ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
አንድነት ብቸኛ መዳኛችን ነው።
ከሰሞኑ በወንድሞቻችን መካከል የተጀመሩ የማህበራዊ ሚዲያ ሽኩቻዎች በስክነት ሊታዩና ሊቀረፉ ይገባል።
ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ቡድን የምድር ኃይልን ተጠቅሞ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ለመቀልበስ በፍፁም እንደማይችል ተገንዝቧል።
በዚህ ምክንያት ሌሎች መንገዶችን ለመከተል ወስኗል።
1) የፋኖ ቁልፍ መሪወችን በውስጥ ክፍፍል፣ ስም በማጥፋት፣ በታኝ ሃይሎችን አስርጎ በማስገባት፣ የጎጥና የሃይማኖት አጀንዳወችን በፋኖ ውስጥ በማናፈስ ለዚህ ችግር ዒላማ ያደረጋቸውን መሪወች ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ትግሉን መሪ አልባ እንዲሆን የመበተን ሥራ ለመስራት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ወደ ሥራ ለመግባት ወስኗል።
2) ዋና ዋና የፋኖ መሪወችን በ Signal፣ በድምፅ (voice)፣ Detector (አመላካች) በመጠቀም ይህን ቴክኖሎጂ በDrone ላይ በመግጠምና በማዘመን ጉዳት ለማድረስ የአገሪቱን ሃብት አሟጦ ለዚህ Technology ለማዋል ወስኗል። በተለይም ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምፅ አሳሽ (Sound Detector)፣ በስልክ ግንኙነት ጠለፋ (Signal interception) ዘዴዎችን ለመጨመር የሚያስችል Technology በ15 ቀናት ለማስገጠም ከቻይና መንግስት ጋር በውድ ዋጋ ተዋውሏል የሚል መረጃ ደርሶናል።
ስለሆነም:-
ሀ) የቆምንለትን ህዝባዊ ዓለማ በመመልከት ከምንጊዜውም በላይ በወንድማማችነት ፀንቶ መቆም ያስፈልጋል። የፈለገው ዓይነት የሃሳብና የአሠራር ልዩነት ቢያጋጥም በፍፁም መከባበርና መተሳሰብ ችግሮችን በንግግር መፍታት መቻል አለበት። በጠላት ሴራ የተደለሉ፣ የተሸወዱ፣ ወይም ለይቶላቸው የተሸጡ ወገኖች ቢያጋጥሙ በጥበብ፣ በምስጢር በአደረጃጀት ደንብና ስነምግባር መሰረት ችግሩን መቅረፍ ላይ መተኮር አለበት። ለውጫዊና ውስጣዊ ተፅዕኖ ጆሮ ሳይሰጡ በመርህ ብቻ ተመስርቶ ችግሩን መፍታት ያስፈልጋል። አሰራር እና ደንብ ማክበርና ማስከበር ትልቁ በመርህ የመምራትና የመመራት ጉዳይ ስለሆነ ፤ መርህ ለድርድርና ለማለባበስ መቅረብ የለበትም።
ጠላት ቅስሙ ከመሰበሩ ጋር ተያይዞ የመጨረሻ ያለውን አማራጭ ሁሉ ሊወስድ መፍጨርጨሩ አይቀርም። በዘር ማጥፋት ወንጀል የተዘፈቀ ወንጀለኛ ቡድን ስለሆነ መለስተኛ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ተስፋ ማድረግ አይችልም። ስለዚህ ትግሉ መራራ ነገሮችን በመጋፈጥ ጫፍ ላይ እንደደረሰ ሁሉም እኩል ግንዛቤ እንዲኖረው አጥብቆ መስራትን ይጠይቃል፤ ለትግሉ አደገኛ የሆኑ የአስተሳሰብም ይሁን የተግባር ምልክቶችን ላፍታም ችላ ሳይሉ በንቃት ውስጣችንን የምንፈትሽበት ግዜ መሆን አለበት።
ለ) የ Drone ጥቃቱን ከተጨማሪ መሻሻሎቹ ጋር ለመቋቋም የስልክ ግንኙነት ሥርዐታችንን ማሻሻል፣ምስጢራዊ ማድረግ፤ በተለይ ወሳኝ ሃላፊነት ላይ ያሉ መሪዎች ከስልክ ግንኙነት የሚርቁበት ወይም በምስጢራዊ code የሚገናኙበትን ብልሃት መፍጠር አለብን።
በመሰረቱ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጅ ባለቤቶች ለአሸባሪ ድርጅቶች እና ኃላፊነት ለማይሰማቸው አምባገነን መንግስታት እንዳይሸጥ የምርቱ ባለቤቶች የርዕዮት ዓለም ልዩነት ሳይገድባቸው ስምምነት የሚያደርጉበት (High protocol agreement) የሚባል የስምምነት ዓይነት አለ። ኒውክሊየር አረሮች፣ ረዥም ርቀት ሚሳዔሎች፣ ሰው አልባ በራሪዎች (Drones) በዚህ ስምምነት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
ይሁን እንጅ የእነኝህ መሳሪያወች አምራች አገራት በመበራከታቸው ምክንያት ወታደራዊ ምርቶቹ በአምባገነን መንግስታትና አረመኔዎች ዕጅ እየገቡ ነው። ለምሳሌ Drone አገልግሎት ላይ ከዋለ በርካታ ዓመታት ያለፈው ቢሆንም በቅርቡ ደንታ ቢስ የሆኑ ቱርክና UAE የመሳሰሉ አገራት እያመረቱም እየገጣጠሙም ለገበያ ማቅረብ በመቻላቸው ዛሬ አብይ አህመድን ከመሰለ አረመኔ ዕጅ ሊገባ ችሏል።
በነገራችን ላይ በዓለም ላይ በራሱ አገር ዜጋ ላይ Drone የተጠቀመ አብይ አህመድና አገዛዙ ብቻ ነው።
አጠቃላይ ከስልክ ግንኙነት ሥርዐት እስከ የጠላትን የዘመቻና ቁጥጥር ማዕከል ማውደም እንዲሁም በተደራጀና የተቀናጀ ዓለማቀፍ ዲፕሎማሲ አውዳሚ ወታደራዊ ምርቶች በአብይ አህመድ ዕጅ እንዳይገቡ እስከ ማስቆም የሚሄድ ዝግጅት እና ተግባር ያስፈልጋል።
የአብይ አህመድ ቡድን የኒውክሊየር አረር ስለሌለው እንጅ የአማራ ህዝብ ላይ ለመተኮስ ዓይኑን አያሽም። ትግላችን የህልውና ነው ስንል በዚህ ደረጃ ሊያጠፋን ከሚፈልግ የጠላት ሃይል ጋር ስለገጠምን ነው።
ድል ለአማራ ህዝብ !!!!
ፋኖነት - አሸናፊነት
የትግላችን ውጤት በትጋታችን የሚወሰንና በክንዳችን የሚረጋገጥ ነው!!
💪💪💪 በርቱ እንበርታ!!
የድል መረጃ!!
በደ/ወሎ ለጋምቦ ጠላት ቀባሪ አጥቷል አሉ!!
እልም ነው ጭልጥ ነው!!
የብልፅግናው መንግስት ንፁሃንን በድሮን የመጨፍጨፍ እኩይ ተግባር ቀጥሎበታል::
ትናንት በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅና እናውጋ እንዲሁም በደብረ ኤልያስ ወረዳዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛ ሰብዓዊና የንብረት ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፣ ዛሬ በጠዋት ደግሞ ሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ቀዩ ጋሪያ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ትምህርት ቤት ላይ ሲሆን ት/ቤቱ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል::
የመጨረሻው እስትንፋሱ ላይ የሚገኜው በንጹሃን ላይ ሚቆምረው አገዛዙ የዛሬው ቁልፍ መረጃዎች!!
ደብረማርቆስ መስከረም ሆቴል ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ ጀነራሎች፣ የከተማ ከንቲባዎችና በአጠቃላይ የአካባቢው የአገዛዙ አመራሮች እስከዚህች ሰዓት ድረስ ስብሰባ ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የዛሬው የድሮን ጥቃት እና አሰሳ ዋናው አላማ ትኩረት የማስቀየስ ስራ ሲሆን የጠላት ግብ የነበረው የአገዛዙን የወረዳ አመራሮች ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ባህርዳር ላይ ለሚያደርጉት ስብሰባ በጉዞአቸው ችግር እንዳይገጥማቸው ለማረግ ንጹሃንን ሲጨፈጭፍና ሲያስስ ውሏል።
ስሜነህ ሙላቱ
የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
የአማራ ፋኖ የነፃነት ጉዞ በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አይደለም። ጉዟችን እስከፍፃሜው በመሆኑ በዚህ ትግል ውስጥ መያዝ፣ መቁሰልና መሞት ትንሹ መስዕዋትነት ነው።
ትግላችንን በጀመርን በሁለት ሳምንት ውስጥ በትኜዋለሁ ፤ መለቃቀም ነው የቀረኝ ያለው ብርሃኑ ጁላ እንዳሰበው ሳይሆን ብልፅግና በከፍተኛ ገንዘብ ከውጭ ሃገራት ያስገባውን መሳሪያ እየማረክን ታጥቀን እየገዘገዝነው እንገኛለን።
ጀግናው ውባንተ አባተ ቢሰዋ ከተራ ተዋጊ እስከ ተወርዋሪ ክፍለጦር በስሙ በመሰየም ትግላችንን በማፋፋም መሃል ሃገር አዲስ አበባ ተኩስ መክፈታችን አይዘነጋም።
እናም የአርበኛ አሰግድ በቁጥጥር ስር መዋል አባታችን የጀመረውን የትግል ጉዞ በልጆቹ በእልህና በቁጭት ከመቀጠል ባለፈ ፤ የሚዝል ክንድ የሚታጠፍ ነፍጥ አላነሳንም። እንደውም ለነፃነት ጉዟችን ተጨማሪ ሃይልና ብርታት ይሆነናል እንጅ።
ያለመስዕዋትነት ድል አይገኝም!!
ድል ለአማራ ህዝብ
ሞገሴ ሽፈራው!
NB. (በአንዳንድ ሰርጎ ገቦች የሚሰጡ አስተያየቶች ተጨማሪ መጓተቶችን እንዳይፈጥር ለጊዜው የሃሳብ መስጫውን መዝጋቴን በትህትና ለመግለፅ እወዳለሁ)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago