ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

Description
MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

hace 21 horas
ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)
hace 21 horas
ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)
hace 21 horas
ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)
hace 2 meses, 3 semanas

የማይፈወሰው ድውይ የማይመለሰው ጊጉይ! ++++++++++++++++++++++++++++++ ዕቅበተ እምነት ላይ እንጂ ተቋማዊ ጥበቃ ላይ ብቻ ማተኮር ማደክደክ ነው።
  ላይኛው ተቋም ለእውነት ሥራ ዝግጁ አይለም።
ከትናንት እስከ አሁን  በቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ውስጣዊ መከራ ተቋሙ የችግር ባለቤት ሳይሆን ራሱ ችግር ነው።
በተለይም የውጭ መከራዎችን እንደ እባብ ሰይጠንን ተጭኖ እየመጣ አዳማውያንን የሚያስትበት ቤት ከሆነ ሰነባብቷል።
ህልው ሁኖ አጀንዳ የሚሰጣችሁ ማን ነው?ይሄንን የማያውቅ ሰው ይኖራል? ካላ በጣም ፈዛዛ ነው።
ይልቅስ እንደ ባለቅኔው የጥፋት መልእክቱ ደርሶና የላካችሁ ሰውየ ደኅና ነውወይ? አትሏቸውም?
ይሄንን የምጽፈው በግል ሁኖ አንዳንድ የቤቱን ተንኮል ያልተረዱ የዋሓን ምእመናን ዛሬም ሲደናገሩ በማየቴ ነው።
የማይፈወሰው ድውይ የማይመለሰው ጊጉይ ሁኖ መድኃኒቱን እያማሰነ እንደገና በደዌ እያመረቀዘ የጥፋት ቫይረስ ተሸካሚ ሁኖ ከተገለጸ ቆይቷል።
አሁንም የአትርሱኝ ጩኸት ወዲያ ወዲህ ሲያወራ ቢሰማም ምእመናንን ዕረፍት ለመንሳት፣ለማደናገር፣የንትርክ አጀንዳ ለመስጠት፣ለሥርዓቱ ጥበቃ ይጠቅማል ተብሎ የተሰጠውን የተልእኮ ዓላማ ለመፈጸም ሲባል..ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚመለከተው ሁኖ አይደለም።
ይሄ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረውበት ተወያይተውበት የአትርሱኝ አስታውሱኝ አጀንዳ እንጂ የእውነት አይደለም።ሁሉም የሚሠሩት አብረው ነው።
ዋናው ጉዳይ ምእመናንን ማደናገር፣ዕረፍት መንሳት፣እምነቱን እንዲተው ማወክ፣ሥርዓቱን መጫን፣ምእመናንን ማሳቀቅ፣ጭር ሲል አልወድም...ነው።
ቢያንስ ሞቱ እንግልቱ ይቅርና ምእመናን ሀዘናቸውን እንኳን ዕርም አውጥተው እንዳያዝኑበት ዲሪቶውን አምጥቶ ይጭንባቸዋል።
እኔ በግሌ ከነነዌ ምህላ እና ከሐምል 9/1015 ዓ.ም.ጀምሮ ጨርሸ ትቻቸዋለሁ።ረቂቅ ውንብድናውን እስከ ጥግ አይቸዋለሁ።
እኔ ግን የለውጥ መንገዱን እስካገኘው እፈልገዋለሁ።ከሕይወቴ አብልጬጬ እጨነቅለታለሁ።ሁልጊዜም ቤተ ክርስቲያን የደረሰባትን ሳስበው አንጀቴ ይላወስብኛል።
ወደ መፍትሄው ብቻ ዓይናችንን እናዙር።
የቤቱ ስም የእኛ ነው ሥራው ግን የአጥፊዎች ነው።
ሁለንተናው ኦርቶዶክሳዊ እስኪሆን ድረስ ዓይናችንን ወደ መፍትሄው ብቻ እናዙር። (የግል ምልከታ፤ ከምሥራቀ ፀሐይ ገጸ )

hace 2 meses, 3 semanas

አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ

በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ማንነትን ማዕከል ያደረገ የከፋ እልቂት ከፊታችን ተደቅኗል፤ ድምፃችንን አሰሙልን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተማጽነዋል።

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከአንድ የፀጥታ ኃይል አዛዥ ጋር ከጠዋቱ ፬ ሰዓት እስከ ፲፩ ሰዓት እንደ ተደረገ በተገለጸልንና እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት የቀበሌው ነዋሪዎች መሣሪያቸውን እንዲያወርዱ ካልሆነ ግን የከፋ ነገር እንደሚጠብቃቸው በእርሳቸው አባባል "ካላወረድክ ... ትታረሳለህ" ማለታቸው እጅግ ሥጋት እንዳሳደረባቸው ለፓርቲያችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ሥጋቱ ይህ ብቻ ሳይሆን "እኛ መሣሪያ ካወረድን በሰዓታት ልዩነት ሸኔ መጥቶ ይጨፈጭፈናል፤ ይህ ደግሞ ያለፉ ዓመታት የቀን ተቀን ሰቀቀናችን እንደሆነ ማንም ያውቃል" ይላሉ ነዋሪዎቹ።
"መተማመን በሌለበትና እስከዛሬ ማን አሳልፎ እንደሚሰጠን ባወቅንበትና አኹን በጥቂቱ በመንግሥት ጥረትም፣ በሬያችንን እየሸጥንም ገዝተን በታጠቅነው መሣሪያ ራሳችንን ለማትረፍ የአልሞት ባይ ተጋዳይ በምናደርግበት ወቅት እንዲህ መባሉ እጅግ አስገርሞናል" ብለዋል። በአካባቢው በግምት 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራውና ራሱን ኦ.ነ.ሰ የሚለው ኃይል ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያካሂድበት ቦታ መሆኑንና እስከ አኹንም በጥቂቱም ቢሆን በዚኹ መንገድ ራሳቸውን እየተከላከሉ እንደቆዩ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በጭንቀት ያሉት እነዚሁ የአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሞት አሳልፎ የሚሰጠንን ውሳኔ "ብትቀበሉ ተቀበሉት" መባሉ አስገራሚ ነው ብለዋል።
"እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት ነበር። እባካችሁ መሐል ላይ ያለ የእኛን ደህንነት የሚያስጠብቅ መፍትሔ ስጡን" እያልን ብንማጸናቸውም ሊረዱን ዝግጁ አልነበሩም፤ ብቻ 'ታወርዳለህ ታወርዳለህ' እያሉ ይዝቱ ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች "በመጨረሻም ባለመግባባት ሕዝቡም አዳራሹን ጥሎ ወጥቷል" ብለዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት መላው የጸጥታ ኃይል አካባቢውን ሲለቅ መንግሥት እኛን አምኖ ራሳችንን እየተከላከልን አካባቢውንም እንድንጠብቅ ያደረገ ቢሆንም አኹን ምን ተገኝቶ ቃሉን አጠፈ ይላሉ።

ውይይቱን የመሩት የጸጥታ ኃይል ስምና ማዕረግ የደረሰን ሲሆን በብዙ ምክንያቶች ለጊዜው መጠቀም አላስፈለገንም።

ፓርቲያችን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን ይኽ አካባቢ የሞት ቀጠና ከሆነ የቆዬና አኹንም ምንም የተለወጠ ነገር ባለመኖሩ ከሰማናቸው ኹሉ የባሰ ዘግናኝ እልቂት ከመፈጸሙ በፊት በተለይ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጉዳዩን በገለልተኝነትና ከነባራዊ ኹኔታ ጋር የተገናዘበ መፍትሔ እንዲሰጡት በአደራ ጭምር ልናሳስብ እንወዳለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@እናት ፓርቲ

hace 2 meses, 3 semanas

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ በአጭሩ ነገሩን ለመቀልበስ 60 ሚሊዮን ብር ገደማ መድቦ የተነቀሳቀሰው የሙስና ኤማፓየሩ አዲስ አ/ሀ/ ስብከት በአሸናፊነት ወጥቷል!። ቅ. ሲኖዶሱ በርካታ መረጃና ማስረጃዎች የቀረቡበትን ጥናት "ባለቤት ያልቀረበበት ክስ" ሲል ውድቅ አድርጎ የሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ አቋቋሟል። ይሄም አጀንዳውን በስልት ከመድረኩ የማሸሽ አካሄድ መሆኑን ከሲኖዶሱ ያለፉት አካሄዶች ለመረዳት ቀላል ነው።

hace 2 meses, 3 semanas
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! …

https://youtu.be/QMlC_WffDiM?si=ABclpslfAUumt39e ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ!
https://t.me/tunbi_media
🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ!
www.youtube.com/@TunbiMedia_
በራምብል
rumble.com/c/c-3688912
በቲክቶክ
tiktok.com/@ethiotunbi

hace 2 meses, 3 semanas

“...ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡”
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ የጥምቅት ሲኖዶስ የመክፈቻ መልእክት!
ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. ቱንቢ ሚዲያ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በጥቅምት 2017 ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፤
“ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖላዊሃ ወዓቃቢሃ ለነፍስክሙ፤ አሁንም ወደ እረኛችሁና ወደ ነፍሳችሁ ጠባቂ ተመለሱ” (1 ጴጥ 2÷!5)
ሁሉን የሚችል አምላካችን እግዚአብሔር በፍቅሩና በፍቅሩ መነሻነት ብቻ ፍጥረታትን በሙሉ እንደፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፤ ከፈጠረም በኋላ የክብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ወዶ ክብሩን አድሎአቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ካደላቸው ነገሮች አንዱ በየዓይነታቸው ጠባቂና መሪ እያደረገ በፍጡራን ላይ ፍጡራንን መሾሙ ነው፤ ይህ ስጦታ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት የተሰጠ የሱታፌ መለኮት ስጦታ ነው፡፡
ይህም በመሆኑ ሁሉም ፍጡራን አራዊትም ሆኑ እንስሳት ይብዛም ይነስ ጠባቂና መሪ እንዳላቸው እናስተውላለን፤ በተለይም የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑ መላእክትና ሰዎች መሪና ሹም እንዳሏቸው የማንክደው ሓቅ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሓፍም ይህንን ደጋግሞ ያስረዳል፤ የእነዚህ ሁሉ ላዕላዊ ጠባቂና መሪ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በፍጡራን ላይ ፍጡራንን ጠባቂዎች አድርጎ ሲሾም ፍጡራንን የክብሩ ተሳታፊ ለማድረግ እንጂ የእሱ ጥበቃ አንሶ ወይም ድጋፍ ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ፍጹምና ላዕላዊ የሆነ ጥበቃው ሁሉንም ያካለለ ነውና ከእሱ ቊጥጥርና ጥበቃ ውጭ አንድም ነገር እንደሌለ የምንስተው አይደለም ፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በአምሳለ እግዚአብሔር በተፈጠረውና በክብር መልዕልተ ፍጡራን በሆነው ሰው ላይ በዚህ ዓለም የተሾሙ ሁለት አካላት አሉ፤ እነሱም የመንፈስና የዓለም መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም የመንፈስ መሪዎችና ጠባቂዎች የተባሉት በመንፈስ ቅዱስ ተሹመን በዚህ ክርስቶሳዊ ጉባኤ የተሰበሰብነው እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነን፡፡
ይህ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መሪና ጠባቂ ነው፤ ከዚያም ባሻገር እንደ ቃሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ቃሉን በመስበክ ፍጥረተ ሰብእን በሙሉ የመጥራት ተልእኮ ለእኛ የተሰጠ የቤት ስራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተሰጠን ኃላፊነት እጅግ በጣም ታላቅ እንደመሆኑ የሚጠበቅብን ውጤትም በዚያው ልክ ትልቅ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል ያለው የጌታችን አስተምህሮም ይህንን ያስታውሰናል፡፡
ሁላችን እንደምንገነዘበው አሁን የምንገኝበት ዘመን የጸላኤ ሠናያት መንፈስ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ከምንም ጊዜ በበለጠ ጦሩን ሰብቆ የተነሣበት ጊዜ ነው፤ አሁን ያለው ዓለም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ፈተና ደቅኖብናል፡፡ ክፉው መንፈስ የሰውን አእምሮ በማዛባት ምእመናንን በቅዱስ መጽሐፍና በሕገ ተፈጥሮ ከተመደበላቸው የጋብቻ ሕግ በማስወጣት እንስሳት እንኳ የማይፈጽሙት ነውረ ኃጢአት እንዲፈጽሙ በመገፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአማንያን ልጆቻችን ላይም በረቀቀ ስልት ግድያ፣ እገታ፣ አፈና፣ የመብት ተጽዕኖ እና አድልዎ በማድረግ እንደዚሁም በአስመሳይ ስብከትና አምልኮ ጣዖትን በማለማመድ ሕዝቡ ሳይገባውና ሳይጠነቀቅ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዲወጣ እያደረገ ነው፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ክፉው መንፈስ በተራቀቀና በተራዘመ ስልት ሊውጠን በተነሣ ልክ እኛም ከእሱ እጥፍ በሆነ መለኮታዊ ኃይል ልንመክተው ካልቻልን በፈጣሪም ሆነ በትውልድ እንደዚሁም በታሪክ ፊት በኃላፊነት መጠየቃችን አይቀርም፡፡ መከላከል የምንችለውም ችግሩን በውል ከመረዳት አንሥቶ ሕዝቡን በደምብ በማስተማርና በመጠበቅ እንደዚሁም ለመሪነታችን ዕንቅፋት ከሚሆኑን ዓለማዊ ነገሮች ራሳችንን በማራቅ ነው፡፡ ሕዝቡም በዚህ ዙሪያ ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው፡፡ ሕዝቡ ሊከተለን የሚችለው እሱን በብቃት ለመጠበቅ ዓቅሙም ተነሣሽነቱም ቁርጠኝነቱም እንዳለን ሲመለከት፣ እንደዚሁም ከዕለት ተዕለት ተግባራችንና አኗኗራችን የሚያየው ተጨባጭ እውነታ ኅሊናውን ሲረታ እንደሆነ አንርሳ፡፡
የምናስተምረው ሌላ የምንሰራው ሌላ ከሆነ ግን ከሕዝቡ አእምሮ መውጣታችን እንደማይቀር መገንዘብ አለብን፤ በመሆኑም በሰብእናችን፣ በአስተዳደራችን፣ በአመራራችንና በጥበቃችን ሁሉ እንደቃሉና እንደቃሉ ብቻ ለመፈጸም መትጋትና በቁርጥ መነሣት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡ ይህ ሲሆን በምእመናንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት አስተማማኝና እንከን የለሽ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ እውነትም የመሪነት፣ የእረኝነትና የመልካም ተምሳሌነት ኃላፊነታችንን በትክክል ተወጥተናል ማለት እንችላለን፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክልል መምራት ይጠበቅበታል፡፡ ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡
እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

hace 2 meses, 3 semanas

መርካቶ ገበያ ላለፉት 5 ሰዓታት በላይ እየነደደ ነው!!! "መንግሥት" ተብሎ በሚጠራው የሴራና የግፈኞች ስብስብ በኩል "ከአቅም በላይ ሆኖ ነው" "ቦታው አስቸጋሪ_ስለሆነ ነው" ወዘተ. የሚል መልስ እየተሰጠ ነው። የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ውድመት የማያደርስ መንግሥት አለን ተብሎ ስለማይታመን! ነጋዴዎች ዘግተው ከውጡ በኋላ የተነሳ እሳት፣ 5 ሰዓታት ሙሉ ፣ አሁንም እየነደደ ያለ እሳት ብዙ ጥያቄ የሚፈጥር ነው!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana