ጥንቅሻ✍🏼🦋

Description
ውስጣዊ የህሊና ድምፅ"
Get it down….
አስተያየት👉🏻 @sumey_afedlu

የመወያያ Group👉🏻 https://t.me/+AWrWNOeYxLpjMWM0

TikTok👉🏻 https://www.tiktok.com/@tenqesha43?_t=8pL3P6glx3u&_r=1
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months, 2 weeks ago
***❤️******❤️***

❤️❤️

2 months, 2 weeks ago

እስኪ ስለሷ አውራኝ አልኩት ብወደውም ስለሷ ሲያወራ ፊቱ የሚፈካው መፍካት፣

ጉንጮቹ ቀይ የሚሆኑት ነገር፣ ቃላት ፍለጋ የሚጨነቀውን መጨነቅ ማየቱ ያስደስተኛል፣

ሊናገር ሲጀምር የአይኑ ብሌን ቅርፁን ሲለውጥ አስተዋልኩ፣ ሰው እንዴት በዚህ ልክ ሰው ይወዳል?

ታድላ....

2 months, 2 weeks ago

እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::

በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤

እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤

ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ፤

ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::

2 months, 4 weeks ago

ሀዘን ያለበት ጹሑፍ ስለሚያምር ሳይሆን እኛን ስለሚስበን ነው።ለምን ሳበት ካልነ የተለያዮ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል

ሁሉም ሰው ያለፈበት የህይወት መስመር ውስጥ ብዙ መከራዎችን አልፏ ሲመጣ ያፈራው ቁስል አለ እናም ያን ሬት ሬት የሚሉ ግጥም ፣ ሙዚቃ ፣ ፊልም ፣ ስነ ጹሑፍ ስራዎችን ሲመለከት የራሱን ቁስል ያከከለት ስለሚመስለው አዘውትሮ ማየት ያስደስተዋል።ልክ እንደ ቃሪያ እያቃጠለውም ቢሆን እየበላ ይደሰታል።

ወይም ደግሞ

'ያልበላኝን ሁሉ ሳክ ሳክ ኑሬ
የበላኝ ላይ ስደርስ አለቀብኝ ጥፍሬ"

እንዲሉ አንዳንዴ ባልበላን ነገር ላይ የሰውን ጉዳይ ስናክ ከርመን እኛ የችግር ቁስል ሲገጥመን ማከኪያ ጥፍር እናጣለን ያኔ  ሬት ሬት የሚሉ ፊልሞችን ማየት ፣ ሙዚቃዎችን መስማት ፣ ጹፏችን ማንበብ እንደ ጥፍር ያገለግሉንና ቁስል ማከኪያነት እንጠቀምባቸዋለን።

ወይም ደግሞ

ህጻን ልጅ ሲያለቅስ ዝም ለማስባት ከፈለግህ አብረኸው አልቅስ ያኔ ብሶቱ በአንተ ዘንድ የተሰማለት ስለሚመስለው ዝም ይላል።እንደ ሚባለው ሁሉ እነሱ'ም የወጡበትን ውጣ ውረድ መከራ በሌሎች ዋጋ ተሰጦት ይህ የጥበብ ስራ መሰራቱ ሲያዮ ጩኸታቸው እንደተሰማ ሲያዩ ይደሰታቱ።

ወይም ደግሞ

'bad news Good' እንደሚባለው ሰው ከመልካም ዜና ይልቅ መጥፎ ዜና የሰውን ትኩረት ይስባል።ምን አልባትም ያ መጥፎ ዜና ቀድሞ በመስማቱ እሱ ላይ እንዳይደርስ ቅድመ መከላከል ለማድረግ ይሆን ?!

.....
ይመስለኛል😊

From: ኒያስ

3 months ago
3 months, 1 week ago

የሰውን ልጅ በትክክል መረዳት ማለት ልብ ውስጥ የሚገኘውን፣
.
ሰው ትክክለኛ እይታውን፣ ሁኔታውን እና ማንነቱን እንዲገለጥ ልብ ውስጥ ቦታ መተው ማለት ነው፣
.
ቀድሞ ፈራጅ አለመሆን ፣ ቀድሞ እሱ እኮ እንደዚህ ነው፣ እሷ እኮ እንደዚህ ነች ፣
ብሎ በር አለመዝጋት ነው ፣
.
ሰውን እንዳመጣጡ መቀበል ነው፣ ቀድሞ አለመወሰን ነው!!

3 months, 2 weeks ago

**የገረጣ ልጅ ታውቃለህ? እናቱ ቀባብታ የምታወዛው
ቆይቶ መገርጣቱ ላይቀር
እንዳያሳጣት በብስጭት የምትቀባባው

እንዲያ ነው...

የገረጣ ህይወቴን ቀባብተህ ያወዛኸው
ነግቶ ንጣት ሊገለው
ቅባት በዞረበት ያላለፈ ሊመስል
ስታየኝ ትንሽ አመር ይላል....**

3 months, 3 weeks ago

እሱስ ቢሆን መች አምልጦ
ጎፈር ፀጉሩ ተመላልጦ
ጡንቻው ጉልበቱ ተሟጦ
ያው ቀረኮ ቤት ተቀምጦ

ፂሙ ላዩ ላይ ሻገተ
እግሩም ለመቆም ታከተ
ወፍራም መነፅር ፍለጋ
እጁ ፍራሽ ላይ ባተተ
እድሜ ይህ ነገረኛ
እሱንም ኪሱ ከተተ

ግን ግን
ምን ተሰማው ያ አንበሳ?
ከነ መኖሩም ሲረሳ
አካል ቁመናው ሲከሳ

©️

6 months ago

የገዛ ህመሜን ማባረር በድንገት ያምረኛል፣

ከፈገግታ መሀል ጥልቅ ስህተቶች የፈጠሩት እንባ እንዳለ አይገባቸዉም፣

ብዙ ጉድለቶችን የሞሉ አስታማሚ መልካም ትዝታዎች አሉ፣

አንድ አንዴ ተቆልሎ የሚታየን የቀድሞ ስህተቶቻችን የወለደዉ ህመም ከህልማችን ገፍቶ እንዳይጥለን እፈራለዉ፥

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana