Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ሰሌዳ | Seleda

Description
የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!

@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month ago
ሲዝንስ የአእምሮ ጤና ማእከል ልምድ ባላቸው …

ሲዝንስ የአእምሮ ጤና ማእከል ልምድ ባላቸው የስነ አእምሮ ባለሙያዎች (Psychiatrists) ፤ የስነ ልቦና ባለሙያዎች  (Clinical Psychologists) እንዲሁም ጠቅላላ ሃኪሞች (General Practitioners) ዘመናዊ ንድፈ ሀሳቦችን በመጠቀም የንግግር እና የመድሃኒት ህክምና እና ክትትል እየሰጠ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱን በአካል በመምጣት አሊያም በቤትዎ ሆነው በስልክ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከሃገር ውጪ ላሉ ደምበኞቻችን ከስልክ በተጨማሪ በ What’s app ከባለሙያዎቻችን ጋር በቪዲዮ ወይም በድምጽ ቆይታ ማድረግም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የአእምሮ አድገት ውስንነት ላላቸው ህፃናት ራስን የመቻል ልምምድ እና ስልጠናም በ Special needs psychology ባለሙያ በሳምንት 1 ቀን እየሰጠን እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
ስልክ +251963400957
        +251962689650
ኢ-ሜይል - seasonsmedicaloffice@gmail.com

1 month ago
**ታይዋን በ25 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ነው …

ታይዋን በ25 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ነው በተባለ ርዕደ መሬት ተመታች

በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካው ርዕደ መሬት፥ በተራራማዋ ኋሊዬን ከተማ አቅራቢያ የተከሰተ መሆኑን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በርዕደ መሬቱ እስካሁን አራት ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ ከፍርስራሾች በህይወት የተረፉ ሰዎችን ለማውጣት የነፍስ አድን ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ባለስልጣናቱ የገለጹት።

ከ50 በላይ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 26 ህንጻዎችም በርዕደ መሬቱ ወድመዋል ነው የተባለው።

ርዕደ መሬቱን ተከትሎ በመዲናዋ ታይፔይና በበርካታ የሃገሪቱ ከተሞች ንቅናቄው የፈጠራቸው ጉዳቶች ሲከሰቱ የሃገሪቱ መንግስትም የሱናሚ አደጋ ጊዜ አውጇል።

ከታይዋን ርዕደ መሬት በኋላ ጃፓንን ጨምሮ በሌሎች የአካባቢው ሃገራት የከባድ ወጀብ አውሎ ነፋስ (ሱናሚ) ምልክቶች መታየታቸውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃዎች አመላክተዋል።

Arada_Fm

1 month ago
እናት ባንኮ በብዙ በጎ ስራዎቿ የምትታወቀውን …

እናት ባንኮ በብዙ በጎ ስራዎቿ የምትታወቀውን ሜላት ንጉሴን የምስጋና እና እና የ 50 ሺ ብር አክስዮን አበርክቶላታል።

ሜላት ንጉሴ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በጎ ተግባራትን እየፈፀመች የምትገኝ ጠንካራ ሴት ናት።

በዚህ ወቅት ለብዙ ወጣቶች ጭንቀት የሆነውን ስራ ማጣትን ለመቅረፍም እየተጋች ትገኛለች ። ከ 1000 በላይ ስራ የሌላቸውን ወጣቶች ስራ እንዲያገኙ ምክንያት ሆናለች።

ታዲያ ይህንን እናት ባንክ መልካምነቷንና ለማኅበረሰቡ እያደረገች ያለችውን በመመልከት የ50ሺ ብር የእናት ባንክ አክስዮን በስጦታ አበርክተውላታል።

3 months ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ የሚያደርገውን …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ሊያሳድግ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካናዳ ዋና ከተማ ቶሮንቶ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ከአምስት ወደ ሰባት ሊያሳድግ መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ የሳምንታዊ በረራ ማሻሻያውን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምርም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ጠቁሟል።

የካናዳ የንግድ፣ የቴክኖሎጂ እና የባህል ማዕከል ወደሆነችው ቶሮንቶ ከተማ የሚያደርገውን አምስት ሳምንታዊ በረራ ከፍ በማድረግ በሰባቱም የሳምንቱ ቀናት በረራ ማድረግ እንደሚጀምርም ነው አየር መንገዱ ጨምሮ ያስታወቀው።

3 months ago
**በዛሬው እለት ፒያሳ አካባቢ ባጋጠመ የእሳት …

በዛሬው እለት ፒያሳ አካባቢ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ አምስት የንግድ መደብር ወድሙ

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ የጄኔሬተር እና የተለያዩ የእሳት ማጥፊያ መሳሪዎች መሸጫ የሆኑ አምስት ሱቆች መውደማቸውን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

ዛሬ ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም  ከቀኑ 7:14  ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ሸዋ ዳቦ እየተበላ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ አምስት የንግድ ሱቆች የተቃጠሉ ሲሆን በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መደረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የንግድ ሱቆቹ  የህንጻ መሳሪያዎች የጀኔሬተር እና የእሳት ማጥፊይ መሸጫዎች ሲሆኑ ከንግድ  ሱቆቹ ዉስጥ በርካታ ንብረት ማዉጣት መቻሉም ተነግሯል ።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ዘጠኝ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሀምሳ ሰባት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት በተደረገ ርብርብ ወደሌሎች የንግድ ቤቶች ሳይዛመት መቆጣጠር ተችሏል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷል።

ዳጉ_ጆርናል

3 months ago
ሰሌዳ | Seleda
3 months, 1 week ago
መንግስት በአማራ ክልል ለመሰበሰብ ካቀደው ገቢ …

መንግስት በአማራ ክልል ለመሰበሰብ ካቀደው ገቢ የእቅዱን 50 በመቶ ብቻ መሰብሰቡን ገለፀ

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ፣ በግማሽ በጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ካቀደው አጠቃላይ የገቢ መጠን ውስጥ የሰበሰበው ግማሹን ብቻ እንደኾነ አስታውቋል። በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ 72 ቢሊዮን ብር መኾኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በግማሽ ዓመቱ የሰበሰበው ገቢ ግን 17 ቢሊዮን ብር ገደማንቾ ብቻ እንደኾነ ገልጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተሻለ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም ያስመዘገቡት፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች እንዲኹም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ናቸው ተብሏል። ቢሮው ዝቅተኛ ገቢ የሰበሰበው፣ በዋናነት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ መኾኑን ጠቅሷል።

3 months, 1 week ago
ብሄራዊ ባንክ በጀት ዓመት መገባደጃ ላይ …

ብሄራዊ ባንክ በጀት ዓመት መገባደጃ ላይ የአገሪቱን የዋጋ ንረት ወደ 20 በመቶ ለማውረድ አቅዷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በቅርቡ የቀረጸው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን በሦስት ዕጥፍ ለማሳደግና ለኹለት ወራት ከግማሽ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት የሚበቃ መኾኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ እስከተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ብቻ ላንድ ወር ሸቀጦችን ለማስገባት የሚበቃ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ክምችት ለመያዝ እንዳቀደ ዘገባው ጠቅሷል። ባንኩ ባኹኑ ወቅት ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ካንድ ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ሸቀጦችን ለማስገባት የሚበቃ ነው።

አንዱ የባንኩ ስትራቴጂ ግብ፣ በተያዘው በጀት ዓመት መገባደጃ ላይ የአገሪቱን የዋጋ ንረት ወደ 20 በመቶ ማውረድ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

3 months, 1 week ago
What is the capital of the …

What is the capital of the Amhara National Religional state🤨

እስቲ ፖተሊካችሁን ህፃናት በማይደርሱበት ስፍራ አስቀምጡ🙊

3 months, 2 weeks ago
የወደፊት ህይወትዎን ዛሬ ላይ ብሩህ ያድርጉ! …

የወደፊት ህይወትዎን ዛሬ ላይ ብሩህ ያድርጉ! ከጀመርናቸው አዳዲስ አማራጮች የሚፈልጉትን በመጠቀም የህይወትዎን አቅጣጫ ያሳምሩ!

አራት ኪሎ ትምህርት ሚንስቴር ጎን አምባሳደር ሞል ላይ እንገኛለን!
ባካል በመምጣት መረጃውን መስማት ይችላሉ ወይም
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን

0951259070
0908436910

መደወል ይችላሉ!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas