ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
*? የተጅዊድ ትምህርት ክፍል - ሐያ አምስት
⭕️ የኢዝሐር (ግልፅ የማድረግ) አይነቶች
➦ ቁርአን በምንቀራበት ጊዜ የኢዝሐር ( ግልፅ የማድረግ ) አይነቶችን በአጠቃላይ ወደ ስድስት ክፍሎች ይከፈላሉ።
እነርሱም፦?
❶) ኢዝሐሩል ሀልቂይ
?ከኑን ሳኪና (ن) ወይም ከተንዊን ( ـٌ ـً ـٍ ) በኋላ ከስድስቱ የጉሮሮ ፊደላቶች ( ء ه ع ح غ خ ) ውስጥ አንዱ ከመጣ ኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ኢዝሐር (ግልፅ) ተደርጎ ይነበባል።
◌ ይህ ኢዝሐር ኢዝሐሩል ሀልቂይ ተብሎ ይጠራል።
ምሳሌ፦ مَن أمَنَ ، يَنهَوْن ، أحَدًا أبَدًا ، حَكِيمٍ حَمِيد
❷) ኢዝሐሩ አሽ-ሸፈዊይ
?ከሚም ሳኪና (مْ) በኋላ የሚመጡት ፊደላቶች ከ"ባ" እና ከ"ሚም" ፊደል ውጭ ከሆኑ ሚም ሳኪናዋ ኢዝሐር (ግልፅ) ተደርጋ ትነባበለች። ይህ ኢዝሐር ኢዝሐር ሸፈዊይ ተብሎ ይጠራል።
ምሳሌ፦ هُم فِيهَا ، لَكُم دِينُكُمْ
❸) ኢዝሐሩል ሙጥለቅ
?ኑን ሳኪና ከድስቱ የኢድጋም ፊደላቶቿ ( ي ر م ل و ن ) ውስጥ በተለይ ከ" و " እና ከ "ي " ፊደላቶች ጋር በአንድ ቃል ላይ የምትመጣ ከሆነ ኑን ሳኪና ኢዝሐር (ግልፅ ) ተደርጋ ትነበባለች። ይህ ኢዝሐር ኢዝሐር ሙጥለቅ ተብሎ ይጠራል።
○ ይህን በቁርአን ላይ የምናገኘው በአራት ቃላቶች ላይ ብቻ ነው።
እነርሱም፦ صنوان، قنوان، بنيان، الدنيا ናቸው።
❹) ኢዝሐሩል ቀመርያ
?ከሀምዘቱል ወስል በኋላ የምትመጣው ላመ ተዕሪፍ ከሷ በኋላ የቀመርያ ፊደላቶች ከሚባሉት 14 ፊደላቶች (ابغ حجك وخف عقيمه) አንዱ ከመጣ ላም ሱኩኗ (ላመ ተእሪፏ) ኢዝሐር ( ግልፅ ) ተደርጋ ትነበባለች። ይህ ኢዝሐር ኢዝሐሩል ቀመርያህ ይባላል።
❺) ኢዝሐሩል ዋጅብ
?ላም ሳኪና በፊዕል (በግስ) ፣ በስም ፣ በአምር (በትዕዛዝ) እና በፊደል ( هل ، بل ) ላይ ስትመጣ ኢዝሐር (ግልፅ) ተደርጋ የምትነበብበት ሁኔታ ኢዝሐር ዋጅብ ተብሎ ይጠራል።
● ስለ ላም ሳኪና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ በዚህ ማስፈንጠሪያ ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ?t.me/Merkezhuzeyfetulyeman/579 ❻) ኢዝሐሩ ሪዋያህ
? በሱረቱል ቀለም { نۤۚ وَٱلۡقَلَمِ وَمَا یَسۡطُرُونَ } እና በሱረቱል ያሲን {یسۤ وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡحَكِیمِ } ላይ ኑን (ن) እና (س) ላይ ያለችው ኑን ሳኪና የምትነበበው ኢዝሐር (ግልፅ) ተደርጋ ነው። ይህ ኢዝሐር ኢዝሐሩ ሪዋያህ ተብሎ ይጠራል።
✍? ??? ???????? ???? ????????
*⛔️ አዲስ የተጅዊድ ትምህርት
? የላይቭ ደርስ ቅጂ
⛽️ ክፍል - 25
? በወንድም አቡ ሁዘይፋህ
?ኪታብ ፦ ተጅዊድ አል-ሙሶወር
➦join ??➴
[Lоаdіпg.. ██████████████] 98%
Lоаdіпg.. ██████████████] 99%](https://t.me/addlist/pThA-JBwhDcwYmZk)
*? እህት ወንድሞች ለመመዝገብ ከመምጣታችሁ በፊት ማስታወቂያውን በደንብ አንብቡት ባረከሏሁ ፊኩም !
ምሳሌ ፦
1) የመመዝገቢያ ቀናቶች
2) የተማሪዎች መብት
3) ለመመዝግብ አስፈላጊ መስፈርቶች
4) የተማሪ ግደታዎች
5) የሚሰጡ ቂርአቶች
6) ቂርአት የሚጀመርበት ቀን ወ.ዘ.ተ
♻️ ሁሉንም መረጃ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
???????????*https://t.me/Merkezhuzeyfetulyeman/1620
?የተጅዊድ ጥያቄ
?የተጅዊድ አርካኖች የሚባሉት ስንት ናቸው ? ዘርዝሩ
መልስ Comment ላይ ?
◈ ስትመልሱ ጥያቄ ይጨመርላችሗል በርቱ እሽ ¡
ማስታወቂያ ለቂርአት ፈላጊዎች ቀን፦ 20 /12 / 2016
? መርከዝ ሁዘይፈቱ ኢብኑ'ል-የማን ከዚህ በፊት በ online ሲያስተምራቸው ከቆየው ነባር ተማሪዎች በተጨማሪ በአድሱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ አድስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።
?በዋናነት በመርከዙ የሚሰጡ ትምህርቶች (በክፍያ)
? ***ቃዒደቱ ኑራንያን በየደርሱ የካሉት የተጅዊድ ህግጋቶችን ከማስረዳት ጋር
? ቁርአን በነዞር እና በሒፍዝ ተገቢውን ክትትል እና ፈተና ከመስጠት ጋር
? የተለያዩ የተጅዊድ ትምህርቶችን ከዝቅተኛ (ከጀማሪ) ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የተጅዊድ ኪታቦች***
===================================
◆ከዚህ በተጨማሪ ለተማሪዎች ብቁነት የሚረዱ በቅደም ተከተል የሚሰጡ ትምህርቶች (ከክፍያ ነፃ)
? ***የአቂዳ ትምህርቶች
? የፊቅህ ትምህርቶች
? የሚንሐጅ ትምህርቶች***
? የመርከዙ ዓላማ በዋናነት ተማሪዎቹን የሚሰጣቸውን ትምህርት ትኩርት አድርገው እስከተከታተሉ ድረስ በተጅዊድ ብቁ አድርጎ የተከበረውን የአላህን ንግግር በሆነው ቁርአን ላይ ምላሳቸውን ከስህተት ጠብቀው በተፈለገው መልኩ እንድቀሩ ማድረግ ነው።
===================================
◆ተማሪዎች ተግባራዊ ማድረግ ያለባቸው ግደታዎች
➊. ***በተሰጣቸው የቂርአት ጊዜ በሰአት መገኘት (አለማርፈርድ) እና ያለ ምንም ምክንያት ወይም ያለፈቃድ አለመቅረት።
➋. የሚሰጣቸውን የቁርአን ትምህርት ኡስታዛቸው ጋር ከማሰማታቸው በፊት ትኩረት እና ጊዜ ሰጥተው ቢያንስ አምስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ ሙራጅዓ ማድረግ አለባቸው።
? ይህ ወሳኝ ነጥብ ነው ምክንያቱም አቀራርን ለማስተካከል በተደጋጋሚ በመቅራት ምላስን ማለማመድ ዋናው ከመሆኑ ጋር ብዙ ተማሪዎች ችላ ያሉት ነው።
➌. ተማሪዎች ከሚሰጣቸው የግሩፕ ጓደኞቻቸው ጋር በሰአት በመገኘት አብረው ሙራጅዓ መደራረግ።
➍. ቂርአት ሲመዘገቡ የሚመዘገቡበትን አላማ አውቀው ለመለወጥ እና ለማወቅ ጉጉት እና ተነሳሽነት ያላቸው መሆን አለባቸው።
?አላማቸውን ሳይረዱ ጉሩፕ ገብቶ ለማጣበብ እና ለመቀመጥም ሆነ ለመተኛት ቦታ የለንም።
➎. የሚሰጣቸው ትምህርት ፈተና ያለው መሆኑን አውቀው ሁሌም በተማሩት ትምህርት ላይ ሁሌም ዝግጁ መሆን አለባቸው።
➏. ክፍያ ለሚያስፈልገው ቂርአት ክፍያውን በጊዜ መክፈል።***===================================
◆**የተማሪዎች መብት
➊. ያልገባቸውን እና ያልተረዱትን በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ
➋. የፈተና ውጤታቸውን በጊዜ የማግኘት እና ማወቅ
➌. ጊዜያቸውን ሙሉ የመጠቀም
➍. ኡስታዛቸውን በሰአታቸው በማግኘት መቅራት**
የመመዝገቢያ ጊዜ
?***ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 1 / 2017 ዓ.ል መመዝገብ ይቻላል።
?ለአድስ ተማሪዎች ቂርአት የሚጀመረው መስከረም 2 / 2017 ዓ.ል ነው።***
የቂርአት ሰአቶች
➨ጠዋት ከፈጅር በሗላ
➨ ቀን ከዝሁር በሗላ
➨ ከአሱር በሗላ
➨ ከኢሻ በሗላ
?የመመዝገቢያ አድራሻዎች
?ለሴቶች◈በቴሌግራም ? @Abu_Huzeyfah6 ◈ቀጥታ ለመደወል ? ? 09 12 03 43 09
? ለወንዶች
◈በቴሌግራም ? @Abu_Huzeyfah3 ◈ቀጥታ ለመደወል ? ? 09 12 03 43 09
ማሳሰቢያ
? በሚሰጣችሁ Username ተጠቅማችው ለመመዝገብ ስትመጡ ለመማር ከወሰናችሁ እና ከላይ የተፃፉትን መልዕክቶች ካነበባችሁ በሗላ ብቻ ነው።
? የተጅዊድ ትምህርት ክፍል - አስራ አምስት
? የመድ ምንነት
➽በባለፈው ክፍል (በክፍል ❶❹) እንዳየነው መድ በአጠቃላይ በሁለት ይከፈላል። እነርሱም መዱል አስሊይ እና መዱል ፈርዒይ ናቸው።
➽ በተጨማሪም ስለ መዱል አስሊይ ምንነት እና ክፍሎቹ በምሳሌ አይተናቸዋል።
በዛሬው ትምህርታችን የምናየው ስለ መዱል ፈርዒይ ምንነት እና ክፍሎቹ ይሆናል ተከተሉኝ ????
===========================
===========================
?የመዱል ፈርዒይ ምንነት እና ክፍሎች
➤መዱል ፈርዒይ ማለት ከሶስቱ የመድ ፊደላቶች በኋላ ሀምዛ (ء) ወይም ሱኩን በመምጣቱ ምክንያት የሚፈጠር መድ ማለት ነው። በሌላ አገላለፅ ከመዱል አስሊይ /ጦቢዒይ በኋላ ሀምዛ (ء) ወይም ሱኩን በመምጣቱ ምክንያት የሚፈጠር የመድ አይነት ነው።
መዱል አስሊይ/መዱል ጦቢዒይ ➛ + ሀምዝ (ء) ወይም ሱኩን = መዱል ፈርዒይ
➛ስለዚህ ለመዱል ፈርዒይ መፈጠር ዋና መሰረቱ ወይም ድልድይ ሆኖ የሚያገለግለው መዱል አስሊይ/ጦቢዒይ ነው።
?መዱል ፈርዒይ አምስት ዋና ዋና መዶች አሉት።
እነርሱም፦
❶. መዱል ዋጅብ ሙተሲል
❷. መዱል ጃኢዝ ሙንፈሲል
❸. መደል ላዚም
❹. መዱል ዓሪድ ሊሱኩን
❺. መዱል ሊን ናቸው።
⭕️እነዚህ የመዱል ፈርዒይ ክፍሎች ከሚፈጠሩበት ምክንያት አንፃር በሁለት ይከፈላሉ።
1) ከመድ ፊደላቶች በኋላ ሀምዛ በምጣቱ ምክንያት የሚፈጠሩ። እነርሱም ሁለት ናቸው። ❴ መዱል ዋጅብ ሙተሲል እና መዱል ጃኢዝ ሙንፈሲል❵ ናቸው።
2) ከመድ ፊደላቶች በኋላ ሱኩን በምጣቱ ምክንያት የሚፈጠሩ። እነርሱም ሶስት ናቸው። ❴ መዱል ላዚም ፣ዓሪዱን ሊሱን እና መዱል ሊን ❵ ናቸው።
♦️እነዚህ አምስት የመዱል ፈርዒይ ክፍሎች ሶስት አይነት ህግጋቶች አሏቸው።
እነርሱም፦?
1) ዋጅብ፦ ይህ ህግ ለመዱል ሙተሲል ብቻ የተሰጠ ነው።
2) ጃኢዝ፦ ይህ ህግ ከላይ ከተዘረዘሩት መዶች ለሶስቱ መዶች የተሰጠ ነው። ❮ መዱል ሙንፈሲል ፣ መዱል ዓሪዲን ሊሱኩን እና መዱል ሊን ናቸው።❯
3) ላዚም፦ይህ ህግ ለመዱል ላዚም ብቻ የተሰጠ ነው።
?እያንዳንዳቸውን በዝርዝር እንያቸው?
➊)መዱል ዋጅብ ሙተሲል
➨ይህ መድ የሚፈጠረው በአንድ ቃል ላይ ከመድ ፊደላቶች በሗላ ሀምዝ (ء) ሲመጣ ነው።
➢ ዋጅብ የተባለበት ምክንያት ይህ መድ ከሁለት ሀረካ በላይ መሳቡ ግድ በመሆኑ ላይ ሁሉም ቁራ'ኦች የተስማሙበት ስለሆነ ነው።
► የመሳብ መጠኑ ከአራት እስከ አምስት ሀረካ ያክል ነው።
ምሳሌ፦ ➛َجَآء ፣ ➛سُوٓءَ ፣ ➛سِيٓأت ወ.ዘ.ተ
➋) መዱል ጃኢዝ ሙንፈሲል
➨ ይህ መድ የሚፈጠረው በተለያየ ቃል ላይ ከመድ ፊዳላቶች በሗላ ሀምዛ ሲመጣ ነው።
➢ ይህ መድ ጃኢዝ የተባለበት ምክንያት ሁለት ሀረካ ያክል (በቀስር ወይም በማሳጠር) ስቦ መቅራት ስለሚቻል ነው።
►የመሳብ መጠኑ ከሁለት እስከ አምስት ሀረካ ያክል ነው።
ምሳሌ፦ ➛قُوٓ أنفُسَكُم ፣ ➛ يَآأيُّها ፣ ➛فِيٓ أعْنَاق ፣ ➛ لآ أُقْسِمُ ፣ ➛وَمَآ أَدْرَاكَ ወ.ዘ.ተ
⛔️ የመዱል ሙተሲል እና የመዱል ሙንፈሲል
አንድነታቸው?
►ሁለቱም መዶች የሚፈጠሩት ከመድ በሗላ ሀምዛ በመምጣቱ ነው።
ልዩነታቸው ደግሞ?
► መዱል ሙንፈሲል ሀምዛው እና የመዱ ፊደል በተለያየ ቃል ሲመጡ ሲሆን መዱል ሙተሲል ደግሞ ሀምዛው እና የመዱ ፊደል በአንድ ቃል ላይ ሲመጡ ነው።
►መዱል ሙተሲል የመሳብ መጡኑ በሁሉም ቁራኦ'ች ከሁለት ሀረካ በላይ መሳቡ ግድ ሲሆን መዱል ሙንፈሲል ፈጠን ባለ (ሀድር) አቀራር ሁለት ሀረካ ያክል ስቦ ማንበብ ይቻላል።
.....ይቀጥላል ኢንሻ አላህ .....
✍️አቡ ሁዘይፋህ ኢብኑ ሙሃመድ
ሀምሌ 20 /2015 E.C
ሙሐረም 9 /1445 H.
ሀምሌ 27 /2023 G.C
⛔️ ክፍል አስራ አራትን ለማግኘት ?
https://t.me/Merkezhuzeyfetulyeman/404
? ሌሎችም ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሸር አድርጉት
? ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል ?
?t.me/Merkezhuzeyfetulyeman
? ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል ?
? t.me/Huzefetulyemanqurancenter
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago