የሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች

Description
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 2 months, 4 weeks ago

2 months, 2 weeks ago

ከቀድሞው የሳዑዲ ንጉስ ፈይሰል ቢን አብዱልዐዚዝ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆንሰን የተላከ መልዕክት። ቀኑ ረመዳን 15 ዓመቱም 1966 ነበር። በሳዑዲ ካቢኔ ሰነድ ቁጥር 342 የተመዘገበ ደብዳቤ። ብዕር ከወረቀት ጋር ተዋህዶ እንዲህ ተፃፈ፡-

"ክቡርነትዎ" ይላል ንጉስ ፈይሰል ለአሜሪካው ጆንሰን በፃፈው ደብዳቤ ላይ "ከላይ አብራርተን እንደገለፅነው በሰፊው እንደዳሰስነው ግብፅ የሁላችንም ታላቅ ጠላት ናት። እንዲሁ ከተተወች ጠላትን በወታደራዊ ትጥቅና በሚዲያ ድጋፍ አደራጅታ ታነሳሳብናለች። የአስተዳደርዎ ኤክስፐርት ሚስተር ከርሚት ሩዝቬልት እንዳሉት 1970 ዙፋናችን ከነጥቅማችን በህልውና የሚጠበቅበት ዓመት ይሆናል።

ከዚህ ቀደም በመንግሥታችን ውስጥ ያሉ አሜሪካውያኖች ያቀረቡትን ምክረ ሀሳብ በመባረክ የሚከተሉትን ነጥቦች ላቀርብ እወዳለሁ:-
- የግብፅን ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ለመያዝ እስራኤል በግብፅ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም አሜሪካ እንድትደግፍ፣ በዚህም ግብፅ ሰራዊቷን ከየመን እንድታስወጣ ብቻ ሳይሆን ከእስራኤል ጋር ለረጅም ጊዜ ውጥረት ውስጥ በመክተት ማንም ግብፃዊ የአብድን-ናስርን የአረብ አንድነትን ምኞት እንዳያስብና አንገቱን እንዲደፋ ማድረግ ይቻለናል።

በዚህም መንግሥታችን ብቻም ሳይሆን በአረብ ሀገራትም ጭምር አጥፊ መርሆችን ለማስወገድ ሰፊ ጊዜ ምቹ ወቅት እናገኛለን። ከጥቃቱ በኋላ (ክፉ ህዝብ ሲዋረድ እዘኑለት) እንዲል ቃሉ ለግብፅም ሆነ ለሌሎች አረብ ሀገራት በሚደረግ እርዳታ ምንም አይነት ተቃውሞ አናቀርብም። እንዲያውም በየሚዲያው ከሚያሰሙት የድረሱልን አስቀያሚ ድምፆች ራሳችንን መጠበቅ ይቻለናል።

- ሶሪያ ከጥቃቱ የማትተርፍ ሁለተኛዋ ሀገር ትሆናለች። ከግብፅ ውድቀት በኋላ ክፍተቷን ሞልታ ከጥቃቱ ነፃ እንዳትሆን ከግዛቷ የተወሰነ ክፍል ተቆርሶ ይወሰድባታል።

- ፍልስጤምን ነፃ አወጣለሁ የሚል የትኛውም አረብ ሀገር እንዳይመቸው፣ ፍልስጤማውያንም በነፃነት መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ዌስት ባንክና የጋዛ ሰርጥን በመቆጣጠር ስደተኞቹ ወደቀያቸው እንዳይመለሱ ተስፋን ማስቆረጥ የተቀሩትን ፍልስጤማዊያን በአረብ ሀገራት ለማስፈር ቀላል ይሆናል።

- በሰሜን ኢራቅ የሙላ ሙስጠፋ ባርዛኒን ጦር ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። የኩርድ መንግስትን በመመስረት አሁንም ሆነ ወደፊት በባግዳድ የአረቦችን አንድነት ማስተሳሰር የሚፈልግ የትኛውንም መንግስት በኢራቅ ምድር ላይ እንዳይፈጠር ማድረግ ይሆናል። እኛም ካለፈው አመት ከ1965 ጀምሮ ለባርዛኒ በቱርክ እና ኢራን በኩል የገንዘብ እና መሳሪያ ድጋፍ ስናቀርብለት ቆይተናል።

ክቡር ፕሬዝዳንት! ይህ ዕቅድ ተፈፃሚ ሆነም አልሆነም እኛም ሆንን እናንተ አንድ ሆነን ለጥቅማችንና ለወደፊት እጣ ፈንታችን በጋራ እንሰራለን። በዚህ አጋጣሚ ለእርስዎም፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ድል እና ብልጽግናን እመኛለሁ። የወደፊት የእርስ በርስ ግንኙነታችን እንዲያድግ፣ እንዲቀራረብ እና እንዲበለጽግ ምኞቴን እገልፃለሁ"
ከሰላምታ ጋር
የሳዑድ ዐረቢያ ንጉስ
ፈይሰል ቢን አብዱልዐዚዝ

ከንጉሱ ሀሳቦች ምን እንደተተገበረ ታውቁ ዘንድ ታሪኩን ከምንጩ እንካችሁ። በመግለጫዎች ጋጋት እንዳትሸወዱ በቃላት እንዳትሸነገሉ የተፈጠረውን ታሪክ እወቁ። ድብቁ መጋረጃ ተገልጦ እውነቱ ይታያችሁ ዘንድ ሐያ ቢና ...

ወራሪዋ እስራኤል በርካታ የሙስሊሙን ግዛቶች የተቆጣጠረችበት “የስድስቱ ቀን ጦርነት" ተብሎ የሚታወቀው የወራሪዋና የአረቦች ጦርነት እንደ አውሮፓውያን አቅጣጠር በ1967 ደብዳቤው ከተፃፈ ከአንድ አመት በኋላ ተተገበረ። ወራሪዋ እስራኤል በኃይልና በጉልበት የፍልስጤምን ሀገር ተቆጣጥራ ሀገር መመስረቷን አንቀበልም ያሉ የአረብ አገሮችን ለመደቆስ ጦር ሰበቀች፡፡ "በአረቦች ከበባ ህልውናዬ አደጋ ውስጥ ነው" ያለችው ወራሪዋ እስራኤል ጦርነቱን ባርካ አስጀመረች፡፡

የቅርቦቹም የሩቆቹም ዐረቦች ተባበሩ። እውነተኞቹም መረጃ ቀድመው የሰጡ የአሜሪካ አጋሮችም አብረው ተሰለፉ። የወራሪዋ የጦር አውሮፕላኖች በንጉስ ፈይሰል ጠላትነት የተፈረጀችው ግብፅ ላይ እሳታቸውን ማዝነብ ጀመሩ። አየር ማረፊያዎቿን በቦምብ አረሷቸው፡፡ በወቅቱ በዮርዳኖስ ስር የነበረው የፍልስጤማውያን የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ (ዌስት ባንክን) ወራሪዋ ተቆጣጠረች፡፡ ቀደም ሲል በፍልስጤማውያን ይዞታነት የተከለለውን ምስራቅ እየሩሳሌም በእጇ አስገባች።

ሶሪያም አልቀረላትም በመድፍና በከባባድ መሳሪያዎች አነደደቻት፡፡ የበረከቱ የአረብ ግዛቶችን በእጇ አስገባች። እጀግ ከፍተኛ ወታደራዊ ፋይዳ ያለውን የጎላንን ኮረብታ ከሶሪያ ነጠቀች፡፡ የግብፅን ሲናይ ልሣነ ምድርንም ተቆጣጥራው ቆየች፡፡

በስድስቱ ቀናት ጦርነት የደቡብ ድንበሯ እስከ 300 ኪሎ ሜትር ተለጠጠ። በምስራቅ 60 ኪሎ ሜትር ያህል ተስፋፋ፡፡ በሰሜንም የ20 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለውን መሬት ያዘች፡፡

አዎ! ወራሪዋ እስራኤል በጦርነቱ በያዘቻቸው መሬቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ አረቦች በፈቃዷና በቁጥጥሯ ስር አዳሪ ሆኑ። በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ አይሁዳውያን የሠፈራ መንደሮችን ገነባች። የጦርነቱ ውጤት ወታደራዊ ሚዛኗንና የድል አድራጊነት ሞራሏን ከፍ አደረገው፡፡

ከጦርነቱ በኋላ ዕቅድ ውጥኑ ያልገባቸው አረቦች የሽንፈት ፅዋቸውን እያጣጣሙ የሚይዙት ጠፍቷቸው ግራ በመጋባት ዋለሉ። በአሜሪካ የነበሩ አምባሳደሮች ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆንሰን ጋር ለመወያየት ወደ ነጩ ቤተ መንግስት አቀኑ። ከፈፉ በወርቅ ቀለም የተለበጠ ካባ በጀለቢያቸው ላይ ደርበው ወደ ውስጥ ዘለቁ። ቦታ ቦታቸውንም ይዘው በተርታ ተደርድረው ተቀመጡ።

ፕሬዝዳንቱ ውሻውን ከኋላው አስከትሎ ሲገባ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሱ። በአክብሮት እጅ ነሱ። እግሩን በእግሩ ላይ አጣምሮ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ። ውሻውን በእጁ አነሳና አቀፈ። ዓይን ዓይኑን እያየ ከውሻው ጋር መነጋገር ጀመረ። ለአረቦች ነበር መልዕክቱ። ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ:-

"ጥቂት ክፉ ሰዎች አለ (አረቦችን) ጎረቤታቸውን አስፈራሩ። አይሁዶችን ማለቱ ነው። "ሲያስፈራሩት የከረሙት ጎረቤታቸው በጥፊ ሲመታቸው በአጭር ቀናት ራሳቸውን ስተው ከመሬቱ ወደቁ። እንግዲህ እነዚህ ወራዳዎች ከዚህ በኋላ ሊታዘዙት ይገባቸዋል። የወቀጣቸውን ጎረቤታቸውን ግን ሳላደንቀው አላልፍም። እንደነጩ በሬ ነጥሎ ዝም አሰኝቷቸዋል" አለና አፌዘባቸው። ፊቱን እንኳ በቅጡ ወደ አረቦቹ ሳያዞር ተነስቶ ወጣ... ውሾቹ ግን እዚያው ተቀምጠው ነበር። ይቅርታ! የአረብ አምባሳደሮች ማለቴ ነው።

ከፍልስጤማዊያን በስተቀር ሁሉም እጅ ሰጠ። ጋዛ ግን በተጠንቀቅ፣ ሁሌም ቀበቶዋን አጥብቃ እንደፀናች ጥላ እየተዋደቀች እነሆ ዛሬም አለች።


Mahi Mahisho

t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

2 months, 2 weeks ago
የሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች
2 months, 2 weeks ago

ብቻውን ጠላትን ያርበተበተ የቀሳሙ ተዋጊ። የኻን ዩኑሱ ጀግና የጂሃድን ጡጦ እየጠባ ያደገ የወንድነት ምልክት። የሸሂድነት ዝናሩን ታጥቆ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የሚታገዘውን የወራሪዋ እስራኤልን ጦር ፊት ለፊት ተጋፍጦ በመንገዱ የተዋደቀ በደም የተፃፈ ታሪክ።

ስሙም ሆነ ማንነቱ አይታወቅም። በእርግጥም እርሱ ገድልና ታሪኩ ግን በጠላቶቹ አንደበት ይወሳል። ለሁለት ቀናት ክፍለ ጦርን ብቻውን የገጠመ ፍልስጤማዊ ተዋጊ ነው። የጀግንነት ታሪኩን ከጠላቶቹ አንደበት ላውጋችሁ።

ዬዲዮት አህሮኖት የተሰኘ ጋዜጣ ትዕይንቱን እንዲህ ይተርከዋል:-
በደቡብ ጋዛ ሰርጥ በኻን ዩኒስ መንደር የእስራኤል ጦር አካባቢውን ለመቆጣጠር በታንክና በትጥቅ ታጅቦ ወደ ቦታው ዘለቀ። በማካናይዝ የተደራጀው ክፍለ ጦር ጥቃት ለመሰንዘር ተጠጋ። ከፍርስራሹ መሐል የመሸገ አንድ የቀሳሞች ወታደር አድፍጦ አፈሙዙን ወደ ወታደሮቹ አዞረ። ጥይቱን ያርከፈክፈው ያዘ።

የእስራኤል ኮማንዶ አዛዥ በታንክ እና በከባባድ ጦር መሳሪያ የተደገፈ ጥቃት እንዲፈፀም አዘዘ። ከፍርስራሹ መሐል የቆመው ቤት ዶግ አመድ አደረጉት። የአቧራ ትበያው ወደሰማይ እየበነነ ወጪ ገቢውን አላሳይ አለ። ሰው አልባ አውሮፕላን ተላከ። በፍርስራሹ መሐል እየተምዘገዘገ ጉዞውን ቀጠለ። ከምድር ቤቱ የሰፍረውን ሙጃሂድ ለመግደል ወደመሸገበት ክፍል ቀረበ። ሙጃሂዱ ጥይቱን ሳያባክን ጠበቀ። መጠጋቱን አስተዋለና ያቀባበለውን ጠመንጀ ተኮሰ። አልሳተውም ከመሬቱ ጣለው። ከወታደሮቹ አንዱንም አጋደመው።

የጓደኛቸውን ጀናዛ እየጎተቱ ከቦታው ሸሹ። ታንካቸውን አነጣጥረው ዙርያ ገባውን ተኮሱ። ሌላ አነስተኛ ድሮን ተላከ። ነገር ግን አሁንም በህይወት ኖሯልና አውሮፕላኑን መቶ መጣሉ ታወቀ።

ከ10 የእጅ ቦምብ ጥቃቶች ተርፎ ቆስሎም እጅ አልሰጥ አላቸው። ማፈግፈግም ሆነ መሸሽ ብሎ ነገር አያቅም። ህመሙ ሲጠናበት "አላሁ አክበር!" ይላል። በዚክር ቁስሉን ያስታግሳል። ንቅንቅ አይልም። በፀሐይ ቃጠሎ በነደደው አሸዋ ላይ እየተንገበገበ ተፋለማቸው፡፡ በኢስሊማዊ ወኔ ተጋጠማቸው፡፡ ከአንዱ ጥግ ወደ ሌላው እየተንፏቀቀ ሰላም ነሳቸው። አራት ትናንሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከድሮን ጋር ተላኩበት። ከሁሉም አቅጣጫ ህንፃውን መነገሉት። አልቻለም እየተኮሰ ወደቀ። እየተዋጋ አላህን ተገናኘ።

"በኻን ዩንስ ከተካሄዱ ከባባድ ጦርነቶች መካከል አንዱ ነበር" ሲል የወራሪዋ ሚዲያ ዘገበ። "ለሁለት ቀናት ይህን ተዋጊ ለመግደል አምስት ተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢደረጉም ሁሉም አላማቸውን አላሳኩም" በማለት መሰከሩ።

ግድ የለም ሰዎች ዘንድ ባይታወቅም አላህ ግን አይዘነጋውም። የተደገፈበት የግንብ አሸዋ በሚገባ ያስታውሰዋል። ትበያ ለብሶ የተዋጋበት ምድር ምስክር ይሆነዋል። አላህ ቀብሩን ኑር ማረፊያውንም ጀነተል ፊርደውስ ያድርግለት


Mahi Mahisho

t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months ago

በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለወራሪዋ እስራኤል በጋዛ የዘር ፍጅቱን ለማስቀጠል በሚመስል መልኩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለመላክ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months ago
የሙስሊሙ የፖለቲካ ዕይታ ማነስ የትላንትን ታሪክ …

የሙስሊሙ የፖለቲካ ዕይታ ማነስ የትላንትን ታሪክ ከዛሬ ጋር አዋህዶ መጪውን መመልከት አለመቻል በእጅጉ ያሳዝናል። በስሜት መሰለፍ ግር ብሎ ያለ እውቀት መደገፍ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። ፈዶሉ ወአዶሉ እንዲል ሐዲሱ በሮይተርስና በቢቢሲ ዘገባ ሰውን ወደ አንድ ጎራ ማሰለፍ ሺህ ጊዜ በአንድ ጉርጓድ ማስነደፍ ሆኗል።

ዛሬ ሒዝቦላህና ወራሪዋ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ለጋዛዎች ግን አላህ አላቸው። በሰፊ ፅሑፍ እመለሳለሁ ኢንሻ አላህ።


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months ago
ይህ የወራሪዋ እስራኤል የቦክስ ሻምፒዮኑ አምታይ …

ይህ የወራሪዋ እስራኤል የቦክስ ሻምፒዮኑ አምታይ አርጋማን ነው። 180 ሴንቲ ሜትር ቁመት ይዞ ጋዛ ደረሰ። በሙጃሂዶቹ ክፉኛ ጥቃት 80 ሴንቲ ሜትር ቁመቱን ብቻ ይዞ ከጋዛ ወጣ። አላሁመ ዚድ!


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months ago

?ዩክሬን የአሜሪካ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ላይ እንድትጠቀም በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፍቃድ ከተሰጣት በኋላ በስድስት አሜሪካና እንግሊዝ ሰራሽ ሚሳኤሎች ሩሲያን መምታቷን ተከትሎ ሃይፐርሶኒክ መካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል በዩክሬን ወታደራዊ ተቋም ላይ በመተኮስ ሩሲያ ምላሽ ሰጥታለች።

ፑትን "በምዕራቡ ዓለም የተቀሰቀሰው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘትን እየተላበሰ ነው" በማለት ተናግሯል።

?ቻይና በሳይበር ዘመቻ የአሜሪካን ኮሙኒኬሽን ኢላማ በማድረግ ምስጢራዊነት ያላቸው መረጃዎችን ማግኘቷ ተገልጿል።

‏salt Typhoon በመባል ከሚታወቀው የቻይና የስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው በሳይበር ስፓይኔሽኖች የአሜሪካን የመገናኛ አውታሮች አልፈው በአሜሪካ ታሪክ የከፋ ጥቃት ማድረሳቸው ተዘግቧል።

የሴኔቱ የስለላ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ ሴናተር ማርክ ዋርነር በሳይበር ጥቃቱ መደናገጣቸውን ሲገልፁ
"ይህ ለአሜሪካ የሳይበር ደህንነቷ የማንቂያ ደወል ነው። በታሪካችን እጅግ የከፋው የመገናኛ አውታሮች ጥሰት ነው በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ዋና ዋና የመገናኛ አገልግሎት ሰጪዎችን ጎድቷል" ብለዋል።

?የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ዩናይትድ ስቴትስ ውጥረቱን እያባባሰች ነው የኒውክሌር ጦርነት ሀገራቸው እንደምትጀምር አስጠንቅቀዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዩናይትድ ስቴትስ ውጥረቷንና የጦርነት ቅስቀሳዎቿን እያባባሰች ነው። የኮሪያ ልሳነ ምድር እንደአሁኑ የኒውክሌር ጦርነት አደጋ ገጥሞት አያውቅም ሲሉ ተናግረዋል።


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months ago
የሙስሊሙን አህጉራት የጦርነት አውድማ አድርገው መሳሪያቸውን …

የሙስሊሙን አህጉራት የጦርነት አውድማ አድርገው መሳሪያቸውን ፈተሹበት። ንፁሐኑን እየፈጁ ድሮናቸውን ሞከሩበት። የጎደለውን እያሻሻሉ ተራቀቁበት። ግን ግን በአላህ ፈቃድ እዚያው በከተማቸው መሐል በዩክሬንና በአውሮፓ መድረክ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ፍፃሜው ይሆናል ኢንሻ አላህ።

ያኔ አውሮፓውያን በሜዲትራኒያን ባህር ወደ አረብያን ምድር ይሰደዳሉ። መጠለያና ምግብ ፍለጋ ባዶግራቸውን ይራመዳሉ። ያስለቀሱን ሁሉ ያለቅሳሉ። ሙስሊሙን እንዳፈናቀሉ በተራቸው በስደተኞች ካምፕ መሐል ልጆቻቸውን ታቅፈው ያነባሉ። አዎ! ወራዶችን እንደሾሙብን ጨካኞቻቸው ሲገዟቸው እናያለን። የአላህ ኃያልነት በበደለኞች ላይ ሲዘንብ፣ የረህማን ፍትሐዊነት በታጋሾችና በተአምራቱ ባመኑ ላይ ሲንቧቧ እንመለከታለን ኢንሻ አላህ።


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

5 months, 1 week ago

ነፍሱን የሚሸጥልን ማነው?!

ዘመቻው ኡሁድ ሰሐቦች የተፈተኑበት ዕለት ነበር። ሙሽሪኮች የነቢን ጥርስ የሸረፉበት አዎ! ያኔ ሙስዐብ እስኪገደል ለነቢ ክብር ተከላከለ። አቡ ዱጃና ብዙ ቦታ በሰይፍ ተተርትሮ አላህን ተገናኘ።

በዚህ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ ተጣሩ። "ነፍሱን የሚሸጥልን ማን ነው?!" አሉ። ዚያድ ኢብኑ ሰከን ተነሳ ቁስሉ ደልቦ ሰይፍ መያዝ እስኪያቅተው ተዋጋ። በቁስሉ በህመሙ ከደሙ ተዋህዶ ከመሬቱ ወደቀ።

የኡሁድ ዘመቻ ቢጠናቀቅም የነብዩ ድምፅ ግን አሁንም ድረስ በየጆሯችን ያስተጋባል "ነፍሱን የሚሸጥልን ማን ነው?!" ይላል። የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን!

ሚስኪን ስታይ የረሱልን ንግግር አስታውስ "ማንነው ነፍሱን የሚሸጥልን?!" እኔ አለሁ በል። ከገንዘብህ ሳትሰስት ስጥ አይዟችሁ እያልክ አፅናና።

ለህመምተኛ ገንዘብ ሲሰበሰብ አሁንም የተናገሩትን አስታውስ "ማንነው ነፍሱን የሚሸጥልን?!" አለሁ በል። የምትችለውን ያህል አበርክት!

የቤተሰብ አለመግባባት ሲፈጠር ሰላምና ስምምነት ለመፍጠር የረሱልን ቃል አስታውስ "ማንነው ነፍሱን የሚሸጥልን?!" አለሁ ብለህ አስያርቅ።

ነፍስን ለአላህና ለመልእክተኛው መሸጥ በጦርነት ወቅት እጅግ የተከበረ ሽያጭ ቢሆንም በየቀኑ ግን ለአላህ ነፍስ የሚሸጥበት ገበያ አለና ራሳችሁን ሽጡ!

ዘገባው የዐብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ነው

Mahi Mahisho

ቴሌግራም
????
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 2 months, 4 weeks ago