ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
@semetnbegtm
..
እንቆቅልህ?
ምን አውቅልህ??
ከእናቷ ሆድ ወጥታ የእናቷን
ሆድ የምትመታ?
ተብሎ ሲጠየቅ ምስጢር እንዲፈታ
ሁሉም ልጅ ስለሆነ ያልፋል በዝምታ
..
ጥያቄ ጠያቂው መልሱን ይመልሳል
መልሱን ሲነግራቸው ዘነዘና ይላል
ያኔ በልጅነት እናት አትመታም
ብለው ጥያቄ ያልሠሩ፣
ዛሬ አዋቂ ሆነው ቲዎሪውን ትተው
ትግበራ ጀመሩ፣
እውቀታቸው ገንፍሎ ምሁራን ነን ያሉ
በጣም ተመራምረው ሰው በዘር ከፈሉ
..
ዘነዘና በዝቶ በሀገር መንደሩ
አውቅን አወቅን ብለው አጣልተው
ከእግዜሩ፣
የእምዬ ኢትዮጵያን ሀሳሯን ከመሩ
ምስጢሯ ላይገባው የሀገሬ ቅኔ
አልፎ ሂያጂ ሁላ በገዛ ራሱ ላይ
ያብዛል ኩነኔ
✍ኤርሚ ግርማ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
🤔
ግራ መጋባቴ እንደዉ ግራ ገብቶኝ፤
ስቋጥር ስፈታ እጅጉን አሳስቦኝ፤
ባስብ ባሰላስል ከልቤ አጣሀት፤
ግራ የገባኝን ግራ ገብቶኝ ተዉኩት።
..........................................
በዔደን ታደሰ
🥰
አየር
ጨረቃም እይደለሽ በማታ ምትመጪ
ፀሀይም አልልሽ በቀን ምትወጪ
ጨረቃ ከዋክብት ብርሃን ቢሰጡም
ከአየር እይበልጡም
እናም አካሌ ሆይ !!!
ጨረቃ ከዋክብት ብዬ አልልሽም
ሕይወቴ ስለሆንሽ አየር ብዬ ልጥራሽ
ጭራሽ አይከፋሽም
በሪሁን ሲራጅ ✍️
#እያደር_አዲስ
[ኢዛና መስፍን]
:
እዚህ በልቤ ውስጥ ፣
የመናኝ ቀብርሽን ፣ ገፁ ላይ የሳለ
ፍቅር እስከ ቀብር ፣ የሚል መጽሀፍ አለ፡፡
ታዲያ ይኽንኑ
የፍቅር ገድልሽን
ሰርክ እንደደገምሁት ፣ ይነጋል ይመሻል
አንደኛውን ዘልቄው ፣
በገለጥኩት ቁጥር ፣ ፍቅርሽ ያገረሻል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አንቺ ምስኪን ሀገር
ሁሉን የቻልሽው ምድር
ከበደኝ ልገልፅሽ
በቃል ልሰይምሽ
እንዲ'ኮ ናት ብዬ ማብቂያ ላበጅልሽ
ቆይ ምን ልበልሽ እስቲ ተናገሪ?
አንቺው ምረጭና ሰይሜሽ ተጠሪ
.
ደሀዋ እንዳልልሽ
በተፈጥሮ የሰጠሽ
ይታየኛል ሀብትሽ
ፈጣሪ ያደለሽ ስጦታሽ ብዙ ነው
እንዳልዘረዝረው የቱንስ ጠርቼ የቱን እተዋለው
.
ሀብታም እንዳልልሽ
ህዝብሽ መቸገሩን መራቡን እያየው
ከብዶት ኑሮ አዙሮት መሰደዱን ሰማው
የነፃነት ሀገር የፍትህ መድረክ ናት
ብዬ እንዳልናገር ሆነሻል የስጋት
ጀግና አያቶቻችን ያኔ የተሰዉላት
በአንድነት ሆነው ዋጋ የከፈሉላት
ተተኪ አባቶች ዛሬ ሸንሽነዋት
የእኩልነት ሚዛን ተዛብቶ የጠፋባት
አብሮነቱ ቀርቶ ልዩነት ሰፍቶባት
እንደ ዶሮ ብልት ዘር የከፋፈላት
ሆነሻል ሀገሬ ከእሳት የጣድዋት
.
ሰላም ለትውልድሽ ሆኖ ተናፋቂ
የራስ ባዳ ሆኗል ባዕድን አድናቂ
ተስፋ ያጣ ወጣት በዝቶ በርክቶብሽ
የተልፈሰፈሰ ሱሰኛ በዛብሽ
ሹመኛም አለልሽ በህዝብሽ ቆማሪ
በጠባብ ሀሳቡ ወደ ጥፋት መሪ
የዘር ጂኒ የያዘው ከእግር እስከ'ራሱ
በደም ተጨማልቆ ንብረት ማግበስበሱ
ደስታን የሚሰጠው የህሊናው ባዳ
ጥቅምን ሲያሳድድ አንቺን የሚከዳ
ኖሮብሽ ከእቅፍሽ ይዘሻል በጉያሽ
ታስገርሚኛለሽ
እንደው ስንቱን ግን ቻልሽ.🤔
.
እኔ ግን ሳስብሽ
በውስጤ ስስልሽ ወይም ስመኝልሽ
ይታየኛል ቀንሽ የብርሀን ማያሽ
መጪው ዘመን ላንቺ መልካም ሲሆንልሽ
ተመልሶ አንድነት ሲሆንልሽ ስንቅ
በልጆችሽ መሀል ሲወርድላቸው እርቅ
በረከት ሲመላ ችግር ካንቺ ሲርቅ
እድገትሽ ሲፋጠን ሰላምሽ ሲመለስ
የወጣቱ መንፈስ በፅናት ሲታደስ
ይታየኛል ተስፋ🥺
✍️የተክልዬዋ
@semetenbegtm
@semetenbegtm
@semetenbegtm
✨ ፭ ✨
ሀገሬ የችግርሽ ቅኔ
ታድለሻል ሀገሬ የ13 ወር ፀጋ
አባት ልጁን ቀጥቶ ያስተማረው ባለንጋ
እማዬ ሲሏት እመት ትላለች እናት
ልጇ ደስ ትላለች ታዛዥ ናት በውነት
በልተው ጠጥተው ኖረዋል በአንድነት
ያኔ ዘመን ነበር የሚታየው ደግነት
አሁን አሁንማ
አሁን አሁንማ
እቲቲ አልኩ ብደርብም ልብሴ ልቤን በረደው
ፍርሀት ወርሮት ልፍስፍስ በዝቶ ደግነት ራቀው
ሀገሬ እምዬ
ተፈጥሮሽ ቸር ሆና ሰማይ ባይነጥፍ ምድር ሲለመልም፣
ከልጇ ልብ ውስጥ ሰላም ስትጠፋ ነው ሀገር የምጨልም።
በታሪኩ እንደማይፅፍ ትውልድ እጁ ታስሮ፣
በትላንቱ እሾህ አሁኑን ሸንቁሮ።
ባልሆነው ተጣልቶ ባልሰራው ተዋቅሶ፣
ለፀብ መጀመሪያ ያያቱን ስም ጠቅሶ።
ላለፈው ሲለፋ ምሬቱን አብዝቶ ለመጪው ሳይተጋ፣
በምን ስሌት ይሁን ትውልዷ ጨልሞ ሀገር የምትነጋ።
ደህና ነኝ
አው እኔ ደህና ነኝ
ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል፣
የወገኔ ስቃይ እንቅልፍ እየነሳ ይቀሰቅሰኛል።
እብደት ተጠግቶኝ ዝም ብዬ እስቃለሁ፣
ሀገሬ ቁጭ ብዬ እንደባይተዋር ሀገር እናፍቃለሁ።
ወንድም በወንድሙ እጁን ካነሳ፣
ፍቅር ሰላም መልካም ስራ ተረሳ።
በምስራቅ በር ስሄድ ወንድምሽተገድሏል፣
በምዕራብ በር ስሄድ እህትሽ ተደፍራለች፣
በቃኝ ቀሪውን በር አልሄድ ነፍሴ ትፈራለች።
እምባዬም ፈሰሰ በረታ ሀዘኔ፣
ሀገሬ ስታንስ ዝቅ ሲል ወገ፣
ሀገሬ ምን ይሻለው የችግርሽ ቅኔ።
እውቀቱ ስላጣሁ ስላልቻለ አቅሜ፣
ልቤ ውስጡ ደማ ተሰበረ ቅስሜ።
እምዬ ሀገሬ የችግርሽ ቅኔ ሲያንኳኳ በሬ፣
እኔም አልገባኝም እፈታው ነበር ዛሬ።
መቼ ነው የሚነጋው መች ነበር የመሸው፣
መቼ ይሁን ድህነት ከምድሯ የሚሸሸው።
፨፨፨፨ሀገሬ የችግርሽ የቅኔ፨፨፨፨፨፨
ሰምና ወርቁ ፈልጌ እንዳገኛት፣
አምላክ ይረዳኝ ዘንድ እስኪ ልመርቃት።
እንዳምና ካቻምና ለፌሽታ ለተድላ ከቶ ባትመችም፣
በምድሯ ሰቀቀን ሙሾ ቢሰለችም፣
ተስፋ አትቁረጡባት ተኝታ ይሁን እጂ
ሀገሬ አልሞተችም።
ከየት የመጣ ነው ይሄ ግላዊነት፣
ምንስ ተገኝቶ ነው የጠፋው እኛነት።
ትውልድ ዘር ተቆጥሮ ብሄር የቀደመው፣
ሰው ከመሆን በላይ ማንነት ምንድነው።
መስከረም ሲገባ እንቁ ጣጣሽ ሲሏት፣
የሰላም የፍቅር የአንድነት ማሰሪያ ቀለበት አድርጋት።
ይሁን ምኞቴ ነው በዪኝ እስኪ አሜን፣
የማቶሳላ እድሜ የአብርሃም የሳራ ይሁን ፍቅራችን።
እንቁጣጣሽ ሀገሬ ሆይ ዕንቁ በዝቶልሽ፣
ጣጣሽ ያጥፋልሽ፣
አሜን ብዪኝ እስኪ በአፍሽ።
፨፨፨፨፨፨ አሜን፨፨፨፨፨
ገጣሚ ደስታ ወንድወሰን ( hasu )
https://t.me/semetnbegtm
ሆ...ቆይ አሁን ባለ ትዳር ማፍቀር ምን ይሉታል በናታችሁ???እንጃ!!ብቻ ግን ገና ሳየው ልቤ ላይ የፍቅር ንፋስ ሽው ይልብኛል፤ደስታ ይንጠኛል፤ፍቅር ፍቅር ይለኛል፤ሰውነቴ ይሞቅብኛል፤ማግባቱ ትዳሩ ይረሳኛል፡፡ጠዋቱ ደርሶ ነጠላውን ለብሶ እንደገና እስካየው ይናፍቀኛል.....
ጆዬ እለዋለሁ።ለማቅረብ እንጂ ትክክለኛ ስሙ ዮሐንስ ነው፡፡እሱም ስሙን ወዶታል መሠል ወድያው ''ወዬ" ይለኛል።በጠዋት ቤተ ክርስትያን አይቀርም፡፡ትሁት ነው፡፡ተጫዋች ነው፡፡በዚህ ፀባዩ ላይ ደሞ ውበቱ ቁመቱ ፂሙ እና ችምችም ያለ ጠጉሩ የሆነ ግርማ ሞገስ ያላብሰዋል፡፡ቅንድቡ የተቀነደበው ያህል ተሰድሯል፡፡ጥርሱ ገና ከሩቅ ያንፀባርቃል፡፡ታድያ ይሄንን አለማፍቀር ይቻላል?? ቀፍፁም!!
ጎረቤት ስለሆንን እሱ በጠዋት ቤተክርስትያን ሲሄድ እኔ ደሞ ስራ ስገባ እየተገናኘን ስሸኘው ተግባብተናል፡፡እንዲያውም መኪናዬ ውስጥ ከዘፈን ውጪ የማልሰማ ሴትዮ ዘማሪ አድርጎኛል፡፡ለዚህ እኮ ነው ምወደው ለዚህ ነው ሚናፍቀኝ ለዚህ ነው ማስበው...
እኔ ምለው ጆዬ...ሚስትህ ግን ቤ/ክ አትሔድም እንዴ? (እለዋለሁ ስለሚስቱ ልጠይቀው ብሞክርም እሱ ግን መልሱ አጭር ነው፡፡ ስለህይወቱ ብዙ አያወራም፡፡ጣቱ ላይ ያለችውን ቀለበቱን ማጫወት ልማድ ሆኖበት አስሬ ይነካካታል፡፡ሰሞኑ ሁኔታው ሁሉ ተለውጦ ከሳስቶብኛል፡፡ዛሬ ደሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ በዝምታ ተውጦ ብዙ ሳናወራ ነው ኪዳነምህረት የደረስነው
ጆዬ ግን ደና ነክ??(አልኩት ልክ ሲወርድ ጠብቄ በስስት እና በፍቅር እያየሁት
ደና ነኝ ማር.. (ብሎኝ በሩን ዘግቶት ነጠላውን እያስተካከለ ሲሄድ በአይኔ ተከተልኩት፡፡በሚወዱት ሰው መቆላመጥ ግን ደስ ሲል....ምናለ የኔ ብታደርጊው??? ምናል ብትሰጪኝ?ብቸኝነት አይበቃኝም??ምናለ አፍቅሬ ባትነሺኝ??እያልኩ ኪዳነምህረትን እየተለማመንኩ ቢሮ እንደገባሁ ነበር የምወዳት አጀንዳዬን የገለጥኳት፡፡በዝች አጀንዳ ጆዬ ስለሚያሾፍብኝ ፈግጌ እያገላበጥኳት ከውስጧ የወጣችው ብጣሽ ወረቀት ቀልቤን ሳበቺኝ፡፡ፅሁፉ የምወደው የጆዬ እጅ ፅሁፍ መሆኑን ሳውቅ ደሞ ተቅበጥብጬ አነባት ገባሁ....
"ማር አውቃለሁ ልነግርሽ ይገባ ነበር ግን ብዙ ተቀራርበናልና ላስጨንቅሽ አልፈለኩም፡፡ዛሬ በህይወት የመጨረሻ ቀኔ ነው፡፡ስለመልካምነትሽ ሁሉ አመ......"
ደብዳቤውን አልጨረስኩትም፡፡እንዴት ከቢሮ እንደወጣሁ እንዴት መኪናዬ ውስጥ እንደገባሁም አላቅም፡፡እራሴን ያገኘሁት ግን ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን በር ላይ እየጮኽኩ ነው....
አይሆንም ጆዬ!!አይሆንም!!!አንተ አደለክም!!! አንተ አትሞትም!!.....እያልኩ እንደ እብድ እያረገኝ የተሰበሰበውን ህዝብ ገፍቼ ስገባ ጆዬን ነጠላውን እንዳደገደገ ከምእመናን መሀል ቆሞ አየሁት
ምን ሆነህ ነው??ምን ተፈጠረ??ለምን ትሞታለህ?? ለምን???ንገረኝ ....
አልሞትኩም ማር ደና ነኝ ተረጋጊ ፀበልተኛ ታሞ ነው እኔ ደና ነኝ፡፡
እኮ ደብዳቤው ምንድነው??የምን መጨረሻ ቀን ነው??
ደብዳቤው የእውነት ነው ማር፡፡ዛሬ የመጨረሻ ቀኔ ነበር፡፡የምነግረው ሰው ስለሌለኝ ጠዋት ነው ደብዳቤዬን አጀንዳሽ ውስጥ ከትቼ የወረድኩት፡፡ካንሰር ከያዘኝ አመት አለፈ የሞት ቀኔን እየተጠባበቅኩ ሳለ ነው የተገናኘነው፡፡ግን ደሞ የሞት ደብዳቤው በኪዳነምህረት በህይወት ተቀይሯል፡፡ዛሬ ዶክተር ትሞታለህ ብሎ ቀጠሮ ሰጥቶኝ ቢሆንም ኪዳነምህረት ግን አትሞትም ብላ በህይወት አቁማኛለች፡፡አሁን የመጨረሻው ቀን አደለም ተመርምሬ ነፃ ነህ ተብያለሁ፡፡ ማር አሁን ነፃ ነኝ፡፡ወረቱን አይኑ ላይ እንባ ሙልት ብሎ እያሳየኝ እቅፍ ሲያደርገኝ ነብሴ እየተንሰፈሰፈች ልቤ ላይ ስንቅር ያለችውን ቃል ወድያው ጠየኩት
ጆዬ ግን እንዴት ግን ማንም የለክ?? ሚስትህስ?? ልጆችህስ??
ማር እኔ ሚስት የለኝም፡፡ብቻዬን ነው ምኖረው፡፡ቀለበቱ እናቴ ስትሞት የሰጠቺኝ ነው ልጆች ያልኩሽም ውሸቴን ነው፡፡ብዙ ተስፋ ስለሌለኝና ስለተቀራረብን መሀላችን አጉል ስሜት እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው እንጂ ልጅ ሚስት የለኝም፡፡ አሁን ግን...
አሁን ግን ምን??( አልኩት ልቤ በጉጉት ቀጥ እንዳለች አንቺ ብትወልጂልኝ ደስ ይለኛል....ብሎ ምወድለት ፈገግታውን አሳየኝ
በመጨረሻውን ቀን የመጀመርያ ደስታዬን መቅደሷ ፊት እፍስ አረኩት...
#የታሪክ_ግዜ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana