Shewa press

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 1 week ago
ከ ሳምንት በኋላ List የሚደረግ እና …

ከ ሳምንት በኋላ List የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ  በኤርድሮፕ ፕሮጀክት ታሪክ ትልቁ የተባለለትን PAWS ኤርድሮፕ ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ጀምሩ ።
👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

1 month, 1 week ago
Shewa press
1 month, 1 week ago
Shewa press
1 month, 1 week ago
የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት …

የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመንዝ ማማ ወረዳን (ሞላሌን) ተቆጣጥሯል። @showapress

1 month, 1 week ago

የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመንዝ ማማ ወረዳን (ሞላሌን) ተቆጣጥሯል።

@showapress

1 month, 1 week ago

ሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ መመሪያ
```````````````````````````````````````````
የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት በመደበኛ ጦርነት በህዝብ ላይ ከሚያደርሰው እልቂት ባሻገር በርካታ የውንብድና እና የሽብር ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል።

በከተሞች አካባቢ በየዕለቱ ወጣቶችን ይረሽናል፤ በየማጎሪያ ካምፖች ያጠራቅማል፤ ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች ያግዛል። ከዚህ ጎንለጎንም የፋኖ ቤተሰቦችን ያስራል፤ ይረሽናል፤ ንብረት ያወድማል።

በማንኛውም ፀያፍ መንገድ የአብይ አህመድን ስልጣን ማስቀጠልን የመረጠው ወራሪ ሰራዊት ባንኮችን፣ ጤና ጣቢያወችን ዘርፏል፤ አውድሟል። በርካታ ትምህርት ቤቶችንም በመድፍ፣ በሮኬት፣ በድሮን እና በጀት አውድሟል። የገበያ ቀናትን እየመረጠ በሚያደርገው የወረራ ዘመቻ የማህበረሰባችንን ደህንነት ከባድ አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል።

ከሰሞኑም በሚተኩሳቸው መሳሪያወች በህዝብ ላይ ከባድ እልቂት እያስከተለ ነው። በመሆኑም እነዚህን እና መሰል ጉዳቶችን ለመከላከል በምናደርገው ተጋድሎ ምክንያት የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ከመጭው ሰኞ ሕዳር 30/ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ:-

1) ከአምቡላንሶች በስተቀር መንገዶች ለሁሉም ተሽከርካሪወች ዝግ እንዲደረጉ መመሪያ ተሰጥቷል።

2) ለህዝብ ደህንነት ሲባል ከጤና ተቋማት በስተቀር ባንኮችን እና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ዝግ እንዲሆኑ ታዟል።

3) በመጨረሻም ሰራዊታችን እና መላው ህዝብ ወራሪውን ሰራዊት ለመመከት ለምናደርጋቸው ተከታታይ ወታደራዊ ጥሪወች በወትሮ ዝግጁነት እንዲጠብቅ እናሳስባለን

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ትስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም!

@Showapress

1 month, 1 week ago

አማራ ክልል የነበራትን ቆይታ ፋኖን በማድነቅ ያሰፈረችው የኒውዮርክ ታይምሷ ዘጋቢ።

የ Moonless and Starless sky (የጨረቃና ክዋክብት አልባ ሰማይ) መፅሀፍ ደራሲ፣ በበርካታው የዓለም ክፍል እየተዘዋወረች የጦርነትና ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በሰራችበት ተግባሯ ''the best travel writter award'' አሸናፊዋ፣ የኒውዮርክ ታይምሷ ሰው የፋኖ የተጋድሎ ውሎና የአማራ ህዝብ ከአገዛዙ ሀይል ጋር እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተመልክታዋለች። የኒውዮርክ ታይምሷ አሌክሲስ ኦኪኦዎ ቀልቧን ስለሳቡት፣ ልቧን ስለገዙት ፋኖዎች ጥፋት ስለታወጀበት የአማራ ህዝብ በስርዓቱ ታፍሰው በማይገባና በማያገባቸው ጉዳይ እየገቡ ስለሚያልቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካሰፈረችው ሀሳብ እነሆ በጥቂቱ።

''ከላሊበላ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ፋኖ ኬላ ላይ አስቆመንና ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠን። እንድናወራቸው እንደምፈልግ በነገርናቸው ወቅት ዩኒፎርም የለበሱ የፋኖ አባላት  አስፖልት ዳር በሚገኝ ሆቴል ይዘውን ሄደው በረንዳ ላይ ቁጭ አልን፡፡'' እያለች የአይን ምስክርነት ትንተናዋን የምትቀጥለው  ጋዜጠኛዋ።

የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በፋኖ ኬላ ላይ ለፍተሻ በሚቆምበት ወቅት ባስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ከፋኖ አባላት ጋር ፎቶ ለመነሳት ይጋፉ ነበር፤ መሳርያም ይዘው ፎቶ ለመነሳት ይጠይቁ እንደነበር ጋዜጠኛዋ ህዝቡ ለፋኖ ያለውን ፍቅር በግልፅ የተመለከተችበትን ሁነት አስፍራዋለች።

ብዙዎቹ የፋኖ ተዋጊዎች ወጣቶች እንደሆኑ የምትናገረው ጋዜጠኛዋ ፈንታ እና ላስታ የሚባሉ ሁለት የ18 እና የ19 ዓመት  ሴት የፋኖ ተዋጊዎችን እንዳገኘችና አማራና  በሰላም እንዳይኖር ስለተደረገ ወደ ፋኖ እንደተቀላቀሉ ትናገራለች፡፡

ስለ ውጊያ ውሎዎቻቸው ሲገልፅም “ የጠላት ሰራዊቶች በብዛት ይሞታሉ ፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ ጦርነት ስንገጥም የዕውር ድንብር ነው የሚተኩሱት ፣ በቁጥር ብዙ ቢሆኑም እግሬ አውጪኝ ብለው ይሮጣሉ እንጂ ቆመው አይዋጉንም። በጣም ነው የሚፈሩን ፤ በዛው በመከላከያ ውስጥ ያሉት አማራዎች እንደውም በጭራሽ ሊዋጉን አይፈልጉም” ስትል መግለጧን ጠቅሳ የአገዛዙን ሀይል ወታደሮች ፍርሀት ሽንፈትና ውርደት በኒውዮርክ ጋዜጣ ላይ በዝርዝር አስቀምጣዋለች።

በላሊበላ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ፋኖ  መሪ ዋኘው ሀምሳ አመቱ ሲሆን ፋኖን ከመቀላቀሉ በፊት ፖሊስ የነበረ ከዛም በኃላ ትራንስፖርት ላይና ኮንስትራክሽን ላይ ይሰራ የነበር ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም የሆነው ሰው የመንግስት ሀይሎች በአማራ ሕዝብ። ላይ የሚፈጽሙትን ድርጊት ተመልክቶና የአማራን የህልውና ስጋት ተመልክቶ ፋኖን መቀላቀሉን ያነሳና ባደረገችለት ቃለ ምልልስም ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት መከላከያ ብሎ የሚያመጣቸውን ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያስማረከና እያስገደለ መሆኑን ፅፋለች።

ጋዜጠኛዋ ከዋኘው ቃለምልልስ በወሰደችውና ባሰፈረችው ሃሳብ በሚካሄደው ጦርነት የአማራ ተወላጅ እናቶችና ሴት ልጆች ይደፈራሉ፣ በከባድ መሳሪያ ይደበደባሉ፤ የፋኖ ትግልም ለመገንጠል ሳይሆን ስርዓታዊና መዋቅራዊ በደልና ጥቃቶች እየተፈፀሙ ህልውናውም አደጋ ላይ በመውደቁ ላለመጥፋት የሚደረግ የህልውና ትግል ነው ስትል አስፍራዋለች።

ጋዜጠኛዋ ''ለታ'' የተባለ የመከላከያ ሰራዊት የነበረና በፋኖዎች የተማረከን የኦሮሞ ተወላጅ ወጣት አናግራ ባሰፈረችው ፅሁፍ ''ከአንድ ዓመት ተኩል በላቀ ጊዜ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና መጠጥ እጅግ አሰልቺና አድካሚም በሆነ ሂደት ውስጥ በመቆየቴ ለፋኖዎች እጅ ብሰጥ ምንም እንደማልሆን አውቃለሁና እጄን ሰጠሁ። ፋኖዎችም ተቀብለው ወታደራዊ የምርኮኞች መብቴን ጠብቀው ይዘውኛል። በዚህ በምርኮ ሁነት ውስጥ እያለሁም ለቤተሰቦቼም ገንዘብ እልካለሁ'' አለኝ ስትል አስፍራለች። ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ የጠየቀችው ጋዜጠኛዋ ምርኮኛው የኦሮሞ ተወላጁ የመከላከያ አባል መሳሪያውን ሸጦ እንደሆነ ሲያስረዳኝም እሱን ጨምሮ ፋኖዎችም ሁሉ በሳቅ ታጀቡ ስትልም አስፍራለች።

ላስታ የተባለችዋ ወጣት ለጋዜጠኛዋ በሰጠችው ቃለ ምልልስና የኒውዮርክ ታይምሷ ሰው ባሰፈረችው ዘገባ ምንም እንኳን ወጣቷ የትምህርት አቅሟ ከፍተኛ የነበረና ጥሩ ውጤት እያስመዘገበች የነበረች ቢሆንም አሁን በሀገርና ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ሁነት እጅግ ተስፋ አስቆርጧት ወደ ፋኖ ተቀላቅላ የህልውና ትግል ለማድረግ ወስና መምጣቷን ጋዜጠኛዋ አስፍራለች።

የፋኖ አመራር የሆነው ዋኘው መቶ ፐርሰንት የአማራ ሕዝብ ፋኖን እንደሚደግፍ ገለፀልኝ ፤ መቅደስ የተባለች የ21 ዓመት ወጣት የፋኖ ተዋጊም ፋኖ በመቀላቀሌ የቤተሰቤ ድጋፍ አለበት ደስተኞችም ናቸው ስትል ነገረችኝ ብላ በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ አስፍራለች።

ሊንኩን ከላይ አያይዘንላችኋል።👆👆

@showapress

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana