Marvelous life | ድንቅ ሕይወት

Description
?YOUR HOST- @FikreabGirma
?Marvelous key for your mind
?inspirational QUOTES?+Educating people,so that they can experience a Healthy lifestyle
?SHARE it with your friends
?COMMENT? @FikreabGirma
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 4 days, 5 hours ago

1 year, 9 months ago

ብቃትን ፍለጋ!

አንድ ጊዜ ፈጣሪ ሰውን ያላካተተ ስብሰባን ጠራና ፍጥረትን ሁሉ ሰብስቦ አንድን ጥያቄ ጠየቃቸው፣ ይላል አንድ ምንጩ ያልታወቀ አፈ-ታሪክ፡፡

ጥያቄው እንዲህ የሚል ነበር፡-

“ለነገሩ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ አንድን ነገር ከሰው ልጆች ልሰውርባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን ከሰዎች ለመሰወር የምፈልገውን ነገር የት ባስቀምጠው ሰዎች ላያገኙት የሚችሉ ይመስላችኋል?” አላቸው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙም የደፈረ እንስሳ ማግኘት ከባድ የነበረ ቢሆንም አራት እንስሶች የየግል ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡

ንስር እንዲህ አለ፡-

“ከሰዎች ለመሰወር የፈለከውን ነገር ለእኔ ስጠኝና ከፍ ብዬ መብረር ስለምችል ጨረቃ ድረስ ይዤው እወጣና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ “አንድ ቀን የሰው ዘር ጨረቃ ላይ የመውጣት ብቃት ስለሚኖረው ማግኘታቸው አይቀርም” አለው፡፡

አሳ እንዲህ አለ፡-

“እንደ ውቂያኖስ ጥልቅ ነገር እንደሌለለና ሰዎች እዚያ ጥልቀት ድረስ እንደማይሄዱ አውቃለሁና እኔ በዋና እዚያ ድረስ መጥለቅ ስለምችል ይዤው ልግባና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ የሰው ልጅ ወደጠለቀው ባህር የመግባት አቅም ለማዳበር ብዙ ጊዜ ስከማይፈጅበት ማግኘቱ አይቀርም” ብሎ መለሰ፡፡

አንበሳ በተራው እንዲህ አለ፡-

“እንኳን ሰው አብዛኛዎቹ የዱር እንስሶች እንኳ የሚፈሩት ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ የምደፍር እኔ ነኝ፡፡ እዚያ ወስጄ ባስቀምጠው ስለማያገኙት ለእኔ ስጠኝ”፡፡ ፈጣሪም፣ “ሰዎች ጫካን መመንጠር ብዙም ስለማይከብዳቸው ቀስ በቀስ ይደርሱበታል” አለ፡፡

ጦጣ በመጨረሻ እንዲህ አለች፡-

“ፈጣሪ ሆይ፣ ከእነዚህ ሁሉ ሃሳብ ሰጪዎች በበለጠ ሁኔታ ከሰው ጋር ቀረብ ብዬ የምኖረው እኔ ስለሆንኩኝ ባህሪያቸው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ሰዎች አብዛኛውን ነገር ፍለጋ ውጪ ውጪውን ነው የሚሉት፡፡ ውስጣቸው ያለው ነገር ትዝም አይላቸው፡፡ ስለዚህ ውስጣቸው ብታስቀምጠው በቀላሉ አያገኙትም” አለችው፡፡

የጦጣ መልስ ተቀባይነት ስላገኘ ፈጣሪ ለመደበቅ ያሰበውን ነገር በሰው ውስጥ አስቀመጠው ይባላል፡፡ ይህ የተደበቀው ነገር የራሳቸው የሰዎቹ እምቅ ብቃት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በውስጣቸው ፈጣሪ ያስቀመጠው አስገራሚና የታመቀ ብቃት እያላቸው ምንም እንደሌላቸው በከንቱ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡

በውስጣችሁ ተዝቆ የማያልቅ እምቅ ብቃት እንዳለ ታውቃላችሁ? ፈልጋችሁ አግኙት! አውጡት! አዳብሩት! ተጠቀሙበት!

@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

1 year, 10 months ago

#Frog_Experiment

ዒላማህን ምታ
______
ውሃ በተሞላ ድስት አንዲት እንቁራሪት ብንጨምር እና ከዛም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር ፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች።

የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች። የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ደረጃ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል ማትችልበት ደረጃ ስለሚደርስ እራሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ፤ ትሞክራለችም ፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም። ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና ወድያው ትሞታለች፡፡

እንቁራሪቷን ምን ገደላት ???

አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል ፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም። እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን እቅም ማጣቷ ነው።

አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መች ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማውቅ ይሳነናል።

አንዳንዴ ነገሮችን እንለምዳቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳለመድናቸው ቢገባንም ማመልጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል።

በጥፋት/ወንጀል መንገድ ውሰጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡

ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን ፍፃሜው ግልፅ ነው፡፡ ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ ግልፅ ነው። እናም ለውሳኔ አንዘግይ !!!

መልካም ምሽት!
@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

1 year, 11 months ago

?በምክንያት አትታሰር❗️❗️

ለውድቀታችን ብዙ ምክንያቶችን መስጠት ለምደናል። ወደ ኃላ ለቀረንበት፤ የፈለግነውን ሳይሆን ያልፍለግነውን ለመሆናችን፤ምክንያቱን ብንጠይቅ፤ እጅግ ብዙ ነገሮችን ለመደርደር
እንችላለን። ግን ሁሌም ምክንያቶች በኖሩን ቁጥር፤ ውድቀታችንን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ማለት ነው ፤ እንደዛ ማለት ብቻም ሳይሆን ለወደፊቱ ውድቀታችንም ዝግጁ ያደርገናል::

ህልም ካለህ እና ህልምህ ለህይወትህ ትልቅ ትርጉም ካለው፤
ከባዶ ማንነት ወጥትህ፤ ትርጉም ያለው ማንነት እዲኖርህ
ከፈለግክ ምክንያት መስጠትህን አቁም። ሁላችንም ለውደቀታችን ማስተባበያ የሚሆን ብዙ ምክንያቶችን ማቅረብ
እንችላለን…..በገዛ ህይወታችን ሃላፊነት ስለሚጎድለን፤
እራሳችንን እንዳንለውጥ ምክንያቶቻችን አስረው ይይዙናል::
ስኬታማ ሰዎች ግን ለውድቀታቸው ምክንያትን መስጥት የማይወዱ ሰዎች ናቸው። ስኬታማ ስል ገንዘብን ወይም የሃብት ክምችትን ብቻ እንደ ስኬት መለኪያ ቆጥሬው አይደለም። ስኬት
በራሳችን መመዘኛ የሚለካ ነው።አንድ የሚያስማማን ነገር ግን
ስኬታማ ሰዎች፤ የመረጡትን ኑሮ መኖር የቻሉ ናቸው። ልባቸው የወደደውን፤ ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጠውን መንገድ የተከተሉ፤ ብርሃናቸው ከራሳቸው አልፎ ለሰው የሚያበሩ ሰዎች
ናቸው::

በዘልማድ ኑሮ ውስጥ ተዘፍቀን፤ ማህበረሰቡ ባወጣልን
መስፈርት፤ አካባቢያችን ባሰመረልን መስመር፤ ችሎታችንን
ገድበን እስከመቼ እንኖራለን? ህልሞቻችንን ሌሎች ማየት
ስለተሳናቸው ብቻ ቅዠት እየመሰለን፤ እውን የሚሆኑ ብዙ ህልሞችን እስከመቼ እናጨልማለን? አላማችንን እንደራሳችን አድርጎ የሚመለከትልን ሰው ስላጣን፤ አላማችንን በተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ቆፍረን ቀበርነው። ችሎታችንን ሰው እንዲነግረን ስንጠብቅ፤ አቅም እና ችሎንታችንን፤ እንደቅጠል ጠወለጉብን:: እራሳችንን የሚመስል ከሰው መሃል ፈልገን ስላጣን፤ ሰውን ለመምስል ሙግት ጀመርን። ሌሎችን መስለን ተራ ሆንን፤ ስራችን የሌላውን መስሎ ተራ ሆነ። መመሳሰል ህይወታችንን የሚያቀልን መሰለንና፤ እኛነታችንን እረስተን ተመሳሰልን፤ ያኔ ልዩነታችን ሞተ፤ ከልዩነታችን ጋር እኛነታችን አብሮ ሞተ፤ከኛነታችን ጋር ህልማች ሞተ። የገዛ ውበታችን ጠፋ ምክንያቱም
ውበት በልዩነት ውስጥ የሚንጸባረቅ ነበርና::

ስንቶቻችን የምንወደውን ስራ አየሰራን ነው? ትርጉም የሚሰጠን ኑሮ፤ ለመኖር ምክንያት የሚሆን እሴት ያለን ስንቶቻችን ነን? አብዛኛዎቻችን ችግራችንን ለምደነዋል፤ ውድቀታችንን ተቅብለነዋል፤ ስለምንኖረው ኑሮ ምንም አይነት ነገር የማድረግ አቅም የሌለን ይመስለናል፤ ህይወታችንን የሚለውጥ ሰው ወይም አጋጣሚ እስኪመጣ እንጠብቃለን፤ በዛ መሃል ውስጣችን ቀስ በቀስ ይሞታል።
ብዙዎች የሚያውቁት ጥቂቶች ግን የሚኖሩበት እውነታ ግን ይህ
ነው።ለህይወትህ ሃላፊነት ከወሰድክ እና  መሆን የምትፈልገውን ከወሰንክ በዚህ ምድር ላይ ካንተ በቀር ከጉዞህ የሚያስቀርህ ማንም የለም። እርግጥ ነው መንገድህ ሁሉ አልጋ በአልጋ አይሆንልህም፤ ብዙ ችግር ያጋጥመሃል ምክንያቱም የስኬት
መንገድ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ይሳካለት ነበር። ግን ከባድ
ነው…….መንገድህ ሊያቀልልህ የሚችለው አንድ ሚስጥር አለ
እሱም ህይውትህን ለመቀየር ምን ያህል ትፈልጋለህ?
ናፖሊዮን ሂል አንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችለውን
ሚስጢር እንዲህ ይናግረዋል “ሰዎች አሸናፊ እንዲሆኑ
ሊኖራቸው የሚገባ ባህሪ አለ እሱም ፤ የሚፈልጉትን ነገር
በእርግጠኝነት ማወቅ፤ መወሰን እና ውሳኒያቸውን በተግባር
ለማዋል የሚያስችላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ማዳበር።” እኒዚህ
ሶስት ነገሮች አንድ ላይ ሲዋሃዱ ህይወታችንን ወደፈለግንበት
አቅጣጫ እንድንመራ የሚያስችለንን መሪ ጨበጥን ማለት ነው።

ብዙዎቻችን በህይወታችንየምንፈልገውን ነገር አናውቅም፤ብናውቅ እንኳን መወሰኑ ይከብደናል። ለምን?ለመለወጥ ስለምንፈራ? ዛሬ ያለንበትን ቦታ ስለለመድነውና መጪውን
ስለማናውቅ?ሌሎች አይሳካም አይሆንም ስላሉን? አቅማችንን
ማንም ነግሮን ስለማያውቅ? ወይስ ውድቀትን ፈርተን?ሁላችንም ምክንያቶች አሉን፤ እኒህ ምክንያቶች ደግሞ ባለንበት
ቦታ እንድንቀር የሚቸነክሩን ሚስማሮች ናቸው። ለውድቀትህምክንያት እስከሰጠህ ድረስ…ካሰብክበት አትደርስም ምክንያቱም ፤ የመለወጥ ፍርሃትህ ሌላ ምክንያት መፍጥር አያቆምምና።ከዚህ አለም ስትሄድ በምን መታወስ ትፈልጋለህ? ዳግም
በማታገኛት አንዴ በተሰጠችህ በዚህች አጭር ህይወት ምን ማድረግን ትመርጣለህ? መለወጥ የምትፈልገው ምንድን ነው?የምትፈልገውን እና የሚያስደስትህን ስራ መስራት?መልካምቤተሰብ መመስረት? መማር? ከሱስ መላቀቅ? የጀመርከውን
ስራ መጨረስ? ለምትወዳቸው ሰዎች መኖር? ወይስ ምን?
የራስህን ህልም መኖር ካቃተህ የሌላውን ሰው ህልም እውን
ለማድረግ ስትለፋ እንደምትኖር እመን፤ አይ የራሴን ህልም
ማሳካቱን እመርጣለው ካልክ ደግሞ፤ ሶስቱን ነገሮች አስታውስ፤
♦️ የምትፈልገውን ነገር እወቅ
♦️ወስን
♦️ለመለወጥ ፍላጎት ይኑርህ። ከምንም በላይ ምክንያት መስጠትህን አቁም።ሁሉም ስዎች ትልቅ እንዳይሆኑ እንቅፋት ሊሆኑባቸው የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሏቸው። ልዩነቱ ደካሞች በምክንያት ታስረው፤ከአቅማቸው በታች ሲኖሩ፤ ጠንካሮች ግን ችግሮቻቸው እና እንቅፋቶቻቸውን የውድቀት ምክንያት ከማድረግ ይልቅ፤
እራሳቸውን ይበልጥ ያጠነክሩበታል………ከመንገዳቸው የሚያቆማቸው ምንም ነገር የለም፤ ማንም ከአላማቸው
አይገዝፍባቸውምና::ያንተስ አላማ ምን ያህል ግዙፍ ነው?
Credit to Fikreab girma

@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

1 year, 11 months ago

#ይቻላል

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

  1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

  2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

  3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

  4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

  5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

  6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

  7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

  8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

  9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

  10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ከሆነ እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን እየሰራን መፈለግ አለብን፡፡
    እኔም አንዳንድ ሃሳቦችን አካፍላችዋአለው
    © @Fikreabgirma

@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

1 year, 11 months ago

አይገርምም!!

?የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው።

?ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው።

?የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው።

?«ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

?ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው።

?ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል።

?እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

? በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱ የበሉት ሌሎች ሰዎች፤ ሰንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው።

⚠️ይህ ሁሉ እውነታ እያለ "ነኝ "እና "አለኝ" በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም። እስቲ ያወሰሰብናትን ሕይወትን
ቀለል እናድርጋትና በተፈጠርንበት ምክንያት በ አገልግሎት ለመትረፍ ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር!!

@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

2 years ago

የቀጠለ
6.ግንኙነትን መፍጠር ወይም መነጠል (Intimacy vs. Isolation.)

ይህ የእድገት ደረጃ ከ 18 አመት እስከ 40 አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ይህ የእድሜ ክልል ሰዎች ከቤተሰባቸው ውጪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩበት ወቅት ነው፡፡የወደፊት የትዳር አጋራቸውንም በዚህ ወቅት ውስጥ ይለያሉ፡፡ይህ ሂደት ስኬታማ ከሆነ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ይኖራቸዋል፣ለግንኙነቱ ቁርጠኝነት ያሳያሉ፣ደህንነት ይሰማቸዋል….ወዘተ፡፡ከሰው ጋር መገናኘትን የማይፈልጉና የሚፈሩ ከሆነ ግን የመነጠል ወይም የብቸኝነት ስሜት ይሰማቸዋል በዚህ የተነሳ ድብርት ውስጥ ሊገቡም ይችላሉ፡፡

  1. ውጤታማነት ወይም ውጤታማ ያለመሆን ስሜት (Generativity vs. Stagnation)

ይህ የእድገት ደረጃ ከ 40 አመት እስከ 60 አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡ይህ ወቅት ሰዎች ስራ ይዘው ፣ትዳር ይዘው ልጅ ወልደው…ወዘተ የሚኖሩበት ወቅት ነው፡፡በዚህም የተነሳ ሰዎች ላሉበት ማህበረሰብ ማበርከት ስላለባቸው ነገር ያስባሉ ጥሩ አገር ተረካቢ ልጅ እንዲኖራቸው ከመፈለጋቸውም በላይ ባሉበት የስራ መስክ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ ነገር መስራትን ይፈልጋሉ፡፡በህብረተሰብ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ውስጥም ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ማሳካት ያልቻሉ ሰዎች ውድቀትና ውጤታማ ያለመሆን ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

8.መተባበር ወይም ተስፋ መቁረጥ( Ego Integrity vs. Despair)

ይህ የእድገት ደረጃ ከ60 አመት በላይ ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ ይህ እድሜ የጡረታ እድሜ ሲሆን ሰዎች ወደኋላ ተመልሰው የመጡበትን ሁኔታ የሚቃኙበት ጊዜ ያገኛሉ፡፡ ወደኋላ ተመልሰው የመጡበትን የሂወት መንገድ ሲቃኙ የስኬታማነት ስሜት ከተሰማቸው ከቀጣዩ ትውልድ ጋር በመተባበር ያላቸውን ነገር ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ስኬታማ ያልሆኑ ከመሰላቸው ግን የተስፋ መቁረጥና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ድብርት ሊሰማቸው ይችላል ከዚህም አለፍ ሲል ሞትን እስከ መፍራት ሊደርሱ ይችላሉ፡፡

ማጠቃለያ፡-የተስተካከለ ማህበራዊ እና ሀይለ-ስሜታዊ እድገት እንዲኖረን መሰራት ያለበት ከልጅነታችን ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ከልጅነት ጀመሮ ከተሰራ ቀላል ይሆናል ነገር ግን አድገንም ቢሆን እራሳችንን የማስተካከል እድል አለን፡፡
በኤሪክሰን አባባል የዛሬ ጸሁፌን ላጠናቅ “ It is not toolate ”

@Marvelous_Life
@Marvelous_Life

2 years, 7 months ago

ልማድ?
"ሰው ስራውን ይመስላል፣ ምርጥነት ተግባር ሳይሆን ልማድ ነው"
#አርስቶትል

ምርጥ ተግባርህን፣ ስሜትህን፣ ፅናትህን... ሁሌ ካልደጋገምከው ምርጥ አይደለም።

@Marvelous_Life
ወዳጆች አብራችሁን ስለሆናችሁ ?

2 years, 7 months ago

ሁሉም ከንቱ ነው፤ እውነት ሞት ነው!

እጅግ አስተማሪ ታሪክ በመሆኑ ወደ አማርኛ መልሼ አቀረብኩላችሁ።
ምን በምድር ላይ ቢደላን የአጭር ህይወታችን የመጀመሪያው ማሳረጊያ ሞት ነው። የሚቀጥለው ዘላቂ ማረፊያ ገነት (መንግሥተ ሰማያት) አሊያም ሲዖል (ገሀነም) መሆኑ ለአማኞች ቅርብ ነው።

የዓለማችን ታዋቂ የፋሺን ዲዛይነር እና ፀሐፊ የነበረቺው ኪርዛይዳ ሮድሪጉዌዝ ከዚህ ዓለም በደረጃ 4 የሆድ ካንሰር በ2018 ከመሰናበቷ በፊት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋ ነበር።

  1. በዓለማችን ውዱ አውቶሞቢል በጋራዤ ውስጥ ነበረኝ፤ አሁን የምንቀሳቀሰው ግን በዊልቼር ነው።

  2. መኖሪያዬ በሁሉም አይነት ዲዛይነሮች በተሰሩ አልባሳት መጫሚያዎች እና ውድ ዕቃዎች የተሞላ ነበር፤ ዛሬ ግን ከሆስፒታል በተሰጠኝ እራፊ ጨርቅ ተጠቅልያለሁ።

  3. በቂ ገንዘብ ባንክ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን ልጠቀምበት አልችልም።

  4. ቤቴ ልክ እንደ ቤተመንግሥት ነው፤ አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በታጣፊ አልጋ/ በድንክ አልጋ ላይ ቀርቻለሁ።

  5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ጊዜዬን የማሳልፈው ከአንድ የሆስፒታል ላብራቶሪ _ ወደ ሌላው የሆስፒታል ላቦራቶሪ በመንከላወስ ነው።

  6. መቶዎች ፈርሚልኝ ይሉኝ ነበር (ከመቶዎች ጋር ስምምነት እፈርም ነበር)፤ ዛሬ ፊርማዬ የዶክተሮች ማስታወሻ ሆኗል።

  7. ፀጉሬን ለማስዋብ ዘጠኝ ጌጣጌጦች ነበሩኝ። አሁን ግን አናቴ ፀጉር አልባ ሆኗል።

  8. በግል አውሮፕላን (ጀት) ወዳሻኝ ስፍራ እበር ነበር። አሁን ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ እንኳ ሁለት የሚሸከሙኝ/ የሚደግፉኝ ሰዎች ያስፈልጉኛል።

  9. የተትረፈረፈ ምግብ ቢኖርም፤ የምመገበው በቀን ሁለት የመድኃኒት እንክብሎች እና ሲመሽ ጥቂት የጨው ጠብታ ብቻ ነው።

ይህ ቤት፣ ይህ አውቶሞቢል ይህ ጀት ይህ ዕቃ በርካታ የባንክ አካውንቶች የበዛ ክብርና ዝና፣ ሁሉም ዛሬ ለእኔ እርባና ቢስ ናቸው። የትኞቹም የከበረ ዋጋ ያላቸው ቁሶች ለህመሜ ማስታገሻ አይሆኑም።

እውነተኛ ህይወት ማለት ለበርካታ ሰዎች እንዲደሰቱ እና በፈገግታ እንዲሞሉ ማድረግ ነው።ከሞት በስተቀር ምንም እውነት የለም። ህይወትም እንደ ጤዛ (አጭር) ናት።

ከታዬ ቦጋለ ገፅ የተወሰደ

ድንቅ ሕይወት
@Marvelous_Life

2 years, 7 months ago

ሕይወት የምትጀምረው መቼ ነው?

ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ይከራከሩ ነበር፡፡ አንዱ፣ “ሕይወት የምትጀምረው ልክ አንድ ጽንስ በተጸነሰበት ቅጽፈት ነው” በማለት ያንን እምነቱን በግለት ያስተጋባል፡፡

ሌላኛው ደግሞ፣ “አይደለም! ሕይወት የምትጀምረው የተጸነሰው ልጅ የመጀመሪያውን ትንፋሽ ወደመተንፈስ ደረጃ ሲደርስ ነው” በማለት የተጋጋለ ምላሹን ይናገራል፡፡

ይህንን ሃሳብ ሳይለቁ ለሰዓታት ሲከራከሩ የተመለከተ አንድ ሰው እያዋዛ አንድን ትምህርት ትቶላቸው አለፈ፣ “ሁለታችሁም ተሳስታችኋል፤ ሕይወት የምትጀምረው ሰው የተፈጠረለትን ዓላማውን ሲያውቅና ያንን መከተል ሲጀምር ነው”!!!

ዓላማችንን እንወቅ! በግለት እንከታተለው! እንኑረው!

ድንቅ ሕይወት ይገባቹሃል::
@Marvelous_Life
ለ ነፃ የምክር አገልግሎት
Inbox @BboyStatus

2 years, 7 months ago

➱ስትወስን?
ራስህን ለመቀየር ስትወስን ልትከፍል የምትሻውን መስዋዕትነትም አትርሳ። ምክንያቱም ከመለወጥህ እና ከመደሰትህ በፊት ዋጋ ልትከፍል ግድ ይልሀል።

@Marvelous_Life
ድንቅ ህይወት የምርጫ ጉዳይ ነው!!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 4 days, 5 hours ago