ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ ከግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ 260 ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆነው ዳቦ በሶስት አይነት መንገድ እየቀረበ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።
ለህብረተሰቡ የሚቀርበው ዳቦ ከ1ሺ በላይ በሚሆኑ በሸገር ዳቦ ማከፋፈያ ፣17 በሚሆኑ በመንግስት የግል ባለሀብቶች ጥምረት የሚቀርቡ እና 1700 በሚሆኑ የግል ዳቦ ቤቶች አማካይነት ለነዋሪዎች እንደሚደርስ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል።
በእነዚህ ዳቦ ቤቶች ላይ የሚቀርቡ ዳቦዎች በሸገር ዳቦ 70 ግራሙ 5ብር፣ የመንግስት የግል ባለሀብቶች ጥምረት የሚዘጋጀው በ6 ብር የሚቀርቡ ናቸው። እንዲሁም በግል ዳቦ መጋገሪያ ቤቶች የሚዘጋጁት ከ7 ብር ጀምሮ የሚሸጡ ናቸው።
ለህብረተሰቡ የሚቀርቡት ዳቦዎች ዝቅተኛው የግራም መጠናቸው 70 ግራም እንደሆነ እና ከተቀመጠው ግራም በታች መጋገርም ሆነ መሸጥ በየትኛውም መንገድ የሚቀርቡ ዳቦዎች ላይ የተከለከለ ነው ብለዋል። ለህብረተሰቡ የሚቀርቡት ዳቦዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ እና ከግራም በታች ሲጋግሩ የተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።
በዚህም በዘንድሮው 2016 በጀት አመት ብቻ ከ260 በላይ ከግራም በታች ሲጋግሩ የተገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። እንዲሁም ዳቦ መሸጫ ሱቆች የዋጋ ዝርዝር ማሳወቂ መለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸው አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ተናግረዋል።
#ብስራትሬዲዮ #አዩዘሀበሻ
===========≠==========
?ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ?
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
"ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን፡ እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥና መከተል ይኖርበታል። የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም።ሰላም ከሌለ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል።
ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል። የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል።ስለሆነም ወደ ሰላም፡ እንመለስ ብለን መወሰን አለብን።ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት።"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን"በሚል ርእስ በሸራተን አዲስ ዛሬ በተካሔደው መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ።
#አዩዘሀበሻ
===========≠==========
?ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ?
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
#በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት የመንግሥት የፀጥታ አካላት በክልሉ የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ሂዩማን ራይት ዎች አስታወቀ‼️****
በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት የፀጥታ ሃይሎች በህክምና ባለሙያዎች ፣ ህሙማን እና የጤና ተቋማት ላይ እስከ ጦር ወንጀል የሚደርስ ድርጊት መፈፀማቸውን አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም የሆነው ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
#በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ በተለያዩ ጊዜያት የፀጥታ ሃይሎች እና የሚሊሻ አባላት በ13 ከተሞች በሚገኙ የጤና ተቋማት፣ የህክምና ሰራተኞች እና አምቡላንሶች ላይ ጥቃት እንደፈፀሙ የሚያመላክቱ መረጃዎች እንደደረሱት የሰብአዊ መብት ተቆቋሪ ተቋሙ ሪፖርት ያሳያል።
“ቆስለው የመጡ ወታደሮች ከሞቱ ተጠያቂው አንተ ነህ፤ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ የጤና ተቋማት” በሚል ርዕስ ሂዩማን ራይት ዎች ያወጣው ባለ 66 ገጽ ሪፖርት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ተባባሪ ሚሊሻዎች በክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ጥቃቶች በዝርዝር አስቀምጧል።
ሂውማን ራይትስ ዎች ከነሐሴ 2023 አንስቶ እስከ ግንቦት 2024 ድረስ 58 ተጎጂዎችን እና ምስክሮችን የህክምና ባለሙያዎችንና የእርዳታ ሰራተኞችን ቃለመጠየቅ ማድረጉን ጠቁሟል።
በዚህም የፀጥታ አካላት በህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በህሙማን ላይ ድብደባ፣ ያለአግባብ እስር እና ማስፈራራትን ጨምሮ የተለያዩ የጦር ወንጀሎች ላይ መሳተፋቸውን አረጋግጠውልኛል ብሏል።
በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው ያለው ተቋሙ በአምቡላንሶች እንዲሁም በህክምና ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በክልሉ ያለውን የህክምና ድጋፍ አሰጣጡን አስቸጋሪ አድርጎታል ብሏል።
በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው ግጭት ሁሉም ወገኖች ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብሩ እና የንፁሃንን ደህንነት እንዲጠብቁ ተቋሙ ጠይቋል።
===========≠==========
?ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ?
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ከግለሰቦች ሞባይል በመንጠቅ ሱቅ ውስጥ ሲያከመቹ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️
አቶ ሱራፌል ቢያብል የተባሉ የግል ተበዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፀሚ ሲሆኑ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት 2 ተጠርጣሪዎች በጥቁር ሞተር ሳይክል ኮድ 2,A 19,21,6 ደ.ሕ( ደቡብ ህዝብ) መልኩ ጥቁር በሆነ 1ኛ ተጠርጣሪ እያሽከረከረ ፣ 2ኛ ተጠርጣሪ ሞተር ሳይክል ላይ ከኋላ በመሆን ከግለሰቡ ነጥቀው በፍጥነት እያሽከረከሩ ከአካባቢው ይሰወራሉ።
የግል ተበዳይ ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ያመለክታሉ ። ፖሊስም የግል ተበዳዩን አቤቱታ በመቀበል ባደረገው ክትትል ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ከሌቦቹ የሚረከቡ 2 ተጠርጣሪዎች በድምሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ህግን በተከተለ አግባብ ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ተከራይተው የሞባይል ጥገና የሚሰሩበት ሱቅ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ግለሰቦች ተቀምተው የተከማቹ 32 ስማርት ሞባይል ስልኮችን በኤግዚቢት ተይዘዋል ።
የንግድ ሱቆችን በመከራየት ወንጀል የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል ።
ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል የሚል ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
===========≠==========
?ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ?
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
በአማራ ክልል ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር በቅርብ ርቀት ላይ ባሉ አካባቢዎች ሰኞ ዕለት ጀምሮ እስከትናንት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልኛል‼️
በአዴት ከተማ ዙሪያ በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ሀይሎች መካከል ሰኞ ዕለት ውጊያ ሲያደርጉ ውለዋል ብለዋል። በአከባቢው የፋኖ ሀይሎች ወደ ከተማው ለመግባት መሞከራቸውን ተከትሎ ጠንክረ ያለ ውጊያ ስለመድረጉም ተናግረዋል። በአከባቢው ዙሪያ በተደረገ ውጊያ ለግዜው በውል ያልተወቀ ቁሳዊ እና ሰብአዊ ጉዳት ያደረሰ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት በአዴት ከተማ ዙሪ የመከላከያ ሰራዊት መኖሩን ገልፀዋል። በተመሣሣይ ከባህርዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘው መርዓዊ ከተማም ተመሳሳይ ውጊያ መደረጉ ተገልጿል። ትናንት ከሰዓት ጀምሮ በአብዛኛው ውጊያው መቆሙን ተናግረዋል።
===========≠==========
?ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ?
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
እንደሀገር ትልቅ ኪሳራ‼️
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ከ20 ሺህ ገደማ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በጦርነት ምክንያት 577 ተማሪዎች ብቻ ይፈተናሉ‼️****በአማራ ክልል አንድ ዓመት የሆነው የትጥቅ ውጊያ በትምህርት ላይ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩ ተመላከተ።
ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ብቻ ከ996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስራ ላይ የሚገኙት 32ቱ ብቻ ናቸው።
በ2016 የትምህርት ዘመን ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ከ539 ሺህ 996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ከ13 ሺህ አይበልጡም ተብሏል።
በብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎች ላይም ግጭቱ መስተጓጎል የፈጠረ ሲሆን የ6ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 791 ትምህርት ቤቶች 42 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች መፈተን ቢኖርባቸውም ለፈተና የሚቀመጡት ከ12 ትምህርት ቤቶች የመጡ 506 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
38 ሺህ 203 ተማሪዎች የ8ተኛ ክፍል ፈተና እንደሚፈተኑ ቢጠበቅም በዞኑ ባለው ከፍተኛ ጸጥታ ችግር ሳቢያ መፈተን የሚችሉት 431 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል። ከ19 ሺህ 657 የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መካከል ለፈተና ዝግጁ የሆኑት 577 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
?ያልተሰሙ አዳዲስ አለማቀፍና ሀገርአቀፍ ዜናዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join አድርጉ???
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana