ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
❝ ለማያውቁት ጦርነት በ'መንጋ ይነጉዳሉ። አይተውት የማያውቁትን እና ያልደረሰባቸውን ሰው ሳያመነቱ ይገላሉ። ጠላትነት አየሩ ላይ ተበትኗል። ሰው እንዴት አይቶት የማያውቀውን ሰው ይጠላል? "ጭካኔ ሀገሩ እዚህ ይመስላል።" ጦርነት ውርሳቸው ነው። የድንቁርና ማህበርተኞች ናቸው። ድድብና አምላካቸው ነው። የሚጠመቁት ፀበል መሀይምነት ነው። ቅዳሴያቸው አመፅ ነው። ዱኣቸው እርግማን፡…
❝ ለማያውቁት ጦርነት በ'መንጋ ይነጉዳሉ። አይተውት የማያውቁትን እና ያልደረሰባቸውን ሰው ሳያመነቱ ይገላሉ።
ጠላትነት አየሩ ላይ ተበትኗል። ሰው እንዴት አይቶት የማያውቀውን ሰው ይጠላል? "ጭካኔ ሀገሩ እዚህ ይመስላል።"
ጦርነት ውርሳቸው ነው። የድንቁርና ማህበርተኞች ናቸው። ድድብና አምላካቸው ነው። የሚጠመቁት ፀበል መሀይምነት ነው። ቅዳሴያቸው አመፅ ነው። ዱኣቸው እርግማን፡ ስግደታቸውም ለጥፋት። ቅዳሴ እና አዛናቸው የጦር ነጋሪት ነው። ቁርአንና መፅሐፍ ቅዱሳቸው የጦርነት መዝገብ ነው። የሚጦሙት ሀሳብ ነው። ሰውን የሚያጠምቁት በደም ነው። የሚያስቡት በደቦ ነው ። ልቦናቸው ተሰልቧል። የአላዋቂነት እድርተኞች ናቸው። ልባቸው አርጧል። የሰይጣን አለቆች ናቸው። እንስሳ ናቸው፡ ከእነሱ መንጋ ያልሆነን ሰው ሁሉ ይበላሉ። ዘረኝነት ደማቸው ነው።
ጭራቅነት ወርሷቸዋል። ለህፃናት የሚራራ ልብ ያለው የለም። ያለ ርህራሄ ይደፍራሉ። ህፃናት እና አዛውንቶችን ብቻ አይደለም የገደሉት፡ ትላንት እና ነገንም ጭምር እንጂ።
ካፋቸው የሚወጣው እሳት ነው። ንግግራቸው ጦር ነው። ሀይማኖታቸው ለሰብዓዊነት አላበቃቸውም። ባልንጀራቸውን እንደ እራሳቸው አልወደዱም። ፈጣሪን የጦር አዝማች አድርገውታል። መገዳደላቸው የፈጣሪ ፍቃድ እንደሆነ ያስባሉ። በከንቱ እንደተዋደቁ ማመን አይፈልጉም።
ዛሬ የበደሉት ሰው ነገ ቀን ጠብቆ እንደሚበቀላቸው ዘንግተዋል። አንድነትን እንደ ባዕድ ይጠየፉታል። ጦርነትን ይባርካሉ። መሀል ቤት ምንም የማያውቁት እንደ ቅጠል ይረግፋሉ። እሬሳቸው በአውሬ ይበላል፡ ነፍሳቸው ማረፊያ አጣ ትቅበዘበዛለች። የተበደሉት ደሞ ለበቀል ቀን ይጠብቃሉ፡ የተደረገባቸውን ያደርጋሉ። ደም በ ደም እየተመላለሱ ፍፃሜ ወደሌለው አዙሪት ውስጥ ይቀረቀራሉ.....ትላንት....ዛሬ......ነገ....
❝ይህ ሁሉ ግን ለምን? ብሎ ከመሀከላቸው የሚጠይቅ አንድ'ስንኳ የለም።❞
[የማወራው ስለ ሀይማኖት አይደለም፡ የማወራው ሀይማኖታቸው ስላደረጉት ጦርነት፣ ዘረኝነት፣ አላዋቂነት....ነው።]
© ሙባረክ
❝ ምሽቱ ድቅድቅ ጨለማ ሲሆን፡ ከዋክብት የበለጠ ይደምቃሉ። ስቃያችን ጥልቅ ሲሆን ወደ ፈጣሪ ቀርበናል።❞
[Dostoyevsky]
❝ አንዳንዴ፡ መኖር ብቻ እራሱ፡ ትልቅ ብርታት ነው። ሌላው ቀርቶ።❞
❝ ከሀጥያቶች ሁሉ፡ ትልቁ ሀጥያት፡ አላዋቂነት ነው።❞
እኮ በሕይወት ፈተና ክንዱ የማይደክምበት፣ ነፍሱስ የማይዝልበት ማን ነው? ሞት ባይኖር የህላዌ ወለፈንዲነት ይቀራል? የእድሜ ሐረግ እንደ ማቱሳላ ቢንዠረገግ፣ የሰው ልጅ ኢመዋቲነትን ቢጎናፀፍ፣ እስከ ዘላለም በፍስሓ ቢጥለቀለቅ ሕይወት ከመራራ ኩሸትነቱ ዝንፍ ይላልን? ያማከረ ባይኖርም ከዚህ ኹሉ ስቃይ አስቀድሞ አለመፈጠር ነበር። ከተወለዱ ወዲያ ግን ወደ ኋላ አይባል ነገር! የቸገረ ነገር። ደግሞስ የአለመኖርን ጣዕም የሚያውቅ ማነው? እኮ ምን ምን ይላል? ለእነዚህ ኹሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘትስ ትርጉም ይሰጣል??
[ ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?]
❝የምትማረው ሰው ሁሉ እውቅና በሰጠው መንገድ ቦታና መተዳደሪያ ለማግኘት ነው። የምታነበው ግን በሕይወት አንተ ብቻ እውቅና የሰጠኸው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው❞
— አለማየሁ ገላጋይ
በደግ ቀን ፍፁም ሰላማዊ ሰዎች በክፉ ቀን አመፃቸው ይበረታል። በሰይጣን ስም የሰው ልጆች ያደረሷቸውን ጥፋቶች እና በደሎች ያስተዋለ የለም።
«...ደካሞችን ችላ በሚል አፅናፍ ውስጥ— ትናንሽ መዳፎች የከሸፈ ሕልማቸውን ትርፍራፊ ለመሰብሰብ ይገደዳሉ።»
(___)
Abdulaziz
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago