የእሁድ ደረስ በቦሌ ጃዕፈር 📖📚

Description
ኡስታዝ መሀመድ ሲራጅ እና በኡስታዝ አቡል አባስ የሚሰጡ ደርሶች የድምፅ ፋይል 🔈
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago

መሸምደድ ያለባቸው አንገብጋቢ ነጥቦች ለሁሉም ሙስሊሞች
👇**
ሙስለሞ ከሆንክ የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ አስመልክቶ ማወቅ ያለብክ ወሳኝ ነገሮች

1_ የረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ) ስሞ ማነው?

ሙሃመድ አብነ አብዲላህ አብነ አብዲል ሙጠለብ አበነ ሃሽሞ:

ሃሽም ከቁረይሽ ጎሳ ነው: የቁረይሽ ጎሳ ደግሞ ከአረበ ዘር ነው: አረቦች ደግሞ የነብዩላህ ኢስማኢል አብኑ አብራሂም ዘር ናቸው።

2_ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መቼ ተወስዳ?

የዝሆን አመት።

3 እናታቸው ማን ትባላለች?

ኣሚና ቢንት ዋህብ።

4_ የተወስዱት የት ነው?

መካ ውስጥ

5_ እናታቸው ስትሞት ስንት አመታቸው ነበር?
ስድስት (6) አመታቸው

6_እናታቸው ከሞተች ቡሃላ ማን አሳደጋቸው?

አያታቸው አብዱል ሙጠለብ ከዛ እሱ ሲሞት ደግሞ አጎታቸው አቡጣለብ ።

7_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በልጅነታቸው ምን አይነት ስራ ይሰሩ ነበር?

እረኝነት ከዛ ደግሞ ንግድ።

8_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው ማን ትባላለች?

ኸዲጃ በንቱ ኹወይሊድ(ረ.ዐ)።

9_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች በአጠቃላይ ስንት ናቸው?

ሰባት (7) ናቸው።

(3) ወንዶች እና (4) ሴቶች።

10_ከኸዲጃ ስንት ልጅ ወስዱ?

ስድስት (6)። አንዱን ደግሞ ከማሪያ።

11_ልጆቻቸው ስማቸው ማን ማን ይባላል?

ወንዶቹ : ቃሲም, አብደላህ, አበሪሂም

ሴቶቹ: ሩቀያ, ዘይነብ, ኡሙኩልሱም, ፋጢማ

12_ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዋህይ ሲወርድባቸው ዕድሚያቸው ስንት ነበር?

አርባ (40) አመታቸው ነበር።

13_ ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) )ዋህይን ያቀበል የነበረው መላዒካ ስሙ ማን ይባላል?

ጅብሪል (ዓ.ሰ)።

14_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለመጀመሪያ ጊዜ ዋህይ ሲወርድላቸው የት ነበሩ?

(ሂራ) የሚባል ዋሻ ውስጥ።

15_መጀመሪያ ረሱል ላይ የወረደው ምን ነበር?

ሱረቱል አለቅ ከ ቁ.(1)

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ (አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡)

ከሚለው እስከ ቁጥር (5) ድረስ።

16_መጀመሪያ የሰለሙት እነማን ናቸው?

ከወንዶች: አቡበከር (ረ.ዐ)

ከሴቶች: ኸዲጃ (ረ.ዐ)

ከወጣቶች: አለይ (ረ.ዐ)

17_ ሰሃቦች ለመጀመሪያ ግዜ ወዴት ተሰደዱ?

ወደ ሃበሻ።

18_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ)በሚስጥር ዳዕዋ እያደረጉ ምን ያክል ቆዩ?

ሶስት (3) አመት።

19_የመዲና ሰዎች እንዲሰልሙ ሰበብ የሆነው ሰሃባ ማን ይባላል?

ሙስዓብ አበኑ ዑመይር (ረ.ዐ)።

20_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና ሰሃቦች ወዴት ነው የተሰደዱት?

ወደ መዲና

21_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መዲና ላይ የገነቡት የመጀመሪያው መስጅድ ማን ይባላል?

ቁባዕ መስጅድ።

22_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የዳዕዋ ዘመን ስንት ዓመት Φρ?

(23) ዓመት።

(13) ዓመት መካ ፧ (10) ዓመት መዲና።

23_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስንት ሃጅ አድርገዋል?

(1) ሃጅ፧ እሷም (ሃጀተል ወዳዕ) በመባል

ትታወቃለች።

24_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የት ነው የሞቱት?

መዲና ::

25_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በስንት ዓመታቸው ሞቱ?

በ (63) ዓመታቸው፡፡

26_ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ውስጥ ሰባቱን (7) ጥቀስ?

1_ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረ.ዐ)

2_ዓዒሻ ቢንት አቢበክር (ረ.ዐ)

3_ሰውዳ ቢንት ዘምዓ (ረ.ዐ)

4_ሃፍሳ ቢንት ዑመር (ረ.ዐ)

5_ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ (ረ.ዐ)

6_ዘይነብ ቢንት ጃህሽ (ረ.ዐ)

7_(ኡሙ-ሰለማ) ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያ (ረ.ዐ)

27_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ዘመቻዎች ውስጥ አምስቱን (5) ጥቀስ?

1_የበድር ዘመቻ

2_የኡሁድ ዘመቻ

3_የአህዛብ ዘመቻ

4_የኸይበር ዘመቻ

5_የ&tሁመካ ዘመቻ

28_የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ሚስታቸው ማን ትባላለች?

መይሙና ቢንትል ሃሪስ (ረ.ዐ)

29 ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በኛ ላይ ምን ምን ሃቅ አላቸው?

1_ንግግራቸውን ማመን

2_ሱናቸውን መከተል

3_ከነፍሳችን አስበልጠን መውደድ

4_ በሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ

30_የተመሩት የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ምትኮች እነማን ናቸው?

1_አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ)

2_ዑመር አበነል ኸጣብ (ረ.ዐ)

3_ኡስማን አበኑ አፋን (ረ.ዐ)

4_አሊይ አብኑ አቢጧአብ (ረ.ዐ)

31_ዙ-ኑረይን በመባል ሚታወቀው ሰሃባ ማነው?

ዑስማን አብኑ አፋን (ረ.ዐ)

32_የሸሂዶች አለቃ ሚባለው ሰሃባ ማነው?

ሃምዛ አበነ አብዲልሙጠለብ (ረ.ዐ)

33_የተሰላው የአላህ ሰይፍ ሚባለው ሰሃባ ማነው?

ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ (ረ.ዐ)።

34_በኢስላም የመጀመሪያዋ ሸሂድ ሴት ማን ነች?

ሱመያ ቢንቱል ኸያጥ (ረ.ዐ)።

35_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙዓዚን ማን ነበር?

ቢላል አብኑ ረባህ (ረ.ዐ)።

በመጨረሻሞ አላህ ሁላችንንም በጀነተል ፊርደውስ የረሱል ጎረቤት አድርጎ ይሰብስበን።

ውዱ ነቢያቸነ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት አውርዱ::**

@bolejafer
@bolejafer

2 months, 2 weeks ago

📌አሰላሙ አለይኩም
ነገ በሁዘይፋ መስጂድ ትልቅ የ ዳእዋ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ደርስ አይኖርም በ ዳእዋ ፕሮግራም ላይ እነ ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ ከሚሴ እነ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
እን ኡስታዝ አቡል ዐባስ ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ... የቻላችሁ ሄዳችሁ ታደሙ

@bolejafer
@bolejafer

2 months, 2 weeks ago

📌ተእሊም አል-ሙተአሊም 📓
تعليم المتعلم طريق التعلم
በኢማም ቡርሃን አል-ዚርኑጂ የተጻፈ🖌
በ ኡስታዝ አቡል አባስ የቀረበ 🎙

@bolejafer
@bolejafer

2 months, 3 weeks ago

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ማታ ደርስ እንዳለ ብናሳውቅም ቢሆን የአሏህ ውሳኔ ሆኖ ዛሬ በኡስታዝ ህመም ምክንያት ደረሰ አይኖረንም።

4 months, 2 weeks ago

?አሰላሙ አለይኩም ኢንሻአላህ በተለያዩ ቦታዎች ቁርአን የቀሩ ተማሪዎች ምረቃት ስለ ሚኖር ነገ ደርስ አይኖረንም.... ተመራቂ ተማሪዎች አላህ በቀራችሁት ተጠቅማችሁ ሌላውንም የምትጠቀሙ ተውሂድን አንግሳችሁ ሽርክን የምትዋጉ ለሱና ቆማችሁ ቢደአን የምትጥሉ አላህ ያድርጋችሁ
ማሻ አላህ እንኳን ደስ አላችሁ
@bolejafer
@bolejafer

4 months, 2 weeks ago

?ከደርስ የተቆረጠ
ኡስታዝ አልዋን

@bolejafer

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana