አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

Description
ያፈቀረን ማሳቅ ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉

#Join ያርጉና የትም

ባልተሰሙ ቀልዶቻችን ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍

ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች...

ከቻልክ❤️ ፍቅርን ተናገር፣ኑር!
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን

👉 @Get_mu 👉 @just_811

Please😊Don't Leave ችግር ካለ አናግሩን
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

1 month ago

ሰዉየዉ ከባለቤቱ ጋር አንድ የከብቶች ማራቢያ ማእከል በመጎብኘት ላይ ነዉ። #በመጀመሪያ የተመለከቱት ኮርማ አንገት ላይ " ይሄ ኮርማ ባለፈዉ አመት ብቻ 250 ቀናት አጥቅቷል "የሚልፅሁፍ ተንጠልጥሎ ይመለከታሉ የሚቀጥለዉ ላይ " 300 ቀናት አጥቅቷል " ይላል የመጨረሻዉ ኮርማ ላይ "ባለፈዉ አመት ብቻ 365 ቀናት አጥቅቷል" ይላል።#በዚህ_ጊዜ ሚስትየዉ አፏን ከፍታ " ዋ...ዉ! በፍፁም አላምንም በቀን አንዴ እኮ ነው ከዚያ ወደ ባሏ ዞር ብላ" እዉነቴን ነዉ ከዚህ ኮርማ ብዙ መማር ይኖርብሀል " ስትለው#ባልም ... "እስቲ ሂጂና 365 ቱንም ቀናት አንዲት ላም ብቻ ነዉ ወይ ያጠቃዉ ብለሽ ጠይቂያቸዉ" 😂

1 month ago

**ረጅም ቅንድብ ሰክታ አይቷት

አንቺ ኳስ ተጨዋች ብትሆኚ ከእግርሽ ቀድሞ ቅንድብሽ ነበር off side ሚገባው 🙊*😂*

1 month ago

**ትዕግስት ምን እንደሆነ ማወቅ ከፈለክ...

2G ሚጠቀሙ ሰዎችን ጠይቅ**

1 month ago

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 24...🌹

ሄሎ ኤፍዬ ደናነህ? ለቀቀህ?"
"ምኑ ቃልዬ?
" ትራፉኩ ካካካ ፣ ድብርቱ ነዋ"
"ምነው በዚህ ሰአት በሰላም ነው ምን ሆነች ብዬ ደነገጥኩ"
"ሰላም ነኝ ኤፍዬ ምን ሆናለሁ ብለህ ነው፣ ገባህ እንዴ ወደቤት?"
"አዋ እቤት ነኝ ቃልዬ"
"ድብርቱ አለቀቀህም ማለት ነው?"
"ሌላ ግዜ በዚህ ሰአት ስራ ላይ ነህ ብዬ ነዋ"
"አንቺስ እስካሁን እንዴት አልተኛሽም ቃልዬ?"
"እያሰብኩ"
"ስለምንድን ነው የምታስቢው "
"ስላንተ እና ስለኔ"
"ስለኔና ስላንቺ ምን?"
"እስቲ በዛሬዋ ቀን ምን ታስታውሳለህ?"
"በዛሬዋ ቀን ማለት ዛሬ?"
"አይ የዛሬ ስድስት ወር ልክ በዛሬዋ ቀን በሀያ ሰባት"
"ምን ላስታውስ ? ያንቺ ፍቅር ስሜንስ ሳያስረሳኝ ይቃራል ቃልዬ እስቲ አንቺ አስታውሽኝ"
"ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚች ቀን በዚች ሰአት  ምሽት ላይ ነበርኮ እዛ ሆቴል በር ላይ የተገናኘነው"
ስትለኝ ልቤ ተረጋጋ።
ስድስት ወር እንደሞላን በደፈናው ባውቅም ቀኗን ለይቼ አላሰብኳትም ነበር። ትኩስ ትንፋሽ በረጁሙ አስወጣሁና።
"ቅድም አብረን እያለን ለምን አልነገርሽኝም ቃልዬ ነው አንቺም ትዝ ያለሽ አሁን ነው?"
"እኔ ነገ ነው የምንገናኘው ስልህ ዛሬ ካልተገናኘን ሞቼ እገኛለሁ ብለህ ስትለኝ ቀኑን አስበህ ነው ብዬ አንተ እንድትነግረኝ ስጠብቅ ነበር አንተ ግን  ሌላ አለም ውስጥ ነበርክ ኤፍዬ ምን ብዬ ልንገርህ"

"ይቅርታ ቃልዬ ረበሽኩሽ አይደል?"
"አንተ መረበሽህ ነው የደበረኝ ለማንኛውም ይህን ላስታውስህ ብዬ ነው በቃ ተኛ ኤፍዬ እንደማፈቅርህ እንዳትረሳ እሺ" ቃላቶቿን  በጆሮዬ የሰማኋቸው ሳይሆን በደምስሬ በስሪንጅ የወሰድኩ እስኪመስለኝ ድረስ በሁለመናዩ ሲሰራጩ ተሰማኝ።
" እንዳትረሳ ማለት ምን ማለት ነው ቃልዬ?"
"ሆሆሆ ኪኪኪ ይሄ ደሞ ሌላ  ምን ማለት ይሆናል ? በቃ እሺ አፈቅርሀለሁ "
አለች። አዎ እንደዛ ነው የሚባለው  እንዳትረሳ ስትይ የመጨረሻ  የ መለያያ ንግግር አስመሰልሽዋ ታድያ ምን ላድርግ ቃልዬ ልላት አልኩና ካፌ መለስኩት።
"እኔም አፈቅርሻለሁ የኔ ማር"
"ቻው"
"ቻው ደና እደሪልኝ"
ኡፍፍፍፍፍ አልኩና ስልኩን ትራሴ ስር ወትፌ በጀርባዬ ስንጋለል።
አውርተን እስክንጨርስ አንዴ ፈገግ አንዴ ጭፍግግ እያለ ሲሰማን የነበረው ኪያ እኔን ተከትሎ በረጅሙ ተነፈሰና።
"ቆይ ለምንድን ነው ስልኩን ማንሳት የፈራኸው ኤፊ?"
"እኔ እንጃ!"
"አቦ ተወና ኤፊ ደሞ ሀይ በቃ እሺ ስሜትህን ሳልረዳ የማይሆን ነገር ተናግሬ ከሆነ ይቅርታ"
"ተጨማሪ ወሬ ለመስማት ብሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው አንተን አየሁ"
"አቦ እኔ ለወሬው ብዬ ነው እንዴ? ወንድሜ አደለህ እንዴ ያንተ ጉዳይ አያስጨንቀኝም ኤፊ"
"ባክህ አንተ ከራስህ ዉጪ ለማንም ተጨንቀህ አታውቅም"
"እሺ ስልኩን ለማንሳት የሸከከህ ለምን እንደሆነ ብቻ ንገረኝ"
"ኧረ ኪያ ልተኛበት ተወኝ ••• በቃ አንደኛ ቃልዬ ሰላም ያልሆነች መሰለኝ ሁለተኛ ቅድም ምን አውርተን ተጦላልበን እንደተለያየን ነግሬህ የለ ስለዛኪ ሌላ ወሬ ሌላ እውነት የምትነግረኝ መስሎኝ ነበር የፈራሁት እኔ ሌላ እሷ ሌላ አለም ውስጥ እንደነበርን ያውቅኩት ግን የደወለችው ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚህ ቀን መገናኘታችንን ልትነግረኝ መሆኑን ስትነግረኝ ነው" አበቃ ይሄው ነው ብዬው ተጠቅልዬ ተኛሁ።

እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ከአንድ ሰአት በላይ ስገላበጥ ቆየሁ፣ ኪያ እንቅልፍ የወሰደው መስሎኝ ስለነበር ድንገት
" ኤፊ !" በማለት ሲጣራ  እየቃዠ መስሎኝ ዝም አልኩት።
" አንተ ኤፍሬም!" በማለት በድጋሚ ተጣራ ።
"አቤት  ኪያ  ምንድን ነው አልተኛህም እንዴ?" አልኩት ቀና ብዬ የክፍሉን መብራት እያበራሁ። ተነስቶ ፍራሹ ላይ ቁጭ ብሏል።
"አንተስ መች ተኛህ "
"እኔማ መች ተኝቼ አውቃለሁ ኪያ በግድ እኮ ነው እንቅልፍ የሚወስደኝ"
"ፍቅር ከያዘህ ወዲህ ነዋ በፊትማ ገና ጋደም እንዳልክ አልነበር••••" ሲል ብስጭት ብዬ•••|
" እንቅልፍ እንቢ ሲልህ ነቆራህን ለመቀጠል ነው የተነሳኸው?"
"ኧረ ጋደኛዬ ምን ሆነሀል   የምናገረው ነገር በሙሉ  ያንተን ስተትና ድክመት እያነሳሁ አንተን ለማብሸቅ እየመሰለህ የተቸገርከው አንተ እኮነህ፣ ለማንኛውም ዝም ብዬ ከስንት ወር በኋላ ዛሬ ዘለግ ላለ ግዜ ብናወራ እንዴት መግባባት አቃተን ቆይ ለምንድን ነው ኤፊ የምለው ነገር በሙሉ ያልጣመው ዋናው እኔን ማማከር የፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው ብዬ እያሰብኩ ነበርና አሁን መጨረሻ ላይ ስልኩን ለምን ማንሳት እንዳልፈለክ የነገርከኝ ነገር አንድ ነገር አመላከተኝ"
"በህልምህ ነው በውንህ"
"ምኑ ኤፊ"
"ያመላከተህ ወይ የታየህ"
"አንተ ማሸፍ ከጀመርክ አይጣል ነው እስቲ ቁም ነገር እናውራ"
"በቁምነገር የሆዴን የውስጤን እውነት ሳካፍልህ እቃቃ ጫወታ መጫወት ያማረህ እኮ አንተ ነህ ኪያ"

"በቃ ይቅርታ ኤፊ ጋደኛዬ ታውቃለህ እኔ  ሌላው ነገር ላይ ትኩረት አድርጌ ያላስተዋልኩት ነገር ግን አንተን በጣም የረበሸህ ጉዳይ የዛ ዛኪ የተባለ ልጅ ጉዳይ መሆኑ ቆይቶ ነው የገባኝ። ልክ ነኝ አደል እራስ ምታት የሆነብህ የልጁ ጉዳይ ነው አይደል  ኤፊ?"
"እና እሺ ነው እንበል እና እሺ ምንድን ነው?"
"እንበል እና እሺ ምንድን ነው አይደለም ነው ወይ አይደለም በለኝ ኤፊ ያ ነው አደል ?
ቃልኪደን ዛኪ  ያክስቴ ልጅ ነው ብትልህም አምነህ ለመቀበል ተቸግረሀል አደል ኤፊ?"
"እኔ ነው አደለም እንድልህ ለምን ትጠብቃለህ ኪያ ቆይ እሱ ቢሆንስ ምን ልትለኝ ነው? "
አልኩት ጮክ ብዬ ። እንቅልፍ የወሰደው እስኪመስለኝ ድረስ  ከአንድ ሰአት በላይ ድምፁን አጥፍቶ ከተኛ በኋላ ምን ሊለኝ እንደተነሳ ግራ ገብቶኝ።
" ኤፊ የሱን ልጅ ጉዳይ በኔ ጣለው በቃ!"
"በኔ ጣለው ማለት?"
"አንተ ልጅቷ የድሬ ልጅ ስላልሆነች ከጎረቤትም ከሰፈሯ ልጆችም ስለልጁ እና ስለሷ የእውነት ዘመዷ ይሁን ፋሟ ማጣራት የማይቻል መስሎህ እንደተጨናነክ አሁን በደንብ ገብቶኛል ፣ ቅድምም ፍቅር ያዘኝ ስትለኝ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብቼ ንትርክ ውስጥ ገባን ሙሉውን ታሪክ ስትነግረኝ ደሞ  እስካሁን ምንም አለማድረጋችሁ •••ሌላ ሌላውን ነገር እያሰብኩ ሀሳቤ ተበታተንና እንዲሁ ያለውን ነገር ልትነግረኝ ብቻ እንጂ  የሆነ ያስጨነቀህ ጉዳይ እንዳለ አላስተዋልኩም ነበር አሁን ተኝቼ ሳስበው ያልኩህ ነገር ሁሉ ያልተዋጠልህ ለምን እንደሆነ ገባኝ። በቃ የልጁ ጉዳይ ሰላም እንደነሳህ ገባኝ። የሱን ጉዳይ እኔ በራሴ መንገድ አጣራለሁ እሱን ለኔ ተወው"
"እኮ በምን መንገድ?"
.
.
@askignkeldoch

1 month ago

የማሽላ ወንድም ስሙ ነው ዘንጋዳ
ወዶ ያልጠቀመ ጠልቶስ ምን ሊጎዳ

1 month ago

**አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል።

ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት።

ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል።

ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዞልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት።

እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው።

ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል።

ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት።

እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!"

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው።

ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ።

ወዳጄ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል 😍*🙌*

1 month, 1 week ago

**የድሮ ፍቅረኛህ ቪትዝ መኪና እየነዳች ስታልፍ አየኋት ብዬ ስነግረው...

ይበላት ገና የኔ ግፍ መቼም አይለቃትም አላለም ☹️*😁*😁

1 month, 1 week ago

"አንዳንዱ ጠዋት ለኃይማኖቴ ስል እሞታለሁ ይላል፣ ምሳ ሰዓት ላይ ከኃይማኖቱ አስተምሮት ውጪ ሲሳደብ ይውላል፣ ከሰዓት ዘረኝነት የተወገዘ ነው ብሎ ሲመክር ይቆይና፣ ማታ ብሄሩን ወክሎ ሌላ ብሄር ሲሳደብ ያመሻል! ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የሰው ልጅ ባህሪ ነው!

1 month, 1 week ago

ለዝናብ🌧 ስትጸልይ ከጭቃው ጋር መስማማት አለብህ !!

1 month, 2 weeks ago

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 14...🌹
አዎ  ተደብቄ ከምከታተላት ይልቅ ቀጥ ብዬ  ሄጄ ድንገት እንዳየኋት ሆኜ በራሷ አንደበት ከማን ጋር ምን እየሰራች ፣ ወዴት ልትሄድ?   ማንን እየጠበቀች?  እንደሆነ ብትነግረኝ ነው  የሚሻለሁ። ግን እኮ የምከታተላት ሊመስላት ይችላል።
ያኔ ኤፍሬም ተጠራጣሪ ነው ብላ ልትጠላኝም ትችላለች።
ምናልባት እኔ እንዳስብኩት ካልሆነና እሷ የሰራችው ስተት ከለል እራሴው ላይ ነጥብ አስቆጥሬ ። እንዲሁም ጨቅጫቃ ሳልሆን ጨቅጫቃ መስያታለሁ ጭራሽ ከጀርባ የምከታተላት ተጠራጣሪ ወንድ እመስላትና ይለይላታል።
አዋ ! አሁን ደውላ አናግራኝ የለ እንዴ! በደቂቃዎች ልዩነት ድንገት ስራ  ላይ እያለሁ በዚህ በኩል ሳልፍ አይቼሽ ነው ብላት በጭራሽ አታምነኝም። በዛ ላይ እሷ የምታውቀው ቀን ቀን ሳይሆን ማታ ማታ እንደምሰራ ነው። ቀን እሷን ለማግኘት ስል ከሷ ጋር ቀጠሮ ሲኖረኝ ብቻ እንደምወጣ እንጂ ስራዬን ወደ ቀን እንዳዞርኩት እስካሁን አልነገርኳትም። ስለዚህ ትናንት ነገ አይመቸኝም ስላለችኝ  ሆን ብዬ እሷን ለመከታተል ግቢ በር ላይ አድፍጬ የጠበኳት ነው የሚመስላት ።
አቦ ፍቅር የስራህን ይስጥህ እሺ ሌላ ምንም አልልህም።
ገና ያየሁትን ያየሁት እኔ እያለሁ ይመስላታል አይመስላትም እያልኩ ለሷ ልጨነቅ ወይኔ ኤፍሬም !፣ የምከታተላት ቢመስላትም ይምሰላታ በቃ!  ካሁን ቡሃላስ ቢሆን ይቀርላታል እንዴ !? እቺ ሀሙስ ቀንማ ሚስጥሯ መታወቅ አለበት። ይሄ አብሯት ያለው ልጅ የግቢ ልጅ ይሁን አይሁን?፣ ከሷ ጋር ምን አይነት ግኑኝነት እንዳለው? ፣ ትውውቃቸው ከመቼ ጀምሮ እንደሆነማ ማጣራቴ የማይቀር ጉዳይ ነው" አልኩ ለራሴ።
"አይ ኤፊ አሁን እጅህ ላይ ያላውን አጣርተህ ሳጨርስ ••• ለወደፊት እንዴት እንደምታጣራ እቅድ ታወጣለህ እንዴ ? ይላል ያ የቃል ጠበቃ  ውስጤ ተዘፍዝፎ ።  እንዳልሰማሁ ሆኜ አለፍኩት።
አልፌኣቸው ከቆምኩ ከሀያ ደቂቃ በላይ  እኔም እነሱን እነሱም የሚጠብቁትን እየጠበቁ ስንጠባበቅ ከቆየን በኋላ አንዲት ባለ አንቴና ባጃጅ ስትክለፈለፍ መጣችና እነሱ ከቆሙበት መደብር ፊት ለፉት ስትደርስ ቀጥ አለች። እኔም ልቤ ቀጥ እንዳለች ቀጣይ የሚሆነውን ለማየት አፍጥጫለሁ።
ከባጃጇ ውስጥ አንዲት ሺቲዋን  ሙታንታዋ ውስጥ የሰቀሰቀች ረጅም ወጣት ሴት ወረደችና እጆቿን ተራ በተራ እያወናጨፈችና   እየተመናቀረች ወደነ  ቃልዬ ተጠጋች።
ቃልዬን እና ልጁን በየተራ እየሳመች ሰላም አለቻቸውና እንደዛው እጇን እያወናጨፈች ማውራቷን ቀጠለች ቃልዬና ልጁ እሷንም እርስ በርስም  እየተያዩ  ይስቃሉ።
"እቺ ልጅ በየሄደችበት መሳቅ ነው እንዴ ስራዋ!"አልኩ በውስጤ።
ወድያው ሶስቱም. ተከታትለው  ልጅቷን ወዳመጣቻት ባጃጅ ውስጥ ገቡ። የባጃጄን ሞተር  አስነሳሁ። በጎን መስታወት( 'በስፖኪዬ')እያየኋቸው  በቀስታ ወደፊት መሄድ ጀመርኩ። ባጃጇ ቀጥ ብላ በኔ አቅጣጫ መምጣት ስትጀምር ሄደን ሄደን መውጫው ላይ ከላይ ከሼል፣ አልያም ከታች ከሳፕያን መስመር የሚመጡ ባጃጆችን ለማሳለፍ ቆም ካልኩ ደርሰውብኝ መተያየታችን ነው ስለዚህ መፍጠን አለብኝ ፣አልኩና ፍጥነቴን ጨምሬ ወደፊት እየገሰገስኩ አየት ሳደርግ•••• እነቃልኪዳን ያሉባት ባጃጅ ጭራሽ ወዳልጠበኩት አቅጣጫ ተኮረበች።
  ወይኔ ተሸወድክ ኤፊ ! እያልኩ  አመቺ ሁኔታ ጠብቄ ዞርኩና ወደሄዱበት አቅጣጫ ተምዘገዘኩ።  ውስጥ ለውስጥ በርሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት  ላይ ስወጣ •••ከየጣጫው ከሚርመሰመሱት ባጃጆች  መሀል እነ ቃልዬ ያሉባትን መለየት ከባድ ሆነብኝ፣  ድንገት አርቄ ወደ ፊት ለፊት አቅጣጫ  ሳማትር ወደ ድል ጮሮ ሀስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ የምትከንፍ አንዲት ባለ አንቴና ባጃጅ ተመለከትኩ።
"እራሷ ነች ፣ ባላንቴናዋ እራሷ ነች!  እያልኩ በሄደችበት አቅጣጫ እየበረርኩ መከተል ጀመርኩ።
እኔ ሆስፒታሉ በር ላይ ስደርስ እነሱ ያልቧት ባለ አንቴና ባጃጅ  አደባባዩን ተሻግራ ወደ ገንደ ቆሬ መስመር  እየበረረች ነው። አፈጣጠኗ አጃኢብ ነው። እየተከተልኳቸው መሆኑን አውቀው••••  "መጣኮ ! ኧረ ንዳው!  ንዳው እንጂ ! አፍጥነው!"  እያሉ ሲንጫጩበት በአይነ ህሊናዬ  ታየኝ።
ዋናውን የገንደቆሬ መንገድ ይዘው በካራማራ ሆቴል ፊት ለፊት  አልፈው  ቁልቁል ወደ ዲፖ መስመር በረሩ። እኔም ከጀርባቸው ሆኜ በረርኩ። በመካከላችን ያለው ርቀት ወደ ሁለት መቶ ሜትር ተጠጋ። ፀሀይ ሆቴል ከመድረሳቸው በፊት ወደ ቀኝ ታጠፉ። ረገብ አድርጌ ተጠጋሁ።  ወደታጠፉበት ሳልታጠፍ በዝግታ እያለፍኩ አየት ሳደርግ  ከዋናው አስፖልት ገባ ብሎ በተሰራ የመኝታ  አገልግሎት ብቻ በሚሰጥ በአንድ  'ፔንስዬን'  በር ላይ ተጠግተው ቆሙ።
እልህ ይሁን ንዴት፣ ቃልዬን የማጣት ፍርሀት ይሁን ቅናት  ብቻ የሆነ ስሜት ተናነቀኝ ••••
"ቃልዬ••••!  አይኔ እያየማ እዚህ ቤት ውስጥ ይዞሽ አይገባም !" አልኩ።

ልቤም እየደለቀች ትንፋሼም ሲሮጥ እንደመጣ ሰው ቁርጥ ቁርጥ እያለብኝ  እስኪወርዱ መጠባበቅ ጀመርኩ።
ከባጇጇ የወረዱት እድሚያቸው የገፋ ጠና ጠና ያሉ  ሴትና ወንድ  መሆናቸውን ስመለከት ክው አልኩ።
ባለአንተና ባጃጅ በሞላበት አገር አንድ ባላንቴና ባጃጅ ስከተል መበላቴን ፣ መሸወዴን ማመን አቅቶኝ ••• የወረዱትን ሰዎች ሂሳብ ከፍለው መልሳቸውን ተቀብለው እስኪገቡ  ድረስ በተናደደ አይን በደንብ አየኋቸው •••ሴትየዋ እድሚያቸው ወደ ሀምሳ ይጠጋል ፣ ግን ሞንደል ያለ ደባና ቀጠን ያለ ወገብ አላቸው።አለባበሳቸውም እንቢ አላረጅም ፣ ቶሎ እግላለሁ ማገዶ አልፈጅም እንደሚሉት አንዳንድ ባልቴቶች  ነገር ናቸው።ወንድየው ወደ ስልሳ አመቱ ሳይጠጋጋ አይቀርም።
የነዚህ በዚህ እድሚያቸው አልጋ ቤት ለአልጋ ቤት መርመጥመጥ ነው እንጂ የሚገርመው፣ ደሞኮ ፍጥነታቸው፣ በእርግጠኝነት ከሚስት እና ከባላቸው የፎረፉ ናቸው ፣ አዋ ናቸዋ! ምን ጥያቄ አለው።
እኔ በቅርብ ግዜ የባጃጅ ስራ ጀምሬ እንካን ስንቱን የነሱን ቢጤ ፎራፊ ነው  ስንት አልጋ ቤት አደረስኩ። ምን ይመስላሉ በፈጣሪ!
ባለአንቴና ባጃጅ ውስጥ ሆነው ሲንቀዥቀዡ እነ ቃልዬ መሰሉኛ እኔ ምን ላድርግ ቀዥቃዦች !" አያልኩ ••• እነቃልን እነሱ ያስመለጡኝ  ይመስል  እስኪገቡ ድረስ ቆሜ ስወርድባቸው ቆየሁ። እነሱም ገቡ ባለባጃጁም እዛው በቆምኩበት አልፎኝ ሄደ።
ወዴት እንደምሄድ ግራ ግብት አለኝ ።
ባጃጄን አስነስቼ በመዞር በመጣሁበት መንገድ ቀስ እያልኩ ሳዘግም ስልኬ ጠራ።
ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ ስመለከተው ቃልዬ ነች የደወለችው። በፍጥነት ወደ ጆሮዬ ላኩትና •••
"ሄሎ ቃሌ የት ነሽ•••?
.
.

@askignkeldoch          

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago