ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ዜና፦
ታላቅ የዘመናችን ግኝት።
አብይ አህምድ አሊ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር፥ "ባለምጡቅ አእምሮው መሪኣችን ማንም ያልደረሰበትን የኋላቀርነታችን ምክንያት በሚያስገርም ምርምር ደረሰበት" ።
ሆያ ሆዬና አበባየሁ የሚዘምረው ማኅበረሰብን ለማጽዳት በእርቅ ስም ከወለጋ፥ ከአርሲ፥ ከባሌና ሀረርጌ፥ ከሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ክርስቲያን እንዲያጸዳ ትዕዛዝ የተሰጠው በሽፋን ኦነግ ሸኔ የሚባለው ግዳጁን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መትቶ ያንን ተግባር እንዲያጠናቅእ እርቅ በሚል ስም ዝግጅት እየተደረገ ነው።
ክብረ-ሰብእን የማያውቅ ሉዓላዊነት የሰይጣን መንግሥት ብቻ ነው!
አገራችን የሕጻናት ቤት ሆነች። የሕወሃትና የኦነግ ድቅል ፍሬ ብልጽግና አገር የሚበትን የአፓርታይድ ሕገ መንግሥት አዝሎ፥ ለ36 ዓመታት በሰው ደም የሚጠብቀውን የጎሣ ፖለቲካ ሥልጣን ለማስጠበቅ "ሉዓላዊነታችን አይደፈርም!" የሚል ሰልፍ ይጠራል።
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ። በምድር ላይ ከእጽዋት እስከ ባሕርና ምድር እንስሳትን ፈጠረ። ሰውን በአርአያውና በአምሳሌ ፈጥሮ ይህን ፍጠረት ግዛ፥ ጠበቅ ብሎ ሾመው።
እግዚአብሔር ዳግም ሲመጣ ሰውን ወደ ራሱ ይወስደዋል። ለሰው ብሎ የፈጠራቸውን ፍጡራን ከመላዕክት በስተቀር ያሳልፋቸዋል። ለእግዚአብሔር ከሰው የሚበልጥበት ምንም የለም።
?? የብልጽግና መንግሥት:-
?? ያፈናቅላል
??ርስት ይቀማል
?? ያደኸያል
?? በመደበኛ ሠራዊት ሕዝብ ይፈጃል
?? ድንበር ያስደፍራል
ዜሪያውን የሚገኘዑ አገራትን ጥቅም የሚጎዳና የአፍሪካን ቻርተር የሚጥስ ተግባር ይፈጽማል
አዲስ አበባ የእገሌ ጎሣ አይገባም ይላል —-
—————————- ይህን ሁሉ ደፍሮህ ሲያበቃ "ሉዓላዊነታችን እንዳይፈር ተሰለፍ ይልሃል"
የሉዓላዊነት ትርጉሙ የብልጽግና ዘረኞች በሥልጣን ቀጥለው የጀመሩትን የዘር ማጥፋት እንዲያጠናቅቁ እኛ ዜጎች ዘብ ሆነን ፕሮጄክቱን ሳያቋርጥ ማስቀጠል ማለት ሆነ እንዴ?
በነፍጠኛ ስም የኦሮሞን ኦርቶዶክስ የማጥፋት ሤራ ናሙናዊ ጥናት
?????? (የቀጠለ)
(፱) በአማራ ሕዝብ ህልውና ላይ የተደቀነው አደጋ በጥቂት የተደራጁ ፋኖዎች ነጻ አውጭነት የሚጠናቀቅ የሚመስላቸውና እጅ እግራቸውን አጣጥፈው የሚጠባበቁ፥ ባሉበት ሁሉ አስተዋጽኦ ማድረግ ቀርቶ ድል እሰኪመጣ ድረስ ይህ አጥፊ መንግሥት የሚያዝዛቸውን ሁሉ እየተወጡ የሚጠብቁ የትግሉ ሸክሞች መብዛት፥ በየአካባቢው (በክልሉና ከክልሉ ውጭ) በዘር አጥፊውና አገር በታኙ የአፓርታይድ ሥርዓት ላይ መደረግ የሚገባውን ጥቃቅን አስተዋጽኦ ባለማድረግ ጫናውን በፋኖ ላይ ማብዛት፤
(፲) ፋኖና በዐሳብ እንደግፋለን የሚሉ አካላት የሚከተሉትን ነገር አለሟሟላት የሚያስከትለው ግራ መጋባት፦
ሀ/ የአማራ ተጋድሎ ፍኖተ ካርታ (ከየት? ወዴት? አንዴት? መጨረሻ ውጤቱና የሚከሰት ሁኔታ፥ በአዲስ ክሱት ሁኔታ የሚጠቀምና የሚገዳ ኃይልና ማኅበረሰብ እንዳለ ወይን አንደሌለ የሚገለጽ ሕዝብ ሁሉ በተለያየ ቋንቋ የሚያበው ሰነድ) አለመኖር፤
ለ/ ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ሕወሃትና ኦነግ-ብልጽግና ለ50 ዓመታት አእምሮውን አጥበው በአማራ ጠላትነት አሠልጥነውና አስታጥቀው፥ ትምህርት ቀርጸውና ባንዲራ ፈጥረው፥ አገር ከልለውና የሐሰት ትርክት ፈብርከው ለጥፋት ያሰለፉትን ተዋጊ ወጣትና፥ ልቡ የተከፈለበትን ማኅበረሰብ ከግራ መጋባት የሚያወጣው፥ በሁሉም ዋና ዋና ቋንቋ የሚነበብ፤ ፋኖ ለድል ቢበቃ ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር መልሶ የሚገነባት አገር ውስጥ የምንከተለው ፖለቲካ፦ የሰውነት ክብር፥ የዜግነት ትርጉም፥ የአገር ባለቤተነት ጉዳጥ፥ የፍትህና እኩልነት ነገር፥ የአገር ሉዓላዊነት፥ ከጎረቤቶቻችን ጋር የሚኖረን ማስተጋብር፥ የአባይና የቀጠናው ፖለቲካ አያያዝን ጨምሮ ልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርና ባለቤትነት ጉዳይን መግለጥ፤ አሁን ከምንገኝበት የጎሣ ሲዖል ጋር ሲነጻጸር ያለውን ብልጫ ማሳየት አለማቻል። ይልቁኑ በአክቲቪስቶችና በኢትዮጵያ ጠላቶች የሚመነጭ የሚመስሉ ተባራሪና እንጭች ድምጾች መብዛት (ለምሳሌ የተጠና እና በዕውቀት ያልተደከፈ ፦መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ፥ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ፥ የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም (ከብአዴንና ወያኔ ስነሰማ የኖርነው)፥ ኢትዮጵያኒስትና አማራዊ፥ ሥልጣን እንይዛልን አንይዝም) ፤
ሐ/ የትግል መርሆዎች፦ የውስጥና የውጭ ግኑኝነት፥ የውስጥና ከጠላት ጋር የሚደረግ የቅጣትና የፍትህ አሠራር (የራሱን ወንድም ሽማግሌ ገበሬ ቪዲዮ እየተቀረጸ በጥይት ጭንቅላቱን የሚነድል ነውር ሁሉ የሚከለከልነበት) ሥርዓት አለመዘርጋቱ ለትግሉ ጎጅ ነው፥
**የአማራ ሕዘብ የህልውናና የፍትህ ተጋድሎ የውስጥ እንቅፋቶች፦
በእኔ ምልከታ ፲ ናቸው።**
ሌሎችም ሊኖሩና በሌላ እይታ ሊብራራ ይችላል። እኔ ቁንጽልና አጭር ምልከታ ነው የማደርገው። በእርግጥ አሁን ባለው የትግሉ አውድ ሰዎች መወያየት የሚፈልጉት ጀግና እንዲሆንላቸው፥ ፋኖን ጠቅልሎ እንዲገዛላቸውና ከትጥቅ ትግል ማብቃት በኋላ የአገር ገዥዎች አድርጎ እንዲያነግሥሳቸው የሚሹ ወገኖች --- ጉዳይ ላይ መወያየት አይፈልጉም። ስለ ግለ-ሰብእና ስለ ቡድን ልዩነትና መበላለጥ፥ ማን ትክክል እንዳልሆነና እንደሆነ በመወጠር ስሜትን በሚቀሰቅስ፥ ማስበን በሚገድብ፥ ርቀት ከማየትን በሚጋርድ ድምጽ ውስጥ ሕዝቡን በራሳቸው ዙሪያ መሰብሰብ ይሻሉ።
እኔ ግን ጠቃሚ የሚመስለኝ ከግለሰቦችና ቡድኖች ጉዳይን አስቀድመን በመነጋገር ግለሰቦችና ቡድኖች ጉዳዮችን አንዳይጠልፉ፥ በተቃራኒው ለትግሉ ዓላማ፥ ፍልስፍና፥ ርእይ፥ ሂደት፥ ውጤት፥ የውጤት ዘለቃዊነትና የመስዋዕትነት መቀነስ አንጻ ብቻ እየተመዘኑ አንዲስተካሉ ማስገደድ/ማስተጋገልና ቀንበር ማስገባት ላይ ማተኮር ይመስለኛል። በዚህ ማኅቀፍ ውስጥ የግል አስተያየት አጥቻለሁ!!!
መወገድ ያለባቸው የትግሉ እንቅፋቶች፦
(፩) በአድዋ በቆሰሉ ቅኝ ገዥዎች፥ በአምላክ-የለሽ ማርክሳዊ ፖለቲካ ውድቀት ላይ የተወለዱት ሕወሃትና ኦነግ በሰፉት የዘረና የአፓርታይድ ሕገ-መንግሥት ውስጥ የተወለደው ትውለድ ከ1942ቱ የቀኝ ገዥዎች አእምሮ አጣቡ ትምህርት ቤት መከፈት ጀምሮ ብናስበው አሁን 70 ዓመታት የሚላው ነው። ሕወሃትና ኦነግ የ50 ዓመት ጎልማሶችን አፍርተዋል። የአማራ ህልውና አደጋ ጥንስ ከ70 ዓመት አስቀድሞ የተጀመረና ባለፉት 50 ዓመታት ሕወሃት/ኢሕአዴግ ወደ ሕግና ፖሊሰ፥ ትርክትና መዋቅር ያደገ፥ በአማራ ጉያ ውስጥ ሰንክሎና ለጉሙ ባሳደገውና ጭኖ በሚጋልበው ፈረስ-ብአዴን አስተዳደር "ክልልን" ፈጥሮ ካሳደጋቸው ወጣቶች መካከል ቅጽረ አእምሮአቸው በተአምር የተረፈ፥ ህሊናቸው ከአውነትና ሞራል ያልተራቆጡ ወጣቶች የጀመሩት የአማራ ነባር ባህላዊ መሠረት ሰውሮ ያሳደጋቸው ወገኖች ንቅናቄ ነው። ይሁን እንጂ “ክልል” አገር የሚስለው፥ አማራን ከልሎ የሚለካ እና ሚሊዮኖች በመላው አገር የተበተነውን አማራ እንደ ትርፍና አገር አልባ የሚያስብ ስነልቦና የተጫናቸው ፋኖዎች ብዙ ናቸው፥ የፖለቲካ አስተሳሰባቸውም ሙሉ በሙሉ ከ50 ዓመቱ ተጽእኖ መላቀቅ አለመቻሉ ለትግሉ እንቅፋት ነው፤
(፪) የፋኖ ርእዮት ዓለም አንካሳነት አሁንም አለመታከም፦ ለምሳሌ፦ ታላቋን፥ ታሪካዊት ኢትዮጵያን መረዳትና ለህልውና ትግሉ ያለውን ፋይዳ ባለመረዳት ወይንም በአክቲቪስትና በስሜት በመመራት "ኢትዮጵያኒስት እና የአማራዊነት" በተባሉ ያልታሰበባቸው የጫጫታ ውጤቶች ግራ መገባት፤ ሁለት ያልተለያዩ የአካልና ወሳኝ ብልት (አካልና ልብ ወይንም አካልና አንጎል) ያህል ቁርኝት ያላቸውን የአማራነትና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብሮች መካከል “አንዱን ምረጡ” የሚሉ የሕወሃትና የኦነግ ትውልድ ምሁራን ሰለባ በሆነ ስነ ልቦና እያነከሰ መሆኑ ለትግሉ እንቅፋት ነው፥
(፫) የፋኖነትን የፍትሕ፥ የሰብአዊነት፥ የአገራዊነት፥ የጀግንነት፥ የሞራል ልዕልናና መልካም ስነ-ምግባራት ሙሉ በሙሉ የሚንዱ ምልቶች እንዲታዩ የሚያደርጉ ሰርጎ ገቦች ሞናረቸው ግልጽ እየሆነ መቷል፤ ለምሳሉ፦ ገንዝብ ወዳድነት፥ ጎጠኝነት፥ (ግላዊ) ሥልጣን ናፋቂነት፥ ሤረኝነት፥ ከትህትና በሚቃረን "እኔ ካልተሰማው” የሚል የትዕቢት መንፈስ የተጎዱ አባላት ብቅ ብቅ ማለታቸው ለትግሉ እንቅፋት ነው፤
(፬) በአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ትግል ደጋፊነት ጥላና ስም ከተሰበሰቡት ወገኖች መካከል ጥቂት የማይባሉት ቡድኖችና በውክልና እነሠራለን የሚሉ የውጭ ወገኖቻችን መካከል የራሳቸውን ጥቅም የሚያሯሩጡ፥ ባለማወቅ ወይንም ባለመዋቅ የጠላት ግቦችን የሚያግዙ ሀሳቦችን በማሰራጨት የሚዲያ አየሩን ሙላትና አንድነትን ማደነቃቀፍ ላይ የተሰለፉ አሉ፥ በትግሉ ስም ገንዘብ የሚያጋብሱ ግብዞችና ቅርብ አዳሪዎች በዝተዋል፤ ይህ በፍጥነት ቁጥጥር ካልተደረገበት ለትግሉ እንቅፋት ነው፤
(፭) በፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ልዩነት እንዲጠናከር የሚሠሩ ሚዲያዎችና ለዚህ የዳያስፖራና አንዳንድ ጎጠኛ የክልል ባለሀብቶች ቀለብ የሚሰፍሩላቸው ጋዜጠኞች መኖራቸው የፋኖን አንድነት መጠናከር፥ መተማመንና በአንድ ዐሳብ መሄድን በማዘግየት ለጠላት ጣልቃ ገብነት በር ከፍቷል፤
(፮) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የውድቀት እንጂ የስኬት ታሪክ የሌላቸው፥ አቋማቸውን በመለዋወጥና ራሳቸውን በሌሎችን የማይገባ መስዋዕትነት በማስከፈልና ራሳቸውን ሰውረው ብዙ ታላላቅ የአገር ልጆችን ያስቀጠፉ፥ ወይንም (እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀውን የልባቸውን ምሥጢር ለእርሱ ለፈጣሪያቸው ትተን) እነርሱ በነገሩን ብቻ “ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብለው በፖለቲካ ተሳትፎአቸው በእሥርና ግርፋት መከራ ሲቀበሉ የኖሩ ወገኖቻችን፥ በስደት የንገላቱ፥ ንብረት አጥተው ቤተሰባቸው የተበተኑባቸው ታጋዮች --- ለከፈሉት ታላቅ መሰወዋእትን ከሕዝቡ ክብር የሚቸራቸው ናቸው፤ ይሁን እንጂ ባለፉት የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ለራሳቸው ሕሊና እና ከእምነታቸው እሤሰት በመነሳት ለሕዝብ የከፈሉት የቀደሙ ዋጋዎች በፋኖ አሁናዊ ተጋድሎ ውስጥ እውቅና ሊያገኝላቸው፥ ብሎም ክፍያቸውን አሁን መሪና አዛዥ ካልሆንኩ ብለው የሚያውኩ ግለሰቦችና ቡድኖች መኖርና ገደብ ማጣት፤ እነዚህ ወገኖች በብቸኝነት ለመደመጥና ማንኛውንም እነርሱን የማያካትት ጠቃሚ ሂደት ሁሉ በሤራ፥ በፕሮፓጋንዳ፥ በሚዲያ፥ በገንዘብ የሚያሰነካክሉ ስንኩላን መብዛትና መፍትሔ አለመሰጠት ትግሉን አዝጋሚ ያደርገዋል፥ ለጠላት ሰርጎገብነት እድል ይሰጣል፤
(፯) በዓለም አቀፍ ሴኩላር ትምህርትና ሙያ ታውቀው፥ አገራቸውን ሳይሆን የአገራችንን ነባርነት ለማይወዱ አገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት በታማኝነት ለአጥፊ ምእራባዊ ፍልስፍናዎች፤ የዓለም አቀፍ ኢፍትሐዊ ግኑኝነቶችና ፖሊሰዊች ላይ ምን አይነት ጥያቄ ሳያነሱ በመኖራቸው ምክንያት የምእራቡ ኃይላት የተጠቀሙባቸው እና "አንቱ" ያሏቸው የአማራ ምሁራን የአማራን ሕዝብ ዕውቀት፥ ባህል፥ አሠራር፥ የታጋዮችን ፖለቲካዊና ወታደራዊ አስተሳሰብ ሁሉ በማጣጣል በታጋዮችና በሕዝብ በራስ የመተማመን ስነ ልቦና ላይ ጫና የሚያደርጉ፤ እኛ የጻፍንላችሁን፥ የመከርናችሁን፥ የምናዝዛችሁን ካልፈጸማችሁ ትክክል አይደላችሁም የሚሉና ልብ የሚከፍሉ እስከ ተደመጡ ድረስ ትግሉ እንቅፋቶች ይበዝቡታል፤
(፰) የአማራን ሕዝብ ለህለውና አደጋ የዳረጉ ዕሳቤዎች፥ ትርክትቶች፥ አገራዊና ዓለም አቀፍ ተዋንያን ትሥሥር፥ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየተካሄደ ያለውን ሂደት ፈጽሞ ባለመገንዘብ እና "ከቀበሌያቸው እና ከወረዳቸው ማዶ ከአለው ተራራ" ባሻገር ስለሚሆነው ነገር በማሰብ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ያለውን ቁርኝት፥ ለርስታቸውና ለሃይማኖታቸው፥ ለታሪካቸውና ለአጠቃላይ ሕዝብ ያለውን ፈጽመው የማያስቡ --- ገንዘብና ጠመንጃ ለሰጣቸው ሁሉ እንደ ሰው ሠራሽ ሮቦት እየተነዱ የሚዋጉ ባንዳዎች፥ ወሬ አመላላሾች መኖር ትግሉን ያዳእመዋል፤ (ይቀጥላል)??????
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana