ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
በመጨረሻም:- በሸዋ ያሉ የአገዛዙን የጥፋት ኃይሎች ላይ እርምጃችንን በመቀጠል በጠላት የተያዙ አካቢቢዎችን ነፃ ለማውጣት በምናደርገው ተጋድሎ የትኛውም የወገን ኃይል ከጎናችን እንዲቆም እያሳሰብን፤ ከጠላት ጋር የተሰለፉ የትኞቹም ኃይሎች በሸዋ ታሪካዊ ግዛቶቻችን ምንም አይነት እድል ፈንታ አይኖራቸውም። አለኝ የሚሉት ሀብትና ንብረት በሙሉ በገጠር ያለ እርሻ ሳይቀር የሚወረስና ለህዝብ የሚከፋፈል መሆኑን በዚሁ እየጠቆምን በምንወስደው እርምጃ ሁሉ ለህዝባችንና ለነፃነታችን ስንል የምናደርገው ስለሆነ ከጠላት ጋር የተሰለፋችሁ በሙሉ አሁንም ባላችሁ ጊዜ ፈጥናችሁ ውጡ የሚል ጥሪያችንን እናቀርባለን። በህዝባችን መሐል የምትገኙ ጥቂት ለዚህ አገዛዝ አማራነትን አዋርዳችሁ በባንዳነት ተግባር የምትኖሩ፤ ለጥፋት ኃይሎች ልዩ ልዩ ድጋፍ የምታደርጉ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድትመለሱ እናስጠነቅቃለን።
ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ወታደራዊ ዋና አዛዥ
ክብር ለተሰውት !
በዚህ ልክ ሸዋን ከፍ ሲል አማራን አንገት ለማስደፋት እና ለመጨፍጨፍ ወደ ሸዋ የገባውን የአገዛዙን ሶላቶ ባንዳ ሰራዊት ግንባር ለግንባር በመፋለም እና በመማረክ ዕዛችን ከፍተኛ የአቅም ግንባታ አድርጓል። በዚህ መሠረት ዕዙ እስካሁን በስሩ ከሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች ማለትም አርበኛ መሐመድ-ቢሆነኝ ክፍለ ጦር፣ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር፣ አስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦር፣ አፄ ሚኒሊክ ክ/ጦር፣ አፄ ዘረያዕቆብ ክፍለ ጦር በተጨማሪ በክፍለ ጦር ቁመና ያደጉ ፬ ብርጌዶችን የክፍለ ጦር ዕውቅና ሰጥቷል። እነዚህ አዲስ ዕውቅና ያገኙ ክፍለ ጦሮች በትጥቅም ሆነ በሰው ኃይላቸው የጠነከሩ ሲሆኑ ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር፣ አርበኛ አስቻለው-ደሴ ክ/ጦር፣ 7ለ70 ክ/ጦር እና አርበኛ ራምቦ ክ/ጦር የሚል ስያሜ አግኝተዋል።
በዚህ መሠረት፦
ኮር ፩ (አምደ-ጽዮን ኮር)
- አርበኛ ራምቦ ክፍለ ጦር
- አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር
- ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር
- 7 ለ 70 ክ/ጦር በመሆን ("አምደ ጽዮን ኮር") ተመስርቷል።
ኮር ፪ (አርበኛ መሐመድ-ቢሆነኝ ኮር)
- አስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦር
- አፄ ዘርዐያዕቆብ ክ/ጦር
- ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር
- አስቻለው ደሴ ክ/ጦር በመሆን አርበኛ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ተመስርቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከክፍለ ጦሩ ምስረታ በፊት የመሐመድ-ቢሆነኝ ክፍለ ጦርን ከክፍለጦር እስከ ሻለቃ አመራሮችና አባሎችን የውስጥ ግምገማ በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን እና የስራ አቅጣጫዎችን ይፋ አድርጓል። በግምገማ ሰነድ ውስጥ የአማራ ፋኖ የትግል መነሻና መዳረሻ፣ የዕዙን አመሰራረት፣ በአማራ ፋኖ አንድነት እንዲሁም ዛሬ ላይ ያለንበትን ቁመናና የጠላትን አሰላለፍ በተመለከተ፣ የትግላችንን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም፣ የድክመቶቻችንን መፍትሄ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ግምገማው እና ውይይቱ አጠናቋል።
በውይይቱም የክፍለ ጦር ፣ የሻለቃ አመራር እና የሻምበል አመራሮች ላይ የነበሩ የስራ አፈፃፀም ክፍተቶች በዕዙ ከፍተኛ የኮማንድ አመራሮች ተገምግመው የአቅም ግንባታ እና ግብረ መልስ ተሰጥቶባቸዋል። እንዲሁም የፋኖ የትግል ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ተገምግሞ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል::
በመጨረሻም አማራን ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለማትረፍና ድረሱልኝ ለምትለን ኢትዮጵያ ሀገራችን በፍጥነት ጠላትን ደምስሰን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሰላም የሰፈነባትን፣ የሰው ልጅ በዘሩ፣ በቀለሙ፣ በሀይማኖቱ ተለይቶ የማይጨፈጨፍበትን፣ ደም የማይፈስባትን እንዲሁም ሀብት ንብረት የማይወድምባትን እና በኢኮኖሚ ያደገች ሀገርና ሀገረ-መንግስት ለማዋቀር ሁሉም የትግል ጓዶቻችን፣ አመራሮቻችን እና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆነን እንድንታገል እያልን በአክብሮት ጥሪያቸንን እናስተላልፋለን።
ስብሰባውና ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ የስብሰባውን ዓላማ በመረዳት የትግላችንን ዓላማ ለማሳካት፣የህዝባችንን ሰቆቃ ዕድሜ ለማሳጠር፣ የተሰውትን ፋኖ ወንድሞቻችንን ላንረሳ በሚልና የውስጥ አሰራሮችን ለማሳለጥ ይጠቅመን ዘንድ ቃለ መሀላ በመፈፀም የተጠናቀቀ መሆኑን እንገልፃለን።
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!!
ድል ለፋኖ!!!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!!
ህዳር 17/2017 ዓ.ም
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት በሚል በምስራቅ ሐረርጌ በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያ መወሰዳቸው ተሰማ!
የአማራ ሕዝብ ወንድማችን እንጂ ጠላታችን አይደለም፡ ልጆቻችን ለማነው የሚዘምቱት የሚል ጥያቄ ያነሱ ወላጆች ድብደባ እና እስር እንደተፈፀመባቸውም ታውቋል።
ገዢው የብልፅግና ቡድን "ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት፡ አባይን ሳይሻገር እዛው ባለበት እናስቀረው" በሚል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ወጣቶችን አፍሶ ወደ ሁርሶ እና ጦላይ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች መውሰዱን የመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ወጣቶቹ ታፍሰው የተወሰዱት በዞኑ ስር ባቢሌ፣ ጃርሶ፣ ጪናቅሰን፣ ኮምቦልቻ እና ኤረር በተባሉ ወረዳዎች ሲሆን የወጣቶቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስመለስ እስከ 100 ሺ ብር ተጠይቀዋል ነው የተባለው።
በጅምላ ታፍሰው ከሚወሰዱት ወጣቶች መካከል ዕድሜያቸው 13 እና 14 ዓመት የሆነ ታዳጊዎችም ይገኙበታል ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በባቢሌ ወረዳ ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ጦላይ እና ሁርሶ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።
ወጣቶቹ በጅምላ ከታፈሱ በኋላ በባቢሌ ወረዳ ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ የሚደረጉት ምን አልባት ልጆቻቸው ወደ ውትድርና እንዳይሄዱ የሚፈልጉ እስከ 100 ሺ ብር ከፍለው ማስለቀቅ የሚችሉ ወላጆች ካሉ እስኪመጡ ድረስ ለመጠበቅ ሲሆን፡ ወላጆቻቸው የተጠየቀውን የገንዘብ መጠን መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች ከቀናት በኋላ ወደ ማሰልጠኛ ይወሰዳሉ ነው የተባለው።
ከባድ የደፈጣ ጥቃት ከሊቦከምከም በቅርብ ርቀት!
በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ከአምቦ ሜዳ በቅርብ ርቀት ግራጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከባድ የሆነ የሽምቅ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።
በጥቃቱ በርካታ የብልፅግና ፓርቲ መከላከያ ሰራዊት አባላት የተገደሉ ሲሆን ቁስለኞች ለሕክምና ወደ አዲስ ዘመን እየተወሰዱ መሆኑን ለማረጋገጥ ችሏል።
ከጥቃቱ የተረፉት ወታደሮች የአከባቢው ነዋሪ አስከሬን እና ቁስለኛ እያነሳ በተሽከርካሪ እንዲጭን ያዘዙ ቢሆንም፡ ነገር ግን ሕዝቡ "የጓዶቻችሁን አስከሬን ከወደቀበት አንስተን በተሽከርካሪ ከጫንላችሁ በኋላ መረጃ ታወጣላችሁ በሚል ምክኒያት ልክ እንደዚህ ቀደሙ ትገድሉናላችሁ"በሚል አንተባበርም ብሏል።
በዚህም በአከባቢው ውጥረት መንገሱ ነው የተሰማው።
መረጃው በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ነው።
የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ለፋኖ ምስጋና አቀረቡ!
"የእውነት አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን"
///////
አማራን ዘር ማጥፋትና የአማራ የሆነውን ሁሉ ማውደምን ዓላማ አድርጎ ጦር ያወመተው ብልጽግናው፤ ።በሺዎች የሚቆጠሩ የስርዓቱ አገልጋይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተማርከው በፋኖ እጅ ይገኛሉ።
ፋኖ እነዚህ ምርኮኛ ወታደሮችን የአለም አቀፍ የምርኮኛ አያያዝ ሕገ ደንብን ባከበረና አማራዊ እሴትን በጠበቀ መልኩ ተንከባክቦ እንደያዛቸው የመረብ ሚዲያ የግምባር ዘጋቢዎች በተንቀሳቀሱበት ቀጠና ለመመልከት ችለዋል።
ከምርኮኛ ወታደሮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ "ይህ ስርዓት የኦሮሞ ስርዓት ነው።እንዳይፈርስ መታደግ አለባችሁ" በሚል ፕሮፓጋንዳ ተታለው መከላከያ ሰራዊትን እንደተቀላቀሉ ይናገራሉ።
የፋኖ አባላቱም በፈቃደኝነት አላማቸውን ተጋርተው ከእነሱ ጋር ለመቀላቀል የፈለጉ ምርኮኛ ወታደሮችን የተሀዲሶ ስልጠና በመስጠት እንዲቀላቀሏቸው ያደረጉ ሲሆን፡ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ የፈለጉትን ደግሞ የትግሉን አላማ በማስረዳትና የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን በሰላም የሚሄዱበትን ቀጠና በማመቻቸት እየሸኙ ይገኛሉ።
ከነዚህ መካከል በወሎ ቀጠና እየተካሄደ ባለው ውጊያ ከ2016 ዓ/ም መጨረሻዎቹ ወራት ጀምሮ የተማረኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ የሚፈልጉ ምርኮኛ ወታደሮች የሚሄዱበትን ሰላማዊ ቀጠናና የመጓጓዣ ወጪ በፋኖ ተሸፍኖላቸው የተሸኙ ሲሆን፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም መቀላቀላቸውንም አሳውቀዋል።
ልጆቻቸው ከሞት ተርፈው በሰላም የመጡላቸው በወለጋ፣ በሸዋ፣ በቦረና እና በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ የምርኮኛ ወታደር ወላጅ የሆኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት፤ ለፋኖ ምስጋና ማቅረባቸውን ነው መረብ ሚዲያ የፋኖ አመራሮችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።
በፋኖ ከተማረከ በኋላ የመጓጓዣ ወጭ ተሸፍኖለት የተሸኘ ልጇን በሰላም ያገኘች በምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ ነዋሪ የሆነች አንዲት እናት ምርኮኛ ልጇ ይዞት በነበረው የፋኖዎች አድራሻ መሠረት ስልክ በመደወል "ልጄን ዳግመኛ እንደወለዳችሁት ነው የምቆጥረው። ይህ አካሄዳችሁ ትግላችሁ ሀቅ እንዳለው የሚያስመሰክር ነው። የእውነት አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነው የፋኖ አመራሮቹ ለጣቢያችን የገለፁት።
ምርኮኛ ልጃቸው በሰላም ወደ ቤቱ የተመለሰላቸው ሌላኛው በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ አባት "ልጄ በፋኖ መማረኩን ስሰማ አለቀስኩ።ምክኒያቱም እኛ በቀበሌ ስብሰባም፡ በኦቢኤንና በኦኤሜን ቴሌቪዥንም የሚነገረን ፋኖ ገዳይና አራጅ ነው በሚል ነው። አሁን ግን የትግላችሁን ሀቀኝነት አረጋግጣችሁልኛል። ዋቃ(አምላክ) ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ልጃቸው በፋኖ ተማርኮ ድምጹን በስልክ የሰሙ የሀዋሳ ነዋሪ፤ "ሊቀ መልአኩ ሚካኤል ስለቴን ሰምቷልና አመሰግናለሁ" ብለው ስለት ማስገባታቸውን ዘግበን ነበር።
አማራን ከብሔራዊ የህልውና አደጋ ራሱን እንዳይከላከል የሚደረገው የኦሮሙማ ሃይሎች ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ራሱን የብልፅግና መንግስት ነኝ የሚለው ፋሺስት ሃይል በአማራ እና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ሰፊ ብሔር ተኮር ጥቃት እንድከፈት የሚያደርገውን ዘመቻ ብሔር ብሔረሰብ እና ህዝቦች እንዲያወግዙት የአማራ ፋኖ ያሳስባል።
ህዝብ እያፈለሰ እና ሃገር እያፈረሰ ያለው ብልፅግና ከአንድ ዓመት በፊት በኦሮሞ የሚሊሻ ሃይሎች የሞተን ወጣት የአማራ ፋኖ አስገደለው በማለት እያስተጋቡት ያለውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ የአማራ ፋኖ በፅናት ያወግዘዋል።
እኛ ጠንካራ አማሮች ነን፤ የአባቶቻችን ልጆች ነን።
ክቡሩን የሰው ልጅ ህይዎትም እንጠብቃለን።
የፋሺስቱ ሃይሎች የፕሮፓጋንዳ ክንፍ ብሔርን ከብሔር በመነጣጠል ሃገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ነውር በፍፁም አንቀበለውም።
የአማራ ፋኖ የሚታገለው በብልፅግና ሃይሎች የሚደረሰውን ሁለገብ ጥቃት እንጅ የግለሰቦችን ሰብአዊና ድሞክራሲያዊ መብት ለመንጠቅ አይደለም።
የአማራ ፋኖ የመታገያ ዓላማ ያለው ፣ጠላትና ወዳጁን ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣ለአማራ ህዝብ መብት እና ጥቅም የሚታገል በዋናነትም የአማራን ህዝብ ከተደቀነብን ብሔራዊ የህልውና አደጋ ለማውጣት እንጅ ለተራ ጥቅመኝነት እና ፓለቲካ አይደለም።
ስለሆነም የአማራ ህዝብ የበርካታ ማህበራዊ ወረቶች ባለቤት ሲሆን ብልፅግና አክራሪ ሃይሎች በሚያደርጉት አሉታዊ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ከኦሮሞ እና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰብ እና ህዝቦች ጋር በጠላትነት እንዲታይ የተደረገውን ሁለንተናዊ ጥቃት በበሳል አሰተሳሰብ እና አርቆ በማሰብ ለአብሮነት የከፈልነውን ሁሉ ነገር በፅናት የምናስቀጥል መሆኑ ይታወቃል።
ስለሆነም የአማራን ህዝብ በሴራ ፓለቲካ ህልውናውን እንዲያጣ የተቃጣውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት የአማራ ህዝብ እና የአማራ ፋኖ አይቀበለውም።
አማራነትን ለመናኛ ጥቅም እና በመሰል አሻጥሮች አሳልፎ መስጠት ዘመኑ ያለፈበት ፋሺን ነው።
ስለዚህ በኦሮሞ እና በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገው ያለው ዘር ተኮር ቅስቀሳ የአማራ ፋኖ በፅናት የሚያወግዘው ሲሆን መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውን ሁሉ ድርጊቱ በብልፅግና ሃይሎች የተፈፀመ መሆኑ ታውቆ የአማራን ህዝብ ከሌሎች ብሔሮች ጋር ደም ለመቃባት የሚደረገውን ሙከራ እንዲታወግዙ በጥብቅ እያሳሰብን ወንጀሉም በገለልተኛ ሃይሎች እንዲጣራ እየጠየቅን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችም የአማራ ፋኖን ጥሪ እንድቀበሉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ነፃነታችን በክንዳችን
ድል ለአማራ ፋኖ
"መቃብር ቦታውን አፍርሼ መናፈሻ እሰራበታለሁ"
በየሄደበት እንደ ሲኖ ትራክ የሚጋጨው ብልጽግና፤ ዛሬ ደግሞ የሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚያስቆጣ ድርጊት ሊፈጽም ነው።
ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል የተባለው ሃይማኖታዊ ቦታ ቅሬታ አስነሳ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዲዮ ዞን፣ ይርጋጨፌ ከተማ የሙስሊም መካነ መቃብር የተወሰነ ክፍሉ ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አስታውቀዋል፡፡
ቢላል የተባለው ይህ መካነ መቃብር የመንገድ ማስፋፊያን ጨምሮ ለሕዝብ መዝናኛ ግንባታ 15 ሜትሩ እንደሚፈልግ መነገሩም በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘነድ ቅሬታ መፍጠሩ ነው የተጠቆመው፡፡
መንገድ ዳር የሚገኘው ይህ መካነ መቃብር ላለፉት 50 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን የገለጹት ቅርታ አቅራቢዎቹ አሁን ላይ ይፈርሳል የተባለበት መንገድ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
የይርጋጨፌ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን ለአምስት ጊዜ ያህል ስብሰባ አድርገው መቃብሩን ለማንሳት ስምምነት ተደርሶ እንደነበር ጠቅሰው፤ በ10 ቀናት ውስጥ አጽም ወደ ዘላቂ ማረፊያ እንዲዘዋወር መስማማታቸውን በማስታወስ አሁን እየተነሳ ያለው ቅሬታም ከምን የመጣ እንደሆነ እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር እስከ እሁድ ኅዳር 8 ድረስ የመካነ መቃብር ቦታውን ለማፍረስ ዝግጅት ማጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል፡፡
ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው።
ህዳር 7ቀን 2017 ዓ.ም ጧት 4 ሰዓት ባህር ዳር ኤርፖርት ወታደራዊ ሄሊኮፍተር ወድቃለች፣ በዚህም በረራ ተቋርጧል!
ዝርዝር መረጃ አለው፣ ይጠብቁን!
መረጃ!!
እሁድ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ የመንግስት ካድሬዎች ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ታወቀ።
ከየወረዳው ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ የሰራም ሰራዊት የተባሉ ሰዎች ተመልምለው በሩጫው ላይ ይሳተፋሉ፤ ለብልጽግናም የድጋፍ ጩኸት ያሰማሉ ። በሩጫው ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አቅጣጫም ተቀምጦላቸዋል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana