ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
👉በምለጥፋቸው ቁምነገሮች እየተጠቀማችሁ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ።
በተጨማሪ ማግኘት ምትችሏቸው አገልግሎቶች
1) ቆዳ ህክምና
2) ማማከር አገልግሎት
ለተማሪዎች ነፃ አገልግሎት።
👉ልታገኙኝ ከፈለጋችሁ @UrSkincare ወይም 0707042466
👌ልጅ መውለድ በተለይ በጊዜ መውለድ የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ታውቃላችሁ??!!
ያ ጀመዐ ከጠቀማችሁ ግሩፓችንን ሼር ብታደርጉ
Hello everyone ?if you are medical student or medical doctor and if you need sketchy visual medical videos for ERMP, USMLE or Qualification and Exit exams you can buy from me @urskincare
ቆዳ ሕክምና በርቀት ስታደርጉ
? ወረፋ፣ ሰልፍ መጠበቅ የለም።
? ክፍያም በአካል ከምትሄዱበት ቅናሽ ነው።
ምርመራ ሚፈልጉ ነገሮችን በርቀት አናክምም።
ቆዳ ሕክምና በርቀት ስታደርጉ
? ወረፋ፣ ሰልፍ መጠበቅ የለም።
? ክፍያም በአካል ከምትሄዱበት ቅናሽ ነው።
ምርመራ ሚፈልጉ ነገሮችን በርቀት አናክምም።
እኔ ና መይግሬን(Migraine)
✍️አበረውኝ ወዳጅ ከሆኑኝ ህመሞች መካከል አንዱ ማይግሬን ነው። መቼ እንደ ጀመረኝ በትክክል ባላስታውስም ዩኒቨርስቲ ከገባው በኃላ እንደሆነ ትዝ ይለኛል። ከአብዛኛው የማይግሪን ታማሚ አኔ ላይ በጣም የጠነከረ እና አንዴ ከጀመረኝ ከ ሁለት ቀን እስከ ሶስት ቀን ሊቆይብኝ ይችላል። አብዛኛው ጊዜ በመርፌ የሚሰጡ መድህሃኒቶችን ካልወሰድኩ አይተወኝም። ከኔ ተሞክሮ እና ከ ህክምና ሣይንስ በማጣመር የተሻለ የምለውን በዚህ ጽሑፍ አስቀምጣለው። ረዥም ጽሑፍ የመጀመሪያዬ ነው።ይቅርታ ይደረግልኝ።
ማይግሬን ሌሎች ራስ-ምታት ከሚያመጡ የሚታወቁ ህመሞች ጋር የልተያያዘ(Primary Headache)የራስ-ምታት ዓይነት ነው። መንስኤው ከቴዎሪ ባለፈ ግልፅ ምክንያት የለውም። በአብዛኛው ከሴሮቶኒን(serotonergic neuron) መዛባት ጋር ይያያዛል። በተጨማሪም ከዘረ- መል(gene) ጋር ሊያያዝ የችላል ። ቤተሰብ ውስጥ አናት ፣አባት፣እህት፣ወንድም፣ልጅ ካላቸው እኛ ላይ የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል። በአብኛው በወጣትነት የሚጀምር ሲሆን በየትኛውም ዕድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል። ሴቶች ከ ወንዶች አንፃር ከ ሁለት እስከ ሦስት እጥፍ ይጠቃሉ። የሆርሞን መዛባት አንዱ ምክንያት ስለሆነ ማይግሬን ያለባቸው ሴቶች በወር አበባ ጊዜ ሊነሳባቸው ይችላል። አንድ ሰው ዝቅ ሲል በዓመት ሁለቴ ከፍ ሲል በሣምንት ከሁለት እስከ ሦስቴ ሊታመም ይችለል። ማይግሬን መሆኑን በምን እናቃለን? ምልክቶቹስ?
✍️ማይግሬን በጥቅሉ በሁለት ይከፈላል። ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ያለው (migraine with aura) እና የሌለው(without aura)።አብዛኛው (70- 80%) ቅድመ-ማስጠንቀቂያ የሌለው ነው። ቅድመ-ማስጠንቀቂይ ምንድን ነው? ምልክቱስ????
ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ራስ-ምታት ልክ ከመጀመሩ በፊት ራስ-ምታቱ እንደሚጀምር የሚጦቁሙ ምልክቶች ናቸው። ብዙ ጊዜ ከ ዕይታ ጋር የተያያዙ ሲሆኑ ልክ እንደ ዝግዛግ መሰመሮች መታየት፣በአንድ ጎን እይታ መጋረድ፣ተጨማሪ ቀርፆች ወይም መስመር መታየት እና ወ.ዘ.ተ. ናቸው። ከዚህ በመቀጠል ራስ-ምታቱ የጀምራል። ራስ-ምታቱ በአንድ በኩል ከፍሎ የሚያም ሲሆን (በግራ ወይም በቀኝ ፣በተለያየ ጊዜ ቦታ ሊቀያይር ይችላል፣አሁን በቀኝ ሌላ ጊዜ በግራ) የመምታት(pulsating )በኃሪ አለው።የህመሙ ክብደት ከ መካከለኛ እስከ ከባድ የሚመደብ ሲሆን አንዴ ከጀመረ ከ 4ሰዓት እስከ ሥስት ቀን ሊቆይ ይችላል። ከራስ-ምታት በተጨማሪ ማቀለሽለሽ፣መስመለስ ሲኖረው ድምፅ፣ብርሃን እና ሽታ ራስ-ምታቱን ያባብሰዋል። ስለዚህ ማይግሬን ያለባቸው ሰዎች ተከናንበው(ተከናንበን) መተኛት እንጂ መንቀሳቀስ አይፈልጉም።
✍️ምን ምን ሊያስነሳው ወይም ሊያባባሰው ይችላል?
1) የስሜት መቀያየር(መበሳጨት፣መናደድ፣ጭንቀት፣
2) የሆርሞን መዛባት(በወር አበባ በሌላ፣)
3) የእንቅልፍ መዛባት(መብዛት ወይም ማነስ)
4) ርሃብ(ምግብ በሰዓቱ አለመብላት)
5) ምግብ ውስጥ ሚገቡ ቅመማ ቅመሞች፣ቸኮሌት
6) ድምፅ እና ብርሃን ዋነኞቹ ናቸው
እዚህ ጋር በጣም አስፈላጊው ነገር ከተዘረዘሩት ውስጥ የትኛው እንደሚያስነሳብን ለይተን ማወቅ አለብን። ለ አንዱ ሚያስነሳው ለሌላው ሰው ላይሆን ይችላል።
✍️ህክምናው ምንድነው?
✍️ሥስት የህክምና ደረጃዎች አሉት።ከሁሉም የመጀመሪያው በጣም አስፈላጊ እና የተሻለው ነው።
ሀ) የመጀመሪያው ህክምና ቅድም ከዘረዘርናቸው ማይግሬንን ከሚያስነሱ ነገሮች እኛን የሚያስነሳብንን መለየት እና እሱን በማስወገድ መከላከል ነው። ማይግሬንን መከላከል ከማካም በብዙ ምክንያቶች የተሻለ አማራጭ ነው። ማይግሬን አንጎል ላይ ሚያመጣውን ጉዳትም ማስቀረት ይቻላል።በጥቅሉ ንዴት እና ጨንቀትን መቀነስ፣በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ምግብ በአግባቡ መመገብ፣እንቅስቃሴ ማድረግ፣ቸኮሌት፣ቅመም የበዛባቸውን ምግብ መቀነስ እና ወ.ዘ.ተ. ?ለኔ የተሻለው ህክምና ይሄ ነው።
ለ) ሁለተኛው ህመሙ ከጀመረን በኃላ የሚወሰዱ የመስታገሻ መድሃኒቶች(abortive treatment)ናቸው
ብዙ ዓይነቶች አሉ እንደ ህመሙ ክብደት የሚወሰን ነው።እነዚህ መድሃኒቶች የራሳቸው የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው። አነዚህን መድሃኒቶች በተደጋጋሚ(frequently) ወይም በተከታታይ(regularly) መውሰድ አይመከርም። አንደኛ በተከታታይ ለብዙ ጊዜ ሲወሰዱ መድሃኒቶች ይለምዱ እና( tolerance) ህመም የማስታገስ አቅማቸው ይቀንሳል ወይም ከነ ጭራሹ አያስታግሱም። ሁለተኛ መድሃኒቶቹ እራሱ በተደጋጋሚ እና በተከታታይ ሲወሰዱ ራስ-ምታት ያመጣሉ( overuse headache) ይባላል. ይህ ለማከም ያሰቸግራል።
ሐ) ሥስተኛው የቅድመ መከላከያ ህክምና( prophlactic treatment) ነው። ይህ የሚታዘዘው በጣም በተደጋጋሚ ጊዜ ከባድ ማይግሬን ለሚያማቸው ማለትም በወር ውስጥ ከ ዓራት ጊዜ በላይ እና በ "ለ" ሥር በጠቀስናቸው መድሃኒቶች መታከም ካልቻል ወይም ማስታገስ ከልቻሉ የሚታዘዝ ነው። አዚህ ውስጥም ብዙ ዓይነት ምርጫዎች አሉ(ወደ ዓራት ሚጠጉ)።
✍️የነዚህ ዓላማ የማይግሬኑን ድግግሞሽ በ ግማሽ መቀነስ ነው ማለትም አንድ ሰው በወር ውስጥ 6ቴ ሚታመም ከሆነ ወደ ሥስት ይቀንሳል ማለት። በጥናቶች መሠረት በተጨማሪም የህመሙን መጠንም ይቀንሳሉ። ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶች የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ቢያንስ ለ አንድ ወር በየ ቀኑ መወሰድ አለባቸው።እነዚህ መድሃኒቶች በ "ለ" ሥር የተጠቀሱት መድሃኒቶች በደንብ እንዲሰሩም በተጨማሪም ይረዳሉ።
ማይግሬን ምን ጉዳት አለው?
ተደጋጋሚ ማይግሬን አንጎል ላይ ጉዳት ያመጣል። በማይግሬን ምክንያት የመናገር ክህሎት ዘዬ(accent)ማጣት የደረሰባቸው ሰዎች አሉ።አንድ አንድ መረጃዎችም ማይግሬን ያለባቸዉ ሰዎች የማስታወስ ችሎታቸው እንደሚቀንስ ይጦቁማሉ።
Mustefa Dilu(MD)
የምፅፋቸው ቁምነገሮች እየተጠቀማችሁ ነው?
በአገልግሎቴስ ደስተኛ ናችሁ?
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago