FastMereja.com

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

1 month, 2 weeks ago
በ2016 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት …

በ2016 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ !

#FastMereja l በየዓመቱ በሚካሄደው በ፵፫ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ መንፈሳዊ የአብነት ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያም ቅ/ፋኑኤል ወቅ/ዮሐንስ ወ/ነጎድጓድ ገዳም በማኅበረ ቅዱሳን ከተገነባው ሕንጻ በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ የመማርያ ክፍሎች አንዲሁም የመምህራንና የደቀ መዛሙርት ማረፊያ ቤቶች መሥራት ተችሏል ተብሏል፡፡

በሀገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡

ዘገባው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ነው

1 month, 2 weeks ago
አማኑኤል ሆስፒታል በቀን በአማካይ 500 ታካሚዎች …

አማኑኤል ሆስፒታል በቀን በአማካይ 500 ታካሚዎች በተመላላሽ ሕክምና እያገኙ መሆኑ ተገለፀ

#FastMereja l አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዕምሮ ሕክምና በተጨማሪ ለታካሚዎች የተሟላ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ሆስፒታሉ ላለፉት 85 ዓመታት ሕብረተሰቡን ሲያገለግል መቆየቱን የገለጹት የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ኃይሌ÷ ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ የባለሙያ ስብጥርና የሕክምና ግብዓቶችን እያሟላ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይም በድንገተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በ239 አልጋዎች የአስተኝቶ ሕክምናና በቀን በአማካይ 500 ታካሚዎች በተመላላሽ ሕክምና እያገኙ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የሆስፒታሉ ታካሚዎች ከአዕምሮ ሕክምና ውጭ ተጨማሪ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሌሎች የጤና ተቋማት በመሄድ ሲገለገሉ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ አሁን ላይ ተቋሙ አድማሱን በማስፋት ለታካሚዎች የተሟላ ሕክምና ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም የባለሙያዎች ቅጥርና የሕንጻ ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው÷ እስከ ጥር 2017 ዓ.ም ድረስ በሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት ለመጀመር መታቀዱን አመላክተዋል፡፡

በቀጣይም ለአካባቢው ሕብረተሰብ የተሟላ ሕክምና የመስጠት ውጥን መያዙን ጠቅሰው÷ ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችል ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ አካላት ከሆስፒታሉ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ከኢዜአ ዘገባ ተመልክተናል።

1 month, 3 weeks ago

#ቃሉ እንደ ጽጌረዳ እየተጎነጎነ በስዕሏ እቅፍ ያርፍ ነበር… 

ልዩና ተአምራት የምታደርግ የእመቤታችን ሥዕል በመመልከቱ በጻድቁ አባ ዜና ማርቆስ አስተማሪነት ከአይሁዳዊነት ወደ ክርስትና የተመለሰው አባ ጽጌ ድንግል ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር ስድስት ቅድስት ድንግል ማርያም የምትመሰገንበትን ማኅሌተ-ጽጌን የደረሰ አባት ነው፡፡ በምንኩስና ሕይወት ሲኖርም ለሥዕሏ ካለው ፍቅር የተነሳ ሳያያት ውሎ አያድርም፡፡ ሊያያት ሲሔድም እጅ መንሻ ይሆነው ዘንድ በሃምሳ ጽጌረዳ አበባዎች ጉንጉን በመስራት በስዕሏ ዙሪያ ያስቀምጥ ነበር፡፡

በቅዱሳን ሥዕላትን ፊት ስንቀርብ ቅዱሳን መካናትንና ገዳማትን ስንሳለም ምን ይዘን ነው የምንሔደው? እንደየአቅማችን መባዕ ይዘን የመሔድ ዝንባሌያችንስ ምን ይመስላል? ምድራዊ ዘመዶቻችንን ስንጠይቅ እንኳ ባዶ እጃችንን አንሔድም እኮ፡፡ ይልቁንም ለቅዱሳን ቦታዎች እንጅ መንሻ ይዞ መሔድ በረከቱ ከፍ ያለ ነው፡፡

አባ ጽጌ ድንግል አበቦች በሚደርቁበት ወራት በዚህች ሥዕል ፊት ሲቆም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ደስታ ይገባሻል እያለ እንዳመሰገናት “በአበባው ቁጥር ልክ እንዳመሰግንሽ ፍቀጂልኝ” በማለት እመቤታችንን ለመናት፡፡ እርሷም እንደፈቀደችለት ያሳየችው በገሃድ ነበር፡፡ እርሱ በየቀኑ ሃምሳ ጊዜ ሲያመሰግን ከአፉ የሚወጣው ምስጋና እንደ ጽጌረዳ አበባ እየሆነ እመቤታችን ተቀብላ ስትታቅፈው በዙሪያው ያሉ ሰዎች እያዩ ክብሯንና ገንናነቷን ያደንቁ ነበር፡፡ በኋላም ማኅሌተ ጽጌዋን ለመድረስ የሚያስችል በረከት አድላዋለች፡፡

ከልብ የሆነ ስጦታ እንዲህ ነው፡፡ ቅዱሳን ገዳማትንና ገዳማውያንን ስንረዳ የቅዱሳኑ በረከታቸው፣ ጸጋቸው ያድርብናል፡፡ በጸሎታቸው ትሩፋት እንጠበቃለን፡፡ ጥቂት ሰጥተን ብዙ እንሰበስባለን፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የወርሃ ጽጌዋ ረድኤትና አማላጅነት፣ የአባ ጽጌ ድንግል በረከት አይለየን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 month, 3 weeks ago

#እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት

ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ለማውጣት በእግዚአብሔር ተመርጦ ኬላከ በኋላ ከሕዝቡ መካከል ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ በግብጽ ምድር በባርነት የተወለደው ኢያሱ ወልደ ነዌ አንዱ ነው፡፡

በጊዜው የ40 ዓመት ጎልማሳ የነበረው ኢያሱ እስራኤላውያን በ40 ቀናት ተጉዘው የሚገቡባትን ቅድስቲቱ ምድር በልባቸው ክፋት በ40 ዓመት እንዲገቡ ሲወሰንባቸው ምድሪቱን ለማየት እድል ካገኙት ሁለት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡

ቅዱስ ሙሴ በናባው ተራራ ካረፈ በኋላም እስራኤልን እንዲመራ እግዚአብሔር የመረጠው ኢያሱ ወልድ ነዌን ነበር፡፡ ይህ ድንቅ አባት ሙሴ ባሕረ ርዳኖስን እንደከፈለ ባሕረ ዮርዳኖስን የከፈለ፣ የኢያሪኮን ግንብ 7 ጊዜ ዞሮ በእግዚአብሔር ኃይል ያፈረሰ፣ ለ12ቱ ነገደ እስራኤል ርስት ሲያካፍል ፀሐይን በገባኦን ሰማይ ጨረቃንም በኤላን ሸለቆ ያቆመ ተአምር አድራጊም ነበር፡፡

እስራኤላውያን ምድራቸውን ከወረሱ በኋላ ሰባት የመማጸኛ ከተሞችን የለየ ሲሆን ለሕዝቡ “እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተስ?” የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም “እኛም እንዳንተ ነን” አሉት፡፡ ይህ ታላቅ አባት አርባ ዘመን በበረሀ ከእስራኤላውያን ጋር ተንገላቷል፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ካረፈ በኋላም ሕዝቡን መርቶ ምድረ ርስት አስገብቶ እግዚአብሔር በገለጸለት ርስት አካፍሏል፡፡ ይህን ሁሉ ስራ ሰርቶ ግን ልሸለም… ልከበር… ወይም ልረፍ አላለም፣ ይልቁንም የሕዝቡ የአምልኮታቸው ጉዳይ ነበር ያሳሰበው፡፡

ዛሬም ገዳማውያን አባቶች ዓለምን ጥለው መንነው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው እየኖሩ ይድላን ይመቸውን ሳይሉ በኃጢያታችን ተቆጥቶ እንዳያጠፋን ሌት ተቀን ስለኛ ይጸልያሉ፡፡ ኢያሱ እስራኤላውያን የሚያመልኩትን ሲመርጡ 3 ገጽ ያላትን ኃውልት በመካከላቸው ለምስክርነት አቆመ፡፡ ይህቺውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ አባቶቻችን ገዳማውያኑም እመቤታችንን አጋዥ አድርገው ስለኛ ይጸልያሉ፡፡

እስራኤላውያን የኢያሱን ውለታ አልረሱም፤ በተወለደ በ120 ዓመቱ ሲያርፍ ለ30 ቀናት አልቅሰውለታል፡፡ እኛም ዘወትር ስለኛ የሚጸልዩ ገዳማውያን አባቶቻችን በአታቸው ሲዳከም፣ የሚጠለሉበት ታዛ፣ የጠሚቀምሱት ጥቂት የምግብ መአዛ ሲያጡ በዝምታ መመልከት አይገባንም፡፡        

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 month, 3 weeks ago
1 month, 3 weeks ago

#እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት

ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ለማውጣት በእግዚአብሔር ተመርጦ ኬላከ በኋላ ከሕዝቡ መካከል ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ በግብጽ ምድር በባርነት የተወለደው ኢያሱ ወልደ ነዌ አንዱ ነው፡፡

በጊዜው የ40 ዓመት ጎልማሳ የነበረው ኢያሱ እስራኤላውያን በ40 ቀናት ተጉዘው የሚገቡባትን ቅድስቲቱ ምድር በልባቸው ክፋት በ40 ዓመት እንዲገቡ ሲወሰንባቸው ምድሪቱን ለማየት እድል ካገኙት ሁለት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡

ቅዱስ ሙሴ በናባው ተራራ ካረፈ በኋላም እስራኤልን እንዲመራ እግዚአብሔር የመረጠው ኢያሱ ወልድ ነዌን ነበር፡፡ ይህ ድንቅ አባት ሙሴ ባሕረ ርዳኖስን እንደከፈለ ባሕረ ዮርዳኖስን የከፈለ፣ የኢያሪኮን ግንብ 7 ጊዜ ዞሮ በእግዚአብሔር ኃይል ያፈረሰ፣ ለ12ቱ ነገደ እስራኤል ርስት ሲያካፍል ፀሐይን በገባኦን ሰማይ ጨረቃንም በኤላን ሸለቆ ያቆመ ተአምር አድራጊም ነበር፡፡

እስራኤላውያን ምድራቸውን ከወረሱ በኋላ ሰባት የመማጸኛ ከተሞችን የለየ ሲሆን ለሕዝቡ “እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተስ?” የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም “እኛም እንዳንተ ነን” አሉት፡፡ ይህ ታላቅ አባት አርባ ዘመን በበረሀ ከእስራኤላውያን ጋር ተንገላቷል፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ካረፈ በኋላም ሕዝቡን መርቶ ምድረ ርስት አስገብቶ እግዚአብሔር በገለጸለት ርስት አካፍሏል፡፡ ይህን ሁሉ ስራ ሰርቶ ግን ልሸለም… ልከበር… ወይም ልረፍ አላለም፣ ይልቁንም የሕዝቡ የአምልኮታቸው ጉዳይ ነበር ያሳሰበው፡፡

ዛሬም ገዳማውያን አባቶች ዓለምን ጥለው መንነው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው እየኖሩ ይድላን ይመቸውን ሳይሉ በኃጢያታችን ተቆጥቶ እንዳያጠፋን ሌት ተቀን ስለኛ ይጸልያሉ፡፡ ኢያሱ እስራኤላውያን የሚያመልኩትን ሲመርጡ 3 ገጽ ያላትን ኃውልት በመካከላቸው ለምስክርነት አቆመ፡፡ ይህቺውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ አባቶቻችን ገዳማውያኑም እመቤታችንን አጋዥ አድርገው ስለኛ ይጸልያሉ፡፡

እስራኤላውያን የኢያሱን ውለታ አልረሱም፤ በተወለደ በ120 ዓመቱ ሲያርፍ ለ30 ቀናት አልቅሰውለታል፡፡ እኛም ዘወትር ስለኛ የሚጸልዩ ገዳማውያን አባቶቻችን በአታቸው ሲዳከም፣ የሚጠለሉበት ታዛ፣ የጠሚቀምሱት ጥቂት የምግብ መአዛ ሲያጡ በዝምታ መመልከት አይገባንም፡፡        

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago
የእሬቻ የሰላም ፌስቲቫል ተካሄደ

የእሬቻ የሰላም ፌስቲቫል ተካሄደ

#FastMereja
በኢትዮጵያ ወጣቶች ስላምና ብልፅግና ተልዕኮ ሊግ የተዘጋጀው የእሬቻ የሰላም ፌስቲቫል ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ቅጥር ግቢ አዳራሽ ዉስጥ አባገዳዎች፥ ሀዳ ስንቄዎች የመንግስት ባለስልጣናት እና ወጣቶች ባሉበት በታላቅ ድምቀጥ ተከብሯል።

በዚህ የሰላም ፌስቲቫል ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሰላምና ብልፅግና ተልዕኮ ሊግ ፕረዝዳንት አቶ ብርሀኑ በቀለ እንደተናገሩት ኢሬቻ የወንድማማችነት ፣ የእህትማማችነት ፣ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ፣የተጣላ የሚታረቅበት የአብሮነትና የሰላም በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስላምና ብልፅግና ተልዕኮ ሊግ የተቋቋመ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ህገመንግስት አንቀጽ ቁጥር 57 ሲሆን አላማዉ አገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና አስተማማኝ ልማት እንዲመጣ እና የአገራችን ትላልቅ በአላት ለቱሪዝም ስበት ስለሚጠቅሙ ለመደገፍ እና ለማበረታታት ነዉ

2 months ago

#የምሰራው ቤት ታላቅ ነው

ንጉስ ሰሎሞን የሰራው ቤተ መቅደስ ምድራችን ካየቻቸው ድንቅ ነገሮች አንዱ አንደሆነ የታሪክ ጸሐፍት ያትታሉ፡፡ በመጽሐፈ ነገስት ካልዕ ምዕራፍ 2 ቤተ መቅደሱን ለመስራት ሲያስብ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ለማሰባሰብ ከነገስታት ጋር ተጻጽፏል ባሕር ተሻግረው ከሊባኖስ በታላላቅ መርከቦች የመጡ እንጨቶች እንደነበሩ ተጽፏል፡፡ ወደ ጢሮስ ንጉስ ወደ ኪራም በላከው መልዕክትም፡- 
“ደግሞም ባሪያዎችህ ከሊባኖስ እንጨት መቍረጥ እንዲያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ የሰንደልም እንጨት ስደድልኝ።” የሚል ዓረፍተ ነገር ቁጥር ስምንት ላይ ይገኛል፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሰራ በዚህ መልኩ ግብአቶችን በአይነት ማቅረብ ጥንታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ ነው፡፡ በዘመናችንም አብያተ ክርስቲያናት ሲገነቡ እንድናደርግ ከምንጠየቀው ገንዘብ እገዛ ውጪ በአይነት እንጠየቃለን፡፡ ሲሚንቶ፣ ጠጠር፣ አሸዋ፣ ብረት ወዘተ ይህን ያህል እንፈልጋለን ተብሎ ይነገረናል፡፡

ጠቢቡ ንጉስ ሰሎሞን ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም በላከው መልእክት “እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘላለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ለማጠን፣ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፣ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራና እቀድስ ዘንድ አሰብሁ። አምላካችንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ነውና የምሠራው ቤት ታላቅ ነው።” ባለው ጊዜ በደስታ ነበር ተባሉትን የተመረጡ እንጨቶች የላከለት፡፡

እነሆ በዘመናችንም ጥሪ እየቀረበልን ነው፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያለውን ቤተ ክርስቲያንና ገዳማውያን አባቶችን ለመርዳት፣ በዓታቸውንም ለመስራት ድንጋይ፣ ሲሞንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠርና ብረት በአይነት ማገዝ የምትችሉ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች ደውላችሁ ብትነግሩን ያላችሁበት ድረስ በራሳችን ትራንስፖርት መጥተን ለመውሰድ ዝግጁዎች ነን፡፡ የምንሰራው ቤት ታላቅ ነውና ከታላቁ በረከት ተሳተፉ፡፡ የገዳማውያኑ በረከትና ረድኤት አይለየን!!! 

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago

#ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነግርህ ባደረግኸው ነበር

የሶሪያው ንጉስ የሠራዊት አለቃ ንእማን ከለምጹ ሊያነጻው የሚችል ነቢይ በእስራኤል እንዳለ ሲሰማ በርካታ ስጦታ ይዞ ወደዚያው አቀና፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤልሳዕም “ሂድና በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ በል” አለው፡፡ ንእማን ነቢዩ የአምለኩን ስም ጠርቶና በእጁ ዳሶ የሚፈውሰው መስሎት ስለነበር ተቆጣ፡፡ “ለወንዝማ በሀገሬ በሶሪያ አባናና ፋርፋን የመሳሰሉ ታላላቅ ወንዞች አሉ” ሲልም ተመልሶ ሊሔድ መንገድ ጀመረ፡፡

በቅዱሳን አባቶች የሚነገረንን ነገር እንደዋዛ የምንመለከት፣ አፋቸውን ቃል እግዚአብሔር አቀብሏቸው የተናገሩት ሳይሆን ከራሳቸው ያነቁት የሚመስለን፣ በተለይ በዚህ ዘመን በዘመናዊነት መስፈሪያ የምንለካቸው በርካቶች ነን፡፡ ልክ እንደ ንእማን ከምናውቀው ነገር ጋር የምናነጻጽራቸው፡፡

የንእማንን መቆጣት ያዩ ባሪያዎቹም ቀርበው “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነግርህ ባደረግኸው ነበር፣ ይልቁንስ ታጠብና ንጹህ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ?” አሉት፡፡ ንእማንም ነቢዩ እንዳለው በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፡፡ ስጋውም እንደገና እንደ ትንሽ ብላቴና ስጋ ሆኖ ተመለሰ፤ ከለምጹም ነጻ፡፡ እርሱም ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ተመልሶ የያዘውን ብዙ ስጦታ ውሰድ አለው፡፡ ነቢዩ ግን ሕያው እግዚአብሔርን ይህን አልቀበልም አለው፡፡

ንእማንም “በእውነት እኔ ባርያህ ከእንግዲህ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም የሚቃጠል መስዋዕት አላቀርብምና ከዚህ ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር ልውሰድ አለው፡፡ ጤና ብቻ ሳይሆን በረከትም ጭምር ይዞ ሔደ፡፡ ብዙዎቻችን ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማውያን አባቶች ወዳሉባቸው ቅዱሳት መካናት እንሔዳለን፡፡ ምክርም እንጠይቃለን፣ የነገሩንን ግን አንተገብርም፤ በቀደመ እውቀታችን እንገመግማቸዋለን፡፡ ይልቁንም ለነፍሳችን ድሕነት ይጸልያሉና ለስጋችንና ለነፍሳችን መዳን እንታዘዛቸው፣ በአታቸውንም እናጽና፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ገዳም ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተአምር ያለበት ገዳም ነው። በአለት መሀል የሚገኝ ማር በመነኮሳት ፀሎት ብቻ እየተቆረጠ እንደ እምነት ለፀበልተኞችና ለምእመናን ይሰጣል። ፀበሉ እንደስሙ ሙት ያስነሳ፣ ብዙ ድዉያንን የፈወሰ ሲሆን አሁን በጦርነቱ ምክንያት ወደዚያ የሚሔድ ባለመኖሩ ገዳማውያኑ ተቸግረዋል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000 44 25 98 3 91
አቢሲኒያ ባንክ
14 10 29 4 44

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-09 18 07 79 57
ወይም 09 38 64 44 ላይ 44 በመደወል ማነጋገር ይቻላል፡፡

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago