም።
ክቡር ዳዊት ግን ሁልጊዜም በአምላኩ ደስ ይለው ነበር። ጾም ስለ ኀጢአታችን እንድናዝን የሚረዳን መሆኑንም ከእርሱ ሕይወት እንማራለን። “እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፣ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች ፤ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ፡፡” መዝ ፷፪፥፬ - ፭። “እህል መብላት ተረስቶኛልና"መዝ ፻፩፥፬። ነፍስ በእግዚአብሔር በአምላኳ በጠገበችና በረካች መጠን የሥጋ ፈቃዳትን ለማስተናገድ ጊዜ አይኖረውም፤ ከይፈቃዳቱ በላይ ይሆናልና። ሥጋም ከነፍስ ጋራ በመንፈሳዊ ምግባር ይተባበራል፤ መሻቶቹንም ሁሉ ይተዋቸዋል። ለዚህም ነው “የጠገበች ነፍስ የማር ወለላ ትረግጣለች፤ የተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል፡፡'' ያለው። መጽሐፈ ተግሣጽ ፫ ፥ ፯። ነፍስ ስትጠግብ ሥጋም ይጠግባል፣ ይህም የሚነግረን መጾም (ከምግብ መከልከል) ነፍስንና ሥጋን በአንድነት። መንፈሳዊ ምግብን መመገብ እንደሆነ ነው። ግዘፍ ያለው ሥጋ መንፈሳዊ ምግብ መመገቡ አስደናቂ ነው። ሥጋውን የማያጾም ለነፍሱ መለኮታዊውን ምግብ (ቃለ እግዚአብሔርን...) የማይሰጥ ሰው ድሀ ነው። ቅዱስ ያሬድ "ቀድሱ ጾመ፣ ጾምን ቀድሱ" እያለ በጾመ ድጓው ማዜሙ ለዚህ
?የጾም ጊዜ የጸጸትና የልብ ንጽሕና ጊዜ ነው:: “ወደ እኔ ተመለሱ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ( ትንቢተ ዘካርያስ ፩ ፥ ፫ ) እንዲል ጾም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራን የሚሠሩበት ፤ በኀጢአት የጎሰቆለች ነፍስንም በንስሓ አጥቦ ቀድሶ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ የሚያነጹበት ጊዜ ነው፡፡
https://youtu.be/odkncFecs9Y?si=U9bjQu01_sbMSJxb
YouTube
የዐብይ ፆም እና የዘወረደ ምንነት የሚያስረዳ እንዲሁም የዘወረደ ሳምንት ጥቅሶች
#mezmur #orthodox #eleni #ethiopia #ethiopian\_orthodox\_sibket #orthodontist #ethiopian #zehabesha #ህወሃት #የበገና\_መዝሙር
ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ እንሰኛለን
በዩትዩብ ከ 600 ሰብስክራይበር በላይ
በቲክቶክ ከ700 በላይ
በቴሌግራም ከ 4900 በላይ ሜምበር ያለው ሲሆን ይህም ቻናል ሀይማኖታዊ ፒክቸር(ፕሮፋይል) ማለትም
.ጥቅስ
.የበዓል ቀን ትምህርት
.አፅዋማት እየሰራ ለማህበረሰቡ
መዝሙር ከነግጥሙ (lyrics) እያቀረበ ይገኛል ይህንን ቻናል ለመቀላቀል
ስለ የአብይ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ትምህርት ፣ ፕሮፋይል ፣ መዝሙር ለማግኘት ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ኦርቶዶክሳዊን ንድፍ ይቀላቀሉ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana