ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 3 days, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 1 week ago
አላህ ሁን ብሎት አሁን ሀፕን እያደረገ ባለ አስቸጋሪ ከረንት ውስጥ ዱዐችሁን አጥብቃችሁ ያዙት፣ከአላህ ጋር መሆናችሁን መልክ ስጡት፣እጣፈንታችሁ እየሆነባችሁ እንደሆነ በማመን ከተስፋ ርቆ መገኘት ውስጥ አትግቡ። ከአላህ በቀር እሱን ስሜታቹ የሚጋራ አንድም አካል የለምና ለነፍሳችሁ ስትሉ ጠንካራ ለመሆን ሞክሩ። የአላህ ነገሮችን በመቀያየር ችሎታ ላይ እምነታችሁ ሙሉ ይሁን። ያኔ ወደተሻለው መዳረሻ እንደሚወስዳችሁ ጥርጥር አይገባችሁም። ግድየለም አብሽሩ🤍
(አብድልቃድር ኑር)
መኖራችሁ ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ዘንድ ያለመኖራችሁስ ዋጋ ምን ያህል ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
ከልቡ ሰው የሆነን ስትፈልጉ አላህን ከቀድራችሁ ጋር የገጠመውን እንጂ ከዛ ሌላ አትለምኑት።
(አብድልቃድር ኑር)
የአንዳንድ ቶሎ አኩራፊ ስስ ልቦችን የልብ ንፅህና የሚረዱ ሰዎች በአለም ላይ እምብዛም ጥቂት ናቸው። ከመናገራቸው በፊት እንባ የሚቀድማቸው፣በትንንሽ ነገር ሆድ የሚብሳቸው ለሆኑ ሰዎች የተፈጠሩ ፍጡሮች ብዙ የሉም።
ስሜታቸውን የሚረዳና አይናቸውን የሚያነብላቸው ብዙ አካል የለም። ልባቸው ስስ መሆኑ ያልገባቸው ሁሉ ሲያኮርፉ ደሞ ጀመራት፣ይኸው ተነሳበት ከማለት በቀር አይረዷቸውም። ንግግራቸውን ከመጀመራቸው እንባ ሲተናነቃቸው ያዩ ሁሉ ከእውነታው እየሸሹ አድርገው ያስቧቸዋል። መነፋረቅ ብቻ የሚሏቸውም ብዙ ናቸው። ዝምታቸው አንደበታቸው መሆኑን ያልተረዱ ሁሉ የተሸነፉ አድርገው በማሰብ ራሳቸውን በነሱ ላይ የበላይ ለማድረግ ይሞክራሉ።
ብዙ ጊዜ የልብ ንፅህና እነዚህ ሰዎች ጋር መኖሩ ስለማይገባቸው ለነሱ ያላቸው ግምት አናሳ ነው። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ጋር ከልብ የሆነ መውደድ አለ፣ከልብ የሆነ ርህራሄና ፍቅር አለ። ሰዎች ሊያዩት የማይችሉት ውብ ልብ አላቸው። ከአንዳንድ ሰዎች በቀር ማንም ሊደርስበት የማይችል ስብዕና አላቸው።
እነዚህን ሰዎች ለማንበብ የተሰጡ ሰዎች ባህሪያቸውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አያያዛቸውን ያሳምራሉ። ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለሚረዱ ቅርበታቸው ላይ ጥንቁቅ ናቸው። እንዲሆን የሚፈልጉትና የማይፈልጉት ሁሉ ስለሚገባቸው ማድረግ ያለባቸውን ማድረግ ከሌለባቸው ይለያሉ። ልክ ነው ለእንደነዚህ አይነት ስስ ልቦች አምሳያ ልብ ወይንም መልካም የሆነ ልብ ያስፈልጋቸዋል። ከቻልን እስቲ ለመረዳትና ለማንበብ እንዲሁም ከአጠገባቸው ለመሆን እንሞክር።
(አብድልቃድር ኑር)
የመፅሐፍ ዳሰሳና ጥቆማ-1 (Book review and suggestion) Episode-1 (በአብድልቃድር ኑር) ★★★★★ (ቢስሚከ ነህያ) <ወንጀሎችህ የቱን ያህል ቢሆኑ ፣ በኀጢአት ውስጥ ብትጠፋ ፣ የትኛውንም ያህል የአላህን መንገድ ብትረሳ አሊያም ብትጥል . . ጌታዬ ሆይ ተመልሻለሁ ብለህ ወደሱ ብትመለስ <አቤት ናልኝ ባሪያዬ ሆይ!> ብሎ ይቀበልሀል። የአላህን እዝነት ጥልቀት ከልብ እንመልከት፦…
አላህ በሙሳ ላይ መች አረፈደ ?
ነብየና ሙሳ ከህዝቦቻቸው ጋር ሆነው በፊርአውንና ጭፍሮቹ ኢላማ በተደረጉበት ክስተት መሀል አላህም አብሮ ነበር። የአላህ ከነሱ ጋር አብሮ የመገኘትና ከሰራዊቱ ኢላማ ነፃ የመሆናቸው cuz ደግሞ ከሰበብ በኋላ የኢማንና የተወኩል ውጤት አይመስላችሁም? አላህ ለእውነተኛ ባሮቹ ጠበቃ መሆኑንስ አያሳያችሁም?
ነብይ ሙሳ ህዝባቸውን ይዘው አላህ ሂዱ ብሎ ወዳዘዛቸው ቀይ ባህር እስኪደርሱ ድረስ የነበራቸው የቂን እንዲሁም ፈርዖን ከበስተኋላቸው እስኪደርስ ድረስ በጌታቸው ላይ የሰነቁት እምነት የኢማናቸውን ጥግ ያሳየናል። የአላህም ከሙሳ እና ህዝቦቹ ጋር መሆን እርሱን ተወኩል ላደረጉ ሁሉ መድህን እንደሚሆናቸው በግልፅ ያየንበት ነው።
ኢቭን የሙሳ ህዝቦች እኛ(የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን ብለው ስጋት ባደረባቸው ሰአት ሙሳ ቅንጣት ተስፋቸውን አላጡም ፣ አላህም አላረፈደም።
በዚህ ክስተት መሀል ታዲያ ሙሳ አንድን ታሪካዊ ንግግር አሰሙ።
«ተዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው በእርግጥ ይመራኛል» አሉ!"
ይህም ቃል እውን ሆኖ አንዲትም ሰአት ሳትባክን ባሉበት ተፈፅሟል።
በየትኛውም ጉዳያችን ላይ አላህ አብሮ አለ። መኖሩን በልበ ሙሉነት አምነን ተቀብለን እንደሆን ሁሉም ገር ይሆናል። ቀደም ሲል እንዳነሳው የአላህ ነብይ ሙሳ አላህ አብሯቸው ስለመሆኑ ጥቂት ጥርጣሬ በውስጣቸው አልነበረምና ሪስክ ውስጥ ቢሆኑም እንኳ ህዝባቸውን ይዘው ወደተባሉበት ቦታ ጉዟቸውን ጀምረዋል።
ነብየና ሙሳም አላህን ብቻ በልባቸው አስቀምጠው የተነሱበት ጉዳይ ነጃ እንዲወጡ አድርጓቸዋል። የዘመናት ሀሳብና ሸክማቸውም በዚሁ ክስተት እንዲያበቃ ሆኗል። ይህ የአለማቱ ጌታ ፍቃድና ችሮታ ነው።
እነሆ አሹራን ስንዘክር የነብየና ሙሳን ተወኩል፣እምነት፣ኢማን bla bla ብዙ ነገሮችን አብረን እናነሳለን።
ጉዳይህን ወደአላህ አስጠግተኸው ና ሙሉ እምነትህን በሱ ላይ አድርገህ ሳለ አትከስርም ወላህ። ተስፋ በቆረጥክበት ክስተት መሀል አላህ ግን ሳይረፍድ ተስፋህን በመሻትህ ፥ ምንአልባትም ከመሻትህም በላይ በሆነ ጉዳይ ይቀይረዋል።
ዛሬ በበዳዮች እጅ ላይ ብትሆንም ነገ ግን ፍትህን የሚሰጥህ አላህ ብቻ ነው። አለመታመን ድርሻህ ቢሆን እና እውነታህን በውሸት ሚዛን ላይ አስቀምጠውብህ ብታይም አብሽር ፥ አላህ ምንጊዜም ከሐቀኞቹ ጎራ ያለ ጌታ ነው። የበታቻቸው ሊያደርጉህ በሚሞክሩ ሰዎች ላይ አላህን የበላይ አድርገህ ያዘው። አላህን ባሰብከው ቦታ ላይ የምታገኘው ጌታ ነውና ነገርህን ከሱ ጋር ተወዉ።
አንተ በጌታህ ላይ የምትይዘው ተወኩል ለሁሉም ጉዳይ ወሳኝ ነውና ተወኩልህን አፅንተህ ቆይ። እሱን ተማምነህ ማታልፈው አንድም ጉዳይ አይኖርም።
«وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا»
«በአላህም ላይ ተመካ ፥ መመኪያም በአላህ በቃ።»
(አብድልቃድር ኑር)
ወንድ ልጅን እንዲያ እና እንዲህ እያሉ ከብዙ ነገር ሊያጥሩት ቢችሉም ፍቅር ዘንድ ሲሆን ግን ፈፅሞ አይችሉትም።
የትኛውም ወንድ ስለፍቅር ወደደም ጠላ ዝቅ ይላል። ፍቅሩ ከልቡ እንደሆን ክብሬን ብሎ የሚገፋው ፍቅር አይኖርም።
በታሪክ መዛግብት ብዙ የተባለላቸው ቀይስ (መጅኑን ለይላ) ፣ ሮሚዮ ለዚሁ ፍቅር የሚሉት አለም የከፈሉት መስዋዕትነት ወንድ ከመሆንም በላይ ነበር። ከሁሉ በላይ ደግም (ረሱሊ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ለፍቅር የነበራቸው መተናነስ ና ቦታ የፍቅርን ማዕና በግልፅ የሚያሳየን ነው። ለኸዲጃ «እሷን መውደድ ተሰጠሁኝ» ያሉበት ንግግር ቃላቶቹ ጥልቅ ናቸው። ስለፍቅር የሆኑትና የተሆነላቸው ሁሉ የፍቅርን ከፍታ የሚያሳዩን ናቸው። ዘለቅ ስንል ደግሞ የአላህና የመልዕክተኛው ሙሀመድ (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ፍቅር ከሁሉ ልቆ በቂ ማሳያችን ነው። በአላህ ቃል ላይ ለዩሱፍ «በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል» የተባለላት ዙለይካ ስለፍቅር የሆነችውን ሁሉ ታሪክ ቆሞ ይመሰክራል። የዐሊይ ና የፋጢማም ፍቅር ምሳሌያችን ነው። ስለፍቅር መተናነስና እጅ መስጠት ማለት ሲሩ ብዙ እንደሆነ ያመላክተናል። ፍቅር መንገዱን አይሳት እንጂ ከሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ ወሳኙ ጉዳይ ነው።
በቃ ከልብ የሆነ ፍቅር ከአላህ ከራሱ የሆነ ኒዕማ ነው።
ታዲያ ግን በኛ ዘመን ስለቆሸሸውና ስለረከሰው ፍቅር አላወራሁም።
(አብድልቃድር ኑር)
ድንገት በሆነኛው ቀን አንዳንድ ገፆችን ከህይወትህ ላይ ትሰርዛቸዋለህ። ቀልብህ ይወደው የነበረውን ሁሉ ማሳደድ ታቆማለህ። አብሮህ ሳለ ከልብ ላልነበረው ጉዳይ ሁሉ ጀርባህን ትሰጣለህ።
ፊትህንም ወደአላህ ብቻ ታዞራለህ። ከልብ የሆነው ብቸኛ ጉዳይህ ወደአንተ እስኪመጣ ልብህን አሳምነህ በትዕግስት ትቆያለህ። አላህም አይቶህ ለቀልብህም ለልብህም በሆነው ብስራት ያበስርሀል።
አብሽርልኝ የኔ ጀግና☺️ ታጋሾች ሆይ ትንሽ ጨምሩ ፥ ጥቂት ብቻ ቀረ ብለዋልና ኢብኑል ቀይም።
ትንሽ ብቻ ፥ ትንሽ ብቻ ጠብቅ?
(አብድልቃድር ኑር)
ወዳጄ! እኚያ የአላህ ነብይ ጧኢፍ ላይ ያን ሁሉ በደልና ግፍ ባስተናገዱበት ክስተት የአላህን ቁጣ ጨምሮ የጧኢፍ ህዝቦች ላይ ያሻቸው እንዲሆንባቸው በመላኢካው ጅብሪል ቢጠየቁ ፥ አይሆንም ያሉበት ታሪክ አዕምሮህ ላይ የሆነ ጭላንጭል እሳቤን አልፈጠረብህም? በዳዮቻቸው ምንም እንዳይሆኑ ያደረጉበት ተአምር አጀብ አላስባለህም?
ይልቅ የረሱሊን ምላሽ ወደሐያትህ ስታመጣው ለይቅርታ ዝግጁ ከመሆን በዘለለ የትኛውም ስልጣንና አቅም ቢኖርህ መሻታህን ብቻ ለማስፈፀም ስትል ልትጠቀመው እንደማይገባ የሚጠቁምህ ነው።
ከሰው በላይ ነኝ ብለህ በማሰብ በአንደበት ና ተግባርህ ጨቋኝ እንድትሆን የሚያደርግህ ego በረሱሊና በጧኢፍ ክስተት ካልተገራ ሰዉ መሆንም መመራመርም ይጎድልሀልና ግድየለም ራስህን መርምር።
ረሱሊ በዛ ሰአት ላይ ከአላህ እገዛ ጋር ያሻቸውን የማስፈፀም አቅሙ ነበራቸው። ነገር ግን ያ አቅም ከሰው በላይ ነኝ ብለው እንዲያስቡ አላደረጋቸውም ፥ ይልቅ ምንም አለማድረግንና ማለፍን እንዲሁም ከአላህ የሆነ ይቅርታን ነበር የጠየቁላቸው። ይህ የነብያቶች መገለጫ ቢሆንም በነሱ መገለጫ የሆነን ትምህርት ካልወሰድክና ካልተመራመርክ ግን ትልቅ ችግር አለና እስቲ ጉዳዩን እሰብበት።
እየቻልክ ልታልፋቸው የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች አሉ። መናገር እየቻልክ በዝምታ የምታልፋቸው ብዙ ቦታዎች አሉ። እውነቱን እያወቅክ ባለማወቅ የምታልፈው አጋጣሚ አለ። ለአፀፋ የሚበቃ አቅም አለህ ግና ዟሊሞችህን በይቅርታህ ታልፋቸዋለህ።
መተላለፍ ነው የሚያቆየን ወዳጄ! በተለይ በኛ ዘመን ሚያኗኑረን ይኸው ነውና አንዳንዴም የመተላለፍን ጥበብ አክብር።
(አብድልቃድር ኑር)
የአላህ ሰላም በሩሀቹ ላይ ይሁን ብያለሁ ክቡራትና ክቡራን☺
ቤተሰብ መሆናችሁን በመውደድ እና በማክበር እነሆ ከልብ በሆነ ዱዐችሁ እንድታስታውሱኝ ከመጠየቅ ጋር አረፍ ብለን መመለሻችን እስኪደርስ በአማንም በኢማንም ቆዩኝ ልል መጥቻለሁ።
ተመልሰን የምንገናኝበትን ጊዜ አላህ ያቅርበው እያልኩ ኸይር የተባለ ሁሉ አይጣን ፥ ቅመም የሆነውም ሁሉ ለሩሀችን ይሁን ለማለት እወዳለሁ?
ደህና ቆዩኝ?
ወሰላም?
ያረብ እርጋታውን ከእርካታው ጋር በልቤ ውስጥ አኑርልኝ በሉት።
የሰላም ባለቤቱ አንተ ነህና ቀልቤንም ልቤንም ፣ በዙሪያዬ ያለውን ሁሉ ሰላም አድርግልኝ በሉት።
(አብድልቃድር ኑር)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 3 days, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 1 week ago