ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ትራምፕ በኢትዮጵያ
"ትራምፕ" የሚባል ምግብ በአዲስ አበባ መኖሩ ተነገረ ።
ይህ ትራምፕ የሚባለው ምግብ ለ3 ሰዎች እንደሚበቃ እና ከተለያዩ ዓይነቶች እንደሚሠራ ተገልጿል።
ዋጋው 250 ብርነው ተብሏል።
የደመወዝ ማስተካከያው አልቀረም - ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን ኮሚሽነር
የተፈቀደው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፥ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው። በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው።
የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት ፈቅዷል። በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል። ሌሎችም እንደዚሁ የከፈሉ አሉ። የቀሩት ደግሞ የማጥራት ሥራ እየሰሩ ሊሆን ይችላል። እነዚያም ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ የተስተካከለው የጥቅምት ወር ክፍያ ታሳቢ በማድረግ የሚከፍሉ ይሆናል"ብለዋል።
ማስታወቂያ
50,000 እና በላይ የቴሌግራም ተከታይ ያለው ቻናል ካላችሁ በኢትዮጵያዊ ድርጅት ሞኒታይዝ ማስደረግ ስለምትችሉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን:: ድርጅቱ በቅርቡ በቲክቶክ እና ዩቱብ እመጣለሁ እያለ ነው:: contact: @ethiodlbot
BREAKING: Bitcoin reaches new all-time high of $75,000 following Donald Trump's winning.
ክልሎች የትምርት መሳሪያዎች ላይ መጠነኛ ክፍያ እንዲያስከፍሉ የሚደነግግ አዋጅ ሊጸድቅ ነው
ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ የሚችሉበት ህግ ለቋ ኮሚቴ ተመርቷል።
ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው አዋጅ ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ እንደማይቻልም ተጠቁሟል።
በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የጸጥታ ችግር በሺህ የሚቆጠሩ ትምርትቤቶችን ከመማር ማስተማር ውጪ እንዳደረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ የተላከ ሲሆን ይጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ትራምፕ ካማላን ሃሪስን በማሸነፍ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ይሆናሉ ሲል " ፎክስ ኒውስ " ጠቁሟል።
ባንዲራ ይዘው የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ የነበሩ ታዳጊዎች ከትምህርት ቤታቸው ታፍሰው ተወስደው እንደተደበደቡ ታወቀ
ጀሞ 1 የሚገኘው የሳውዝ ዌስት አካዳሚ ተማሪዎች የሰንደቅ አላማ ቀንን ለማክበር እያንዳንዳቸው አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ለየብቻ፣ ማለትም አንዱ ተማሪ አረንጓዴ ሌላው ቀይ ሌላው ቢጫ ለብሰው እና የጥላሁን ገሰሰን "ኢትዮጵያ" መዝሙር ሲዘምሩ ቆይተው ኋላ ላይ ግን ለምን ይህን ቀለም ያለበት ልብስ ለበሳችሁ ብለው የፀጥታ አካላት የጅምላ እስር እንደፈፀሙባቸው መሠረት ሚድያ ያሰባሰበው መረጃ ያሳያል።
በሶስት መኪናዎች ተጭነው የመጡት የፖሊስ አባላት ባለ ኮከቡን የኢትዮጵያ ባንዲራ ጭምር ይዘው ሲዘምሩ የነበሩ 30 ገደማ ታዳጊ ተማሪዎችን ጭነው በመውሰድ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ድብደባ እንደፈፀሙባቸው ታውቋል።
ከተደበደቡት ተማሪዎች መሀል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
እነዚህ የ10ኛ ፣የ11ኛ እና የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ዳይሬክተሩ ሀሙስ እለት ካሰሩዋቸው በኋለ አርብ የተወሰኑትን ከፈቱዋቸው በኋላ ዳይሬክተሩን እና የተወሰኑ ተማሪዎች አስረው አቆይተዋል ተብሏል።
"የራሱን የመንግስት በአል ማክበር ያሳስራል ወይ? በጣም ነው ያዘንነው" ያሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል ይወቅልን ብለዋል።
ባንዲራ ከመልበሳቸው ጀርባ የሆነ አላማ አለ በሚል ጥርጣሬ እስሩ እና ድብደባው እንደተፈፀመ ምንጮቻችን ጠቅሰው የወረዳ አመራሮች የልጆቻቸውን ከእስር መፈታት ሊጠይቁ ሲሄዱ "የፈለገ በክላሽ መግጠም ይችላል፣ ምላሽ እንሰጣለን" የሚል አሳዛኝ ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ማርያም ሰፈር በሚገኘው ፖሊስ ጣብያ በታዳጊዎቹ ላይ የተፈፀመው ድብደባ ልባቸውን የሰበረው ወላጆች "ፖለቲካ ምንድን ነው ቢባሉ እንኳን ምላሽ የሌላቸውን የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች አጉሮ መደብደብ የግፍም ግፍ ነው" ብለው በምሬት ተናግረዋል።
Meseret Media
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ - አንድ መምህር የሙያ ፈቃዱን በየ2 ዓመቱ ማሳደስ አለበት
👉የተማሪዎች ምዘናን በሚመለከት እስከ 1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የሚባለው እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥን ይከለክላል፡፡
👉ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወርን በሚመለከት ደግሞ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የሚቻለው ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት አይነቶች 50 ከመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲያመጡ ብቻ ነውም ተብሏል፡፡
👉ክልላዊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሁለት ጊዜ በላይ በነጻ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም የተባለ ሲሆን ተፈታኞች በግላቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል ይላል ረቂቅ አዋጁ፡፡
👉በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይም የመምህራንን ትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮችን በሚዘረዝርበት አንቀጽ ስር ሴቶች ለመምህርነት ስልጠና በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምልመላ የሚያስፈልጉትን አጥጋቢ መስፈርት አሟልተው በውድድር ወቅት ከወንዶች ጋር እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ወቅት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ደንግጓል፡፡
👉እንዲሁም አንድ መምህር በስራ ላይ እያለ በመንግስት ወጪ ደረጃውን የሚሻሽል ስልጠና ከወሰደ ለእያንዳንዱ የስልጠና ዓመት አንድ ዓመት በሙያው ማገልግል አለበት ሲልም ግዴታ ተጥሏል፡፡
👉አንድ መምህር የሙያ ፈቃዱን በየሁለት ዓመቱ ከክፍያ ነጻ በሆነ መንገድ ማሳደስ እንዳለበት የደነገገ ሲሆን የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከምረቃ በኋላ የ2 ዓመት ልዩ የመምራን ሙያ ስልጠናን መውሰድ እንዳለበትም በረቂ አዋጁ ለይ ተደንግጓል፡፡
👉የግል ትምህርት ቤትን ማቋቋም ስለ ሚከለከልበት ሁኔታ በሚያትተው አንቀጽ ስር በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም እዳ መክፈል ያልቻለ ሰው፣ ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ፈቃድ ከሚጠይቀው አመልካች ውስጥ ድርሻ ያለው ሰው በወሲባዊ ወንጀል አልያም በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተወሰበት ሰው ፈቃድ ማግኘት አይችልም ብሏል፡፡
👉መንግስት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርትን በብቃት እና በጥራት ለማዳረስ ያለበትን ግዴታ ለመወጣት ሀገር አቀፍ የትምህርት ፈንድ እንዲቋቋም አዋጁ ይፈቅዳል ይላል፡፡ #alain
የቻይናው አሊባባ ቡድን ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ንግድ አካዳሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊከፍት እንደሆነ ተገለጸ
በአሊባባ ግሎባል ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከፈተው የስልጠና አካዳሚ ኢንሼቲቩ በአፍሪካ የሚከፍተው የመጀመርያው የስልጠና ማዕከል እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን የሀገር ውስጥ የዲጂታል ክህሎትን የማዳበር ዓለማ አለው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ መንግሥት የዲጂታል ምጣኔ ሃብትን እውን ለማድረግ በፖሊሲ በዲጂታል ክህሎትና በመሰረተ ልማት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከአሊባባና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚወስዷቸውን ልምዶች ወደ ተግባር በመቀየር ዲጂታል ምጣኔ ሃብትን እውን ለማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
ኢኒሼቲቩ ሙያዊ ስልጠና በመስጠት ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ለሌባ መርዶ ለስልክ ባለቤቶች መልካም ዜና ነው ተብሏል
ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አሳወቀ።
ኩባንያው ኤአይን በመጠቀም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች ወደ ስልኩ አምራች ተቋም ሪፖርት የሚያደርጉበት አሰራርን ዘርግቻለሁ ብሏል
አዲሱ የጎግል አሰራር የስልክ ንጥቂያ ወንጀሎችን ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል።
እንደ አልዓይን ዘገባ ከሆነ ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡
ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡ #alain
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago