ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
PAWS👏👏👏
ከ50 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ተጠቃሚ ያገኘዉ አዲሱ የቴሌግራም ኤርድሮፕ PAWS አነጋጋሪ ሁኗል፡፡
Paws በDecember ወር Farming እንደሚጠናቀቅ በይፋዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።
ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለልጃቸው ሀንተር ስልጣናቸውን ተጠቅመው ይቅርታ እንደማያዱርጉ ቢናገሩም ቃላቸውን ሻሩ ‼️
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምህረትን ላለማድረግ ቃል ቢገቡም በፍርድ ቤት በጦር መሳሪያ እና በታክስ ጥፋተኛነት በተፈረደበት በልጃቸው ሀንተር ላይ ይቅርታ አድርገዋል። ባይደን እሁድ እለት እንደተናገሩት ልጄ በቤተሰቡ ግዙፍ ስም ምክንያት “ተለይቷል” እናም "ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ” ተከሷል ሲሉ ተደምጠዋል።ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ ሀንተርን ለመስበር ጥረት ተደርጓል ፤ ለአምስት ዓመት ተኩል በማያቋረጡ ጥቃቶች እና በተመረጡ ክሶች ውስጥ እንዲያልፍ ተደርጓል ብለዋል።
ሀንተርን ለመስበር ሲሞክሩ እኔን ለመስበር ሞክረዋል ፤ እናም እዚህ ጋር ያበቃል ብለን የምናምንበት ምንም ምክንያት የለም ግን በቃ ማለት አለብን ሲሉ ባይደን መናገራቸውን የዋይት ሀውስ መግለጫ አመላክቷል።
እውነቱ ይሄ ነው ያሉት ባይደን እኔ በፍትህ ስርዓቱ አምናለሁ፣ ነገር ግን ከዚህ ጋር ስታገል፣ ፖለቲካም ይህን ሂደት በመበከሉ እና ፍትህ እንዲጓደል አድርጓል ብዬ አምናለሁ። እናም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ይህን ውሳኔ በመወሰን ከዚህ የበለጠ እንዲዘገይ አልፈቀድኩም ሲሉ ተደምጠዋል።
ሃንተር ባይደን በጠመንጃ ምርመራ ወቅት ስለ አደንዛዥ እፅ አጠቃቀሙ የውሸት መግለጫ በመስጠቱ እና ቢያንስ 1.4 ሚሊዮን ዶላር ግብር ካለመክፈል ጋር በተያያዙ ተከታታይ ወንጀሎች ላይ የቅጣት ውሳኔ ከሳምንታት በፊት እንደተላለፈበት ይታወሳል።ይህ የባይደን ውሳኔ ውዝግብ ፈጥሯል።የተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የበኩር ልጅ የባይደን ይቅርታ የሚጠበቅ እርምጃ ነበር ብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር “ሁሉም ሰው ይህንን ባይደን እንደሚያደርገው ያውቅ ነበር "ሲል በኤክስ ገፁ ላይ ያጋራውን መልዕክቱን ኤሎን ማስክ ሪፖስት አድርጓል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ኢትዮጵያ ፣ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር ጀመረች‼️**** ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባላት ድጋፍ አግኝታለች ተብሏል
ኢትዮጵያ፣ የኦርጋናይዜሽን ኦፍ እስላሚክ ኮፕሬሽን (የእስላማዊ አገራት ትብብር) ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር መጀመሯን ዋዜማ ሰምታለች።
ተቀማጭነቱ ጅዳ የኾነውና 58 አባል አገራትን ያቀፈው ድርጅቱ፣ በዓለም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀጥሎ በአባላት ብዛት ትልቁ የበይነ መንግሥታት ማኅበር ነው።
ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን ንግግር የጀመረችው፣ ከድርጅቱ በቀረበላት ግብዣ መሠረት እንደኾነ ታውቋል።
ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን፣ የቱርክን፣ ፓኪስታንንና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶችን ድጋፍ አግኝታለች።
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ 15 ሺህ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ተገለጸ‼️****
ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ጥር አጋማሽ ላይ ስልጣን የሚይዙ ሲሆንካቢኔያቸውን ከወዲሁ እያዋቀሩ ነው።
የፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ፔቴ ሄግሴትን የመከላከያ ሚንስትር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ታይምስን ዋቢ አል አይን አስነብቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
BreakingNews‼️
መንግሥት ሁለት ታዋቂ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን አገደ
የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል።
ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል።
ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም።
ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።
የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል።
ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ድርጅቶቹን እና ባለሥልጣኑን ለማነጋገር እየሞከርን ነው።
[ዋዜማ]
==============================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
የኔቶ አባል ሀገራት ህዝባቸውን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ናቸው‼️****
አሜሪካ ዩክሬን ሩስያን ለማጥቃት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን እንድትጠቀም መፍቀዷን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል
የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ሀገራት ዜጎቻቸውን ለጦርነት እንዲዘጋጁ በማሳሳብ ላይ እንደሚገኙ ተነገረ፡፡
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በአውሮፓ በተፈጠረው የደህንነት ስጋት ኔቶን የተቀላቀሉት የኖርዲክ ሀገራት ኖርዌይ ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ ዜጎች ለተወሰኑ ጊዜያት የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ቁሶችን ገዝተው እንዲያከማቹ አዘዋል፡፡
ሀገራቱ ህዝቦቻቸው ለጦርነት ወይም ለሌላ ያልተጠበቁ ቀውሶች እንዴት እንደሚዘጋጁ የሚመከር የተለያዩ መረጃዎችን አሳትመው ማሰራጨታቸው ነው የተሰማው፡፡
በዩክሬን ግጭት እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ስዊዲን በዚህ ሳምንት “በቀውስ ወይም ጦርነት ውስጥ” የሚል ርዕስ የተሰጣቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ በራሪ ወረቀቶችን አሳትማ አሰራጭታለች፡፡
የስዊድን የሲቪል ድንገተኛ አደጋዎች ጥበቃ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሚካኤል ፍሪሴል በራሪ ወረቀቶቹን አስመልክቶ በሰጡት ማብራርያ፤ “የጸጥታው ሁኔታ አሳሳቢ ነው እናም ሁላችንም የተለያዩ ቀውሶችን እና በመጨረሻም ጦርነትን ለመጋፈጥ እንዲሁም ለመቋቋም ማጠናከር አለብን ሲሉ” ተናግረዋል።
ፊንላንድ “ለአደጋዎች እና ቀውሶች መዘጋጀት” የሚል አዲስ ድረ-ገጽ የከፈተች ሲሆን ኖርዌያኖች በአስከፊ የአየር ጠባይ፣ ጦርነት ወይም ሌሎች አደጋዎች ለአንድ ሳምንት ያህል ማቆየት የሚስችል ግብአቶችን እንዲያዘጋጁ የሚያሳስብ በራሪ ወረቀት መቀበል መጀመራቸው ተዘግቧል።
በማስጠንቀቂያ በራሪ ወረቀቶቹ ላይ የሀይል አቅርቦት ቢቆራረጥ ምግብ ለማብሰል እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ የሀይል አማራጮች ፣ ምግብ ፣ መሰረታዊ መድሀኒቶች ፣አልባሳት እና ሌሎችም ቁሶች እንዲከማቹ የሚያዝ ሲሆን ሀገራቱ ጥቃት የሚፈጸምባቸው ከሆነ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ይገልጻል፡፡
የመጠጥ ውሀ ፣ እንቁላል ፣ ድንች ፣ የስጋ ውጤቶች እና በጽሀይ ብርሀን የሚሰሩ የሀይል አማራጮች በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱ መሰረታዊ ግብአቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ከሰሞኑ የጆ ባይደን አስተዳደር ዩክሬን በሩስያ ውስጥ የሚገኙ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የረጀም ርቀት ሚሳኤሎችን እንድትጠቀም ፈቃድ መስጠታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ያለውን ውጥረት አባብሶታል፡፡
ውሳኔው ሀላፊነት የጎደለው እና ሶስተኛው የአለም ጦርነትን የሚያስከትል ነው ያሉት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ለዩክሬን የሚሳኤል ጥቃት በኒዩክሌር ጦር መሳርያ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ለወትሮው አመጻ ፣ ብጥብጥ ፣ ግድያ እና ጦርነት የማያውቃቸው በሰላማዊነታቸው ከሚጠቀሱ ግንባር ቀደም የአለም ሀገራት መካከል የሚገኙት የኖርዲክ ሀገራት ህዝባቸው በስነልቦና እና በሌሎችም መንገዶች ለጦርነት ራሱን እንዲያዘጋጅ በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
==============================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
አሜሪካ ቱርክ ሀማስን እንዳታስጠጋ አስጠነቀቀች‼️
አሜሪካ የቱርክ መንግስት ከሀማስ ጋር የተለመደውን አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ዋሽንግተን አስጠንቅቃዋለች
የሽብርተኛ ድርጀት መሪዎች ተመቻችተው መቀመጥ የለባቸውም ያለችው አሜሪካ ቱርክ ሀማስን እንዳታስጠጋው ትናንት አስጠንቅቃለች።
የተወሰኑ የሀማስ መሪዎች ከኳታር ወደ ቱርክ ሄደዋል ስለሚሉት ሪፖርቶች የተጠየቁት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ሪፖርቶቹን አላረጋገጡም፤ ነገርግን አላስተባበሉም።
ቃል አቀባዩ የቱርክ መንግስት ከሀማስ ጋር የተለመደውን አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ዋሽንግተን አስጠንቅቃለች ብለዋል።
ሚለር አክለውም እንደገለጹት የተወሰኑት የሀማስ መሪዎች በአሜሪካ ክስ የተመሰረተባቸው ስለሆኑ ዋሽንግተን ወደ አሜሪካ መመለስ አለባቸው ብላ ታምናለች።
"የሽብርተኛ ቡድን መሪዎች በየትኛውም ቦታ ተመችቷቸው መኖር አለባቸው ብለን አናምንም..." ሲሉ ሚለር በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ሀማስ የፖለቲካ ቢሮውን ከኳታር ዶሃ ወደ ቱርክ ቀይሯል የሚለውን ቀደም ሲል የወጣውን ሪፖርት የቱርክ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ማስተባበላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኳታር እስራኤል እና ሀማስ ለእውነተኛ ንግግር ያላቸውን ቁርጠኝነት እስከሚያሳዩ ድረስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማድረግ ስታደርግ የነበረውን የማሸማገል ጥረት ባለፈው ሳምንት አቁማለች።
ዶሃ ሀማሰ ሀገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ነግራዋለች የሚሉት የሚዲያ ሪፖርቶችም ትክክል አይደሉም ብላለች።
ምንጮቹ "የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ አባላት በየጊዜው ቱርክን እየጎበኙ ነው። የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ወደ ቱርክ ተዛውሯል የሚለው መረጃ ግን እውነታውን አያንጸባርቅም"ብለዋል።
ሀማስም ሰኞ እለት ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ ሪፖርቶቹን አሉባልታዎች ናቸው ሲል አጣጥሏል።
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ጦርነት በጽኑ የምታወግዘው የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክ ሀማስን እንደ አሸባሪ ድርጅት አታየውም።
ቱርክ እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለውን ጥቃት በመቃወም ከእስራኤል ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አቋርጣለች።
ከዚህ በተጨማሪም ሀገሪቱ ደቡብ አፍሪካ በአለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ ደግፋ ለመከራከር ማመልከቷ ይታወሳል።
==============================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
እስራኤል በሶርያ ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ደቡብ አፍሪካ አወገዘች ‼️
ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሳምንቱ መጨረሻ ላይ እስራኤል በሶሪያ ላይ የፈፀመችውን የጥቃት እርምጃ በፅኑ ሁኔታ እንደምታወግዝ አስታውቃለች።
ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በሶሪያ ዋና ከተማ በደማስቆ ማዜህ የተፈፀመው ጥቃት ለደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ፣ ለሌሎች ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እና ለተባበሩት መንግስታት ቢሮዎች ቅርበት ያለው ዓለም አቀፍ ህግንና የሶሪያን አረብ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት መናቅ ነው በማለት የደቡብ አፍሪካ መንግስት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የፕሪቶሪያ መንግስት እንዳከው ይህ የቀጠለው ጥቃት ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ሰላም እና ደህንነትን የሚጎዳ ነው ብሏል። "ከጥቅምት 7 2023 ጀምሮ በሶሪያ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ከ120 በላይ መሆኑን እና በአሁኑ ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የከፋ የሰብአዊ ቀውስ አስከትሏል ሲል አስታውቋል።
ደቡብ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር ላይ በተደነገገው መርሆች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቃለች። ደቡብ አፍሪካ ለሶርያ መንግስት እና ህዝብ በተለይም በጥቃቱ ለተገደሉት ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝታለች። ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ያለውን የዘር ማጥፋት መቀጠሉን ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቷ ይታወሳል።
በቀጣዩ 2025 ዓመት የፍልስጥኤል ግዛት የሆነችውን ዌስት ባንክ ወደ እስራኤል የምትጠቃለለበት ዓመት እንደሚሆን የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች የሰጡትን መግለጫ ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሳምንት ማውገዟ አይዘነጋም። የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ዲፓርትመንት መግለጫ የተሰማው ስሞትሪች በእስራኤል በኃይል በተያዘው ግዛት ሰፈራዎች እንዲደረግ ዝግጅት ማዘዛቸው ከተነገረ በኋላ ነው። መምሪያው እስራኤል በፍልስጤም ግዛቶች ላይ የምታደርገውን የሰፈራ መስፋፋት እና ፀብ ቀስቃሽ ፖሊሲዎችን በመቃወም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ወሳኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥቷል።
==============================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
POWS VERIFY ተደርጓልልልል ☑️☑️
በዶግስ ተይዞ የነበረውን ብዙ ተጠቃሚ የማፍራት ሪከርድ የሰበረው POWS አሁኑኑ ጀምሩት በዚህ ፕሮጀክት በቀላሉ እስከ 50 ሺህ ብር ታገኛላችሁ 🔥🔥👇
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago