Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

Description
በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 1 week ago
ሀዋሳ***‼️***

ሀዋሳ‼️
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአምስት ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩ ተገለጸ‼️
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ 5 ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩን ያስታወቀው መረጃው ከፓርኩ ወደ ሀዋሳ ሐይቅ የሚገባ ፍሳሽ አለ መባሉንም ጠቁሟል።

ከሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ከቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ እርሻ ማሳ የሚገባ ፍሳሽ መኖሩም በኦዲት ሪፖርቱ መመለካቱን አስታውቋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተጠናላቸው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ውጪ በሆኑ ዘርፎች ሲሰማሩ ተገቢው ጥናት አልተደረገም ተብሏል።

በምርት ሂደት የሚጠቀሙባቸውን ኬሚካሎች ይዘት ለኮርፖሬሽኑና ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚያሳውቁበት መመሪያ አለመኖሩ ተገልጿል።
ጥቆማ👇
👉 ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣ከስር ባለው ሊንክ join አድርጉ👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 1 week ago

🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯👇👇

StoreX Dropshipping                                                                                          🎯Dropshipping ከእቃ አቅራቢ ምንም አይነት እቃ ሳይከፍሉና ሳይረከቡ ከራሱ ከአቅራቢው እጅ ላይ ለተጠቃሚው መሸጥ ሲሆን አየር በአየር እንደሚባለው የእቃው አቅራቢ ለገዢው እቃውን ሲሰጥ ድሮፕሺፐሩ የራሱን ትርፍ ይዞ ለአቅራቢው የእቃውን ዋጋ የሚከፍልበት ቢዝነስ ነው‼️
🎯Dropshipping የትም ቦታ ሆነው በስልክ ወይም በኮምፒውተር መስራት ስለሚቻል የቦታ እና የጊዜ ነጻነት አለው‼️
🎯ታዲያ ይህን ወጪ ሳይሆን ወቅቱን የዋጀ እውቀት የሚጠይቅ ስራ ከቤትዎ ሆነው በአንድ ወር የኦንላይን ስልጠና ማስተር ማድረግይችላሉ‼️
🎯Store X ስልጠናውን live በቀላል አማርኛ ልምድ ባላቸው ድሮፕሺፐሮች  ስለሚሰጥ ያልገባችሁን ለመጠየቅና ለመረዳት ተመራጭ ያደርገዋል‼️
🎯ዋናነት dropshipping አሜሪካ ገበያ ላይ እንደመሰራቱ ገቢው በዶላር ሲሆን ኮርሱ ከመጠናቀቁ በፊት ስራ ስለምናስጀምሮት ገቢዎ በዶላር ይቀየራል‼️

🎯በተጨማሪም የስልጠናው ሰአት ከስራም ሆነ ከትምህርት በኋላ ስለሆነ በጣም ምቹ ነዉ። ምናልባት በአጋጣሚ ክላስ ቢያመልጣቹ እንኳን ቀጥታ ስርጭቱ record ተደርጎ ስለሚሰጥ ምንም የሚያልፋቹ ነገር አይኖርም‼️

🎯ለስራው አስፈላጊ የሆነውን
MasterCard እና PayPal ያለምንም ተጨማሪ  ወጪ በነፃ ይሰጦታል ያውም ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኖትን ደብቀው Risk ውስጥ ሳይገቡ‼️

🎯በየስልጠናው መሀል አክቲቪቲ ሲሰራ ደግሞ Give away አለው‼️

🎯ከሁሉም በላይ የ StoreX ቤተሰብ በመሆኖ ብቻ Lifetime Support ያገኛሉ‼️

🎯በዝግጅታችን እና በአገልግሎታችን ጥራት ስለምንተማመን ኮርሱ መጠናቀቅ ካለበት ጊዜ ሶስት ቀን ካለፈው የከፈሉትን ብር ማስመለስ ይችላሉ‼️

🎯 አንድ ወር ይረዝምብኛል የተወሰነ እውቀቱ አለኝ የምትሉ ሰዎች በጠየቃቹን መሰረት የሶስት ቀን የ15 ሰአት  PREMIUM CLASS ማለትም Niche, Target market, MasterCard, Store building, Payment integration, Suppliers, Product listing and Organic traffic ሙሉ ስልጠናውን በአማርኛ መውሰድ የምትችሉበትን አማራጭ  አዘጋጅተናል‼️

🎯ለጥራት ሲባል ያዘጋጀነው ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ‼️
🎯የ30% ታላቅ ቅናሽ እስከ መጋቢት 15 ለሚመዝገቡ ብቻ
👉Join us
              በዚህ ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@StoreX_dropshipping

@StoreX_dropshipping

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

StoreX‼️
Let's find your store's X-factor with us‼️

1 month, 1 week ago

"እድሮች በህጋዊ መንገድ ካልተመዘገቡ እንቅስቃሲያቸው የህቡዕ አደረጃጀት ነው የሚሆነው” የአዲስ አበባ አስተዳደር‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ የሚገኙ ዕድሮች እና የዕድር ምክር ቤቶች ተመዝግበው “ሕጋዊ እውቅና” እንዲያገኙ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣ።

የከተማዋ የሴቶች፣ የህጻናት እና የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያወጣው ይህ መመሪያ የጸደቀው ባለፈው የካቲት ወር ሲሆን፣ መመሪያው ከዚህ በፊት የነበረውን የሰርኩላር የፈቃድ አሰጣጥ እንደሚሻር መግቢያው ላይ ሰፍሯል።

ከመመሪያው ዓላማዎች መካከል በከተማይቱ የሚገኙ ዕድሮች እና የዕድር ምክር ቤቶች ከወረዳ እስከ ከተማ በሁሉም ተዋረድ እንዲመዘግቡ እና ሕጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው ማድረግ አንዱ ነው።

በቢሮው የማኅበራዊ ጥበቃ ማስተባባሪያ፣ መከታተያ ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ከማል በከተማዋ የሚገኙ ዕድሮች በዚህ መመሪያ መሠረት ተመዝግበው ሕጋዊ ዕውቅና ማግኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ መሐመድ “ማንኛውም አደረጃጃት ሕጋዊ መሠረት ይዞ ነው መሄድ ያለበት፤ ካልተመዘገበ ግን ህቡዕ አደረጃጀት ነው የሚሆነው” በማለት መመዝገብ ግዴታ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ መሐመድ አክለውም “እኛም ዕድሮችን [ካልተመዘገቡ] በልማት ለማሳተፍ እና ሌሎች ሥራዎችን እንዲሠሩ [ለማድረግም] አይታወቁም። ስለዚህ ተመዝገበው ሕጋዊ አሠራሩን ተከትለው መሄድ አለባቸው” ብለዋል።

“ሕጋዊ ሳይሆኑ እንዴት ሕዝብን ያሳትፋሉ?” የሚሉት አቶ መሐመድ፤ “አንደኛ በሕግ አሠራር ሕዝብ ቢሰበስብ ሕገ ወጥ ተብሎ ሊታሰሩም ይችላሉ። ሁለተኛ ሕጋዊ ካልሆነ ሕጋዊ [መሆን] ካልፈለገ እኛም ደግሞ እንዲበተኑ ነው የምንፈልገው” ሲሉ ያክላሉ።

የዕድሮች ምዝገባ ሂደትን በተመለከተ መመሪያው “ማንኛውም ዕድር የሕግ ሰውነትን ለማግኘት በሥራ አስፈፃሚ አባላቱ ወይም በሕጋዊ ወኪሎቹ አማካይነት በቢሮው የቀረበውን ቅጽ በመሙላት በዚህ መመሪያ መሠረት የተመለከቱትን ሰነዶች ለወረዳው ጽ/ቤት ያቀርባል” ሲል ያትታል።

ዕድሮች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች መካከል የዕድሩ አባላት ስም እና መኖሪያ፣ የዕድሩ ንብረት፣ የዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ዝርዝር፣ የዕድሩ አድራሻ እንዲሁም የዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ ናቸው።
(ቢቢሲ)
ጥቆማ👇
👉 ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣ከስር ባለው ሊንክ join አድርጉ👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 2 weeks ago

በአማራ ክልል በተደጋጋሚ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ በኦሮሚያ ክልልም እንዲፈጸም ሊፈቀድ አይገባም‼️
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

#Ethiopia | በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ዓርብ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ ያልታወቁ ሰዎች በመከላከያ ሠራዊት አባል ላይ የፈጸሙትን ግድያ ተከትሎ የመንግሥት ወታደሮች የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ በቀበሌው አርሶ አደሮች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸማቸውን ፓርቲያችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል። የመንግሥት የጸጥታ አካላት ግድያ የፈጸሙ ግለሰቦችን ፈልገው ለሕግ ማቅረብ ሲገባቸው በአካባቢው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ቅዳሜ ከጠዋቱ ፪: ፴ - ፯ ሰዓት ባለው ጊዜ በእልህ በቀበሌው ነዋሪዎች ላይ በከፈተው ጥቃት ከአስራ ስድስት (፲፮) በላይ ንጹሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

አቶ በላይነህ ጌትነት፣ አቶ አወቀ ይበልጣል፣ አቶ ዳምጠው ስንቄ፣ አቶ ገበያው ካሴ፣ አቶ ሀብቴ አስናቀው፣ አቶ ሠናይ አስናቀው፣ አቶ አየኸኝ ወንዴ፣ አቶ ምንላርግህ ታፈረ፣ አቶ ይበልጣል ካስዬ እና አቶ ፈንታሁን በቃ መረጃቸው በስም ተዘርዝሮ የደረሰንና በመከላከያ ሰራዊት ከየቤታቸው ተለቅመው የተገደሉ መሆናቸውን ከመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠናል። በተጨማሪም ሶስት ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ አለመታወቁንም ለመረዳት ችለናል። የቀበሌው ነዋሪዎች መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ሟቾችን በክብር ለመቅበር ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የሁለት ሰዎች እሬሳ በጅብ መበላቱን የተቀረው አስከሬንም ሰብዓዊ ክብርን ባጣ መልኩ በየተገደሉበት ሥፍራ መቀበሩንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀበሌው አርሶ አደሮች መንግሥት "ኦነግ ሸኔ" እያለ ከሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳቸውን ለመከላከል በመንግሥት ተመዝግቦ የታጠቁትን የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የመከላከያ ሠራዊት በቤት ለቤት አሰሳ እንደወሰደባቸውና ይህ ደግሞ ለከፍተኛ የአደጋ ተጋላጭነት እንደዳረጋቸው አስረድተዋል። እናት ፓርቲ ባለው ግምገማ የጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ በአንጻራዊ መልኩ ወደ ተሻለ ሰላምና መረጋጋት እየተሸጋገረ ያለ አካባቢ የነበረ ቢሆንም የአባሉን ግድያ ተከትሎ በመከላከያ ሠራዊት የተወሰደው ሕገ ወጥ እርምጃና ይህን ተከትሎ የተፈጠረው ስጋት የአካባቢውን ሰላም በእጅጉ እንዳያናጋና በአንጻራዊ መልኩ ሰላማዊ እየሆነ የነበረውን አካባቢ ወደ ሌላ የጦርነት ቀጠና እንዳይለውጠው ስጋቱን ይገልጻል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፓርቲያችን:-

፩. በመከላከያ ሠራዊት አባል ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወግዛል።

፪. የመከላከያ ሠራዊት አባል ግድያን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች የፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለው የበቀል እርምጃን ወደ ኦሮሚያ ክልል የማዛመት ሥራ በመሆኑ በጽኑ ያወግዛል። ይህን ዘግኛኝ ድርጊት የመሩ፣ የፈጸሙና የተሳተፉ ኹሉ በአስችኳይ ጉዳዩ ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ይጠይቃል።

፫. አካባቢው ወደ ነበረበት አንጻራዊ ሰላም እንዲመለስ ኹሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ያሳስባል።

በመጨረሻም በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፤ ለሟቾች እረፍተ ነፍስን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ደግሞ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ጥቆማ👇
👉በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣join አድርጉ👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 2 weeks ago

ከሁለት ወር በኋላ በአዲስ አበባ የሚገኙ  መገናኛ ብዙኃን ለሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ክፍያ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ተባለ‼️
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የላባችን ፍሬ ያሉትን የሮያሊቲ ክፍያ ለማስጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ የሙዚቃና የቅጂ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የሙዚቃ ዘርፍ ማህበር ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ እንዳለው ከሁለት ወር በኋላ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሮያሊቲ ክፍያን በፌደራል ደረጃ መሰብሰብ እንደሚጀምር ገልፆል።

የሙዚቃው ዘርፍ የፈጠራ መብት ተካፋዮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ በ2009 ዓም በአዋጅ የፀደቀውን ህግ ለማስፈፀም ባለፉት አራት አመታት በርካታ ውጣ ውረጆችን አልፈን እዚህ ደርሰናል ያሉት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጂና ዘርፍ ማህበሩ ፕሬዝዳንት የክብር ዶ/ር አርቲስት ዳዊት ይፍሩ፤ አሁን ወደመጨረሻው ተቃርበናል ብለዋል።

"የሮያሊቲ ጉዳይ መሳካት የኤሊያስ መልካ ሐውልት ነው።" ያሉት ደግሞ የአ/አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ሃላፊው አቶ ሰርፀፍሬ ስብሃት ናቸው። አክለውም የኪነጥበብ ባለሙያውን ሸክም ለማቅለል የሮያሊቲ ክፍያ እና የኪነጥበብ ኢንቨስትመንት ኮድ መኖሩ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

"በጥቂት ሰዎች ትግልና ትጋት እዚህ ደርሶ ማየቴ እጅግ ደስ አሰኝቶኛል።" የሚለው የኢትዮጵያ የሙዚቃ የቅጂና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የቦርድ ሰብሳቢው ድምፃዊ ሐይሌ ሩት ነው። ማህበሩ በአስተዳደር፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በቴክኖሎጂ ሰዎች ተደግፎ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የሮያሊቲ ክፍያን በፌዴራል ደረጃ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እንደሚጀምር ገልፆ፤ በቀጣይም ከሆቴሎች (መዝናኛ ስፍረዎች) እና በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የሬዲዮና የቲቪ ጣቢያዎች ተግባራዊነቱ እንደሚታይ ጠቁሟል።

"ፍሬያማ ተግባራትን አከናውነን ስኬታማ ጉባኤንም ከአባላቱ ጋር አድርገናል።" የሚለው ሙዚቀኛ ሔኖክ መሐሪ በበኩሉ፤ በዛሬው ገለፃ አባላቱ ስለሮያሊቲ አሰባሰብና አከፋፈል ጥሩ ገለፃ ያገኙበት ነው ብሏል። አመታትን የፈጀው የሮያሊቲ ጉዳይ ወደተግባር ይገባል ተብሎ ከታሰበበት የዘገየው በተለያዩ ሻካራ ምክንያቶች እንደሆነ ገልጾ፤ አሁን ግን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ሲል ሙዚቀኞችና የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ጥቆማ👇
👉በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣join አድርጉ👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 2 weeks ago

“ሕዝቡ የፓርክ ሳር እና አበቦች የሚያገኙትን ያህል ውሃ እንኳን እያገኘ አይደለም”- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ አቅርቦት ችግር አለ‼️
ለአብነት በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 4፣5 እና 7 አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ ችግር እንዳለ እና በሳምንት አንድ ጊዜ የሚመጣው ውሃ በበቂ ሁኔታ ሳይዳረስ እና የሚመጣበትም ሰአት ለሊት በመሆኑ ለመቅዳት አስቸጋሪ በመሆኑ ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነገር ግን በተለያዩ አካባቢዎች ውሃ በሳምንት አንድ ቀን እንደሚመጣና ኃይል የሌለው በመሆኑ አንድ ጀሪካን ለመሙላት ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ይፈጃል ሲሉ ነዋሪዎች በምሬት ይናገራሉ። 

“እሱን ሌሊት ስንቀዳ አድረን ጠዋት ተነስተን ስራ መግባት አልቻልንም። ከሳምንት ሳምንት መድረስም ከብዶናል” ሲሉም ጠቁመዋል። 

በተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ የአካባቢው ሰው ገንዘብ በማዋጣት የታንከር ውሃ በመኪና እያስመጡ እየተጠቀሙ እንደሆነ እና ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን እንዲሁም በመኪናው ለሚመጣው ውሃ የመክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎች በእጅጉ እየተጎዱ መሆኑን ቅሬታቸውን አመላክተዋል። 
እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ልደታ መናፈሻ አካባቢ “ውሃ ከጠፋ አንድ ወር ሆኖታል” የሚሉት ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ እየገዙ እንደሚጠቀሙ፤ ነገር ግን ልብስም ሆነ እቃዎችን ለማጽዳት እየተቸገሩ መሆኑን ይናገራሉ። 

በተመሳሳይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቤተል ሮም ሰፈር ባጃጅ መጨረሻ “ንጹህ ውሃ ካየን አመት አለፈን በሳምንት ሁለት ቀን የሚለቀቅልን በጣም የቆሸሸ እና የተበከለ ነው። በመሆኑም ንጹህን ውሃ በሮቶ እያመጡ ይሸጣሉ ይህ ደግሞ ወንጀል ነው” ሲሉ ያሉበትን ችግር አስረድተዋል። 

በአንጻሩ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ምርት ጥራን ለማረጋገጥ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ብቻ 8 ሺህ ናሙናዎችን በመውሰድ የማይክሮ ባይሎጂካል፣ የባይሎጂካል እና የፊዝኮኬሚካል ምርመራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። 

በምርመራዎቹ መሰረትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዓለም  የጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት ንጹህ የመጠጥ ውሃ አምርቶ በማሰራጨት ላይ ይገኛል ተብሏል።
#አዲስማለዳ
ጥቆማ👇
👉በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣join አድርጉ👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 3 weeks ago
የፌዴራል\_መንግስት እና [#ህወሓት](?q=%23%E1%88%85%E1%8B%88%E1%88%93%E1%89%B5) ለ [#ፕሪቶሪያው](?q=%23%E1%8D%95%E1%88%AA%E1%89%B6%E1%88%AA%E1%8B%AB%E1%8B%8D) የሰላም …

የፌዴራል_መንግስት እና #ህወሓት#ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋገጡ‼️
#አፍሪካ ህብረት መሪነት ትላንት መጋቢት 2/ 2016 ዓ/ም በ #አዲስ_አበባ በተካሄደው የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ ግምገማ፤ የፌደራል መንግስቱ እና ህወሓት ህዳር 2022 በፕሪቶሪያ ለተደረሰው ዘላቂ ግጭት የማስቆም ስምምነት ተግበራ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋግጠዋል።
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ከተካሄደው የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ስብሰባ በኋላ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፤ ሁለቱ አካላት “በ #ትግራይ ክልል ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስቀጠል ሁለገብ ምክክር ለማድረግ እና በየጊዜው ለመመካከር ተስማምተዋል” ብሏል።

በተጨማሪም “በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ተመሳሳይ ስብሰባ ለማድረግ ወስነዋል” ተብሏል።

በስብሰባው #የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት፣ የ #ትግራይ ጊዜያው አስተዳደር/ህወኃት እና #የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ # የአውሮ_ህበረት፣ #የኢጋድ#የአሜሪካ እና #የአፍሪካ_ልማት_ባንክ ተወካዮች ያሳተፈ መሆኑ ተገልጿል።
👉ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 3 weeks ago

መንግሥት በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
ከ USAID ጋር በመተባበር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያስችላል በሚል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መድረክ በአማራ ክልል በ2023 የፈረንጆች አመት ብቻ 689 ግጭቶች የተመዘገቡ ሲሆን 22 የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸውን በመድረኩ ላይ ሪፖርት ቀርቧል። በግጭቱ ሳቢያ የማህበራዊ መስተጋብር እና ግንኙነት በእጅጉ እየተጎዳ መሆኑን እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተመላክቷል።
አዩዘሀበሻ
👉ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

1 month, 3 weeks ago
Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)
1 month, 3 weeks ago

አሳዛኝ ነው‼️
በቀን 26/06/2016 በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ገላውዲዎስ ቀበሌ አንዲት እናት ምጥ ተይዛ ጤና ጣቢያ ስትሄድ ለአንበሳሜ ሆስፒታል ሪፈር ትባላለች ። አንቡላንስ ስለሌለ ባለቤቷ ባጃጅ ተከራይቶ እየወሰዳት እያለ ሰኔ ማርያም እሚባል ቦታ ሲደርሱ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች አስቁሞ መታወቂያ ሲጠይቃቸው የቀበሌ መታወቂያ ሲያሳዩ እናንተማ ከእስቴ ስንመጣ ገላውዴዎስ ላይ ስለተመታን የእነዛ ሰዎች ናችሁ በማለት ቄሱ ባሏ ኧረ ሪፈርም ይዣለሁ ሰላማዊ ነኝ ቢልም ሊሰሙት ባለመፍቀድ ቄሱን ባሏንና የባጃጅ ሹፌሩን ገደሉት ። ምጥ የተያዘችዋ በድንጋጤ ከባጃጅ ወርዳ ስትወድቅ ወለደች የተወለደውም ሞተ ።
ደቡብ ጎንደር ላይ አንቡላንስ ባለመኖሩ 40 እናቶች 300 ህፃናት ህይወታቸው ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች ገልፀውልኛል። ተፋላሚ ሀይሎች አምቡላስ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ የእናቶችን እና የህፃናትን ሞት መታደግ አለባቸው ብለዋል።
ሰላም ከሁሉም በላይ ነው፣ሰላም ለሀገራችን🕊🕊🕊🕊
አዩዘሀበሻ
@ayuzehabeshaofficial
የማስታወቂያ እና ጥቆማ መቀበያ👇
http://t.me/ayulaw

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas