ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
• « አንቱ ሰው እንባዬ ደረቀ፣ፍላጎቴም ሞተ፣ መኖሬም ትርጉም አጣብኝ። ምን ላድርግ?» ብሎ ጠይቃቸው።
እሳቸውም፦ « የኔ ልጅ ልብ ተስፋ ስትቆርጥ በድን ትሆናለች። እንባ የልብ ወንዝ ነው። ምንጩ ሲደርቅ አይን አታለቅስም። ፍላጎት የልብ ማሳ ነው። ካልተኮተኮተ ይጠወልጋል። መኖር አላህን የማወቅያ አንድ ድልድይ ነው። ልብ ስትዝል ድልድዩ ይሰበራል። የኔ ልጅ ሕያው ወደ ሆነው ጌታህ ዘንድ ከመሄድ በቀር ያጣኸውን በተሻለ መንገድ አታገኘውም!»
ልጁም፦«የተጣላሁት ከጌታዬ ጋር ከሆነስ? » አላቸው።
እሳቸውም፦«ጌታህን አምፀኸው አይምረኝም ብለህ ካልክ በእርግጥም ስለ ጌታህ የምታውቀው ጥቂትን ነውና ከፍጡራን ጋር አመሳስለኸዋል። የኔ ልጅ ጌታዬ እኮ እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ እንደሚያምፀው አውቆ እንኳ ሸይጧንን የጠየቀውን ልመና ተቀብሎታል። ታድያ አንተ ያመፅኩህን ይቅር በለኝ ብትለው የማይምርህ ይመስልሀልን?
የኔ ልጅ የሞተ ልብህ ላይ ሕይወትን የሚዘራው ያ ሕይወትን ሰጥቶህ ያመፅከው ጌታህ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። ጌታዬን ከፍጡራን ጋር አመሳስለኸው ይጠየፈኛል ብለህ አታስብ። የኔ ልጅ እስከነ ነውርህም ቢሆን ወደ አላህ ሒድ።»
=t.me/Sle_qelbachn1
ኢላሂ…!
የተሰበረ ክንፍ ይዘዉ ከልባቸዉ ወደአላህ የዞሩት የሚበሩ ሁነዉ ተመልሰዋል ።
الله الله في الصدق
ሳጠፋ ነፍሴ በእጅጉ ታሳዝነኛለች። ብዙ እንዳትጎዳ ብዬም እሳሳላታለሁ። ለዚህም ሲባል ቶሎ ላርማት እሞክራለሁ።
ሰው ነኝ መቸስ ...እያንዳንዱ ዉድቀቴና ዉርደቴ የማንም ሳይሆን የእጄ ዋጋ፣ የራሴ ሥራ ዉጤት እንደሆነ እገነዘባለሁ። አላህ ያለው ሁሉ ሐቅ ነው። ጥፋቴን ወደማንም መግፋት አልፈልግም። በስህተቴ ማንንም አልወቅስም። ዉድቀቴን በሌሎች አላሳብብም።
ሁሌም የክብር ይሁን የንቀት፤ ከወዲያ በኩል የማገኘው ምላሽ ሁሉ የራሴ ሥራ ወይም ደግም ይሁን ክፉ የባህሪዬ ነፀብራቅ ነው ብዬ አምናለሁ። አንድ ደግ ሰው እንዲህ ይላሉ - «የእጄን ዉጤት በምሳፈረው ፈረስ ላይ ጭምር አያለሁ። በሚስቴ ምላሽ ዉስጥ አስተዉላለሁ።»
ስለዚህ የሆነ ነገር ስናጠፋ ወይ ኃጢአት ላይ ስንወድቅ ወደማንም ሳይሆን ወደራሣችን እንጠቁም። ከራሣችን እንጀምር። ስህተታችንን እንመን። ለጥፋታችን ኃላፊነት እንውሰድ። ራሣችን ወድቀን እገሌ ጣለን፣ እንትና አሳሳተኝ አንበል።
እኔ ስስተካከል እኔም ሌላዉም ይስተካከላል።
ችግሩ ከራሴ ነው ማለትን እንልመድ።
=t.me/Sle_qelbachn1
ከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን።
ኢማኔ ደከመ፣ቀልቤ ደረቀ፣ከአላህ ራቅኩኝ፣
የቂኔ ከዳኝ፣ተወኩሌ ጠፋ፣ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣
ቁርአንን ዘነጋሁ፣አዘኔታ አጣሁኝ፣
ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣ሱና መስገድ ተውኩኝ፣ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣…
አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር።
=t.me/Sle_qelbachn1
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago