ዮም ቲዩብ Yome tube

Description
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
@Bkcqbot ወይም
@Sfbkcbot ወይም @abfbkcbot
Youtube ቻናል subscribe በማድረግ አዳዲስ ቪዲዩዎችን ይመልከቱ ?
https://m.youtube.com/channel/UCsxlzPVjyuJJKGn9rAYbSrw
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 years, 11 months ago

"ሊቃጠል ያሰበ አንፖል ከአቅሙ በላይ ያበራል"
(ቡሩክ ካሳሁን)
ይህን አባባል ስሰማ ምን ትዝ ይለኛል? አንድ ጊዜ አንድ ሰው የጋራ ከሆነ መብራት ቆጣሪ ለብዙ ቤቶች ኤሌክትሪክ መቀጠል ይፈልጋል። ይህ ሰው እውቀቱ ኖሮት ሳይሆን "ድፍረት ያበላል ድመት" ይሉት አይነት መደፋፈር ውስጥ ገብቶ ነው። አብዛኞቻችን ቤት ውስጥ ያለው ቆጣሪ "ሲንግል ፌዝ" የሚባለው አይነት ሲሆን 220 ቮልት ወደ ቤታችን ሶኬትና መብራቶች ሀይል ያስተላልፍልናል።
ሌላኛው አይነት ደግሞ ለፋብሪካዎችና አንዳንድ መኖሪያ ቤቶችም ውስጥ ምናገኘው 3 ፌዝ ምንለው አይነት ነው። ይህኛው አይነት ቆጣሪ እያንዳንዱ "ፌዝ" ከ"ኒውትራል" ጋር 220 ቮልት ሚያወጣ ቢሆንም ቅሉ እርስ በእርስ (phase to phase) ሲለካ ግን 380 ቮልት የሚያወጣ ነው። እናም ሰውየው እንደብዙዎቻችን ቤት ያለው "ሲንግል ፌዝ" መስሎት ያገኛቸውን ሁለት ገመዶች ጠልፎ በል ግባ በለው ይለዋል። በዚህን ጊዜ ከሁለት "ፌዞች" ነበር የጠለፈው እና 220 ቮልት ለሚጠቀሙ ቤቶች 380 ቮልት ያዙልኝ በሞቴ ይላቸው ጀመር።
ልክ ቀጥሎ እንደጨረሰ በስፍራው ደርሼ "መብራት እየቀጠልክ ነው?" ብዬ ጥያቄ ከማቅረቤ አንዲት ሴትዮ እየሮጠች መጥታ… "ኸረ መብራቱ ልክ አይደለም መሰለኝ" አለች። "ምነው ምን ሆነ?" ብለን ስንጠይቃት "አይ ቲቪው ምናምን አይሰራም እእእ 0ሻማ አምፖሌ ደግሞ እንደ 100ሻማ በጣም ቦግ አለች" ብላ ነበር የመለሰችው። 0ሻማ አምፖሏ እንደ 100ሻማ አምፖል ስትምቦገቦግ የነበረችው እድሜዋ ሊያጥር ሲል ነበር። አንዳንድ ሰዎችም ከአቅማቸው (አስተሳሰባቸው ሊሸከመው ከሚችለው) በላይ ሀላፊነት፣ ስልጣን ይሸከሙና ልክ እንደ 0 ሻማ አምፖሏ የ100 ሻማ ያክል ያበራሉ፡፡ ያ ደግሞ የእድሜ ማጠር ምልክቱ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ልክ እንደ ኤሌክትሪኩ ያለ እውቀት በድፍረት በሚቀጥሉ፣ በሚሾሙ በሚሸልሙ ደፋሮች ነው፡፡ ቤቷ ሲቃጠል “አሁን በራልኝ” እንዳለችው እብድ ካልሆንን በስተቀር የ0 ሻማ አምፖል እንደ 100 ሻማ ሲንቦገቦግ ማይት የጤና እንዳልሆነ ልንረዳው ይገባል፡፡ ይኄ ትልቅ ውሳኔ የሚፈልግበት ሰዓት ነው፡፡ የጤና እንዳለሆነ አውቆ ችግሩን ለመፍታት መሞከር፤ አዋጪው መንገድ ነው፡፡ አልያም እንደ እብዷ “እሰይ እንዲህ ነው እንጂ መብራት ማለት” ብለን ቤት ውስጥ ያለው እቃ አንድ በአንድ ተቃጥሎ እስኪወድም መጠበቅ፡፡ ምርጫው የራሳችን ነው!!!

?      @burukassahunc
?? @burukassahunc
?      @burukassahunc

2 years, 11 months ago

Hello ?
I am Eyuel Ayele from YENETA (Young Engineers Nascent Electro-Mechanical & Technological Association), we have been selected to participate in TotalEnergies startup of the year Challenge. We highly demand your vote to proceed to the next stage.
Please ? take a minute of your time and vote for us via the link below ?, we highly appreciate your support, Thank you!
https://startupper.totalenergies.com/juries/tF0jMkGxQCV-3X2XtzeWFA/participations/24388/vote?order=random&scope=all

Totalenergies

Startupper of the Year

Manufacturing and selling a machine which can produce a plastic products using plastic wastes, the machine uses an injection molding type process for producing the recycled plastic products.

Hello ***?***
2 years, 11 months ago
***?*** [@burukassahunc](https://t.me/burukassahunc)

?      @burukassahunc
?? @burukassahunc
?      @burukassahunc

3 years, 1 month ago

Watch "ሐራሲቦን | እንደ ሐራሲቦን ቆላ ነፍሴ በፍቅርሽ ተቃጥላ | ኤፍሬም ስዩም | Ephrem seyoum Harasebon" on YouTube
https://youtu.be/OfuWmai0t74

YouTube

ሐራሲቦን | እንደ ሐራሲቦን ቆላ ነፍሴ በፍቅርሽ ተቃጥላ | ኤፍሬም ስዩም | Ephrem seyoum Harasebon

Watch "ሐራሲቦን | እንደ ሐራሲቦን ቆላ ነፍሴ በፍቅርሽ ተቃጥላ | ኤፍሬም ስዩም | Ephrem seyoum Harasebon" on YouTube
3 years, 3 months ago

"ፍካሬ እውነት"
{☞በዕውቀቱ ሥዩም☜}
'ሰማዩ እንዲህ እንደ ዛሬ እርቆ ሳይወረወር
ሁሉ እንዳሻው የሚቆርሰው÷
ሁሉ እንዳሻው የሚቆርሰው ግዙፍ እንጀራ ነበር'
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለው
ምክንያቱም ወድሻለው ÷
'አያቴ 300 ዓመታት ኖሩ
የመቶ አመት ሰው እያሉ ÷ ብርቱ ጽኑ ነበሩ
ዝሆን በጥፊ ጣሉ÷
አንድ ጥይት ተኩሰው ሶስት ነብሮች ገደሉ'
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለው
ምክንያቱም ወድሻለው ÷
'አባቴ ከሰዎች ሁሉ ይለያል
በዓይኖቹ ብቻ ሳይሆን በማጅራቱም ያያል'
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለው
ምክንያቱም ወድሻለው ÷
ግና ጅል እንዳልመስልሽ አይደለሁም ተላላ
በርግጥ 'በጄ!' 'በጄ!' ብላሻለች ነብሴ ሁሉን ተቀብላ
እውነት ማለት ከሚወዱት መስማማት እንጂ አይደለምና ሌላ!
_________________________

?      @burukassahunc
?? @burukassahunc
?      @burukassahunc

3 years, 3 months ago

ሀራሲቦን
(ኤፍሬም ስዩም)

እንደ ሀራሲቦን ቆላ
ነፍሴ በፍቅርሽ ተቃጥላ
ነዘርባብ እንዳይነድፈኝ አንድ እንዲሆን ሁለት ገላ
አለች እስከዛሬ አንችን ብላ ላንቺዉ ምላ
ትንሹ አካሌ ወርዝቶ
ሲታደስ ለመኖር ከወይንሽ ጠጥቶ
ነይ እንሂድ ይላል አንቺን ብቻ ሽቶ አንቺን ተመኝቶ
ፍቅሬ ጊዜ መጣ ጎህ ደም ቀደደ
ነገ ዛሬ ሆነ ዘመን ተሰደደ
ንፋስ አለፈና እሳት ተወለደ
ወይን አበቀለ ሮማን አፈራ
ልጅነት አረጀ ዉርዝውና ደራ
ያሻዉን ቢሆንም ቢበቅልም መከራ
አሉና መላእክት የሰማያት ጭፍራ
አትፍሪ ዳገቱን እንዉጣ ተራራ
ምልክቱ መስቀል ፍቅር ነዉ መከራ
እንደ ቀድሞስ ጠረን እንደ ናርዶስ እፍረት
እንደ ሰለሞን ፍቅር ሱናማዊት እንስት
በፍቅርሽ ዋኝቼ ልገባ ከገነት
ወቅታቸዉ ነጎደ አለፉ ነፋሳት
ይንቀለቀል ጀመር በልቤ ዉስጥ እሳት
እምቡጡም አካሌም ወረዛ
እሳቱም አየለ ቃጠሎዉም በዛ
እንደ ሀራሲቦን ቆላ አለችልሽ ነፍሴ በፍቅርሽ ተቃጥላ
ስሚኝ ፍቅሬ
ላውጋሽማ አንዳች ወሬ
እኔ ላንቺ ሀይልም ካለኝ እንደ ሶምሶን ድብቅ ነገር
ላልሰዉርሽ ስለፍቅር
ንግስናም ቢሰጡኝ እንደ ዳዊት
አንቺን ካገኘሁሽ ኦርዮን እንኳ ቢሞት
እግዜር ይላካቸዉ ይዉቀሱኝ ነቢያት
አንገትሽን አቅፌ እገባለሁ ገነት
ምድሪቱ አጊጣ ሰማይ ተሸልማ
ጨረቃ እንድታየን ቁልቁል በተደሞ
ዘወትር ከሚኖር ልቤ ባንቺ ታሞ
ልቤ በንቺ ታሞ
ነይ ተከተይኝ እንዉጣ ከአፋፍ
አራዊት ይጭኁ ይዘምሩ አእዋፍ
ድካም ሁሉ ይቅር ልቤ ባንቺ ትረፍ
ንፋሱ እንደሁ ነፍሷል እስኪያልፍ እሳቱ
ፍቅርሽ ስላወደኝ እንደ ናርዶስ ሽቱ
ነይ እንግባ ከገነቱ ካ”ማሩበት ምንጣፋቱ
ወሬዛዉ አካሌ እሳቱን አጥፍቶ
መኖር እንዲጀምር ከእቅፍሽ ገብቶ
ከደረትሽ ተጠግቶ
ከልቦናሽ ዋኝቶ
ፍቀጂለት ፍቅሬ እምቡጡ አካሌ ወርዝቶ
መኖር ስላልቻለ እሳቱ በርትቶ
እናም ፈጠን በይ ጊዜያት ሳያልፉ
በነደደው ልቤ ማያት ሳይደፉ
እሳቱን ሊያጠፉ ቀናቶች ሳይጎርፉ
ክረምቱ ሳይመጣ ክረምቱ ሳይመጣ
ዝናማት ሳይዘንቡ በረዶ ሳይወጣ
ቀኑ ሳይመሽብን ድጥ ሳይሆን ጨለማ
እሺ በይኝ እንስማማ
እንቡጡ ገላችን ሳለልን ወርዝቶ
መኖር እንድንችል እሳቱ ተረቶ
እጆቼን ያዥና አውጭኝ ከዚ ቆላ
ውሃሽን አፍስሽ ውረጅ በኔ ገላ
እንደ ሀራሲቦን ቆላ ምድር ልቤ በፍቅርሽ ተቃጥላ
አለች እስከዛሬ አንችን ብላ ላንችው ምላ፡፡

? @burukassahunc
?? @burukassahunc
? @burukassahunc

3 years, 3 months ago

Watch "መሀሙድ አህመድ ስንቱን አስታወስኩት ከግጥም ጋር | Mahmud ahmed sintun astaweskut with lyrics" on YouTube
https://youtu.be/xOMQ6gPmgCk

YouTube

መሀሙድ አህመድ ስንቱን አስታወስኩት ከግጥም ጋር | Mahmud ahmed sintun astaweskut with lyrics

ይህ የአንጋፋው ሙዚቀኛ መሀሙድ አህመድ ዘፈን እጅግ በጣም ስሜት ኮርኳሪ ከሆነ ግጥምና በትክክልም ወደ ድሮ በውድም ይሁን በግድ ሀሳብን ከሚያሳፍር ዜማ የተሰራ ድንቅ ዘፈን ነው። ግጥሙን እያበበቡ ሙዚቃውን ያጣጥሙ። I hope you will enjoy it.

Watch "መሀሙድ አህመድ ስንቱን አስታወስኩት ከግጥም ጋር | Mahmud ahmed sintun astaweskut with lyrics" on YouTube
3 years, 4 months ago

ኑሮ ውድነቱ እንዲህ ጩርቁን ጥሎ ሳያብድ በፊት አንድ ቀልድ ነበረች...
አንድ ታክሲ ረዳት ትርፍ ሊጭን ፈልጎ አንዲትን ሴት "እናቱ እስኪ ትንሽ ጠጋ በይ" ይላታል። የታክሲው ወንበር ጠባብ ነበርና ልጅቷ "ወንበሩ እግር ይይዛል አልጠጋም!" ስትል ትመልስለታለች። ይህን ጊዜ ታክሲ ረዳቱ በንዴት "የቀበሌ ዘይት አረግሽው እንዴ እግር ይይዛል ምትዪው" ሲል መለሰላት።
...የምትል።
የኑሮ ውድነቱ እየበርታ ሲመጣ ይቺን ቀልድ በመጠኑም ቢሆን ለመቀልበስ ምትችል ሌላ ቀልድ ተፈጠረች። "የቀበሌ ዘይት ሳይሆን ለቀበሌ ዘይት ምንሰለፈው ሰልፍ ነው የእግር በሽታ እየሆነብን ያለው።" የምትል። አሁን ኑሮ "ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ተሸጋግሮ" እግር የሚይዘው የቀበሌ ዘይት ሳይሆን ኑሮ ውድነቱ ነው፤ ምን ተይዞ ጉዞ?! "ዶሮ 650 ብር እየተሸጠ፤ ዶሮ ለገዛ ሰው መንግስት 1 የሪፐብሊካን ጋርድ አለመመደቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ንዝላልነት አመላካች ነው" ሲል አንድ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሰጠውን ትንታኔ በአንድ የራዲዮ ጣቢያ ሰምቼ ነበር።
በ2014 የኑሮ ውድነቱ ቢቻል ወርዶ እሱ ቢቀር እንደ ሎጥ ሚስት ባለበት ደርቆ ሚቀርበት አመት ያድርግልን። ሰላምና ፍቅር የዘወትር ዜናዎቻችን ይሁኑ። መልካም አዲስ አመት ይሁንልን።

መስከረም 1 2014 ዓ.ም
ቡሩክ ካሳሁን

?      @burukassahunc
?? @burukassahunc
?      @burukassahunc

3 years, 4 months ago

ጠቢቡ ሰለሞን ታላቅ ድግስን አዘጋጅቶ ከምድር ነገስታትን ከሰማይ መላዕክትን ጠርቶ ይጋብዝ ነበር። በዚህ ታላቅ ድግስ ትርምስ መሀል ግን አንድ የጠቢቡ ሰለሞን አገልጋይ መልአከ ሞት አተኩሮ እያየው እንደሆነ ያስተውልና ልቡ ይሸበራል። አገልጋዩ ትንሽ ቆይቶም ወደ መልአከ ሞቱ ቢዞር አሁንም አተኩሮ እያየው እንደሆነ ባወቀ ጊዜ ፈጠን ብሎ ወደ ጠቢቡ ሰለሞን ይሄድና "ጌታዬ መልአከ ሞት ከቅድም ጀምሮ እያየኝ ነው፤ ይሄ ነገሩ ምንም ምቾት አልሰጠኝም እና ቢያንስ ድግሱ እስኪያልፍ ከዚህ ዞር ብታደርገኝ" ብሎ ይጠይቀዋል። ጠቢቡ ሰለሞንም "ወደ የት መሄድ ትፈልጋለህ?" ብሎ አገልጋዩን ጠየቀው። "ህንድ ውቂያኖስ ዳርቻ ብሆን ደስ ይለኛል" ብሎ መለሰለት። ጠቢቡ ሰለሞንም "እንደ ቃልህ ይሁን" ብሎ አውሎ ነፋስን አዘዘለት። ግብዛው ተገባዶ ጨዋታ ሲጀምሩ ጠቢቡ ሰለሞን ወደ መልአከ ሞት ጠጋ ይልና "እኔ የምልህ ቅድም አንድ አገልጋዬም አተኩረህ ስታየው እንደነበር ነገረኝ ምነው በሰላም ነው?" ሲል ይጠይቀዋል። መልአከ ሞትም "አይ ዛሬ ማታ ከህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ሄደህ አምጣው ተብዬ ነበር እና እዚህ ሳየው ገርሞኝ ነው! ምን ሊያደርግ መጣ ብዬ" ብሎ መለሰለት ይባላል።

?      @burukassahunc
?? @burukassahunc
?      @burukassahunc

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana