Information Office - CMHS|TGSH - BDU

Description
This page disseminates information that comes out of College of Medicine and Health Sciences/TGSH, Bahir Dar University, Ethiopia.
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 1 week ago

3 weeks, 6 days ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
3 weeks, 6 days ago

?Reminder: Workshop on Simulation in Healthcare - Happening Tomorrow!
????????????????????????????
Join us for an insightful workshop on "Simulation in Healthcare: Where are we and the way forward."

#Date:  September 23, 2024 
#Time: 8:30 AM 
#Venue: CMHS, Anesthesia Simulation Room 

#Objectives
Recognize the role of simulation in medical education, training, and quality of care 
Unfolding the status quo and the way forward 

#Targeted Audience:
Healthcare simulation enthusiasts 
Anyone interested in healthcare simulation 

Don't miss out on this opportunity to learn and engage! 

For more info, contact: 09 91 73 73 35 

#HealthcareSimulation #WorkshopReminder #StayInformed

4 weeks ago

College of Medicine and Health Sciences Hosts Internal Curriculum Workshop

Bahir Dar, September 17, 2024 – College of Medicine and Health Sciences at Bahir Dar University held an internal curriculum review workshop at Tibebe Ghion Campus. The event focused on enhancing three critical academic programs: Ph.D. in Nursing, MSc in Emergency and Critical Care Nursing, and MSc in Clinical Pharmacy.

The workshop brought together a diverse group of participants, including faculty members ftom Medical Education and Services Directorate, Public Health Education and Services Directorate, Pharmacy Education and Services Directorate, Medical Laboratory Education and Services Directorate and Nursing and Midwifery Education and Services Directorate. Their collective insights and collaborative discussions were instrumental in shaping the future direction of these critical health science programs.

The workshop is supposed to have huge contribution to the college’s growth and development as it continues to expand its postgraduate programs in health sciences, further solidifying its role as a leading institution for medical education in Ethiopia and beyond.

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia/

1 month ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
1 month ago

#ቸልተኝነት:- የጤና ባለሙያዎችና ህሙማን በሚያደርጉት ያልተቋረጠ የቀን ተቀን መስተጋብር አንዳንድ ጊዜ በስታንዳርዱ መሰረት መደረግ የነበረበትን አስፈላጊ የምርመራ ወይም የህክምና እርዳታ ባለማድረግ ሌላ ጊዜ ደግሞ መደረግ የሌለበትን ነገር በማድረግ ህሙማን ላይ አላስፈላጊ ጉዳቶች ሊደርሱ ይችላሉ።

#አሉታዊ_የባህል_ተጽኖ_መኖር:-ሰው እንኳን ውስብስብ የሆነውን የጤና አገልግሎት ሲያከናውን ቀርቶ ማንኛውንም ስራ ሲሰራ ስህተት እንደሚያጋጥም ታውቆ ስህተቱ ሲያጋጥም፣ ለስህተቱ ወይም የጎንዮሽ ጉዳቱ መፈጠር ምክንያት የሆነው አካል ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት አድርጎ ሌላ ጊዜ እንዳይደገም መማሪያ ከማድረግ ይልቅ ከጉዳዩ የመሸሽ እና ራስን የመከላከል ልማድ ያለ ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው የደረሰውን ጉዳት ለምን እና እንዴት እንደደረሰ፤ ተቋማዊ አስተዋጾ መኖር አለምኖሩን መርምሮ ወደፊት እንዳይደገም ከመስራት ይልቅ ጉዳት አድርሷል የተባለውን ባልሙያ የጦስ ዶሮ የማድረግ ልማድ ስላለ ነው።

ስህተት ሰዋዊ (to err is human) መሆኑን መረዳት ነገር ግን ደግሞ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ፣ ጥሩ የቡድን መንፈስ እና ተግባቦት በመገንባት፣ የስራ ከባቢውን በማሻሻል እና ምቹ በማድረግ፣ የስራ ጫናን በመቀነስ፣የህሙማን ደህንነት ባህልን በማጠናከር አብዛኛውን ማለትም 80% የሚሆነውን የህክምና ስህተት እና የጎንዮሽ ጉዳት መቀነስ እንደሚቻል በመገንዘብ እና ጉዳዩ የሁሉንም ትኩረት የሚሻ ስለሆነ ሁላችንም የህሙማንን ደህንነት ለመጠበቅ የበኩላችንን በመወጣት፤ የጎንዮሽ ጉዳቱ እና ስህተቱ ይዞት ከሚመጣው መዘዝ ታካሚዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን እንጠብቅ!

የህሙማን ደህንነት ቀንን (World Patient Safety Day Sep. 17) አስመልክቶ የተጻፈ

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia/

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

1 month ago

#የህሙማን_ደህንነት
???????

**በዶ/ር ነቢዩ ሽታዬ

የጠቅላላ እና ልዩ የህጻናት ቀዶ ህክምና ባለሙያ
በሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና አገልግሎት፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ እና ኢኖቬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር**
የህሙማን ደህንነትን ማረጋገጥ ማለት ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜ እና አገልግሎቱን በሚያገኙ ጊዜ ከህክምና ስህተት ወይም ህክምናው በሚሰጥ ጊዜ ከሚደርስ የጎንዮሽ ጉዳት መጠበቅ ማለት ነው። ህሙማን ላይ የሚደርስ የህክምና ስህተት ወይም የጎንዮሽ ጉዳት ችግር በአንድ አካባቢ ወይም በአንድ ሀገር የተወሰነ ሳይሆን ምንም እንኳ የችግሩ መጠን ቢለያይም ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ ያላችውን ሃገራት፤ የምስራቁንም ሆነ የምዕራቡን ሃገራት ሁሉ የሚያካልል አለማቀፋዊ ችግር ነው።

የህሙማን ደህንነት ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም አሁንም በዓለም ላይ በየቀኑ የሚያጋጥም አሳሳቢ ክስተት ሆኖ ቀጥሏል:: በዓለም ላይ በየአመቱ 134 ሚሊዮን የሚሆኑ ህክምና አገልግሎት ከመስጠት ሂደት ጋር የተያያዙ ጉዳቶች የሚያጋጥሙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 2.6 ሚሊዮን የሚሆኑት ለሞት ይዳረጋሉ። ህሙማን ላይ የሚደርስ የህክምና ስህተት ወይም የጎንዮሽ ጉዳት ታካሚዎች ላይ፣ የታካሚ ቤተሰቦች ላይ እንዲሁም በሂደቱ የሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ እና የስነልቦና ጫና ይኖረዋል።

የህሙማንን ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉንም የሚመለከታቸውን አካላት ማለትም ታካሚዎችን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ የጤና ተቋማት አስተዳዳሪዎችን እና መሪዎችን፣ በተዋረድ ያሉ የጤና ጥበቃ ቢሮዎችን፣ በዚሁ ጉዳይ ላይ የተሰማሩ አለማቅፋዊ የጤና ድርጅቶችንና ግብረ ሰናይ ተቋማትን፣ የሙያ ማህበራትን እንዲሁም መላውን ህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ የሚፈልግ ጉዳይ ነው!

በጥናት ከተለዩት እና በተደጋጋሚ ከሚከሰቱት የህሙማንን ደህንነትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

መድሃኒቶች ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ጎጅ ክስተቶች: - እነዚህ ችግሮች የሚፈጠሩት ማዘዣው በሚጻፍበት ጊዜ፣ መድሃኒቱ ከፋርማሲ ክፍል ለታካሚው በሚሰጥበት ጊዜ፣ ታካሚው መድሃኒቱን ከተቀበለ በኃላ በሚያስቀምጥበት ቦታ፣ ታካሚው መድሃኒቱን በሚወስድበት ጊዜ እና የመሳሰሉት ናቸው። በማዘዣ ጽሁፍ አለመነበብ ወይም በሌላ ምክንያት መድሃኒቱ በአይነቱ የመቀየር፣ አይነቱ ራሱ ሆኖ በመጠን የመብዛት ወይም የማነስ፣ የአለርጂ ሂስትሪ ባለማዎቅ አለርጂክ የሆነውን መዳኒት መስጠት፣ የሚወሰደው በደም ስር ወይም በቆዳ ስር ሆኖ ሳለ በኣፍ መውሰድ፣ የማይገባ ቦታ (በጣም ሙቀት/ በጣም ቅዝቃዜ) ማስቀመጥ፣ የሁለት ተመሳሳይ ሞክሸ ስም ያላቸው ታማሚዎች መድሃኒት የአንዱ ለሌላኛው መቀያየር እና ሌሎችንም ያጠቃልላል። ከዚህም በተጨማሪ ኬሞቴራፒ (የካንሰር ኬሚካል ህክምና) በአንጻራዊነት ከሌሎች መዳኒቶች ከፍ ያለ የጎንዮሽ ጉዳት በማምጣት ይታወቃሉ።

ጤና ተቋማት ውስጥ ከመቆየት ጋር የተያያዙ የጎንዮሽ ኢንፌክሽን መያዝ ችግሮች:- ለምሳሌ የሃሞት ጠጠር ኦፕራሲዮን ሊያሰሩ የገቡ ታካሚዎች ረዘም ያለ ግዜ ሆስፒታል በመቆየታቸው በሳንባ ኢንፌክሽን መያዝ ወይም በሽንት ኢንፌክሽን አለያም በቁስል ማመርቀዝ ኢንፌክሽን መጠቃት እና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡

ከቀዶ ህክምና እና ሰመመን አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ክስተቶች:- እነዚህ ህሙማን የቀዶ ህክምና እና ሰመመን አገልግሎት በሚያገኙበት ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርሱ ስህተቶች እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያጠቃልሉ ናቸው።

ደህንነቱ ያልተጠበቀ የመርፌ (ኢንጀክሽን) አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች:- ይህ በደም ንክኪ የሚተላለፉ ተላላፊ በሽታዎች እንደ ኤች.አይ.ቪ፣ ሄፓታይተስ ቢ፣ ሄፓታይተስ ሲ እና ሌሎችም ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።

የህመምን አይነት እና ምንነት ከማዎቅ ችግር ጋር በተየያዘ ህሙማን ላይ የሚደርስ ጉዳት:- በጊዜው እና በትክክል የህመምን አይነትና ምንነት መለየት አለመቻል ለአላስፈላጊ መዘግየት እና የህመሙ ደረጃ ማደግና ስር መስደድ አስተዋፆኦ ያደርጋል። በተለይ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገሮች ከዘመናዊ የላቦራቶሪ እና ዲያግኖስቲክ እቃዎች እና መሳሪያዎች እጥረት ጋር በተያያዘ የህመምን ምንነት በጊዜ እና በትክክል የማዎቅ ከፍተኛ ችግር ይስተዋላል። በዚህም ምክንያት ብዙ ህሙማን የህመማቸው ምንነት ሳይታዎቅ ወይም በጣም ዘግይቶ በመታወቁ ብዙም እርዳታ ሳያገኙ ለህልፈተ ህይዎት ይዳረጋሉ።

ደም መርጋት እና ተያያዥ ችግሮች:- ህሙማን በጤና ተቋማት ተኝተው አገልግሎት በሚያገኙ ጊዜ በቂ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው ወይም ደግሞ ደም መርጋትን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መድሃኒቶች በጊዜው እና በበቂ ባለማግኘታቸው በደም መርጋት እና ተያያዥ ችግሮች ሊጠቁ ይችላሉ፥ ውጤቱም እስከሞት ሊያደርስ ይችላል።

በምርመራ ጊዜ ለጨረር ከመጋለጥ እና በጨረር ህክምና ጋር በተያያዘ የሚመጡ ችግሮች: - ታካሚዎች የህመምን ምንነት ለማዎቅ በሚደረግ የተለያዩ ምርመራዎች (ለምሳሌ x-ray እና CT scan) ወይም የጨረር ህክምና (ራዲዮቴራፒ) በሚሰጥበት ጊዜ የሚያጋጥሙ ስህተቶች ወይም የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያጠቃልሉ ናቸው!

ደህንነቱ ያልተጠበቀ የደም ልገሳ አገልግሎት (unsafe blood transfusion):- ምንም እንኳን ደም እጅግ በጣም አስፈላጊ ህይዎት አድን ነገር ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ደም ከመውሰድ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ተላላፊ በሽታዎች እና ሌሎች ጉዳቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ።

ከላይ የተጠቀሱት የጎንዮሽ ጉዳቶች ወይም የህክምና ስህተቶች እንዲከሰቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

#ህክምናው_የሚሰጥበት_የስራ_ከባቢ_ምቹ_አለመሆን:- የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታው በመስፈርቱ መሰረት የክፍሎቹ ብዛት እና ስፋት በቂ አለመሆን፣ በቂ ብርሃን እና አየር አለመኖር፣ በየክፍሉ የሚገኙ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና እቃዎች አለመኖራችው ወይም የተበላሹ መሆናቸው፣ አስፈላጊ ቴክኖሎጂ አለመኖር፣ የህክምና አገልግሎት መስጫ ጋይድላይኖች እና ፕሮቶኮሎች አለመኖር፣ የጤና ባለሙያዎች እርካታ ማነስ እና ሌሎችም የስራ ከባቢ ምቹ አለመሆን ጋር የሚገናኙ ነገሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የህሙማንን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ።

#የህክምና_አገልግሎቱን_በሚሰጡት_የቡድን_አባላት_መካከል_ያለ_የተግባቦት_ማነስ_እና_አለመከባበር፥- የጤና አገልግሎት የቡድን ስራ እንደመሆኑ መጠን በቡድኑ አባላት መካከል በዲሲፒሊን የታነጸ እና በጣም ጥሩ የሆነ የቡድን ተግባቦት እና መከባበር ያስፈልጋል። ይሄ በሌለበት ሁኔታ በቡድኑ አባላት መካከል የሚደረግ የጽሁፍም ሆነ የቃል መስተጋብር ህሙማን ላይ ለሚድርስ ጉዳት የራሱን ድርሻ ያበረክታል።

#የአሰራር_ቢሮክራሲ_እና_የስራ_ጫና ባለሙያዎች ለረጅም ሰአት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነው ስራ ላይ ሲቆዩ፤ የህክምና አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የህክምና እቃዎች እና ግባቶች በሌሉበት ሁኔታ እንዲሰሩ ሲገደዱ ወይም ደግሞ አንድ ባለሙያ ማገልገል ከሚገባው ቁጥር በላይ ታካሚዎችን እንዲያገለግል በሚደረግበት ጊዜ ለስህተት የመጋለጥ እድሉን ከፍ ያደርገዋል።

1 month ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
1 month ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
1 month ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
1 month ago
Information Office - CMHS|TGSH - BDU
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 1 week ago