Addisu Derebe

Description
ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉኝ "ዘጠኙንም ግባ በሉት" የምል ኩሩ አማራ ነኝ!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 3 weeks ago

~ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!

አማራን ለመጨፍጨፍ በአገዛዙ የተላከን የኦሮሞ ልጅ ማርኮ ተንከባክቦ ወደቤተሰቦቹ የሚልከው የፋኖ ሠራዊት ሰላሌ ድረስ መጥቶ አንድ ምስኪን ታዳጊ የሚገድልበት ምድራዊ አመክንዮ የለም።

ይልቅስ እነ በቴ ኡርጌሳን የበላው አገዛዝ ፣ ሐጫሉንም የገደለው ሥርዓት፣ የከረዩ አባገዳዎችን የጨፈ*ጨፈው አገዛዝ ፣ በኦሮሚያ የሚታፈሱ ወጣቶች የፈጠረውን የሕዝብ ቁጣ ለማስታገስ የፈፀመው ርካሽ ተግባር ነው።

አለሁ የሚል "መንግስት" ካለ የሰላሌ ሕዝብ ቀንበር ተሸክሞ የጠየቀው ጥያቄ ቢኖር "አርሰን እንድንበላ የሚያሠማራውን ታጣቂ ያስታግስልን" የሚል ነው።

ፋሽስቱ አብይ ሆይ፥ በእንደዚህ አይነት እንጭጭ ድራማ በፍፁም አትድንም!

አዲሱ ደረበ

1 month, 3 weeks ago

~ የአንድ ብሔር ማንነት ቅርፅ የሚያገኘው በቀውስ ወቅት ነው!

የአማራ ማንነትና ምንነት ቅርፅ የሚይዘው በዚህ የጥፋት አዋጅ በታወጀበት ወቅት ነው። ለአንድ ብሔር የተሟላና አንድነት ያለው እድገት በአማራነት ላይ፣ በጋራ ጥቃትና ፀጋዎች ዙሪያ የሚገነባ (የበጎም ሆነ አስከፊ) ትዝታዎችና ገጠመኞች አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ነው።

የዚህ መሣሪያው ደግሞ ብሔርተኝነት ነው!

ብሔርተኝነት ያሳለፍነውን ለማስታወስ ፣ ሕልማችንን ለመተንተን እና በግል ጉዳያችን ተደብቀን የጋራ ሕልውናችን እንዳይጠፋ የሚያደርግ ነው።

ፈተናዎች የማሕበረሰብን አንድነት በመፍጠር የተወረሱ ልዩነቶችን የማጥፋት ጉጉት ይፈጥራሉ። ለጋራ አላማና አንድነት ስንቆም ጥቃቅን የልዩነት መንስኤዎችን እናፈርሳለን። በጋራ ጥቃት ውስጥ ልዩ የጥቃት ተረክ አሉታዊ ስለሆነ!

ምሑራንን የሚጠቅሰው ወዳጄ እንደሚለው፦

"Deliberate forgetfullness and misrepresentation of historical facts constitute the importance of Nation building." ሲል ሰምቼው አውቃለሁ።

ማንነት ሲፈተን ክብር ፈተና ይገጥመዋል። ምክንያቱም፦

"National identity is fundamentally a matter of dignity. It gives people a reason to be proud of." ብሎም አሳርጎታል።

የምንኮራበት አማራነት የመሰባሰቢያና በአንድ የመሰለፍ ልዩ ማንነታችን ነው።

በአማራነት ጥላ ስር ለአንድ አላማ፤ በአንድ እንሰለፍ!

አዲሱ ደረበ

2 months ago
Addisu Derebe
2 months ago
Addisu Derebe
2 months ago
~ የአማራ አንገቱ አንድ ነው!

~ የአማራ አንገቱ አንድ ነው!

"ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ቢመጣ ተነሳሁ የሚለው አማራው ሕዝብ ላይ እንጂ ለይቶ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ አይልም፡፡

እኛም ወደድንም ጠላንም የአማራው አንገት አንድ መሆኑን ማወቅ አለብን። ስለዚህ አማራው መተባበር አለበት"

ደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቁስላሴ 1965 ዓ.ም

2 months ago

~ ሰበር!

~ ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጧት 4 ሰዓት ባህር ዳር ኤርፖርት ወታደራዊ ሄሊኮፍተር ወድቃለች፤ በዚህም በረራ ተቋርጧል!

2 months ago

~ የሚና ድንበር እና አንድነት የትግሉ መሠረት ነው!

በአማራ ትግል ውስጥ ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ሚናን ማወቅ እና በአንድነት መታገል መሠረታዊ ናቸው።

አማራነት፣ በማንነት መጠቃት፣ የጋራ ትግል ማድረግ፣ የጋራ ተስፋና አማራዊ ፍላጎት አንድ ቢያደርገንም በትግሉ ውስጥ ሁሉም አማራ ተመሳሳይ ሚና የለንም፤ ሊኖረንም ያስቸግራል።

ትግሉ ሁለገብና ዙሪያ መለስ ነው!

የፖለቲካዊ አላማዎቻችንን ለማሳካት እንደሚናችን በተለያየ መስኩ መሠለፍና ሚናችንን መወጣት ይጠይቃል። የወታደራዊ ትግል፣ የሚድያና ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ የመረጃ ትግል፣ የዲፕሎማሲ ትግል ፣ የእውቀትና የሪሶርስ ትግል የመሳሰሉ ሰፊ ሚናዎች ያሉበት ነው።

እንደችሎታችንና እንደአቅማችን እንሠራለን እንጂ ሁላችንም ሁሉንም ልንሆንና ልንሠራ አንችልም።
ሚናችንን ማወቅ፣ በሚናችን ውስጥ የሚደረጉትን ተግባሮች መለየት፣ በዚያ ሚና የምንሰለፍና የምንሳተፍ አካላት በአንድነት ቆመን ኃላፊነታችንን መወጣት ቁልፍ ጉዳይ ነው።

የምንሠማራበትን የትግል መስክ ማወቅና ውጤታማ የሚያደርግ ስራ ነው የሚጠበቀው። በተሰለፍንበት መስክ ትግሉ እንዲያሸንፍ መስራት የግድ ይላል። ሚናን አውቆ አለመታገል ትግሉን ይጎዳልና!

የዲፕሎማሲ ሥራ የሚሠራ ዲያስፖራ ወታደራዊ አደረጃጀትን ልወቅላችሁ ካለ ይበላሻል። የሚድያ ስራ መስራት ያለበት የውጊያ አካሔድ ካልመራው ካለ ችግር ይፈጠራል። ሚናንና ችሎታን ማወቅ ጠቃሚ ነው!!
በዚህ ውስጥ አንድነት የግድ ነው። የቆምነው ለአንድ ሕዝብ ነው። የምንታገለው ለጋራ ማንነታችን ነው!

ሚናን ባለማወቅ ከአንዱ ወደአንዱ መዝለል አንድነትን ያበላሻል።ሚናን ያዳክማል!

ሰሞኑን የተጀመረው የዲያስፖራው ንቅናቄ ጥሩ ጀምር ነው። የአሜሪካ ኮንግረስ እጩዎችን ሁሉ ቀርቦ ለመቀስቀስ የተሠራበት፣ በየአሕጉራቱ በአማራዊ አንድነት ለአንድ ሕዝብ ድምፅ የመሆን መልካም ጅምር ነው።
ሚናው ዲፕሎማሲያዊ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ያንን ሚና ወታደራዊ አደረጃጀቶች ወይም የአገር ውስጥ የፖለቲካ መሪዎች አያደርጉትም። ዲያስፖራው ግን እያደረገው ነው። ዝም ያለውን አማራ እየቀሰቀሰ ነው። የመንግስታትን በር እያንኳኳ ነው።

በዚህ የዲፕሎማሲ ትግል የላቀ ድል እስኪመጣ መቀጠል ያለበት ነው። የሪሶርስና የእውቀት አበርክቶውም እንዲጨምር በስፋት መሔድ ያለበት ነው።
አውሮፓና አሜሪካ ሆኖ የፋኖ ሠራዊት አደራጅና መሪ መሆን አይቻልም። ሚናን ያበላሻል!

በወቅቱ የዲያስፖራ ንቅናቄ ተመልካች የሆኑ በርካቶች መኖር የአንድነት ስራው ላይ የጎደለውን ሥራ ጠቋሚ በመሆኑ ሰፊ ትግል ይጠይቃል።

ከምንም በላይ ዲያስፖራው ትግሉን ወጥ የሆኑ የጋራ ተቋማትን በማጠናከርና ወደአንድ በማሰባሰብ የመስራት ኃላፊነት አለበት። የተኳረፈ ሁሉ በየፊናው ኮሚቴ፣ ድርጅት፣ ፎረም እየመሠረተ የጋራ ሚናን በአንድነት ለመወጣት ይቸግራል።

ሚናን በብቃት እና በአንድነት መወጣት የድል መንገድ ነው። ሚናን ተቋማዊ ማድረግ ደግሞ የዘላቂ ድል ሐዲድ ነው!

አዲሱ ደረበ

2 months ago

ከተወዳዳሪነት ይልቅ ወደ ተባባሪነት እንለወጥ!

ለተወሰነ ዓላማ ሳይሆን ለአማራዊ አላማ እንሰባሰብ!

አጠር ላለ ሽርክና ሳይሆን ለዘላቂ አማራዊ ጥቅማችን እንተባበር እና በአንድነት እንቁም!

ድል ለአማራ!

#WarOnAmhara
#AmharaGenocide

2 months ago

~ ትግል ነው መሪዎችን የሚፈጥረው ወይንስ መሪዎች ናቸው ትግል የሚፈጥሩት ?

ይሔ ሀሳብ በያለንበት ብንመክርበት መልካም ነው። በመሪዎች እና አስተባባሪዎች ሁናቴ የሚቆም ትግል፥ ትግል አይደለም።

የሚመራን ሰው አንድ ነገር ከሆነ ፣ የሚያታግለን ድርጅት አንድ ነገር ከሆነ፥ አለቀልን የሚመስል ስጋትና አመለካከቶች በልካቸው መጤን አለባቸው።
የአማራ ትግል ፡ የሆነ ሰውዬ ደሕና እስከሆነበት ድረስ ፥ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ጤነኛ እስከሆነ ብቻ ሕልውና የሚኖረው አይደለም፤ ሊሆንም አይገባም!

ምናልባት የአላማ ጥራት ፥ የስትራቴጂ እና ስልቶች ትክክለኛነት ላይ የጠራ ግንዛቤ አለመያዝ የፈጠረው ሊሆን ይችላል። የአላማ ስትራቴጂ እና ስልቶች ጥራት ቢኖር ፣ አላማው ከግለሰቦች በላይ መሆኑን እንረዳ ነበር። የአላማው አልፋና ኦሜጋ ሕዝብ እንደሆነ እንገነዘብ ነበር።

ፊት መጥተው የአማራን ጉዳይ በሚችሉት ልክ የሚታገሉና የሚያታግሉትን ግለሰቦች ማድነቅ ተገቢ ነው ማለት ፥ ግለሰቦቹ ትግሉንና አላማውን ይተካሉ ማለት አይደለም ። ወይንም በዚያ መጠን ውዳሴና እርግማን መቅረብ አለበት ማለት አይደለም።

በዚህ ትግል ላይ ፊታውራሪ የሆኑ መሪዎች በግልም ሆነ በቡድን ለአማራ ሕዝብ ትግል የየራሳቸውን አወንታዊና አሉታዊ ሚና ሊወጡ ይችላሉ። መቼም ቢሆን ግን የአማራን ብሔራዊ ትግልና አላማ አይተኩም። የአማራ ትግል ከግለሰቦቹ በላይ ነው። ሁሉም ከአማራ በታች ናቸው። ከአማራ አላማዎች በታች ናቸው። የአንድ ትውልድ አላማ ከያዝን አዎ ፥ ትግላችን የሕልውና ይሆናል።

ከፕ/ር አስራት ፣ ከጀነራል አሳምነው ፣ ከዶ/ር አምባቸው ፣ ከጎቤ መልኬ ፣ ..... ከሌሎችም ፣ ከሌሎችም ጋር የተቀበረ ትግል እና አላማ አለመኖሩን ማረጋገጥ እስከቻልን ድረስ የአማራ ትግል ዛሬም ነገም ሕያው ነው

አሁን፥ ፊት ካሉት እና ከሚመጡት ጋር የሚቀበር አላማ እና ትግል አለመኖሩን ማረጋገጥ የሚቻለው አላማችን የትውልድ፣ ትግላችን የሕዝብ ሲሆን ነው።

ጠላት ይሔንን ይወቅ

በሚታሠር ወይ በሚወድቅ ታጋይ የሚቆም ትግል፣ የሚዳፈን አላማ የለም። በፕ/ር አስራት፣ በጀራል አሳምነው ፣በአምባቸው ወይ በሌሎች ሞት ቆሞ የቀረ ትግል የለም።

የምንታገለው ለላቀ አማራዊ ሕልውና እንዲሁም የፍትሕና ርትዕ መረጋገጥ እስከሆነ ፥ በጥቂት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የትግል ዘመን ብቻ የሚቆምና የሚቀጥል፣ የሚሳካ እና የሚወድቅ እንዳይሆን አድርገን ባሕር ለሆነው ሰፊ ሕዝባችን እናስርፀው

ግለሰቦች የላቀ ሚና አላቸው!!
አያከራክርም !!
መሪዎች ያስፈልጋሉ!! ማክበርና መጠበቅ ይገባል!!
አያከራከርም!!

በትግል ትክክለኛነት ላይ ያመነ ማሕበረሰብ ሲኖር መሪዎች ሁሌም ይወጣሉ።የእነዚያ መሪዎች ሚናቸው ፣ ቆራጥነታቸው፣ ተቆርቋሪነታቸው፣ አላማቸው ፣ የሚከፍሉት ዋጋ ለሕዝብ የተጋራ እሳቤ መሆኑን ማረጋገጥ እንጂ፥ እነሱን ራሳቸውን ትግል ማድረግ አይጠቅምም !!

አንዳንድ መሪዎች የሚታገሉለትን ትግል አላማና ማስፈፀሚያ ለሌላው ሳይሸጡትና ሳያጋሩት ይቀራሉ። ስለሆነም ግለሰቦቹ እንጂ ሀሳባቸው የትግል ማዕከል አይደረግም። ብዙ ጊዜ ግለሰቦችን ትግል የሚያደርጉ ሰዎች፥ ስምና ፎቶ ይዞ መዞር እንጂ የሚያነሱ የሚጥሏቸውን ሰዎች አላማ እና የትግል መንገድ አያውቁትም።

በግለሰቦች ላይ የሚንጠለጠል አጀንዳና ትግል አደገኛ ነው።

➙ አንደኛ ግለሰቦቹን ያሳስታቸዋቸል፥ አይተኬነት ስሜት ይፈጥራል።
➙ ሁለተኛ ግለሰቦቹ ከሆኑትና ከሚችሉት በላይ የሆነ ገፅታ (Image) በመፍጠር የሚሠሩትና የሚጠበቅባቸው የተራራቀ ሲመስለን እንቀየማቸዋለን።
➙ ሶስተኛ የመሳሳት ተፈጥሯዊ መብታቸውን ይነፍጋል።
➙ አራተኛ ቢሳሳቱ ወይ ቢጠፉ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይፈጥራል።

ሕዝብን በተግባር የሚያንቀሳቅስ አጀንዳ እናስርፅ፣ እንታገል !!

ድል ለአማራ!

#WarOnAmhara
#AmharaGenocide

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana