ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

Description
አትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ በሀገር ውስጥ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ፕሮግራም
ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ከ3-4 እና ሰኞ ምሽት ከ12-1 በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሚቀርብ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ስላቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ …

ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ስላቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ ማወቅ ያሉብን ጉዳዮች

ይህ የአክሲዮን ድርሻ ሕብረተሰቡ የኩባንያው ባለቤት እንዲሆን ታስቦ የተከፈተ ነው፡፡

የአክሲዮን ሽያጩ ሁለት ዙር ይኖረዋል፤ የመጀመሪያው ዙር ከትላንት ጀምር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡

ስለመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ማወቅ ያሉብን ጉዳዮች፦

• የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር ነው፤

• ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው 33 አክሲዮን ሲሆን፣ ጠቅላላ ዋጋው 9 ሺህ 900 ብር ነው፤

• ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው 3 ሺህ 333 አክሲዮን ሲሆን ጠቅላላ ዋጋው 999 ሺህ 900 ብር ነው፤

• ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፤

• የአክሲዮን ግዢ የሚከናወነው በቴሌ ብር ሲሆን፣ ክፍያው የሚጠናቀቀው በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው፤

• የአክሲዮን ሽያጩ የሚቆየው ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ነው፤

• አዳዲሶቹ የአክሲዮን ባለቤቶች የሚታወቁት ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም፤

• አክሲዮን ገዢዎች ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፤

• ከዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን በታችም ሆነ፣ ከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም፤
(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን

3 months ago

ዳሸን ባንክ 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ብር 6.4 ቢሊየን ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ፡፡ የባንኩ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በሚሊንየም አዳራሽ ዛሬ የተካሄደ ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ባለፈው በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው አውንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ አገራት የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ያወጧቸው ጥብቅ ፖሊሲዎች፣ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፣ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢ የሚፈፀመው ጥቃት በአለም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደሯቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለአብነት አንስተዋል፡፡አቶ ዱላ ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ የነበረው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ በተለያዩ ቦታዎች የቀጠሉ ግጭቶችና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ የበኩሉን አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል፡፡

የበጀት ዓመቱ ሲጀምር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ጥብቅ የገንዘብ ፓሊሲ ይፋ ማድረጉንም አስታውሰዋል፡፡ እነዚህና ሌሎች የፖሊሲ ለውጦች ባንኮች በሚያቀርቡት የብድር መጠንና ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውንም አመልክተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የባንክ ኢንዱስትሪው የገንዘብና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ውስጥ የነበረ ቢሆንም ዳሸን ባንክ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በተሌብር በኩል እንዲሁም ሳፋሪኮም በኤምፔሳ አማካኝነት በሞባይል ባንክ አገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ ፉክክር እንዲፈጠር ያደረጉበት አመት መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን አቶ ዱላ አውስተዋል፡፡

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11.1 ቢሊየን ብር እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡ ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተመልክቷል፡፡ ዳሸን ባንክ ከተለያዩ አገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት መቀጠሉን ያመለከቱት አቶ አስፋው ከኤግልላየን ሲስተምስ ቴክኖሎጂ ጋር የተፈራረመው ስትራቴጂክ ስምምነት አዳዲስ ዲጂታል አገልግሎቶችን ይበልጥ ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያስችለው አስገንዝበዋል፡፡

ባንኩ ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት እና ከኔዘርላንድ የልማት ባንክ ጋር የፈጠረው አጋርነት የ40 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዳሸን ባንክ በበጀት አመቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የ40 ሚሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ ዋስትና ፈንድ ማግኘቱንም አቶ አስፋው አመልክተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ማህበራዊና አካባቢያዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት አቶ አስፋው ከዚህ አኳያ ባለፈው በጀት ዓመት የአካባቢ ማህበራዊና አስተዳደር (Environment, Social and Governance) ፓሊሲ በማዘጋጀትና ቢሮ በማቋቋም መስራት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የተለያዩ ሽልማቶችን ከተለያዩ አህጉራዊና አለምአቀፍ ተቋማት ተቀብሏል፡፡

ባንኩ በእንግሊዝ በሚታተመው ዘባንከር መፅሄት በኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ባንክ ተብሎ የተሸለመ ሲሆን የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዳሸን ባንክ ለአነስተኛ ተቋማት ብድር በማቅረብ ዘርፍ ቀዳሚ ባንክ በመሆን ከ“አፍሪካ ባንክ 4.0 ጉባኤ” ሽልማት ተቀብሏል፡፡

(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን

3 months ago

የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ 10 ግለሰቦች በማታለል ሙስና ወንጀል ተከሰሱ

#Ethiopia | የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ 1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣ 3ኛ የተቋሙ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ "በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት እንዲሁም ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው አቅርቦባቸዋል።

ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ-9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው፤ በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።

እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን ÷የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana