EEP Communication

Description
EEP Communication
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 weeks, 1 day ago
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ
........///.......
በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

ሁለቱ ቡድኖች በድሬዳዋ ስቴዲየም ዛሬ ባከናወኑት ጨዋታ አቤል ሀብታሙ፣ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ እና ያሬድ የማነ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሶስቱን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል።

ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ጎሎች አንጋፋው አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከመረብ አሳርፏል።

ብርቱ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመስመር ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲከተል ፋሲል ከነማ በአንፃሩ ኳስን በመቆጣጠር የጨዋታ ብልጫ ለመውሰድ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ በሊጉ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

4 weeks, 1 day ago
EEP Communication
4 weeks, 1 day ago
የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያን …

የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ
........///..........
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች የደዴሳ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያን ዛሬ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የፌዴራል  ፖሊስ የምዕራብ ኦሮሚያ አዛዥ ኮማንደር ማሙዬ አባተ እንዳሉት የተቋሙ አመራሮች በግዳጅ ላይ ያሉትን የሠራዊት አባላት መጎብኘታቸው ለሠራዊቱ አባላት የሞራል ጥንካሬ ይሰጣል።

ማከፋፈያ ጣቢያው በረሃማ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የውሃ አቅርቦት እንዲስተካከል እና የወባ መከላከያ አጎበር እንዲሰጣቸው እንዲሁም የጥበቃ ማማ እንዲገነባላቸው ጠይቀዋል።

በተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ደህንነትና ቁጥጥር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደተናገሩት ተቋሙ ከፌደራል ፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የመሠረተ ልማት ስርቆትን ለመከላከል በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

በሠራዊቱ አመራሮች ለቀረቡት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር እንደሚነጋገሩም ገልፀዋል።

በተቋሙ የንብረት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው  ለጥበቃ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የንብረት ማስቀመጫ መጋዘን ለመገንባት መታቀዱንና ያልተሟሉ ፋሲሊቲዎችን ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመነጋገር ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

1 month ago
የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ደም ለገሱ

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ደም ለገሱ
………///………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮችና ሠራተኞች በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት የደም ልገሳ ዛሬ አካሂደዋል፡፡

የደም ልገሳ መርሃግብሩ በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው የተቋሙ የፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለፁት በተቋሙ ዋና መ/ቤት የደም ልገሳ ፕሮግራም መዘጋጀቱ የሠራተኛው የሥራ ሰዓት ከመቆጠቡም በላይ ደም ለመስጠት ፈልገው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ አገልግሎት ለመሄድ ያልቻሉትን ሠራተኞች በቅርበት ለማግኘት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

በተቋሙ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሐ ጌታቸው በበኩላቸው ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች ግንዛቤያቸውን በማሳደግ የደም ባንክ አባል ሆኖ ደም በመለገስ ህይወትን የመታደግ በጎ ተግባርን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብለዋል፡፡

ደም ለመጀመሪያ ግዜ ሲለግሱ ያገኘናቸው አቶ ካሰሁን ጸሀይ፣አቶ አብደላ ሻንቆ እና አቶ ታምሩ ባቱ ቢያንስ የሶስት ሰው ህይወት ሊታደግ የሚችል ደም ደ መለገስ በመቻላቸው እንደተደሰቱ እና ተቋሙ ይህን በማመቻቸቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም መሰል የደም ልገሳዎች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ሙሉቀን ዮሴፍ እና ወ/ሮ ፋናዩ ዘበነ በበኩላቸው ደም ልገሳውን ለመጀመሪያ ግዜ ቢሰጡም የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸው ከማያውቁት ሰው በተለገሰ ደም በመትረፉ ደም ለመስጠት መወሰናቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ ያለውአይቀር ማንደፍሮ እና አቶ ኤርሚያስ ጥላሁን እንደተናገሩት ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት ደም መለገሳቸውን አውስተው ደም መሥጠት ዘር፣ጎሳ እና ጾታ ሳይለይ ህይወቱን ሊያጣ የነበረን ሰው ህይወቱን መመለስ ከስጦታዎች በላይ ስጦታ እና የበጎ ተግባርም ምሳሌ እንደሆነ መረዳታቸውን ተናግረዋል ፡፡

ከ 1984 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 118 ጊዜያት ደም የለገሱት በደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የትምህርት እና የቅስቀሳ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ እንደተናገሩት ደም መለገስ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትል እና ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮችና ሠራተኞች በደም እጥረት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ የበርካታ ወገኖቻቸውን ህይወት መታደግ እንደሚቻል በመረዳት በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብላዋል፡፡

ደም የሚሞት እና የሚያረጅ እንዲሁም ራሱን የሚተካ በመሆኑ ክቡሩን የሰው ህይወት ልናድንበት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተቋሙ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሼን መምሪያ ይህን ፕሮገራሙ አስተባብሮ ማዘጋጀቱ የሚመሰገን ተግባር እንደሆነ ያወሱት ሲስተር አሰጋሽ በልገሳ መርሃግብሩ 27 ዩኒት ደም መለገሱንና በቀጣይም በተሻለ እንደሚሰበሰብ ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል ፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

1 month ago
EEP Communication
1 month ago
EEP Communication
1 month, 1 week ago
ኢትዮ - ኤሌክትሪክ በሊጉ የመጀመሪያውን ድል …

ኢትዮ - ኤሌክትሪክ በሊጉ የመጀመሪያውን ድል አስመዘገበ
……….////………
በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው 4ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ - ኤሌክትሪክ ባህር ዳር ከተማን 1 ለባዶ በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኢትዮ - ኤሌክትሪክ በ16ኛው ደቂቃ ላይ አቤል ሀብታሙ ባስቆጠራት ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ መምራት ችሏል፡፡

ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ባህርዳር ከተማ ቢሆንም ኢትዮ - ኤሌክትሪክ ያገኘውን ዕድል ወደግብ በመቀየር 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡

ኢትዮ - ኤሌክትሪክ በውድድር ዘመኑ 4 ጨዋታዎችን አድርጎ በሁለቱ አቻ ሲወጣ፣ በአንዱ ተሸንፎ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፏል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ከዚህ በፊት በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች ባህርዳር ከተማ ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

1 month, 1 week ago
EEP Communication
1 month, 1 week ago
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቁጥር ኢ.ኤ.ኃ/8.4/23/16 ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በሾፌር - 3ኛ እና በሾፌር-4ኛ የሥራ መደብ ለውጭ አመልካቾች ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በሾፌር - 3ኛ እና ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በሾፌር - 4ኛ የሥራ መደቦች ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ መንጃ ፈቃድ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና ስለሚሰጥ በፈተናው ቦታ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦ በፈተና ሰዓት የእጅ ስልክ (ሞባይል) ይዞ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

1 month, 2 weeks ago
በሪጅኑ የሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል የመጫን …

በሪጅኑ የሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል የመጫን አቅማቸው ከ70 በመቶ በላይ ደርሷል
.........///........
በደቡብ አንድ ሪጅን የሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኤሌክትሪክ የመጫን አቅማቸው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ
አስታወቀ።

በዘርፉ የሪጅኖች ማስተባበሪያ መምሪያ ከደቡብ አንድ ሪጅን የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች ጋር በኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎች እንዲሁም እያጋጠሙ በሚገኙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ በሐዋሳ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

በሪጅኑ የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽና ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያለው አማረ እንደገለፁት በሪጅኑ ከ132 እስከ 400 ኪሎ ቮልት ኃይል የመጫን አቅም ያላቸው 12 የማከፋፈያ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

በአስራ ሁለቱ የማከፋፈያ ጣቢያዎች የተለያየ አቅም ያላቸው 23 ትራንስፎርመሮች እንደሚገኙ  የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ ጣቢያዎቹ በአሁኑ ወቅት ኃይል የማቅረብ አቅማቸው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

አስራ ሁለቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች 1 ሺህ 910 ሜጋ ዋት ኃይል የመጫን አቅም ቢኖራቸውም በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 710 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረቡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የሻኪሶ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ቁጥር 1፣ ይርጋዓለም ቁጥር 1 እና ቡኩሉ ጉማ እንዲሁም ያዶት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ በመሆናቸው የማሻሻያ ሥራዎች እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ያለው ተናግረዋል።

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በተያዘው በጀት ዓመት በሪጅኑ በሦስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የ15/33 ኪሎ ቮልት የጂ.አይ.ኤስ ብሬከር ቅየራ ሥራ ይከናወናል።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጆቹ በበኩላቸው አንዳንድ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የአቅም ማነስ ችግር እየገጠማቸው በመሆኑ የተበላሹ ትራንስፎርመሮች እና ብሬከሮችን በወቅቱ እንዲጠገኑና እንዲቀየሩ ጠይቀዋል።

ለኦፕሬሽን ሥራ አስፈላጊ የሆነው የተሽከርካሪ አቅርቦት፣ የሥራ ላይ መሳሪያዎች አቅርቦት እና የሰው ኃይል እጥረት በሥራቸው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ እንዲሟላላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ጣቢያዎቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ምቹ የሥራ ከባቢ ከመፍጠር ጀምሮ እየተስተዋሉ ለሚገኙ ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

በተቋሙ የሪጅኖች ማስተባበሪያ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ በሪጅኑ በሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያዎች የታዩ ችግሮችን ለመፍታት ዘርፉ ጥረት ያደርጋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ;
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago