ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 1 day ago
Last updated 2 weeks, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ፣ ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
መጥፎ ሰጥተህ ጥሩ ለመቀበል ማሰብ አትችልም፣ ጥሩም ሠጥተህ መጥፎ እቀበላለሁ ብለህ አትጠብቅም። ትክክል እንዳልሆነ ለምታውቀው ነገር ይሄን የውሸት ምክንያት አትስጥ! አንተ በሰራኸው ስህተት ሕይወትን አትውቀስ!!!
#ደግነትን ፣ ርህራሄን ፣ አዛኝነት ፣ ቅንነት እና በጎ አሳቢነት በተፈጥሮ ለሰው ልጅ የተቸረ ነው።
#ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም።
#የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው። ደጎች የፍቅር ልብ ያላቸው፣የሰው ችግር የሚገባቸው ።ከራሳቸው ሰውን የሚስቀድሙ ፣በሰው ላይ የማይፈርዱ ና ሩህረሩህ ናቸው ።ውስጣቸው ከክፋት የጠራ ብዙ ደስታ ና ፍቅር የሚገኝባቸው ጥበበኞች ናቸው።
ሰው በውስጡ በመልካም እና ሰናይ ምግባራት የተሞላ ፍጥረት ነው።
እኩይ ተግባር ግን የልምምድ ወጫዊ ተፅእኖ ተግባር ነው።በውጫዊ ተጽእኖ ሳይደናቀፉ እና ሳይቀየሩ ይህን የተፈጥሮ ጸጋ መጠቀም ደግሞ ታላቅነት ነው ሰብአዊነት ነው አርቆ አሳቢነት ነው አስተዋይነት ነው።
#?በአስተዋይነት_ከተጓዝን ደስታ ፣ ፍቅር ፣ እርካታ እና ነጻነት ደግሞ የህይወት ሽልማት ናቸው።
መልካም ቃላትን አስብ። ወዳጅነት፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ተስፋ፣ እድገት፣ እረፍት፣ በጎነት፣ ነጻነትን አስብ። ሁሉ መልካም እንደሆነ አስብ። ስለሁሉ ነገር አላህ አመስግን።
??
??https://t.me/eross_heart
? ተቃውሞ
ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ ለውጥ ለመፍጠር ያግዛል!
▶ ከሚሰጡን ምላሾች ከአውንታዊነት(Positivity) ይልቅ አሉታዊነት (Negativity) እኛ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል‼️
➽ ሁሌ ከተጨበጨበልን ጉድለታችንን ላናውቀው እንችላለን በዚህም አልበቃ ብሎ - - - - -
➝ልክ እንደሆነን ፣
➝ሙሉ እንደሆንን
➝ ጉድለት የሚባል ነገር እንደሌለብን
➝ መሻሻልና መቀየር እንደሌለብን ሊሰማን ይችላል!
ያ ደግሞ አዲስ ነገር ለማወቅና ለመጨመር አንጓጓም፤ በአንድ መስመር ላይ ብቻ እንሄዳለን!!!
➽ ይሄኔም ልባችን ላይ ኩራት እያደገ፣ ውስጣችን በእብሪት እየተሞላ፣ አዕምሯችን ውስጥ መጥፎ አመለካከት ስር እየሰደደ ይመጣና በዙሪያችን ላሉ ሰዎች መጨነቅና ማሰብ እናቆማለን።
➝ በዚህም አያበቃም ትላንት የነበረን ማንነት መጥፎ ሆነ ጥሩ ለይተን ሳናውቀው በደፈናው በራሳችን ዓለም ውስጥ እንኖራለን! ይህ ደግሞ ከኛ ውጭ ያለን አመለካከትና ዕይታ ስህተት የኛው አመለካከትና ዕይታ ደግሞ ትክክል መስሎ እንዲታየን ያደርጋል።
ተቃውሞ፣ ትችት፣ እንዲሁም የአስተያየትና የጥያቄ መብዛት ሲከሰት መልስ ለማግኘት ሌላ እይታ ልንመለከት እንችላለን! ያ ደግሞ በእጅጉን ትላንት ላይ በቃን ብለን እንዳንቆምና ዛሬ ላይ ፈርጣማዎች እንድንሆን ያግዘናል!!! ይህ እገዛም በህይወታችን ውስጥ ትልቅ የሆነ ለውጥ ያመጣልናል። ከሰውም ሆነ ከራሳችን በገኘናቸው (በቀሰምናቸው) መልካም አመለካከቶችና ዕይታዎች ራሳችንን ሆነ ሰውን እንቀይርባቸዋለን!!
በዚህም አያበቃም ትላንት ትክክል መስሎ ይታዩን የነበሩ የህይወት መስመሮች ትክክል ወይም ስህተት መሆናቸውን ዛሬ ላይ ለይተን እንድናውቅ ያደርጉልናል‼️
ስለዚህም ይህን እንላለን - - - - -
▶ ከሚሰጡን ምላሾች ከአውንታዊነት(Positivity) ይልቅ አሉታዊነት (Negativity) እኛ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል‼️
▶ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ ለውጥ ለመፍጠር ያግዛል‼️
▶ ወቀሳዎች በፍርኃት ሳይሆን ጥንካሬን ይወልዱልንና በስኬት ያጎናፅፉናል‼️
▶ ከተለያዩ ሰዎች የታዘብናቸው ወይም የቀሰምናቸው የተለያዩ ዕይታዎች በርካታ ነገሮችን እንድናስተውልና “ አሃ ” ለካ እንዲህ ነው እንድንል ያስችሉናል‼️
▪️ያኔም ነው ነገሮችን በተረዳንና ባስተዋልን ጊዜ ይቺህ “አሃ” ከኛ ውስጥ የምትወለደው‼️
▪️ ያኔም ነው ያሰመርነው ወይም የተሰመረልን መሥመር እና እየሄድነበት ያለው ወይም ሰዎች ያመላከቱን መንገድ ቀጥተኛ ይሁን ወልጋዳ፤ ትክክል ይሁን ስህተት አበጥረን ማወቅ የምንችለው‼️
*✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል*
════════════════
ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil ይ?ላ?ሉን?*? share?***
Telegram
𝐑𝐞𝐬𝐡𝐚𝐝 𝐌𝐮𝐳𝐞𝐦𝐢𝐥
➤ ህይወት አንድ ንግድ አይደለችም፤ መቀበልና መስጠት ብቻ የሚካሄድባት። t.me/SharpSwords1
✍ #Idonisia SinAr pp 50page Ex book (ፒፒ ስነር ደብተር )
? አድራሻ?
መርካቶ:- አፍሪካ የገበያ ማዕከል አጠገብ
ለማዘዝ ስልክ ይጠቀሙ???
? 0963339669
ቴሌግራም ?
https://t.me/Golden_jej
በትክክለኛ መንገድ ላይ ሁን
በድጋሚ
Mubark Ahmed
???
https://t.me/Golden_jej
? መነፅራችንን አውልቀን ከቆሻሻ እንጨምረው!
➤ በአለም ላይ ሁሉም ሰው ነው፤ ቢሆንም ሁሉም የተለየ ማንነትና መታወቂያ አለው‼️
ይህ ማለት ደግሞ:-
● ከኛ የተለየ አመለካካት ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ እይታ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ የፍትህ አሰጣጥ መንገድ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ውሳኔ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ሀሳብና አስታየት ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ችሎታ፣ ክህሎት፣ ብቃትና ጥበብ ያላቸው፤ አለም ላይ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው!!
ነገር ግን ታዲያ ይህ ማለት አደለም፤ እነሱ ስህተት ናቸው እኛ ደግሞ ትክክል!
ይህ ማለት አደለም፤ የነሱ የእይታ አድማሳቸው የጠበበ የኛ ደግሞ የሰፋ!
▼ ምናልባትም ሁለታችንም ልክ ነን፤ ነገር ግን እርሰ በርስ ስለምንናናቅ ብቻ የአንዳችን ውሳኔ አንዳችን አይመቸንም!
▼ የአንዳችን ፍርድ ሌሎቻችን ላይ ትክክል ያልሆነ መስሎን ፍርደ-ግምድል ይመስለናል!
▼ ጠንከር ያሉ መልካምና ሰናይ ተግባር የሆኑ ስራዎች ራሱ የደካሞች ምልክት ይመስለናል!
◉ ውስጣችንን እልከኝነት፣ አልሸነፍ ባይ ጅልነት፣ ኩራትና ፣ ‟እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው” የሚባል «አላዋቂነት» ፣
◉ “እኔ ነኝ የበላዩ” እሱ እንዴት ሀሳብ ሊሰጠኝ ይችላል የሚል የጅሎች አስተሳሰብ፣
◉ ከኔ ስር ያሉ ሰዎች ያሉት ከኔ ስር ነውና የነሱን ሀሳብ አልቀብልም የሚል ‟እብሪት˝ እንደ ወረርሽን እርሰበርስ ተዛምቶብን ጤነኛ የሆኑ አመለካከቶች ራሱ ስህተት ይመስሉናል። መልካምና ከድንቅም በላይ የሆኑ ስራዎች ራሱ ‟የሰይጣን ስራ” መስሎ ይታየናል!
➻ ችግሩ የእይታችን አድማስ ጠቦ፣ የመነፅራችን ቀጡር አንሶ ወደ ዜሮ ተቀይሮ፤ ሌሎች ስራዎችንም በዜሮ እያባዛ ውጤቱንም ዜሮ እያደረገው መሆኑን ሳናስተውል እንቀራለን!
➻ “የበላያቸው” ነኝ የሚለው እብሪታችን ወደታች እየጎተተን መሆኑን ሳንገነዘብ መቁማችን እንሞታለን!
↪️ እንደ ብርኃን ብልጭታ ጥርሳችንን እያሳየን፤ ፈገግ ያልን መስሏቸው እነሱ መሳቅ ሲጀምሩ እናስለቅሳቸዋለን!
↪️ ለጥቅማችን ብለን *ባበራነው ሻማ እነሱ ብርኃን አገኘን፣ ብርኃን ከወዲያ ብልጭ አለ ብለው፤ በብልጭታዋም በታዬቻቸው ልክ ስራ መስራት፣ ያለምንም ምላሽ ሰዎችን ማፍቀር(መውደድና ማክበር)፣ ደካሞችን መርዳት፣ መልካም ትውልድን ማፍራት፣ ማህበረሰብን ማገልገል ሲጀምሩ፤ ያቺንም ትንሿን ብልጭታ መልሰን እናጠፋባቸዋለን!
➻ እኛ መልካም የሆኑ ህልሞችን ማለማችንን ትተን ሌሎችም እንዳያልሙ የመብረቅ ጋጋታ እንሆንባቸዋለን!
➻ ጤነኛ ህልሞችን ማለም ትተን በጤነኞች በሽታ እንሆንባቸዋለን!
➻ ተደጋግፈን፣ ተዋደን፤ በፍቅር አንድ ላይ አብረን የስኬት ማማ ላይ መድረስ ሲገባን፤ ደካማ መስለው የታዩንን ሰዎች ስንወቅስና ስንጨፈልቅ እንከርማለን‼️
➻ ጀልባችን ውኃ ከሌለበት ቦታ እንድትሰምጥ እናረጋታለን!
ከዚህ ሁሉ ግን የሚበጀን.......
⓪‟እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው”
⓪“እኔ ነኝ የበላዩ”
⓪ “እኔ ብቻ ነኝ ጠንካራው” ፤፤ ከሚሉ ቢቀነሱ፣ ቢደመሩ፣ ቢካፈሉ፣ ቢባዙ ውጤታቸው ዜሮ(⓪) ከሚሆኑ፤ ‟እብሪቶች˝........
...ደክመንም፣ ብዙ መንገድ ተጉዘን፣ ላባችንን አጠፍጥፈን፣ ጉልበታችንን ጨርሰን የገዛነው ቁጥሩ ዜሮ የሆነ የዕይታ መነፅር ካለ አውልቀን ከቆሻሻ እንጨምረው!! ፤
◉ አረ እንደውም ሌላ ሰው እንዳያገኘው አድርገን ቆፍረን እንቅበረው‼️
*✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል*
════════════════
ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil
Telegram: t.me/SharpSwords1 ይ?ላ?ሉን?*? share?***
Telegram
𝐑𝐞𝐬𝐡𝐚𝐝 𝐌𝐮𝐳𝐞𝐦𝐢𝐥
➤ ህይወት አንድ ንግድ አይደለችም፤ መቀበልና መስጠት ብቻ የሚካሄድባት። t.me/SharpSwords1
ወንድሜ…
እድሜህ ዛሬ ብቻ ነው!
????
https://t.me/Golden_jej
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 1 day ago
Last updated 2 weeks, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago