ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
✍&🎙RominaYabatua
.........✍be RominaYabatua
ሷቋ ለተመልካች ይመስላል እልፍ ደስታ
ፈገግታዋን ያየ ይመኛል መሆን በሷ ቦታ
ግና ከሚፍለቀለቀዉ ፈገግታዋ ባሻገር
ዉስጣን የሚተናነቃት አላት አንድ ነገር
እንባዋን ዋጥ አድርጋ ወደዉስጥ ምታፈሰዉ
የልባን አዋቂ የምታማክረዉ አታ እኮ ነዉ ሰዉ
አታሳዝንም እ😌
.............✍
እንሰሳ እና ሰዉ ከአንድ መድብል ላይ
ቢሉ ተመለከትኩ እኔነኝ አኔን የበላይ
ዳኛ በሌለበት አንድ እንኳን አዋቂ
ሙግቱ ተያያዙ እየበዛ ጠያቂ
እኔሻል እኔ እሻል ነገሩ ሲጧጧፍ
ተመልካች ሁላ ገጠመ አፍ ለአፍ
ከብዙ ክርክር ከጊዜ ቡሀላ
የሰዉነት ልክ በእጅጉን ላላ
ዳኛም ተገኘ ከራስ ህሊናም ፈረደ
የሰዉ ልጅ ከሰዉነት ተራ ወቶ ተሰደደ
ወዴት...........
✍ Yoadan
..................✍
አመመኝ ቢለኝ አብሬ ታመምኩኝ
ተሽሎት ባየዉ ተንሰራርቼ ዳንኩኝ
ሲከዳኝ አመንኩ ስርቀኝ ተከተልኩ
ሚጠዘጥዝ ቁስል እላዬ እየከተብኩ
ለስኬቱ ባከንኩ ለህልሙ ተገበርኩ
ለሱ እርባነ ቢስ መወጫጫዉ ነበርኩ
ዋጋ የለኝማ ....አለማመን አይዳዳኝም
እያመኑ መከዳት ዛሬም አይደክመኝም
✍RominaYabatua
..................✍( ክፍል 8) ሰአታት እያለፉ ሲሄዱ ስጋቴ እየጨመረ መጣ።'በየቀኑ ላንገናኝ እንችላለን' ያለበትን ምክንያት መገመት እንኳ አለመቻሌ ሆዴን ቆርጦታል።ከዚህ በፊት የእሱ አዘውትሮ ወደ እኔ መምጣት ምናልባትም ማንም ሰው ወደ ክፍሉ በስህተት እንኳ እንዳይገባ ሳያደርግ አይቀርም።አሁን ግን አንድ ሰው በሩን ብርግድ አድርጎ ቢገባስ?ጸጉሬን እየነጨና ከግድግዳ ጋር እያጋጨ ሲያስወጣኝ…
...............✍ክፍል( 7) በጥድፊያ ወዳሰበው ምድር ቤት ወሰደኝ።እስካሁን ካየኋቸው ክፍሎች በጣም የተለየ ነበር።ጨለም ያለ እና ጠባብ ነበር።እንደሌሎቹ ክፍሎች የተለየ ገጽታ የለውም።እዚያው ክፍል ወስጥ ሰወር ብሎ የተሠራ ሌላ ክፍል አሳየኝ።ባኞ ቤት ነበር።እዚያ ደግሞ በጣም ጠባብ መስኮት የነበረ ሲሆን ግጥም ተደርጎ የተዘጋና በእንጨት የተሠራ በመሆኑ ወደ ውጪ ለማየት የሚያስችል አልነበረም።ከዚያም…
.....................(ክፍል=6) "ይኸውልህ ዛክ፣እስከ አሁን ነገሮችን በከፍተኛ ጥንቃቄ ሳከናውን ቆይቻለሁ።አሁን ግን በአንተ ትንሽ ስህተት ምክንያት ሁሉ ነገር እንዲበላሽ አልፈቅድም።ስለዚህ ይህችን ሴት ወይ አስወግዳት ወይ ከዚህ አውጥተህ ጣላት።ብቻ ከእኛ እይታ አርቃት።ስመለስ በጭራሽ ላያት አልፈልግም።" "ግን እኮ..." አላስጨረሰውም።ጥሎት መሄዱን ኮቴው ነገረኝ። ዘካርያስ…
ናፍቀኸኛል......
.............✍
ንፋስ እንዳወዛወዘዉ እንደ ዛፏ ቅጠል
ልቤን ባየህልኝ በቅፅበት ሲንጠለጠል
በሰአት ደቂቃ በናፍቆት ሆዴ እየባባ
አንተ ብዘገይ ጊዜ ትዝታህ ስንቴ ወቶ ገባ
ብዙ ........
በጣም ብዙ.......
እጆቼ አንተን ለማቀፍ ላመታት እንደዳዱ
እግሮቼ በየመንገዱ እንደተወላገዱ
ስንት ዘመን አለፈ ስንት ጊዜ ከነፈ
በኔ ጥፋት በደል ሁሉም በትዝታ አለፈ
ግና.......
እየዳህኩ ወዳንተ ለምምጣት ይከጅለኛል
ለምን እንደዉ እንጃ ዛሬም በጣም ናፍቀኸኛል
በብዙ ብበድል ይቅርታ ባያሰኘኝ ያለፈ ጥፋቴ
ሸሽጎ መደበቅ ተሳነኝ ገዝፎብኝ ሀጢያቴ
ሆኖም ነፍቀኸኛል ጥፋቴ ለፍቅርህ ቢሆነኝ መቀጣጫ
ላልገቡኝ እዉነትቶች ለጠፉብኝ ትላንት ጠፍቶኛል መቋጫ
ብቻ ላልተመልከትኩት ስቃይህ እንዲያ ስኮበልል
ናፍቆትህ ቀቶኛል ደጋግሜ ስምህን እንዳነበንብ
ሆኖም ናፍቀኸኛል..........
✍RominaYabatua
;::::አ::::::::::ለ:::::::::::::✍
ድፍን ሀገር ያወገዘኝ ተነቅሬ የተተፋሁ
ላመታት ሀቄን ተቅምቼ በሀሜት የተገፋሁ
ቁስሌን ሲነካኩት ደጋግሞ እየመረቀ
ዉስጤን ሲብከነከን ሰዉነቴ ቀዘቀዘ
አይለዉ ስቃይና ህመም እንደምጥ ሲታገሉኝ
ነፍስ ዉጪ ነፍስ ግቢ ቃላቶች አደከሙኝ
ቻል ዋጥ አርጌ ምንም እንኳን ለታይታ ብፈካ
አለ የደበኩት ህመም ጭራሽ ያልተነካ
አለ......
✍RominaYabatua
?RominaYabatua
ጠብቄህ ነበር.......
::::::::::::::::::::
ካልከኝ ከዛ ቦታ የክት ልብሴን አጥልቄ
ቅባት ያወዛዉ መልኬ በጨርቄ ጠርጌ
ከወዲና ከወዲያ ዐይኔ እያማተረ
ካላፊ አግዳሚዉ መሀል ጠብቄህ ነበረ
ጠብቄ.......
.......ጠብቄ.......
ሠዐቱም ነጉዶ ለጨለማ ተሰናዳ
ያለወትሮ መቅረትህ ሆነብኝ ዛሬ እንግዳ
ለጨለማዉ ንጋት ሲታረቀዉ እንዳየሁ
ትመጣ እንደዉ ብዬ ዳግም እወጣለሁ
በአዲስ ቀን አዲስ ቀጠሮ ልቤ እየሰነቀ
ጠበቄህ ነበር ሰዉነት ወዜ እየደረቀ
ያጠለኩት የክት ልብስ ሽንሽኑ ቀሚሴ
ሳይወልቅ ተጣበቀ ዝንት አለም ከራሴ
ትመጣለህ እያልኩ ከቀናት በአንዱ
ብትቀር ጊዜ ወዝ እና እድሜዬ ነጎዱ
ግና......
.... እኔ........
ዛሬም እንደጥንቱ እንደለጋዉ እድሜ
ጠብቄህ ነበረ ከተቃጠርንበት ቆሜ
እልፍ ፀሎት እልፍ ደጅ መጥናት
በጥቂት ተስፋ በብዙ ማጣት...
ጠብቄህ ነበር ሳልል እዚ እና እዛ
ፀጉሬ እስኪሸብት ወዜ እስኪጠፋ
ጠብቄህ ነበር.........
✍BeRominaYabatua✍
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago