ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የከተማ ግንባታን በተመለከተ
ጨረታ
አዲስ ዘመን ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍና አሰራሩ ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር ነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሪልስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።
ረቂቅ አዋጁ በሚወጣበት ወቅት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው በማድረግ ከተሞች ልማታቸውን ማፍጠን በሚችሉበት ሁኔታ ለመምራትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የንብረት ዕሴት ጭማሪ መሰረት ተድርጎ የከተሞች የገቢ መሰረት ማስፋት እንደሚያስችል ተገልጿል።
በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስት ጥቅምን እያሳጣ ስለሚገኝ፣ ወደፊት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ማደግ ጋር በተያያዘ የንብረት ገበያው እየሰፋ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ ችግሩ አብሮ እንዳይሰፋ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በመሬት ላይ ለተደረገ ማንኛውም ንብረት ባለንብረቱ የንብረቱ ተገቢ የገበያ ዋጋ መረጃ ኖሮት የካፒታል ገበያው ተሳታፊ እንዲሆን አስፈላጊ ነው ተብሏል።
በማይንቀሳቀስ ንብረት ልማቱና ግብይቱ እንዲቀላጠፍ፤ ከብልሹ አሰራር የነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆንና የተዋዋይ ወገኖችን ፍላጎት የሚያረካ፤ ጤናማ የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲኖርና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ የሚያግዝ ወጥነት ያለው የህግ ማዕቀፍ መኖር ስለታመነበት ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ከፍላጎት አንጻር የሪልስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረ በመሆኑ ቤት ለመግዛትና ለመከራየት የሚፈልጉ ወጎኖች በከፍተኛ ሁኔታ የሚቸገሩበት ሁኔታ መቀየር ስላለበት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና የቤት አቅርቦት እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም በመድረኩ ላይ ተብራርቷል።
በውይይት መድረኩም የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የአርክቴክቸር ማህበራት፣ ኮንትራክተሮች፣ የዩንቨርስቲ ምሁራን እንዲሁም የተለያዩ የሙያና የንግድ ማህበራት የተገኙ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መነሳት የሚገባቸውን የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንዲሁም መሻሻልና መዳበር ይገባቸዋል ያሏቸውን ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
(ፖርላማ)
*ማስታወቂያ
? ለ7ተኛ ዙር ሰልጣኞች በሙሉ!
?የሰባተኛ ዙር የHealth and Safety in Construction እንዲሁም Ethics in Construction (Code of Conduct for Members of CCAE) ስልጠና ከ CMI ጋር በመነጋገር የሚሰጥበትን ቀን የወሰንን ሲሆን ስልጠናው ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሦስት ሙሉ ቀናት ቦሌ ሜጋ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ሀንሰም ህንፃ ላይ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት 8ተኛ ፎቅ ላይ ባለው የስልጠና አዳራሽ ይሰጣል፡፡
⏺ ስልጠናውን ለመውሰድ የማኅበራችን አባል መሆን ስለሚያስፈልግ የሰልጣኞች የመጨረሻ ስም ዝርዝር የሚገለጸው የማኅበራችን አባል የሆኑት ድርጅቶች ብቻ ይሆናል፡፡
⏺ አባል ያልሆናችሁ ድርጅቶች የ7ኛ ዙር ስልጠናውን ለማከናወን እስከ ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016ዓ/ም ጠዋት ድረስ ባንቢስ ኃይለገብርኤል ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የማህበሩ ፅ/ቤት በአካል በመምጣት የአባልነት ምዝገባችሁን እንድትጨርሱ እናሳስባለን፡፡
➡️ ማሳሰቢያ
⏺ ማኅበራችን ስልጠናውን ለማስተባበር ለሚያወጣቸው ወጪዎች 2,500.00 ብር ክፍያ እንደሚጠይቅ ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
??"Think safety, work safely."ደህንነትን አስብ ፤ በጥንቃቄ ስራ"
?የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማኅበር
??♂የግንባታ ላይ ደህንነት
⏺ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት አንዱና ዋነኛው ትኩረት ማድረግ የሚገባው በሰው ልጆች ደህንነት ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግንባታዎች በሚገነቡበት በዋናነት ለሰውልጆች አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች የስራ ላይ ደህንነት ሥጋት የሌለባቸው እንዲሁም ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ለአካባቢ የተመቹ እና ደህንነታቸው የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡
⏺ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮንስትራክሽን ስራ እንዲኖር ቁጥጥር በማድረግ ሂደት ትኩረት እንደሚሰጥ ቢነገርም ደህንነት በቁጥጥር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሁሉም የግንባታው ዘርፍ አካላት በየራሳቸው ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ነጥብ ነው፡፡
?♀?የግንባታ ሂደት ውስጥ የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ በግንባታ ስራው ላይ የሚሰማሩት የመስክ ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ እንዲሰሩ የሚያስፈልጋቸውን የግል የአደጋ መከላከያዎችን በማቅረብ ሰራተኞቹም የስራ ላይ ትጥቃቸውን በመጠቀም በስራ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ በህንጻ ግንባታ ሆነ በሌሎች ግንባታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡
???የህንጻ ግንባታዎች ላይ በተለይም የግንባታ ስራ የእቃ መስቀያ፣ መወጣጫዎች እንዲሁም ወደ መንገድ እና ወደ አጎራባች ህንጻዎች፤ መኖሪያዎች፣መተላለፊያዎች የሚወርዱ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የግንባታ ግብዓቶች በሰው እና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ሆኖም በእነዚህ አደጋዎች የሚፈጥሩትን ኪሳራ የግንባታ ጊዜ ማስታወቂያዎች መከላከያዎች በማድረግ እንዲቀነሱ ማድረግ ይቻላል፡፡
?በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሙያተኞች ወደስራ ቦታቸው ሲገቡ አስፈላጊውን የደህንነት መጠበቂያ ባለማድረጋቸው የሚደርሱ የአካል እና የመንፈስ ስብራቶች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የራስ (የአናት) መከላከያ ቆብ፣ ጓንት፣ አስፈላጊ የደህንነት ጫማዎች፣ የመለያ አልባሳት ወ.ዘ.ተ ለደህንነት ዓላማ የተዘጋጁ ቁሶች እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለደህንነት በመስጠት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀላል የሚቀረፉ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች በብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
⏺ ግንባታ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ ኪሳራዎች ደግሞ በግለሰብ በማህበረሰብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ታሳቢ ቢያደርገውና ቅድሚያ ለደህንነት በማለት የመጀመሪያውን እርምጃ ለደህንነት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
(ኢኮባ)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana