Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

የሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

4 days, 13 hours ago
ይህ የፊልም ትዕይንት አሊያም ግራፊክስ አይደለም …

ይህ የፊልም ትዕይንት አሊያም ግራፊክስ አይደለም በእውኑ አለም የተከሰተ በጋዛ ምድር የተከወነ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የወለደው ኢ ሰብዓዊነት እንጂ ሌላ አይደለም።

አላሁመ አለይከ ቢልየሁድ

#mahi mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 days, 5 hours ago
ምዕራባዊቷ አዛውንት ሰውነቷ ፓራላይዝ ከመሆኑ ጋር …

ምዕራባዊቷ አዛውንት ሰውነቷ ፓራላይዝ ከመሆኑ ጋር የመተንፈሻ ችግር ያለባት አፏ ላይ በተገጠመላት መሳርያ መሐል የፍልስጤምን ባንዲራ አንጠልጥላ በዊልቼር እየተገፋች በተጠራው ሰልፍ ላይ ተሳተፈች። አጋርነቷን አብሮነቷን ለማሳየት ህመሟን ዋጥ በሽታዋን ስልቅጥ አድርጋ ምንም ማድረግ እንኳ ባልችል ስለናንተ እጮኻለው አለች።

አጂብ ነው እዚያው ጎረቤት ሀገር መቶ ሚሊዮን ግብፃውያን እኮ ስለወንድሞቻቸው ክብር አልዘመቱም፤ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ባህሬን እና ሳዑድ አረቢያ ከጎናቸው አልተሰለፉም።

#mahi mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 days, 9 hours ago
የሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች
1 week, 2 days ago
ህመም ግፍ መከራ በረፈህ ምድር እየተሰማ …

ህመም ግፍ መከራ በረፈህ ምድር እየተሰማ ነው። አንደበት የማይገልፀው ጭካኔ! ቃል የማይወስፈው ስቃይ በህፃን አረጋውያን ላይ መዝነቡን ቀጥሏል። ጌታዬ አቻቻልህ የሌለህ አስመሰለብህ ትዕግስትህ የአላህን ጠላቶች አስፈነጨ። በእርግጥም አንተ ሙንተቂም ነህ ተበቀልልን።

#Mahi mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch

1 week, 2 days ago
ይህን ዘግናኝ ትዕይንት በመልቀቄ ይቅርታ አልጠይቅም። …

ይህን ዘግናኝ ትዕይንት በመልቀቄ ይቅርታ አልጠይቅም። ህመማቸው አጥንትህን ሰርስሮ ይገባ በልጄ በቤተሰቤስ ቢሆን ብለሀ እያሰብክ ብርድልብስህን ገፈህ ዱዓ አድርግ። እጅህን ከፍ አድርገህ አላህን ለምንላቸው።

#Mahi mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch

1 week, 2 days ago

የረፈህ ምድር በሸሂዶች ጀናዛ ተሞልታለች። ህፃናት እዚህም እዚያም ከግንድም ከግንብም ጋር እየተላተሙ ትበያ ለብሰዋል። ምድር በንፁሀን ደም መርጠብ ጀምራለች።

ድል አሊያም በክብር እየተፋለሙ መሞትን መርሀቸው ያደረጉት ሙጃሂዶች ከስተው ኮስምነው የአላህን ጠላቶች እየተፋለሙ በአቋማቸው እንደፀኑ እነሆ ዛሬም አሉ። ቀለባቸው ተምርና ውሀ ነው እርሱም ከተገኘ! ካጡም ለሆዳቸው አይጨነቁም። የበረሀውን አፈር በውሀ ለውሰው ይጎርሱና በኺን በኺን እያሉ ወደ ጂሃዱ ሜዳ ይሮጣሉ።

በኺን በኺን ማለት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?! ጀነትን እየናፈቁ በተድላዋ ለመንፈላሰስ መጓጓት አይደለምን?! እንዴታ! ስለዚህ ቃልማ ታላቁ ሰሐባ ዑመይር ይንገርህ
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የጀነት ስፋት የሰማያትና የምድሮች ያህል ነውን?" አላቸው በጂሃድ የሚገኘውን ምንዳ አስቦ በመገረም ጠየቃቸው "አዎ" አሉት ሐቢቢ። "በኺን በኺን" በማለት ተጣደፈ።

የአላህ መልእክተኛም "በኺን በኺን እንድትል የገፋፋህ ምንድነው?" አሉት ፊቱን አተኩረው እየተመለከቱት። "የዚያች ጀነት ባለቤት መሆን ፈልጌ ነዋ" አላቸው። "አንተማ የጀነቷ ባለቤት ነህ" ሲሉ አበሰሩት።
ዑመይር ሊበላት ከአፉ ያስገባትን የተምር ፍሬ እየተፋ "ይህችን ተምር እስክበላ የሚያቆየኝ የህይወት ጊዜ ካለማ ጀነት ለመግባት ዱንያ ላይ ረዥም ቆይታ ይሆንብኛል" እያለ ተምሮቹን ወደመሬት ወረወረ። ጦር ሜዳውን ሰንጥቆ ገባ። በአላህ መንገድ እየተፋለመ ጥሎ ወደቀ።

አጂብ የነርሱ ነገር!!
ሲገደሉም ሲገድሉም አንደበታቸው አላህን አይዘነጋም። እስትንፋሳቸው እየተቋረጠም እጃቸው እንደተቀሰረ ወደ ሰማይ ይነሳል። ዱዓ ሲያደርጉም እንዲህ ናቸው አይፈታም ጣታቸው። አይቦዝንም አንደበታቸው። አላህ አላህ ይሉታል። በችግር ጊዜም ያወሱታል። ሲደሰቱም ይዘክሩታል። የሩህ ቀለባቸው አላህ ነው። ስሙን ማውሳት ልምዳቸው እርሱን ማመስገን ባህላቸው ነው። አይደክሙም ሰልችተውም አያውቁም። ልጆቻቸውን ነጥቋቸው ሱጁድ ተደፍተው ያመሰግኑታል። እስክትወድ ከነፍሳችን ውሰድ ይሉታል። ጀናዛ ታቅፈው ማደር፣ በመቀበርያ እጦት በጅምላ መቀበር ልምዳቸው ሆኗል። ስደት ርሀቡ አላህን አላስረሳቸውም። ቁስለት ህመሙም አላዘናጋቸውም። ከፍርስራሽ መሐልም ይዘክሩታል። በጥቅሻም በጉንብሻም ይቅጣጩታል። ደግመው ደጋግመው አላህ አላህ ይሉታል።

አጂብ ነው የነርሱስ ነገር

ፅናታቸው ጠላትን ያሸብራል ብቅ ሲሉ ይደነግጣል። ግርማሞገሳቸው ይለያል። መሳርያን የሸከፈው በፍርሀት ያቀረቅራል እያለቀሰ እግሩ ይንቀጠቀጣል።
"ሐስቢየላህ ወኒዕመል ወኪል" መለያቸው ነው። መፈክራቸው ተክቢራ የህመማቸው ማስታገሻ ተስቢህ ነው። መፅናኛቸው ጀነት ምኞታቸው የረሱልን ጉርብትና ማግኘት ነው።

የማወራችሁ ስለነዚያ ብርቱዎቹ የጦር ጀት ስለማያስበረግጋቸው ሞት ከአላማቸው ስለማያዛንፋቸው ፅኑዎች ነው! ስለነዚያ በምላሳቸው ሸሃዳን በጣታቸው ብቸኛ ጌታቸውን ስለሚዘክሩት እውነተኞች! ቃል ተገጣጥሞ ፅናታቸውን መግለፅ ስለሚሳነው፣ አለም ተረባርቦ ሊያጠፋቸው ስለቸገረው ስለነዚያ ስለፍልስጤም ህዝቦች ነው።

ዱዓ ላረግ ነው አሚን በሉ
የወረወራችሁት ሁሉ ኢላማውን አይሳት የተኮሳችሁት ባሰባችሁት ቦታ ይረፍ
አላህ ይደግፋችሁ
አላህ ያበርታችሁ

ጌታዬ ሆይ ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
#Mahi mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch

2 weeks, 2 days ago
የአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቃሳም ሙጃሂዶችን …

የአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቃሳም ሙጃሂዶችን አርማ ጭንቅላታቸው ላይ አስረው ፍሪ ፍሪ ፓለስታይን የሚል ድምፅ ማሰማታቸውን እነሆ ዛሬም ቀጥለዋል።

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

2 weeks, 5 days ago
ከጥቂት ቀናት በፊት በግብፅ ብሄራዊ ደህንነት …

ከጥቂት ቀናት በፊት በግብፅ ብሄራዊ ደህንነት ኢንተለጀንሶች በኩል አንድ መልዕክት ተላከ። ከዋሽንግተን ነበር። ለቀሳሙ መሪ ለየህያ ሲንዋር።
ለግሉ 15 ቢሊዮን ዶላር ስጦታ፣ ምቹና ቅንጡ መኖርያ፣ ጋዛ ከተማን መልሶ ለመገንባት ቃል የሰፈረበት ደብዳቤ! በምትኩ የህያ ሲንዋር ቀሳሞችን ከውስጥ በኩል ሰርስሮ በመናድና በመሰነጣጠቅ ህብረታቸውን እንዲንድላቸው ይጠይቃል።

አደራ ይላል መልዕክቱ መጨረሻ ላይ "አደራ ከግብፅ አስታራቂዎች በኩል የቀረበውን ልዩ ጥያቄ ተጠቀምበት ይህ እድል እንዳያመልጥህ" በማለት ይቋጫል።

የህያ ሲንዋር ከአራት ቀናት በኋላ ለዚህ ጥያቄ በአንድ አንቀጽ ምላሽ ሰጠ እንዲህ ይላል፡-

فَلَمَّا جَاءَ سُلَيْمَانَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَا آتَانِيَ اللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّا آتَاكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ

"ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ"
[አን-ነምል 36]

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

2 weeks, 5 days ago

አስገራሚውን ፅናት የተላበሱት የቀሳም ሙጃሂዶች የወራሪዋን ጦር እያነደዱት ይገኛሉ። አዎ ወጀቡ ሳይንጣቸው በንፋሱ ሳይወዛወዙ እየደሙ እየወደቁ የተዛነፈውን ፍትህ አስፍነው የአላህ ጠላቶች አደብ ሊያስይዙ ከእህል ውሀ ተራርቀው ጠመንጃቸው ከሰበቁ ሁለትመቶ ቀናት አለፉ። ከዋሻው ጥግ ተደግፈው ቁርአኑን እያነበቡ በዚክር ታጅበት በበስመላ ይተኩሱታል።

የጋዛ ምድር ስለነርሱ ያወጋል ብሶት ስሜቱን በሊሳነል ሀሉ ያወራል
"ለበራሪው ጎጆ፣ ለሰው ለአራዊቱ ጥላና ከለላ ነበርን የምድር ድምቀት የተፈጥሮ ውብ ስጦታ" አዎ ለዘመናት የተከፈለውን መስዋዕትነት ያስታውሰናል ላዩ ላይ የተፈፀመውን ያየውንና የታዘበውን ጀግንነት በደልና ግፍ ሊያወጋን ከቦታው ተሰይሟል ሲቃ እየተናነቀው እንዲህ ንግግሩን ይቀጥላል

"የበይተል መቅዲስን ክብር ለማስመለስ በኛ ላይ ለተጠለሉ ጀግኖች ዱዓ እያደረግን ስለ ውለታቸው ስለኛም እጣ ፈንታ እናነባለን። የተሰሩት ፎቆች ረግፈው ተራቁተን ተመናምነን የፍርስራሽ ክምር ሆነናል። ለተጠጉን ሙጃሂዶች ጎጆና መጠልያ ሆነን እነሆ ዛሬም ድረስ አለን"

ዛሬ የወራሪዋ እስራኤል ሎጀስቲክና ተጨማሪ አጋዥ ኃይሎች በሰላሀዲን ጎዳና በኩል ሲያልፉ በቀሳሞች ዶግ አመድ ሆነዋል። የወራሪዋ ጀቶችና ሚሳኤል የሚተፉ ድሮኖች ከሰማይ እሳቶቻቸውን እየለቀቁ መኖርያ ቤቶችን በማደባየት ህፃናት አረጋውያን ሴቶችና ሰላማዊ ሰዎችን እየቀጠፉ ይገኛል።

ድርድሩ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል አዲሱ የስምምነት ምዕራፍ ወራሪዋ እስራኤል ጦሯን ከከተማው ለማስወጣትና የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለመስማማት ዳር ዳር እያለች ይገኛል። የሐማሱ ኢስማኤል ሀኒያ ዛሬ ከሉብናን ከተውጣጡ ዲፕሎማቶች ጋር ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ቱርክ ገብተዋል።

ድልና ብስራትን የምንሰማበትን ቀን አላህ ቅርብ ያድርግልን።

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

4 weeks ago

ወራሪዋ እስራኤል ዛሬ ማለዳ ኢስፋሀን የሚገኘውን የኢራን የጦር ሰፈር ለማጥቃት የላከቻቸው ድሮኖች በኢራን አየር መከላከያ ተመተው ወድቀዋል። ኢላማውን ጠብቀው የወደቁ ሚሳኤሎች አለመኖራቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል። ይህን ተከትሎ ኢራን የአየር ክልሏን ለመጠበቅ ፀረሚሳኤሎችን በተጠንቀቅ አቁማለች።

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago