Minab Book Club

Description
Amharic Books
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 7 Monate, 1 Woche her

Last updated 7 Monate her

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 6 Monate her

10 months, 3 weeks ago

ይችላል። ነገር ግን ወደኛ ሀገር አውድ በማምጣት አስፈላጊ እና አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳዮቻችን ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል።
በርግጥ እንደ ጃፓን ያሉ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች በበዙበት ቦታ ሰዎችን ተክቶ የሚሰራ ሮቦት ስራ ላይ ቢያውሉ
ምርታማነታቸውን ያሳድጋል። ይህንኑ ቴክኖሎጂ ወደኛ ሀገር ብናመጣው ግን የስራ አጡን ቁጥር በማብዛት ኢኮኖሚያችንን
ከዚህ የባሰ ይጎዳዋል። በሀገራችን ሰፊ የሆነ ስራ አጥ ሰው በመኖሩ እና አብሻኛው የህብረተሰባችን ክፍል ወጣት እና ትኩስ
ሀይል ያለው በመሆኑ የሰውን ጉልበት ስራ ላይ ማዋል ይሻላል። ነገር ግን አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን የእርሻ ስራችንን
ብናዘምንበት ከእርሻ የምናገኘውን ገቢ በማሳደግ እና ምርታማነታችንንን በመጨመር የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ይረዳል።
ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ስርዓት እንዲሻሻል በማድረግ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ
የተማረ እና ስራ ፈጣሪ ትውልድን ለመቅረጽ ብንጠቀምበት ትልቅ ለውጥን በአጭር ጊዜ ለማስመዝገብ ይጠቅማል።
በጤናውም መስክ የሀኪም ቁጥር ለበሽተኞች በማመጣጠንበት የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ላይ ተግባራዊ ቢደረግ ያለ ጊዜያቸው
የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ እና መድሀኒቶችን በቶሎ ለማግኘት ይረዳል። ስለዚህ ትልቁ ቁም ነገር ቴክኖሎጂዉን በምን
እና እንዴት ባለ መንገድ እንደምንጠቀመው ማወቅ ነው።
በዚህ ቪዲዮ ስለ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምንነት እና አጀማመር እንዲሁም ጥቅሞቹ እና ስጋቶቹ በወፍ በረር ዳሰሳ
አድርገንላችኋል። ወደፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዙ ዶክመንታሪዎችን ይዘን እንቀርባለን። እስከዛው ድረስ ስለ ዘርፉ ያላችሁን
እይታ በኮሜንት መስጫው ስር አስቀምጡልን። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ስለነበረ እናመሰግናለን።

10 months, 3 weeks ago

በመተንበይ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ ካላ ያሳውቃል። አንዳንዴም እንደ አንበጣ መንጋ ያሉ ወረራዎች በሚከሰቱበት ጊዜ
ሰዎች የግድ በቦታው መገኘት ሳይገኝባቸው ጸረ ተባይ ኬሚካሎችን ለመርጨት ይጠቅማል።
በስዕል
ስዕሎች በሰዓሊያን ምናብ ውስጥ ያለውን ንጽረት አለም ወደ ገሀዱ አለም የሚያመጡ ምናልባትም አንዴንዴ ያው ራሱ
ሰዓሊው ካልገለጸልን በስተቀረ በራሳችን የማንረዳቸው መልዕክቶች የሚተላለፍባቸው የጥበብ መንገዶች ናቸው። አንዱ
የሳለውን ሌላው ሰው እሱኑን አስመስሎ ለመሳል ሊቸገር ይችላል ። አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ግን ከዚህ አልፎ እኛ ያሰብነውን
ቃል ብቻ ስንሰጠው እሱ ስዕሉን ፊታችን ላይ በቶሎ ስሎ ማስቀመጥ ጀምሯል። ከዚህ አልፎ ፋሽን ልብሶችንም ዲዛይን
ማድረግ ጀምሯል።
በመዝናኛ
በመዝናኛው መስክ የፊልም ስክሪፕቶችን በማዘጋጀት፣ የፎቶ ማቀናበሪያ filterሮችን በማዘጋጀት ፣ የሰዎችን ፊት ወደ ካርቱን
በመቀየር እንዲሁም እንነሱን ከሚመስሉ ታዋቂ ሰዎች ጋር በማመሳል ለሰዎች ደስታ እና ተዝናኖትን ይፈጥራል። ከዚህ
በተጨማሪም በጌሞች ላይ በስፋት ላይ ጥቅም ላይ ይውላል። እንደምሳሌ ያህል ቼዝ ጌምን በኮምፒውተር ለመጫወት
ብትፈልጉ ሌላ ተጋጣሚ ሰው ሳያስፈልጋችሁ በሰው ሰራሽ ክህሎት በመታገዝ መጫወት ትችላላችሁ።
በትራንስፖርት
በእግራችንም ይሁን በመኪና ወይም ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ በምንጠቀምበት ጊዜ ያለምንም ችግር ያሰብነው ቦታ
ለመድረስ እንደ Google map ያሉ አፕሊኬሽኖች የምንሄድበትን አቅጣጫ እና የት እንደደረስን በመጠቆም እንዲሁም
የሚቀረንን ርቀት በማስላት ይጠቅማሉ። ከዚህ በተጨማሪም ሹፌር ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው መሽከርከር የሚችሉ Self-
driving መኪናዎች ስራ ላይ ውለው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
እንግዲህ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጋብራዊነቱ እየጨመረ እና አድማሱ እየሰፋ በቀላሉ የግባራዊ ይሆናል
ብለን በማንገምታቸው መስኮች ሁሉ ውስጥ እየገባ ስራዎችን እያቀለለ ይገኛል። ዛሬ እኛ የጠቀስንላችሁ ነገሮች እግጅ በጣም
ጥቂቶቹ ናቸው።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እንዴት ተጀመረ
ከ1960ዎቹ በፊት አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከልብ ወለድ እና ምኞት ያለፈ ነገር አልነበረም። የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ
እናት በመባል የምትታወቀው እንግሊዛዊቷ አዳ ወደፊት እንደ ሰው ሰራሽ ክህሎት አይነት የመማር እና የማገናዘብ አቅም
ያላቸው ኮምፒውተሮች ሊሰሩ ይችላሉ ብላ እምነቷንንና ተስፋዋን ተናግራ ነበር። ከ1940 ወዲህ የተለያዩ የማቲማቲክስ ፣
ሳይኮሎጂ፣ ፖለቲካል ሳይንስ፣ ኢኮኖሚክስ እና ኢንጂነሪንግ መስኮች ላይ ያሉ ተመራማሪዎች በየጊዜው በሚያደርጓቸው
ጥናቶች እርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እውን ለመሆን ችሏል።
ለAI ጥናት በተለይም ደማቅ አሻራ ካሳረፉት ሰዎች መካከል አንዱ አለን ቱሪንግ /Alan Turing/ ነው። የራሱ የሆነ ፈተና
በማዘጋጀትም የማሽኖችን አፈጻጸም ለመገምገም ችሏል። ይህ መመዘኛውም Turing test በማባል ይታወቃል። በቀዝቃዛው
ጦርነት ወቅትም አሜሪካዊያን የራሽያን ቋንቋ መረዳት እና መተርጎም የሚችል ማሽን ለመስራት በሚታትሩበት ጊዜ እግረ
መንገዳቸውን አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እንዲያድግ ትልቅ ስራን ሰርተዋል። ዛሬ ላይ Natural Language Processing /NLP/
በመባል የሚታወቀው የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘርፍም የመጣው ከዚህ ጥናት ነበር። አሁን ባለው ቴክኖሎጂ ማሽኖች
የሰውን ልጆች ቋንቋ መረዳት ፣ ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎም እና እነሱም የሰውን ቋንቋ መናገር ይችላሉ። በርግጥ ሙሉ በሙሉ
በሚፈለገው ደረጃ ባይደርስም ነገር ግን ትልቅ እርምጃን ተራምደዋል። ለዚህም እንደምሳሌ የሚሆኑት የGoogle Translate
ቋንቋ መተርጎሚያ፣ የAlexa , Cortana እና Siri Voice assistant ይጠቀሳሉ።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና የሰው ልጆች ስጋት
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሰሩ ያሉ የሳይንሳዊ ልብወለድ ዘውግ ያላቸው ፊልሞች ሮቦቶች በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በመታገዝ
የሰው ልጆች ላይ ጦርነት ሲከፍቱ እና ሰውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሲነሱ ያሳያሉ። ከዚህ የተነሳ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ስለ
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምንም አይነት እውቀቱ ሳይኖራቸው እንዲሁ በደሀናው ለሳይንሱ ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል።
ፊልሞቹ ነገሩን አሁን ካለው እውነታ ለጥጠው እና አጋንነው ነው ያቀረቡት። ይሄ ማለት ግን አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እንከን
አልባ ነው ማለት አይደለም። በሰው ልጆች የተሰራ ነገር እንደመሆኑ የራሱ የሆነ መልካም ገጽታ እና ስጋት አለው። በመጥፎ
ሰዎች እጅ ከገባ እና ለመጥፎ አላማ ከዋለ ቀላል የማይባል ጉዳት ያስከትላል።
በቅርብ ጊዜ በGoogle ካምፓኒ የበለጸገ የFace Recognition ቴክኖሎጂ የጥቁር አሜሪካዊያንን ፎቶ የዝንጀሮ ነው በማለቱ
ትልቅ ክርክር አስነስቶ ነበር። ለዚህም ምክኒያቱ ደግሞ የቴክኖሎጂው ችግር ሳይሆን ሶፍትዌሩን ያበለጸጉት ሰዎች ለሲስተሙ
እንዲማር የሰጡት የሰዎች ፎቶ የነጮችን ብቻ በመሆኑ ነው። ሆን ተብሎ ይሁን አይሁን ሌላ አከራካሪ ጉዳይ ቢሆንም ለማሽኑ
እንደሚገባ ብዙ አይነት ዳታዎችን ከሰጠነው ደግሞ በሚገባ ተምሮ የትኛው መልክ የማን እንደ ሆነ መለየት ይችላል። እንደዚህ
አይነት በተለይም ዘር እና ቀለም ተኮር መገለል እንዳይከሰት ለማድረግ ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ ዶክተር ትምኒት ገብሩን
ጨምሮ ብዙ የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች Black In AI የሚል ድርጅት አቋቁመው ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ከዚህ ባለፈም የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ መስፋፋት ብዙ ስራዎችን ሊያስቀር ይችላል። ይህም የብዙ ሰዎችን የስራ እድል
ሊዘጋ እንደሚችል ግልጽ ነው። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምክኒያት ደግሞ ሌሎች ብዙ
አይነት የስራ እድሎች ይከፈታሉ። ስለዚህ ዋናው ነገር ዘመኑን አውቆ በወቅቱ ወደእ ሚያዋጣው ዘርፍ መዞር እና አስቀድሞ
ያሉትን ስራዎች በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ማዘመን ነው። ይሄ ያለ እና የንበረ የህይወት ሂደት ነው። ዘመናዊ ትምህርት ቤት
ባልነበረበት እና ፊደል መቁጠር የሚችሉ ሰዎች ቁጥር እጅግ ውስን በነበረበት ጊዜ ለሰዎች ደብዳቤ በመጻፍ ገቢ ማግኘት
ይቻል ነበር። አሁን ላይ ዘመናዊ ትምህርት በመስፋፋቱ ያ ስራ አያዋጣም። ስለዚህ የኮምፒውተር የጽህፈት አገልግሎት
መስጠት ጥሩ አማራጭ ይሆናል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የግል ኮምፒውተር ያለው ሰው እየበዛ ሲሄድ ደግሞ ይህንን መንገድ ትቶ
ሌላ የተሻለ አማራጭ መከተል ግድ ይላል።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በኢትዮጲያ
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በኢትዮጵያ የኮምፒተር ኢንጂነሪንግ እና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ውስጥ ተካቶ በዩንቨርሲቲ ደረጃ
ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪም ኦንላይን የሚገኙ ትምህርቶችን በመከታተል በግላቸው የእውቀት አድማሳቸውን እያሳደጉ ያሉ
ወጣቶች አሉ። በመንግስት ደረጃም ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በዚህ መስክ ላይ ያደረገ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ማዕከል በ
ዓ.ም ተመርቆ ስራውን ጀምሯል። በቅርቡ የሳውዲ አረቢያ ዜግነት የተሰጣት ሶፊያ የተባለችው ሮቦት ላይም የውስጥ ሲስተሟን
በመስራት ተሳትፎ ያደረጉ iCogLabs የሚባል የሶፍትዌር ድርጅትን አቋቁመው እየሰሩ ያሉ ወጣት ኢትዮጲያዊያንም ለሌሎች
በዘርፉ መስራት ለሚፈልጉ ወጣቶች እንደምሳሌ የሚታዩ ናቸው።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ለኢትዮጵያ?
ምናልባት አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በጣም የተራቀቁ ስራዎችን ማድረግ መቻሉ እንደኛ ሀገር ላሉ እንደ ቅንጦት ሊታሰብ

10 months, 3 weeks ago

ሰውሰራሽ ክህሎት (Artificial Intelligence)

በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ እንደ ተአምር በሌሎች እንደ ትንግርት በተቀሩት ደግሞ እንደ ትልቅ ሰው ሰራሽ የወደፊቱ የምድር
ፈተና ይታያል። አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ። የበሽተኞችን መረጃ ከመመዘን እስከ መድሀኒት መቀመም ፣ ሰዎችን ከማዝናናት
ትልልቅ ቀዶ ጥገናዎች እስከ ማካሄድ እንዲሁም በደህንነት ዘርፍ ፣ በንግድ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በመዝናኛ አርቲፊሻል
ኢንተሊጀንስ ያልዳሰሰው የሰው ልጅ እንቅስቃሴ የለም። ከምናስበው በላይ ኤአይ አጠገባችን ደጃችን ያንም አልፎ ጓዳችን
አልፏል። በርግጥ አንዳንድ ሰው ስለ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ሲነሳ ሮቦቶችን ብቻ ያስባል። ሮቦቶች በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ
ታግዘው ለተሰሩበት አላማ ይውላሉ ግን አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በሮቦቲክስ ብቻ የተገደበ አይደለም። ይልቁንም ዘርፈ ብዙ
መስኮችን የሚዳስስ እና በተለያዩ አማራጮች ተግባር ላይ የሚውል ነው። ማንኛውም ስማርት ስልክ ያለው ሰው ቢያንስ
የፌስቡክ ፣ የዩትዩብ ወይም የጎግል ብሮዘር ተጠቃሚ ነው። እነዚህን አማራጮች በመጠቀም መረጃ ሰርች ያደረገ፣ ፍሬንድ
ሪኩዌስት የላከ፣ ቪዲዮ ያየ ብዙ ሰው ነው። ስልኩን በጣት አሻራ (Finger print) ወይም በፊት መለያ (Face Recognition)
የቆለፈውን ደግሞ ቤቱ ይቁጠረው። ይሄ ሁሉ ሰው አወቀውም አላወቀዉም ባንድም በሌላ መንገድ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ
ተጠቃሚ ነው ማለት ነው።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሰው ልጆች ህይወት ጋር እየተቆራኘ በብዙ ዘርፎች ውስጥ እየገባ ይገኛል። እጅግ
ብዙ መልካም የሆኑ እድሎችን ይዞልን ቢመጣም በአግባቡ ካልተጠቀምነው ደግሞ የሚያስከትለው ችግር እንዳለ ግልጽ ነው።
እንግዲህ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን ተፈላጊነት እና ተግባራዊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄድ ልናስቀረው የማንችለው
ነገር እንደመሆኑ እሱም እኛ ጋር ሊሰነብት እንደመምጣቱ እሱን እንዴት እንደምናጠና፣ በምን አግባብ ተግባር ላይ
እንደምናውለው፣ በምን መልኩ ለሰው ልጆች ጥቅም ብቻ እንዲውል ማድረግ እንደምንችል ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ
ነው። በተለይም እንደኛ ሀገር ባሉ ለማደግ በሚታትሩ የሰው ልጅ ኑሮ፣ የህክምና መሳሪያዎች በውስንነት በሚገኙበት፣
ትምህርት በጥራት ባልተስፋፋበት፣ ግብርናው እጅግ ኋላ ቀር በሆነበት፣ የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጥፍ በሚያድገበት
ሀገር እንዲሁም የምግብ ዋስትና ባልተረጋገጠበት ሀገር ያለውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እና የመካከለኛ ገቢ ካላቸው ለመሰለፍ
የተቀረው የአለም ክፍል ዛሬ ላይ ለመድረስ የሄደበትን መንገድ መከተል እጅግ አድካሚ ከመሆኑም በላይ በእሳት የመጫወት
ያህል ዘመኑን ያላመዛዘነ ነው የሚሆነው።
ታዲያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምንድን ነው?
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ የአማርኛ አቻ ትርጉሙ ሰው ሰራሽ ክህሎት ማለት ሲሆን በኮምፒውተር ሳይንቲስቶች እና ሶፍትዌር
ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች ዘንድ ኤአይ በመባል ባጭሩ ይጠራል። ኮምፒውተሮች ከተሰሩበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊው መረጃ
ይሰጣቸው እና እሱን ኮምፒውት በማድረግ አስፈላጊውን ውጤት ያሳያሉ። ምንም እንኳን ፈጣን፣ ተአማኒ፣ ጊዜ ቆጣቢ
ቢሆኑም ነገር ግን ለረዥም ጊዜያት ያህል የኪምፒውተሮች ድክመት ተደርጎ የሚቆጠረው የራሳቸው የሆነ ክህሎት ወይም
Intelligence የሌላቸው መሆኑ ነበር። አሁን ግን ይሄ ነገር ታሪክ ሆኗል። ስማርት ስልኮች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ ስማርት መኪኖች
even ስማርት ቤቶች በዙሪያችን አሉ።
የሰው ልጆች በተፈጥሮ የተቸረን ነገሮችን የመገንዘብ፣ የማስተዋል እና ካየነው ነገር የመማር ችሎታ አለን። ይህን ክህሎት
ኮምፒውተሮች እንዲኖራቸው ማስቻል ሰው ሰራሽ ክህሎት (Artificial Intelligence) ይባላል። የሰው ሰራሽ ክህሎት ያላቸው
ማሽኖች አካባቢያቸውን በመቃኘት የተሰጣቸውን አላማ ለማሳካት እርምጃ ይወስዳሉ።
AI ተግባራዊ የሆነባቸው መስኮች
በንግድ
አንዳንዴ ገርሟችሁ አያውቅም እናንተ ከገዛችሁት እቃ ጋር አብሮ የሚሄድ ምርት ወይም እናንተ በልባችሁ ለመግዛት ስታስቡት
የነበረው ነገር ፊታችሁ ላይ አንድ ሲስተም ሲያቀርብላችሁ? ይሄ አስማት ወይም የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። ይልቁንም የሰው
ሰራሽን ክህሎት በመጠቀም የሚሰራ Recommendation System ነው። በዚህ ሲስተም ኦንላይን ባሉ የመገበያያ አማራጮች
ተጠቅማችሁ በምንሸምቱበት ጊዜ ለናንተ የሚሆኑ ምርቶችን ያቀርብላችኋል። ይህም የሚሆነው ከዚህ በፊት ሰርች
ያደረጋችኋቸውን ፣ የገዛችኋቸውን እና ፍላጎታችሁን በማጤን እና በማዛመድ ነው። ይሄም ከኋላው የማቲማቲክስ ቀመሮችን
እንዲሁም እንደ Collaborative filtering ያሉ የMachine Learning ዘዴዎችን በመጠቀም ተግባር ላይ ይውላል። ይሄ
መንገድ ደንበኞች የሚፈልጉትን ነገር በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ነጋዴዎችም ምርታቸው ወደሚፈልገው ሰው በቶሎ
እንዲደርስላቸው እና ብራንዳቸውንም በደንብ ለማስተዋወቅ ይረዳል።
በትምህርት
በርግጥ የትምሀርት መስክ ከጥንት ጀምሮ በሰው ልጆች የተቀረጸ እና እየተተገበረ ያለ ትልቅ መስክ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስም እጁን እያስገባበት ይገኛል። ከመምህራን በኩል ብንመለከት የውጤት አሰጣጥ እና አደማመር ላይ፣
ትምህርት ቤትም ተማሪዎችን ለመመዝገብ፣ ውጤታቸውን ለማቀናጀት፣ የመምህራንን እና ሌሎች ሰረተኞቻቸውን ደሞዝ
ለማስላት፣ የትለያዩ ትምህርቶችን ተማሪዎች የትም ቦታ ሆነው ለመከታተል እንዲችሉ ለማድረ እየጠቀመ ይገኛል። ከዚህ
ባለፈም እንደ Voice Assistant ያሉ featureሮችን በመጠቀም መምህራን እንኳን ባይኖሩ በእነዚህ ድምጾች በመታገዝ
ተማሪዎች በቀላሉ ለማጥናት እንዲችሉ እድልን ፈጥሯል። ትንሽ ከተለመደው ወጣ ያለ እና የሚያስገርም AI በትምህርቱ
መስክ ያሳረፈው አሻራ ደግሞ ተማሪዎች ምን ያህል ትምህርት እየተከታተሉ እና እየተረዱት እንደሆነ የሚመዘግብ እና
ለመምህራን የሚያሳውቅ ቴክኖሎጂ ነው። ይሄ ቴክኖሎጂ የበለትደገው በቻይናዊያን ሲሆን Xian Jiangnan በሚባል ትምህርት
ቤት ውስጥ ተማሪዎች ራስ ላይ የሚጠልቅ ባንድ በማድረግ ተሞክሮ ነበር። ማን እየተከታተለ እንደሆነ፣ የማን ትኩረት ደግሞ
ሌላ ቦታ እንደሆነ ለምምህራንም ጠቁሟል። ይህም መምህራን የተማሪዎቻቸውን ትኩረት ሰብስበው እንዲያስተምሩ እና ወደ
ኋላ የሚቀር ተማሪ እንዳይኖር ረድቷል።
በጤና
በጤናው መስክ አንዳንድ በሽታዎች ከመከሰታቸው በፊት ያላቸውን ምልክቶች በማየት ምርማ ለማካሄድ እና ቅድመ ጥንቃቄ
በማድረግ በሽታው እንዳያድግ እና ከቁጥጥር እንዳይወጣ ይጠቅማል። በተለይም የካንሰር ሴሎች ሳያድጉ እና ሳይስፋፉ
ለመለየት በእጅጉ ይረዳል። በሽታዎችን ከመለየት አልፎ መድሀኒቶችን በመቀመም ሂደት ላይ የሚደረጉ ጥናቶች ትክክለኛ
የሆነ ስሌቶችን እንዲያካሂዱ ያግዛል። ከዚህ ባለፈም ውስብስብ የሆኑ እና ረዣዥም ሰዓት የሚወስዱ ቀዶ ጥገናዎችን
ያደርጋል። በተለያየ መንገድ የተለያየ የሰውነት ክፍላቸውን ያጡ ሰዎችም እንዳይቸገሩ እቃዎችን በማቅረብ በማገዝ እንዲሁም
ደግሞ ለሰዎቹ በመገጠም እንደ እጅ እና እግር በመሆን ያገለግላል።
በግብርና
እንደ Computer Vision ያሉ የAI አገልግሎቶችን በመጠቀም ሰብሎች እና አፈር ላይ ችግር ካለ ለመመርመር እና ለማከም
ይጠቅማል። እንዲሁም እየበቀሉ ያሉ አረሞች ካሉ እነሱን ለመለየት ያግዛል። ከዚህ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጦችን አስቀድሞ

10 months, 3 weeks ago

። ቀለማት ለእናንተ ምን ናቸው? ከቀለማት ሁሉ የምትወዱት ቀለም የትኛው ነው?
ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን።

10 months, 3 weeks ago

የቀለማት ከምድር ገጽ ቀስ በቀስ መጥፋት

እስቲ በዙሪያችሁ ያሉ የተለያዩ ህንጻዎችን፣ መኪናዎችን እና መገልገያ መሳሪያዎችን ለማጤን ሞክሩ። በእርግጠኝነት
ተፈጥሮአዊ ከሆኑ ነገሮች ውጭ ያሉ በዙሪያችሁ ያሉ ነገሮች ልብሳችሁን ጨምሮ በብዛት ጥቁር ፣ ነጭ ወይም ብረታማ ቀለም
ያላቸው ናቸው። ምናልባትም ጊዜን ወደ ኋላ ተጉዘን ለመመልከት ብንችል እና የዛሬ 300 ወይም 400 አመታት ብንመለስ
አካባቢያችሁን ከአሁኑ በተሻለ በቀለማት አሸብርቆ እናገኘዋለን። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየወጡ ያሉ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት
ቀለማት ከምድረ ገጽ ቀስ በቀስ እየጠፉ ነው። ለዚህም ምክኒያቱ የአየር መበከል ወይም የተፈጥሮ አደጋ አይደለም። ይልቁንም
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሰው ልጆች ቀለማትን ከመጠቀም ራሳቸውን እየቆጠቡ ይገኛሉ።
በጥንት የሰው ልጅ ስልጣኔ ታላላቅ ከተሞች በህብር ቀለማት የተዋቡ እና ያሸበረቁ ነበር። እያንዳንዱ ከተማም ሲገባ የራሱ
የሆነ መታወቂያ መልክ ያለው እስኪመስል ድረስ የራሱ የሆነ የሕንጻ ኪነ ጥበብ እና የቀለም አጠቃቀም ነበረው። ወደ አሁኑ
ዘመን ስልጡን ከተሞች ስንመጣ ግን ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ወደ አንድ አይነት የህንጻ አሰራር እና ቀለም እየመጡ
ነው። በሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች እየተሞሉ ለህንጻዎቻቸውም ግራጫ እና ብረት ቀለማትን ይመርጣሉ። በጥንት እና በአሁን
ዘመን ያለው ልዩነት እጅግ ግልጽ ነው። አድዲስ በማደግ ላይ ያሉ የላቲን አሜሪካ እና የአፍሪካ ከተሞችም የራሳችቸውን
ጥንታዊ ስልጣኔ እና የአባቶቻቸውን ፈለግ በመተው የምዕራባዊያንና የዱባይን መልክ ለማምጣት ሲሯሯጡ ይግኛሉ።
ወደ ድርጅቶችም ስንመጣ በፊት ከነበራቸው በቀለማት የተዋበ ሎጎ ይልቅ ጥቁር ወይም ግራጫ የሆነ ቀለምን ምርጫቸው
እያደረጉ ነው። ከእነዚህም መካከል አይ.ቢ.ኤም (IBM) እና Appleን መውሰድ እንችላለን። በርግጥ የአብዛኛዎቹ ድርጅቶች
ሎጎ መቀየር ምክኒያት በብዙ ሀገራት ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ለማሳደግ እና ቀለማት ከሀገር ሀገር የተለያየ ትርጉም
ስለሚሰጣቸው በተቻለ መጠን አብዛኛው ሰው ጋር የሚስማማውን ቀለም ለመምረጥ ከሚል እሳቤ ነው። በፊት በቀይ እና
ቢጫ ቀለማት ይዋብ የነበረው የማክዶናልድስ (MacDonald’s Burger) በርገርም ሱቆቹ አሁን በጥቁር ተተክተዋል። በግለሰብ
ደረጃም ብንመለከት የሰዎች የግል መኪኖች ቀለማት በብዛት ግራጫ እና ጥቁር ናቸው። ከዚህ አለፍ ሲልም ነጭ ናቸው።
ታዲያ ከዚህ ሁሉ ተነስተን አለም ከህብር ቀለማት ወደ ነጭ እና ጥቁርነት እየሄደች ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ታዲያ ቀለማት ቢጠፉ ይህንን ያህል ሊያሳስበን ይገባል?
ከምታስቡት በላይ ቀለማት ለእኛ ሰው ልጆች እጅግ ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው። ቀላል ከሚመስለው ጥቅማቸው ብንነሳ
ቀለማት የሰውን ስሜት የመቀየር ትልቅ አቅም አላቸው። የተጨነቁ ሰዎች የደስታ ስሜትን የሚፈጥሩ ቀለማትን ሊያገኙ
የሚችሉበት እድል ሲፈጠርላቸው ከጭንቀታቸው ቀስ በቀስ ለመልቀቅ ይችላሉ። ለዚህም ምክኒያቱ ቀለማት የደስታ ስሜትን
የሚፈጥረው ዶፓሚን (Dopamine) የተሰኘ ሆርሞን እንዲለቀቅ ወደ ሰውነታችን ስለሚያደርጉ ነው። እንደ ሰማያዊ እና ነጭ
ያሉ እርጋታን እና ሰላምን የሚሰጡ ቀለማት ደግሞ ሰዎች ከድካም ስሜታቸው እረፍት እንዲያገኙ እና የሰላም እንቅልፍ
እንዲተኙ ለማድረግ ትልቅ ሚና አላቸው።
ከዚህ ባለፈ ቀለማት ሰዎች ባህላቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልጹባቸው መንገዶች ናቸው። ለምሳሌ ለፈረንሳይ ህዝቦች
ከfrench revolution ወዲህ መታወቂያቸው ለሆነ እና እንሞትለታለን ለሚሉት አቋማቸው “ነጻነት ፣ እኩልነት እና
ወንድማማችነት” ወይም እነሱ እንደሚሉት “ሊበሪቴ ፣ ኢጋሊቴ፣ ፍራተርኒቴ” (Liberté, égalité, fraternité) መለያ የሚሆኑ
ሰማያዊ ነጭ እና ቀይ ቀለማትን ይወዳሉ። በሰንደቅ አላማቸው፣ በቤታቸው እና ዋና ዋና መንገዳቸው ላይ ይጠቀሙታል።
በአፍሪካ ሀገራት ዘንድም የአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት ትልቅ ትርጉም አላቸው። የነጻነት እና የቅኝ አገዛዝ ተቃውሞ
ምልክት ናቸው። ከዚህ ባለፈም ለተለያዩ ቤተ እምነቶችን እና የሀይማኖት ተቋማት ቀለማት የተለያየ ትርጉም እና ቦታ
አላቸው። ከዚህ የተነሳ ቀለማት ከሰው ልጆች ባህል እና ማንነት ጋር የተቆራኘ ህብረት እንዳላቸው ግልጽ ነው።
የተለያዩ የጥንት ጽሁፎች እና ታሪኮች እንደሚያመላክቱት በተለይም ከክርስቶስ ልደት 2000 አመታት በፊት በጥንታዊ ግብጽ
እና ቻይና ቀለማት ለህክምና ይውሉ ነበር። በአሁኑ ጊዜም ቢሆን እንደ አርት ቴራፒ (Art Therapy) እና ክሮሞቴራፒ
(Chromotherapy )ያሉ ህክምናዎች በጭንቀት ውስጥ ላሉ ህሙማን ቀለማትን በመስጠት እንዲስሉ፣ እንዲቀቡ እና
ከቀለማት ጋር እንዲጫወቱ በማድረግ ሰዎችን ከተለያዩ የአዕምሮ ጭንቀቶች ፋታ እንዲያገኙ ለማድረግ ያገለግላሉ።
ቀለማት ስለነገሮች ያለንን እይታ በጣም ይለውጣሉ። እቃዎችን የመለየታችንን ሁኔታ ላይም ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ለምሳሌ ኮካ
የሚባለው ስም ሲጠራ ቶሎ ብሎ ወደ አዕምሯችን ቀይ ቀለም ይመጣል። ከዚህም በመነሳት ቀለማት አንድን ብራንድ
እንድንለይ በማድረግ በንግዶች ላይ ትልቅ አሻራ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም በምንገዛው ልብስ እና በምንበላው ምግብ
ቀላል የማይባል ድርሻ አላቸው።
እንደ ቀይ ያሉ ቀለማት ደንበኞች የምግብ ፍላጎታቸው ከፍ እንዲል በማድረግ ቶሎ ቶሎ እንዲመገቡ ያደርጋሉ። ቀይ ቀለማት
ለረዥም ጊዜ ሲቆዩ እረፍት ስለሚነሱ ደንበኞች የሚፈልጉትን ተመግበው ለሌሎች ደንበኞች ቦታ ይለቃሉ። ይሄ
በሬስቶራንቶች እና በተለይም እንደ ፋስት ፉድ አይነት አገልግሎት በሚሰጡ ምግብ ቤቶች ዘንድ ይዘወተራል። እንደምሳሌም
ፒዛ ሀት እና ኢንጆይ በርገርን ማየት በቂ ነው። ታላላቅ የሆኑ ሆቴሎች ደግሞ በመጋረጃ፣ በብረቶች እና በህንጻቸው ላይ
ወርቃማ ቀለማትን ይጠቀማሉ ይህም ቅንጡነት እና ሀብትን የሚያሳይ በመሆኑ ሀብታም እና ዝነኛ ሰዎች ያዘወትሯቸዋል።
ከዚህ አለፍ ሲልም ቀለማት ውሳኔዎቻችንን የመለወጥ አቅም አላቸው። አንዳንድ ቀለማት ልክ ስናያቸው በኛ ዘንድ ተቀባይነት
የሌላቸው በመሆኑ ምንም እንኳን እቃው ጥሩ ቢሆንም የቀለሙ ጥሩ አለመሆን ሳንገዛው እንድንቀር ያደርጋል። ወደ አንዳንድ
ሱቆች ለመሄድ እግራችን ሲፈጥን አንዳንዶቹን ለማየት እንኳን ያስጠላናል። ይህም የቀለም ውጤት ነው። አንዳንድ ቀለማት
ጭንቀትን ሲፈጥሩ የተቀሩቱ የተስፋን እና ሀሴትን መንፈስ ይፈጥራሉ።
ሆኖም ግን ቀለማት በባህሪያቸው መጥፎ ብቻ ወይም ጥሩዎች ብቻ አይደሉም። እንደየአገባባቸው እና አጠቃቀማቸው የተለያየ
አንድምታ አላቸው። ለምሳሌ ጥቁር ቀለምን ብንመለከት አንዴ የጨለማ፣ የባዶነት፣ የጭካኔ እና የሀዘን መልዕክት ሲኖራቸው
ሌላ ጊዜ ደግሞ የደስታ (የሰርግ እና የምርቃት) ፣ የመንግስታዊ እና ቢዝነስ ተቋማት መሪዎች ልብስ በመሆን የልህቀት ምልክት
ይሆናሉ። ቀይ ቀለምም በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ የቁጣ እና ደም የማፍሰስ ምልክት በአንጻሩ ደግሞ የፍቅር እና
የመስዋዕትነት ምልክት በመሆንም ያገለግላል።
እንግዲህ ቀለማት ከህክምና፣ ከንግድ እና ከሰው ልጆች ደስታ ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዳላቸው ካየን ቀለማት ለሰው ልጆች
አስፈላጊ ነገሮች መሆናቸው እሙን ነው። ታዲያ ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ ሰዎች የቀለማት አጠቃቀማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ
ቀለም የለሽነት እየሄደ መሆኑ አሳሳቢ ነው። ስለዚህ ቀለማትን በጥበብ ለሰው ልጆች ጥቅም መጠቀም የተሻለ አማራጭ ነው

10 months, 3 weeks ago

በምትነጋገሩበት ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ችግር ላይ ብቻ አተኩሩ።ትንሽ አለመግባባት ሲፈጠር የከረመና ከዚህ በፊት የተፈጠረ ነገር ባነሳችሁ ቁጥር አለመግባባቱን ለመፍታት አስቸጋሪ ያደርገዋል። እነዚያን የተደራረቡና የቆዩ ችግሮችን በአንዴ መፍታት ስለማይመች በአንድ ጊዜ አንድን ችግር ብቻ ነጥላችሁ አውጥታችሁ፣ የችግሩን መንስኤ ለይታችሁ መፍትሄ ለማበጀት ሞክሩ።
እንደ አለቃ ወይም እንደ መምህር ጮክ ብላችሁ ስታወሩ አጋራችሁ ጆሮ ባይሰጣችሁ አይድነቃችሁ። ይሄ አይነቱ አነጋጋር እና ድምጸት እነሱን ከማናደድ ውጪ ምንም አይጠቅማችሁም። ጥያቄያችሁ በትህትናና ግልጽ በሆነ መንገድ አቅርቡ እነሱምእንዲመልሱላችሁ እድሉን ስጧቸው። እናንተም መልስ ስትሰጧቸው አለቃ መስላችሁ አትታዩ። መረጃ ስጧቸው እንጂ ምክራችሁን እስካልጠየቁ ድረስ አትምከሯቸው። ለምሳሌ “ሰዎች የሚሰሩትን ነገር ሲወዱት ውጤታማ ይሆኑበታል” የሚለው አነጋገር ለሰሚው የውሳኔ ምርጫን ይሰጣል ነገር ግን “ስራህን ይሄን ያህል የምትጠላው ከሆነ ለምን አትተወውም” የሚለው አነጋገር ደግሞ ትዕዛዝ ነው የሚመስለው።
ነገሩ ላይ እንጂ አጋራችሁ ላይ አታተኩሩ
ሰዎችን “ዘልዛላ” ብላችሁ ብትጠሯቸው በጣም ታናድዷቸዋላችሁ።  እነሱም በሌላ ስድብ ሊመልሱላችሁ ይችላሉ። ይቺ እንደቀላል የተጀመረችው ነገር ደግሞ እየተባባሰች ወደ ትልቅ ግጭት ሊያመራችሁ ይችላል። ለምሳሌ የትዳር አጋራችሁ ልብሳቸውን ወንበር ላይ እንዳይከመሩና በአግባቡ አጣጥፈው እንዲያስቀምጡ በግልጽ አማርኛ ብትነግሯቸው። በእሺታ ይመልሱላችሁና ለነገሩ አስፈላጊውን ትኩረት በመስጥጠት ይሄንን ልማዳቸውን ለማስተካከል ጥረት ያደርጋሉ። አያችሁ አይደል አንድ ችግር ወይም ስህተት አይታችሁ እንዲያስተካክሉት ከፈለጋችሁ ችግሩ ላይ ብቻ አተኩራችሁ ስለዛ ነገር መነጋገር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ? በአንጻሩ ደግሞ ከችግሩ ተነስታችሁ አጋራችሁ ላይ ትኩረት በማድረግ አጋራችሁን ከችግሩ ጋር አያዛመዳችሁ ስም መስጠት አለመግባባትን ከማባባስ ውጪ ትርፍ የለውም። አንቺ አርፋጅ ነሽ ከማለት ዛሬ በማርፈድሽ ቅር ብሎኛል ይሄንን ነገር አስተካክይ ማለት ትህትናን የተላበሰ ከመሆኑ አልፎ አጋራችሁ ነገሩን ለማስተካከል እንድትነሳ ያደርጋል። የመጀመሪያው አነጋገር ግን ለግጭት ነው የሚጋብዘው።
መቼም ቢሆን ስተነጋገሩ አውቃለሁ አውቃለሁ አትበሉ። ይሄ አይነቱ ባህሪ እናንተ ጋር ካለ ጊዜ ወስዳችሁ ልታስተካክሉት ይገባል። ምክኒያቱም ከአጋራችሁ ጋር ብቻ ሳይሆነ ከሌሎች ጋር ስትኖሩ የሰዎችን ሀሳብ መስማትና ማክበር መቻል እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ስለምታውቁት ነገር እያወሩ ቢሆን ሰዎች ስለአንድ ነገር የተለያየ እይታ ስላላቸው እናንተ ነገሩን ካያችሁበት የተለየ እይታ ሊኖራቸው ይችላል። እይታዎቻቸውን ደግሞ ልብ ብላችሁ ልታደምጧቸውና ልታከብሩላቸው ይገባል።
ቶሎ ወደ ድምዳሜ አትድረሱ
ሰዎች ምን እያሰቡ እንደሆነና ምን ለማለት እንደፈለጉ በራሳችሁ ቶሎ ወደ ድምዳሜ አትሂዱ። እንደዚህ ማድረጉ ከሰዎች ጋር ያላችሁን መስተጋብር ከማመሳቀል በላይ ለጤናችሁ በጣም ጎጂ ነው። በመሆኑም እንደዚህ አይነቱን ባህሪ ልታቆሙ ይገባል። አስታውሱ ከዚህ በፊት እንደዚህ ይሆናል ብላችሁ የሰጋችሁባቸው ነገሮች ሁሉ እንደፈራችሁት ሳይሆን ለመልካም ተለውጧል። ስለዚህ እናንተን ስለመሰላችሁ ብቻ አጋራችሁ ለማለት የፈለገውንና ያሰበውን በራሳችሁ አትደምድሙ።


የሚያስማማችሁን ምክኒያቶች ፈልጉ
እናንተም ሆነ አብረዋችሁ ያሉ ሰዎች በጣም ተናዳችሁ እየተነጋገራችሁና ግጭታችሁ ከፍተኛ ውጥረት ላይ እንኳን ቢሆን የሚያስማማችሁን አንድ ነገር ፈልጉ። “አዎ” “ልክ ነው” ስትሉ ያ ሰው በናንተ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳለው እንዲሰማቸው ያደርጋል። ስለዚህ የጋራ የሆኑና የሚያስሟሟችሁ ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረኛ በመደማመጥ በመሀላችሁ ያለውን ነገር ለማረጋጋት ትችላላችሁ።
የገጠማችሁን ወቅታዊ ሁኔታ ከድሮ አጋጣሚያችሁ ጋር በማያያዝ በድሮው መነጸር አትዩ። በተልይም ደግሞ አሁን አብራችሁት ካለው ሰው በፊት በፍቅር ውስጥ ከነበራችሁ አሁን አብሯችሁ ያለውን ሰው ከድሮዎቹ ጋር አታስተያዩ። በድሮዎቹም እይታ ይሄኛውን ሰው አትገምግሙ።
ማስታወሻ ጻፉ
አለመግባባት በሚፈጠርበት ጊዜ  ዲያሪ ወይም ማስታወሻ መጻፍ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ፍርሀታችሁን ስሜታችሁን ሀሳባችሁን በዝርዝር አስፍሩ። የተሰማችሁን ነገር መፃፍ ጭንቀትን ለማቃለል እጅግ በጣም ይጠቅማል።  የተሰማችሁን ነገር በምትጽፉበት ጊዜ ምክኒያታዊና ተንታኝ የሆነውንበስተግራ በኩል ያለውን የአዕምሯችሁን ክፍል ያነቃቃል።  ይሄም በስተቀኝ በኩል ያለውንና ስሜታዊ የሆነውን የአዕምሯችሁን ክፍል ያረጋጋዋል። ከፈለጋችሁ በምትጽፉበት ጊዜ ጽሁፉን ላናደዳችሁ ሰው እንደምትልኩት ደብዳቤ አድርጋችሁ መጻፍ ትችላላችሁ። ምናልባትም አለመግባባቱ በተፈጠረበት ጊዜ ለመናገር ያልቻልችሁትን ነገር ልታሰፍሩበት ትችላላችሁ።
የሌሎች ሰዎችን እሴቶች አክብሩ
ከሰዎች ጋር በተመሳሳይ ነገር በተደጋጋሚ እየተጋጫችሁ ከሆነ ምናልባትም ለነገሮች ያላችሁ እሴት ወይም ዋጋ ልዩነት አለው ማለት ነው። ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ እንዳትግባቡ በሚያደርጋችሁ ነገር ላይ ከሰዎች ጋር በግልጽ ተነጋገሩበት። ምናልባትም ይሄ ነገር ከአስተዳደጋችሁ ልዩነት የተነሳ የመጣ ይሆናል። ሁሉም ሰው ያደገበት መንገድ የተለያየ ስለሆነ እናንተም ስታድጉ ወላጆቻችሁ ያስተማሯችሁ ነገሮች እያስተማሯችሁ ያሳደጓችሁና እነዚያም ሰዎች ያደጉበት መንገድ ይለያያል። ከዚህ የተነሳ ለገንዘብ፣ ለህይወት ፣ ለስራ እናለሌሎች ነገሮች የምትሰጡት ክብደት ሊለያይ ይችላል። በርግጥ ሰዎች ስለነገሮች ያላቸውን እይታ ወይም እሴት ማስቀየር ቀላል ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ልዩነቶችን በመረዳትና በማክበር ወደ መግባባት መምጣት ይቻላል።
አንዳንድ ጊዜም ሁሉንም ሰው ሊያስማማ የሚችል መፍትሄ ላይገኝ ይችላል። እንደዚህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥማችሁ ጊዜ ላለመስማማት መስማማትን መልመድ አለባችሁ። ያለው አማራጭ ነገርን መቀበልና ማለፍ ነው። ምክኒያቱም በእያንዳንዱ ነገር የግድ ሙሉ በሙሉ ልትስማሙና አንድ አይነት አቋም ይኖራችሁ ዘንድ ግዴታ አይደለም ነገሩ ዋና እና መሰረታዊ ጉዳይ አስካልሆነ ድረስ።
ምንጊዜም ቢሆን አለመግባባት ተፈጥሮ እሱን በእርቅ ከፈታችሁና ከተሰማማችሁ በኋላ በጋራ ጥሩ ጊዜ አሳልፉ። መታረቃችሁን አስመልክቶ አክብሩ ፣ አንድ ላይ ፊልም ማየት ውወይም ወጣ ብሎ መዝናናት ወይም ሌላ የሚያስደስታችሁን ነገር አብሮ በማድረግ መታረቃችሁን አክብሩ።

10 months, 3 weeks ago

ግጭትን መፍታት
ሰዎች ከራሳቸው ጋር፣ ከሌላ ሰው ፣ ከፍጥረት ጋር እንዲሁም ከፈጣሪ ጋር ይጋጫሉ። ከራሳቸው ጋር አቅደው ያላሳኩትን ነገር እያሰቡ፣ ያደረጉትን የተሳሳተ ውሳኔ እያነሱ እንዴት ይሄንን አደርጋለሁ በሚል ስሜት ከራሳቸው ጋር ይጋጫሉ። ከሌላ ሰው ጋር በትንሹም ሆነ በትልቁ አለመግባባት ይፈጠራል። ከዚህም አልፎ ምንም ከማይናገሩ ግዑዛን አካላት ጋር ሊጋጩ እና ያገኙትን ነገር ሁሉ ላይ ሊያማርሩ እና ሊያወድሙት ይነሳሉ። ስለደረሰባቸው ክፉ አጋጣሚዎች በማሰብ እና በማማረርም ከፈጣሪያቸው ጋር ይጋጫሉ። ከዚህ ሁሉ የምንረዳው ግጭት ማለት በሰው ህይወት ውስጥ ያለ ነገር መሆኑን ነው። ታዲያ ግጭት በብልሀት ካልተፈታ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። አንድ ሰው እጅግ ሀብታም እና የተሳካለት የሚባል ሰው ቢሆንም ግጭትን የሚፈታበት ጥበብ ከሌለው ያለውን ነገር ሁሉ ዜሮ ሊያደርገው ይችላል። ታዲያ ግጭትን እንዴት በጥበብ መፍታት ይቻላል?
ከማንኛውም ሰው ጋር የገጠማችሁን አለመግባባት በቀላሉ ለመፍታት የምትፈልጉ ከሆነ በምትነጋገሩበት ጊዜ ከባባድ የሆኑ እና በሰው ላይ ፈራጅ የሚያስመስሏችሁን አትናገሩ። ”መልካም” “ጥሩ ነው” የሚሉትን ቃላት ከመጠቀም ይልቅ ደግሞ “ተመችቶኛል” ፣ “ወድጄዋለሁ” የሚሉትን ቃላት ተጠቀሙ። ምግቡ አይጣፍጥም ወይም መጥፎ ነው ከማለት ይልቅ ደግሞ ምግቡን ያልወደድኩት ትንሽ የማቃጠል ስሜት ስላለው ነውብትሉ በጭፍኑ አጋራችሁን እየተቃወማችሁ ሳይሆን እውነትም ምግቡ ጣፋጭ እንዳልነበረ ያሳያል። ትክክል ነው ወይም አይደለም የሚሉትን ቃላትም ስምምነትን ወይም አለመስማማትን በሚያመላክቱ ቃላትና ሀረጋት ብትተኩ ይመረጣል። “እውነቱ እኮ” የሚለውን ቃል ተውና ቀጥታ ወደ ጉዳያችሁ ግቡና ሀሳባችሁንም በግልጽ ተናገሩ።
አንድ ነገር ስትጠይቁም በፍቅርና በትህትና ይሁን። ሰዎች እኮ ምግብ ከበሉ በኋላ የበሉበትን ያጥባሉ ብሎ በአሽሙር ከመናገር እባክህ ሰሀኖቹን በማጠብ ልትረዳኝ ትችላለህ? ብትሉ ይሄኛው አባባል ትህትናን የተላበሰ በመሆኑ የመጀምሪያው ግንፍርድ የተሞላበት ስለ ሆነ ለሰሚውም ምቾት አይሰጥም።
ሌላው መስተካከል ያለበት ነገር ደግሞ ከዚህ በፊት የተነጋገራችሁበትን ነገር በየጊዜው ደጋግማችሁ አታንሱ። የተነጋገራችሁበትንና የቋጫችሁትን ነገር በየጊዜው ደጋግማችሁ ማንሳታችሁ እናንተን ተጨቃጭዐቂ እንድትመስሉ ከማድረጉም በላይ አጋራችሁ በናንተ እንዲማረር ነው የሚያደርገው።
“ታውቃለህ” “ታውቂያለሽ” ከሚሉት ንግግራችሁን ሊያጋግሉ የሚችሉ ቃላት ስለሆኑ እነደዚህ ቃላትን ባትጠቀሙ መልካም ነው። ሁሌም ቢሆን ስትናገሩ “እኔ...” ብላችሁ ሀሳባችሁን ብታስተላልፉ ለአጋራችሁ ስለንግግራችሁ እናንተው ሀላፊነት እየወሰዳችሁ እንደሆነ ያሳየዋል።
“ሁልጊዜም አትሰማኝም” ከማለት ይልቅ “እያዳመጥከኝ እንዳልሆነ ይሰማኛል” ብትሉ እንዲሁ ሁሉንም ጊዜ በማጠቃለል እየወቀሳችሁ ሳይሆን የተፈጠረው ነገር ከናንተ እይታ አንፃር ምን እንደሚመስል ለአጋራችሁ ግልጽ እንዲሆንለት ስለሚረዳው ለንግግራችሁ ምላሽ ለመስጠት አይቸኩልም። ይልቁንም የናንተን ስሜትና ሁኔታ እንዲረዳ ይጠቅመዋል።
አብዛኛውን ጊዜ አዕምሯችሁ የንዴት ስሜታችሁን እና ቁጣን አለመግባባቱ ከተፈጠረበት ቦታ ጋር የማያያዝ ዝንባሌ ስላለው ቦታን መቀየር ነገሩን ለማርገብ ጥሩ አማራጭ ነው። ለምሳሌ ጭቅጭቅ የተጀመረው ወጥ ቤት ከሆነ ወደ ሳሎን ጎራ በሉ። ቦታ መቀየራችሁ ብቻ እንድትረጋጉና ነገሩን በተለየ መንገድ እንድታዩት ይረዳችኋል።
በጣም ፍጥን ፍጥን እያላችሁ ወይም በዝግታ ፣ በጣም ቀስስ ብላችሁ ወይም በጣም ጮክ ብላችሁ ስታወሩ  ያኛው ሰው እናንተን የመስማት እድሉ አነስተኛ ነው። በእያንዳንዱ አረፍተ ነገር መጨረሻም ረዘም ያለ ነገር እየቀጠላችሁና ከአንዱ ሀሳብ ላይ ሌላ ሀሳብ እየደራረባችሁ ነገር የምታስረዝሙ ከሆነ አድማጫችሁን ከማሰላቸት ውጪ ምንም ጥቅም የለውም።
አለመግባባት ላይ እያላችሁ ፊት ለፊት ቆሟችሁ ከምትነጋገሩ ይልቅ ጎን ለጎን ሆናችሁ ማውራታችሁ የተሻለ ነው። ምክኒያቱም ስሜታዊ ሆናችሁ እያለ ፊት ለፊት ሆናችሁ በምትነጋገሩበት ጊዜ ፊታችሁ ያለው ችግር አጋራችሁ ራሱ እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል።  በአንጻሩ ደግሞ ጎን ለጎን ሆናችሁ እየተነጋገራችሁ ከሆነ እናንተ ሁለታችሁ በአንድ ላይ ችግራችሁን እየተጋፈጣችሁ እንደሆነ እንዲሰማችሁ ያደርጋል። በተጨማሪም የሆኑ አንዳንድ ስራዎችን አብራችሁ ብትሰሩለምሳሌ ቤት ማጽዳት፣ እቃ ማጠብ ወይም ዎክ ብታደርጉበመካከላችሁ ያለውን ነገር ያረጋጋዋል። ነገሮች ከተረጋጉ በኋላበሰከነ መንፈስ ስለጉዳዩ መወያየት ትችላላችሁ።
መልዕክታችሁን ለማስተላለፍ አሽሙር የሚመስሉ ጥያቄዎች አትጠይቁ። ይሄ አይነቱ አነጋጋር ነገሮችን ከማጋጋል ውጪ የሚሰጠው መፍትሄ የለም። “ለምንድን ነው ሁልጊዜ የምትጮኽብኝ” ነገሮችን የሚያባብስ ሲሆን “ጮኽ ብለህ ስትናገር ጥሩ ነገር አይሰማኝም ይህንን ባህሪ ልታስተካክልልኝ ትችላለህ” የሚለው አባባል ግን ለአጋራችሁ ከእነርሱ ምን እንደምትጠብቁ በግልጽ እንዲረዱ ይጠቅማቸዋል።
ስለተጋጫችሁበት ነገር ስታወሩም “ሁሌም” እና “መቼም” የሚሉ ቃላትን አትጠቀሙ። “አንቺ እኮ በቃ ስለኔ ስሜት መቼም ግድ አይልሽም” ስትሉ አጋራችሁ ራሷን ለመከላከል ጥረት ማድረግ ትጀምራለች። ከዚህም የተነሳ ከዚህ በፊት ስለናንተ ስሜት እየተጠነቀቀች የነበረበትን ጊዜያት እያነሳች ልፀረዝርላችሁ ትችላለች። ከዚህ ባለፍም እናንተ ራሳችሁ ስለነሱ ስሜት ያልጠጠነቀቃችሁበትን ጊዜያት እንደምሳሌነት ሊያነሱላችሁ ይችላሉ። ይሄ ደግሞ ነገሩን ከማክረር ውጪ ወደ መፍትሄ አያመጣም። ስለዚህ ከአንዷ ቀን ተነስታችሁ ሁሉንም ቀን ባጠቃላይ እያነሳችሁ ከመውቀስ ይልቅ “ትናንትና በጣም አዝኜ ስለነበረ እንድታግዢኝ ፈልጌ ነበር ነገር ግን አጠገቤ ልትሆኝልኝ አልቻልሽም በዚህም አዝኛለሁ” ብትሉ ነገሩን አጋራችሁ እንዲረዱ ይበልጥ ያግዛቸዋል ፣ እናንተም ቶሎ ወደ መግባባት እንድትመጡ ይረዳችኋል።
በግጭት ጊዜ ስሜታችሁን መቆጣጠር እስክትችሉ ድረስ ባትነጋገሩ መልካም ነው። ተናዳችሁ ፣ እርቧችሁ ፣ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ወይንም የድካም ስሜት እየተሰማችሁ ከሆነ እንደ ግጭት ያሉ ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመቋቋም ይከብዳችኋል። ስለዚህ እስክትረጋጉ ድረስ ከንግግር ብትርቁና ያን ያላችሁበትን ስሜት በሚገባ አስተናግዳችሁ ተረጋጉና ወደ ውይይታችሁ ብትመለሱ ይመከራል። እርቧችሁ ከሆነ በደንብ በልታችሁ ረሀባችሁን አስታግሱ ፣ ተናዳችሁም ከሆነ የሚያረጋጋችሁን ሙዚቃ ማዳመጥ ፣ ሻወር ወስዳችሁ ቀለል ሲላችሁ ከአጋራችሁ ጋር የተፈጠረውን ነገር ለመፍታት የሚያስችላችሁ ጥሩ የስነልቦና ደረጃ ላይ እንድትሆኑ ይረዳችኋል።
እንዲህ አድርጋችሁ ራሳችሁን ካረጋጋችሁ በኋላ ደግሞ አጋራችሁ ያለበትን ሁኔታ ማየትና ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ምክኒያቱም እናንተ ያላወቃችሁት ሌላ ያስጨነቃቸው ወይንም ያሳሰባቸው ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል። አሁን ማውራት አልችልም ካሏችሁ ስሜታቸውን ተረዱላቸው እና እስኪረጋጉ ድረስ የሚያስፈልጋቸውን ጊዜ ስጧቸው።
“ይገባኛል ፣ እረዳሻለሁ ፣ አዎ በዚህኛው ሀሳብህ እስማማለሁ” የሚሉት ቃላት እጅግ ወርቃማ የሆኑ ቃላት ናቸው። ምክኒያቱም ለሚሰማችሁ ምን ያህል ስለነሱና ስለፍቅራችሁ ግድ እንደሚላችሁ እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል።

10 months, 3 weeks ago

ሚንጊ

ሚንጊ ማለት በደቡባዊው የኢትዮጲያ ክፍል በተለይም በኦሞ ወንዝ አካባቢ ኑሯቸውን ባደረጉ የኦሞ እና የሀመር ህዝቦች የሚዘወተር ባህላዊ ልማድ ነው። በባህሉ መሰረት ሚንጊ ናቸው ተብለው የተፈረጁ ልጆች ንጹህ እንዳይደሉ እና በማህበረሰቡም ላይም እርግማን ያመጣሉ ተብሎ ይታሰባል። ከዚህም የተነሳ የተለያዩ እርምጃዎች ህጻናቱ ላይ ይደርስባቸዋል።
አንድ ህጻን ሚንጊ ነው የሚባለው ከታችኛው ጥርሱ ቀድሞ የላይኛው ጥርሱ ከበቀለ፣ ልጆቹ መንታ ሆነው ከተወለዱ እንዲሁም ከጋብቻ ውጪ የተወለዱ ልጆች ሲሆኑ ነው። ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምሮች እንደሚያሳዩት የህጻን ልጆች ጥርስ የአንዳንዱ የላይኛው ቀድሞ ሲበቅል የአንዳንዱ ደግሞ ታችኛው ቀድሞ ይበቅላል። ይህም በልጆቹ ጤንነት ላይ የሚያሳድረው ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ የለም። መንታ ልጅ መውለድም ቢሆን በረከት እንጂ እርግማን አይደለም።
ከዚህ ባለፈም ልጆች በጤናማ ትዳር ውስጥ ቢወለዱ እናትና አባታቸውን አውቀው ፍቅራቸውን ጠግበው ቢያድጉ መልካም ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ከጋብቻ ውጪ በተለያዩ ምክኒያቶች ልጆች ይወለዳሉ። ይሄ ማለት ግን ልጆቹ መወለዳቸው በራሱ ችግር ነው ማለት አይደለም። ልጆቹ ፈልገው ወደዚህ አለም አልመጡምና። የሆነው ሆነው በኦሞ እና በሀመር ህዝቦች ዘንድ ይሄ ሁሉ ነገር እንደ እርግማን ይቆጠራል። ከዚህ የተነሳም ሚንጊ የሆኑ ልጆች በአካባቢው ውስጥ መኖር በቤተሰባቸው ብሎም በአካባቢው ሰዎች በሙሉ ላይ መቅሰፍትን ያመጣል ተብሎ ይሰጋል።
ጉዳዩ በስጋት ብቻ አያበቃም። የጎሳ መሪ የሆኑ ሰዎች በአካባቢያቸው ሚንጊ የሆነው ልጅ እንዳለ ካወቁ ቶሎ ብለው መጥተው ልጁን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ወይም ወንዝ በመወርወር ፣ አፉ ውስጥ ብዙ አፈር በመጨመር እንዲሁም ህጻኑን ጫካ ውስጥ በመጣል ህይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋሉ። በዚህ ባህል እጅግ በጣም ለዉጥር የሚታክቱ ብዙ ህጻናት ተሰውተዋል።
ሚንጊ ናቸው ተብለው ከሚፈረጁት ህጻናት ባለፈ የአካል ጉዳተኛ ሆነው የሚወለዱ ወይም ከተወለዱ በኋላ በለጋ እድሜያቸው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናትም ይሄው እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ የሚሞቱ ህጻናት ስርዓቱን የጠበቀ የቀብር ስነ ስርዓት እንኳን አይደረግላቸውም። ሚንጊ እንደሆኑ እንደታወቀ የጎሳው መሪ አካላት ወደ ቤታቸው በመሄድ ህጻናቱን ከእናታቸው እጅ ነጥቀው በመውሰድ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደርጋሉ።
ይሄ ባህል መቼ እና እንዴት እንደተጀመረ በውል የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ነገር ግን በተለያየ ምክኒያት ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥንክሮ በመስራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ማይችሉትን ለመቀነስ ታስቦ የተጀመረ ባህል እንደሆነ አንዳንዶ መላ ምታቸውን ያስቀምጣሉ። ከዚህ መላ ምት ያለፈ የተጻፈ እና የተሰነደ ስለ ባህሉ ታሪካዊ አመጣጥ የሚገልጽ የታሪክ መዝገብ የለም።
ሆኖም ግን ለረዥም ጊዜያት ሲተገበር እንደኖረ ግልጽ ነው። በዚህ ባህል ምንም የማያውቁ ህጻናት ገና ምንም ሳያውቁ እርግማን ታመጣላችሁ በሚል ሰበብ ህይወታቸው እንዲያልፍ ይደረጋል። እናቶችም ለዘጠኝ ወራት በሆዳቸው ተሸክመው፣ በብዙ ስቃይ አምጠው ወልደው፣ አጥብተው ያሳደጉትን ልጅ የጎሳቸው መሪዎች በጉልበት ነጥቀው ወስደው አይናቸው እያየ በሚዘገንን ሁኔታ ጭካኔ በተሞላው መንገድ ሲሞቱ ማየት ቀላል ነገር ሊሆንላቸው አይችልም። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከፍተኛ የሆነ የሞራል ጉዳት እና ስብራት ይደርስባቸዋል። ሆኖም ባህሉ እጅግ ስር የሰደደ እና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ስለሆነ ልጃቸውን በእምባ ከመሸኘት በስተቀር አማራጭ የላቸውም።

ይሄ ጎጂ እና አሰቃቂ ባህል ለዘመናት ተግባር ላይ ለመዋሉ አንዱ እና ትልቁ ምክኒያት የእውቀት ማነስ ነው። ማህበረሰቡ ዘንድ በቂ ትምህርት ተደራሽ ቢሆን መንታ መውለድ እርግማን እንዳልሆነ፣ አካል ጉዳተኝነት መቅሰፍት እንዳይደለ እንዲሁም የጥርስ አበቃቀል ሁኔታ የአጋጣሚ ጉዳይ እንጂ የወደፊት ሂወት ጋር የሚገናኝ ምንም አይነት ጉዳይ እንደሌለው ይረዱ ነበር። የሰው ልጅ ህይወትን ክቡርነት ቢያውቁ የእጅግ ብዙ ህጻናት ደም በከንቱ ባልፈሰሰ ነበር።
እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር ከ1936 - 1947 ዓ.ም ባለው ጊዜ ጣሊያን ኢትዮጲያ የኔ ግዛት ናት ባለችበት ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የኢጣሊያ ግዛት ናቸው በተባሉ ቦታዎች ሁሉ ላይ መሰል ድርጊቶች እንዳይደረጉ አግዳ ነበር። በዚህ መቀትም ሚንጊ ናቸው ብሎ ልጆችን መፈረጅ እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረግ እንደ ትልቅ ወንጀል ይቆጠር እና ያስቀጣ ነበር።
ከብዙ አመታት በኋላም በ2012 ዓ.ም የካሮ ህዝቦች ሚንጊ የሚለው ባህል መቀረት እንዳለበት ስምምነት አድርገው ነበር። ሆኖም ይሄው ስምምነት በተፈለገው ደረጃ መሬት ላይ ሊወርድ አልቻለም ነበር። አሁን ድረስም  ከ680,000 ያላነሱ የማህበረሰቡ አካላት ይህንኑ ጎጂ የሆነ ባህል እንደሚተግብሩት ይታወቃል።
ላሌ ላቡኮ የተባለ የካሮ ጎሳ ተወላጅ ገና የአስራ አምስት አመት ልጅ እያለ ሚንጊ ነው ተብሎ በማህበረሰቡ የተወገዘ ህጻን ልጅ ሲገደል በማየቱ እጅግ በጣም አዝኖ ነበር። ላሌ ከዚህ ፣አህበርሰብ ከተገኙ ሰዎች መካከል በሚሽነሪ ትምህርት ቤቶች የመማር እድል ያገኘ ልጅ ነበር። ካደገ በኋላም እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም አንዲት ህጻን ወላጆቿ በትዳር ሳይጣመሩ የወለዷት በመሆኗ ብቻ ልትገደ እያለ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ህይወቷን ያተረፋል። ከዚህም በኋላ ቀስ በቀስ እንደዚህ ሚንጊ የተባሉ ልጆችን ከሞት በማትረፍ እና ወደ ከተማ በመወሰድ ለህጻንቱ የሚሆን መጠለያ ስፍራ በማዘጋጀት ያሳድጋቸው ጀመር። ይሄ በጎ ስራውም ቀስ በቀስ እየተሰማ ሄዶ የዚህን ህዝብ ታሪክ እና የእርሱን መልካም ስራ የሚዘክሩ ሁለት ዶክመንታሪዎች ተሰርተዋል። የመጀመሪያው drawn from the water የሚል እና በ2012 የተሰራ ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም በ2015 ዓ.ም ጆን ሮው (John Rowe) በሚባል እውቅ ፊልም ፕሮዲዩሰር አማካኝነት omo child : the river and the bush የሚል ዶክመንታሪ ተሰርቶ ለእይታ በቅቷል። ዶክመንታሪዎቹም ሽልማትን አግኝተው ነበር።
ከጊዜያት በኋላም ላሌ ከፕሮዲዩሰሩ John Rowe ጋር በመሆን የኦሞ ልጆች ድርጅትን ከፍተው ህጻናትን ከሞት ለማትረፍ እየሰሩ ይገኛሉ። በjohn rowe አጋዥነት ለዚሁ አላማ በተሰራ መጠለያ ቤት ውስጥም ወደ 50 የሚደርሱ እድሜያቸው ከ 1 እስከ 11 የሆነ ህጻናት ከሚንጊ ሞት ተርፈው ይኖራሉ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 7 Monate, 1 Woche her

Last updated 7 Monate her

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 6 Monate her