Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

Description
☀ሁዳ መልቲሚዲያ - ‌🇭‌🇺‌🇩‌🇦 ‌🇲‌🇺‌🇱‌🇹‌🇮‌🇲‌🇪‌🇩‌🇮‌🇦 -قناة هدى الاسلامية

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን!

ለአስተያየት @nuugaa
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 1 week ago
ረመዷን አስራ አምስት የቁርኣን መልዕክት

ረመዷን አስራ አምስት የቁርኣን መልዕክት

1 month, 1 week ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙

*🖌 በኢልያስ አሕመድ*

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
              ››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነውበተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ!
ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445
____
@ustazilyas

1 month, 1 week ago
1 month, 2 weeks ago

የተራዊህ ሰላት በኡስታዝ ከማል ሙሉዉን በዚህ 👇👇👇ሊንክ ያገኙታል ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ተቀላቀሉን
https://youtube.com/shorts/ePIVIqM5SMg?si=ivlNtART84YAIWEM
የቢላል ኮካ መስጅድ እና መድረሳ

YouTube

18 March 2024

የተራዊህ ሰላት በኡስታዝ ከማል ሙሉዉን በዚህ ***👇******👇******👇***ሊንክ ያገኙታል ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ተቀላቀሉን
1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago

የዘካህ ህግጋት አጭር ማብራሪያ

📌 የተሻሻለ አዲስ እትም (ረመዳን 1445 ዓ.ሂ)

📖 የ pdf ፋይል

*🖌 በኢልያስ አሕመድ***

@ustazilyas

1 month, 3 weeks ago

መልዕክት ከወንድም ዩኑስ ሀሰን።

ስለ ፈረሰው ሰላም NE Site መስጂድ።

በንግግሩ መሀል ["የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር አዱኛ" የሚለው "ዶ/ር ተሾመ አዱኛ" በሚል ይስተካከላል ]

1 month, 3 weeks ago
***🌙***የረመዷን ፊዲያዎችንና ከፋራዎችን ማስፈፀሚያና ሚስኪኖችን ማስፈጠሪያ …

🌙የረመዷን ፊዲያዎችንና ከፋራዎችን ማስፈፀሚያና ሚስኪኖችን ማስፈጠሪያ መርሃግብር ከሐኒፍ ጋር!

📍የረመዷን ፊዲያና ከፋራዎን ለማን እንደሚሰጡ አልያም የተቸገሩ ፃመኞችን የት እንደሚያስፈጥሩ ግራ ተጋብተዋል? 

☑️እነሆ ! ሐኒፍ ይህን ጭንቀትዎን ሊያቃልል መሰናዶውን ጨርሶ እርሶን እየጠበቀ ነው።
*📦የአካውንት ስም: ሐኒፍ ኢስላማዊ ድርጅት*

1.ዘምዘም ባንክ..............   (0033239710301)
2.ሒጅራ ባንክ ..................  (100442626002)
3.ንግድ ባንክ ..................... (1000584808137)
4. አቢሲኒያ ባንክ ............... (161161705)
5. ዳሽን ባንክ ..................... (7955764311011)
6. የኦሮሚያ ኅ/ሥራ ባንክ .. (1000094682928)
7. ንብ ባንክ  ....................... (7000050648422)
8. አዋሽ ባንክ  .........(014321240042600)

"ሐኒፍ የከፍታዎ ማዕቀፍ"

1 month, 3 weeks ago
**ታላቅ የመድረሳ መዝጊያና የሀፊዞች ምርቃት ፕሮግራም

**ታላቅ  የመድረሳ  መዝጊያና  የሀፊዞች ምርቃት ፕሮግራም
በቢላል   ኮካ  መስጅድ እና መድረሳ

እንኳን  ለ1445  የረመዳን  ወር  በሰላም   አደረሳችሁ 
  ቢላል  ኮካ መስጅድ እና መድረሳ አመቱን መሉ ሲያስተምራቸው የቆዩትን የመድረሳው  ተማሪዎች የተማሩትን  በሚያቀርቡበት ፣ሁፋዞች በሚመረቁበት እና  የረመዳን ዳእዋ በሚደረግበት ታላቅ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙልን  ስንል  በአክብሮት  ጠርተኖታል

በእለቱ  የሚቀርቡ  ፕሮግራሞች
1 አፍ  የሚያሲዙ የህፃናት መልዕክቶች
2 ቀልቦን  የሚነኩ  የሀፊዞች  የቁርአን   ድምፆች
3  በኡስታዝ   ፉአድ  ነስሩ ( ልጆቻችን  እንዴት  እናሳድግ የሚል   ጠቃሚ ምክር)
እነዚህ እና የተለያዩ  ፕሮግራሞችን  ይዞ  ይጠብቃቹሀል  

መቼ ካሉ   እሁድ  የካቲት  24/06/2016  ከጠዋቱ  2:30 ጀምሮ**

1 month, 3 weeks ago

ለረሱል ﷺ ነሲሀ መሆን

------------------------------------------------

ሸኽ_ኤልያስ_አህመድ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
በ ቲክ ቶክ
@huda4eth
ያግኙን

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas