የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

Description
بسم الله الرحمن الرحيم


📮እንኳን ወደዚህ ቻናል ተቀላቀሉ‼️


በዚህ ቻናል ቂርአቶችን፣ ሙሐድራዎችን፣ዳዐዋዎችን እና ሌሎችንም ከአረብገንዳ መስጂድ በቀጥታ የምታገኙበት ቻናል ነው።

ሃሳብ አስተያዬት ካለ በዚህ ያድርሱን ⤵️
@ye_Arebgenda_mesgid_wetatoch_bot
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 months ago

3 months ago

(وَلَمْ أَكُنۢ بِدُعَآئِكَ رَبِّ شَقِيًّۭا)

🥀 አንተን በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! ምንጊዜም ዕድለ ቢስ አልሆንኩም

አልሀምዱሊላህ

3 months ago

ኸሚስ ❤️❤️

በሰለዋት የደመቀ ምሽት ተመኘሁላችሁ አህባቢ 🥰🥰

3 months, 1 week ago

*ለሁሉም ነገር ጊዜ መልስ ይሰጠዋል ዋናው ነገር ሶብር ነው*?

3 months, 1 week ago

የልብ እርጋታን ማገኘት ከደስታ በላይ ነዉ
ደስታ ሰአታት ነዉ  የልብ እርጋታ ግን ሁሌም ነዉ
ትልቁ ምክንያት አላህን ማዉሳት ነዉ
ألا بذكر اللهِ تطمئنُ القلوب"
"ልቦች አላህን በማዉሳት ይረጋጋሉ"

اللهم ارزقنا الأنس بك، والحياء منك، والطمأنينة بذكرك ...

طاب يومكم بذكر الله . ??

3 months, 1 week ago

.

❤‍? هَلْ جَزَاءُ الْإِحْسَانِ إِلَّا الْإِحْسَانُ

የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን

3 months, 1 week ago

?የምሽት መልእክት?

ምናልባት ጠዋት ከእንቅልፋችን ላንነቃ እንችላለን'ና ተውበት እናድርግ!!

5 months, 3 weeks ago
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
6 months ago

የኢልም አሻራ በጋራ!    #بصمة_العلم

በሸይኽ ሀሰን ሓሚዲን የሚመራው ወሎ መናገሻ ደሴ ከተማ የሚገኘው ሸይኽ አደም ሙሳ ኢስላማዊ ኮሌጅ ላለፉት 4 አመታት ያስተማራቸውን ኡስታዞች እና ዱዓት እሁድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ል ከጧቱ 02:30 ጀምሮ በደሴ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ያስመርቃል።

በዕለቱ የኮሌጁ መስራች እና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሸይኽ ሀሰን ሓሚዲንን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ኡለማዕ እና ዱዓቶች በክብር እንግድነት የሚገኙ ሲሆን እርስዎም በዚህ ታላቅ እና ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ ይታደሙ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ለበለጠ መረጃ
0913366673
0921042700
0910139340

በእነዚህ የማህበራዊ ድህረገጾች ያገኙናል

YouTube
http://surl.li/yrofrq
Facebook
http://surl.li/nvxfhm
Tiktok
http://surl.li/evhnxq
Telegram channel
https://t.me/sheikhademmusacollege
Sheikh hassen hamiddin "fb"
http://surl.li/mpavlb

6 months, 2 weeks ago

እንደዛሬው ባለ ቀን... ለይሉ ጁምዓ ሲሆንና የኸሚስ ጀንበር ወደ ማደሪያዋ ስትሸኝ፤ የመልከ ብዙ ትሩፋት ከንዝ የሆነው የሶለዋት ሞገድ አየሩ ላይ ይናኛል። አላህ ያገራለት አማኝ ደግሞ እንዲህ ባለ ቀን ከእንቅልፍ ተኳርፎ፤ የከውኑን ሞገስ፣ የዓለሙን ዓይነታ የሚያወድሱ ዓይነተ ብዙ ሶለዋቶችን ያለመታከት እየተቀኘ ሌቱን ሕያው አድርጎ ያነጋል።

አዎ! እንደዛሬው ባለ ምሽት ከነፋሱ ጋር የሚነፍሰው ሶለዋት ዳር እስከ ዳር በቅብብሎሽ ሲከረር፤ የዩኒቨርሱ ብሔራዊ መዝሙር የሆነ ያህል ልብ ያሞቃል።
اللَهُمَّ صلِّ وسَلِم وبَارِك على سيدنا محمد (ﷺ)
youtube// @arebgenda_mesjid ​
t.me// @arebgendamesjid
Instagram // arebgenda_mesjid
tik tok //arebgenda_mesjid
Facebook //mesjid5043

በመጎብኘት የማህበረሰብ ሚዲያዎቻችንን በሚለቀቁ ትምህርቶች እና ጠቃሚ ምክሮች ይከታተሉ።
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የሚዲያ ማዕከል

9 months, 1 week ago

8ቱ የጀነት በሮች

ነቢዩ (ﷺ) ስለ ጀነት በሮች ብዛት ሲናገሩ

«ጀነት ስምንት በሮች አሏት። አንደኛው አር-ረያን ሲሆን ከጿሚዎች በቀር የሚገባበት የለም።» ብለዋል።
(ቡኻሪይ 3257/ ሙስሊም 1152)

በሌላ ሐዲሳቸው ደግሞ፦

«አንድ ሰው ለአላህ ብሎ ሁለት ነገሮችን ሰደቃ ቢሰጥ አላህ ጀነትን ግባ ይለዋል። እንዲሁ ሶላትን የሚሰግዱ በሶላት በር ግቡ ይባላሉ። በጂሐድ የተሳተፉ በጂሐድ በር ግቡ ይባላሉ። ሰደቃ የሰጡ በሰደቃ በር ግቡ ይባላሉ። ፆም የፆሙ በአር-ረያን በር ግቡ ይባላሉ።» አሉ። አቡበክር ሲዲቅም «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በሁሉም በር እንዲገባ የሚጠራ ይኖራልን?» አሏቸው። ነቢዩም (ﷺ) «አወ! አንዱ አንተ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ።» አሉ።»
(ቡኻሪይ 1897/ ሙስሊም 1027)

ዑለማዎች ከእነዚህና ሌሎች ሰነዶች በመነሳት የስምንቱን በር ስሞች ያስቀመጡ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦

❶ ባብ አስ-ሶላት
♦️ ሰጋጆች የሚገቡበት

❷ ባብ አል-ጂሐድ
♦️ በጂሐድ የተሳተፉ የሚገቡበት

❸ ባብ አስ-ሰደቃህ
♦️ ሰደቃ የሰጡ የሚገቡበት

❹ ባብ አር-ረያን
♦️ ጿሚዎች የሚገቡበት

❺ ባብ አል-ሐጅ
♦️ ሐጂ ያደረጉ የሚገቡበት

❻ ባብ አል-ኢማን
♦️ ፅኑ ኢማን ያላቸው የሚገቡበት

❼ ባብ አል-ካዚሚን አል-ገይዝ
♦️ ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩና ይቅር ባዮች የሚገቡበት

❽ ባብ አዝ-ዚክር
♦️ ዚክር የሚያበዙ የሚገቡበት
? የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች ?

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 months ago