ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ተአምረኛው የጃንሆይ የጃማይካ ጉዞ ሚስጥሮች! - ዶኪዩመንታሪ ፊልም | Haile Selassie Visit To Jamaica
በሉቱኒያ የጭነት አውሮፕላን ተከስክሶ የአንድ ሰው ሕወት አለፈ‼️
የዲ ኤች ኤል የጭነት አውሮፕላን በሉቱኒያ ተከስክሶ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡
ቦይንግ 737-400 የጭነት አውሮፕላኑ ከጀርመን ሌፕዚሽ ከተማ ተነስቶ በሉቱኒያ ዋና ከተማ ወደሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ሲቃረብ ነው በአቅራቢያው በሚገኝ አንድ ቤት ላይ ተከስክሶ አደጋው ደረሰው።
የሀገሪቱ ባለሥልጣናት የአደጋው መንስኤ እስካሁን አለመታወቁን ገልፀዋል።
በተከሰከሰበት ቤት ዙሪያ ያሉ መሠረተ ልማቶች በእሳት የተጎዱ ቢሆንም፤ በአካባቢው ያሉ ሰዎችን ማትረፍ መቻሉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት መናገራቸውን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
ሂዝቦላህ በሚሳኤሎችና ድሮኖች በመታገዝ እስራኤል ላይ ጥቃት ፈጸመ‼️
በእስራኤል እና በሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦህ መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡
ከሰሞኑ እስራኤል በሊባኖስ መዲና ቤሩት የተለያዩ አቅጣጫዎች በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በጥቃቱ እየደረሰ ያለውን ውድመት ተከትሎም በቤሩት እስከ ቀጣዩ ጥር ወር ድረስ ት/ቤት መዘጋቱን የሊባኖስ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ለጥቃቱ አጸፋም ሂዝቦላህ 340 በሚሆኑ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙ ነው የተገለጸው፡፡
በጥቃቱም በሰሜንና ማዕከላዊ እስራኤል በርካታ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን÷ ህንጻዎችና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውም ተጠቁሟል፡፡
እስካሁን ድረስ በ11 ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት መድረሱን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
በጥቃቱ ከደረሰው ውድመት ባሻገር በሚሊየን የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከጥቃቱ ሽሽት ወደ ምሽግ መግባታቸው ተጠቁሟል፡፡
ከሳምንት በኋላ ዛሬም የመርካቶ ሱቆች በአብዛኛው ዝግ ሆነዋል
በዛሬው እለት በርካታ የመርካቶ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ዝግ እንዳደረጉ ታውቋል፣ ምክንያቱ ደግሞ ከሰሞኑ በመንግስት አካላት እና በነጋዴዎች መካከል ውዝግብ የፈጠረው የገቢዎች የደረሰኝ አጠቃቀም ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።
ነጋዴዎች እየተጠየቁ ያሉት የደረሰኝ ቅጣት እና የቅጣት አፈፃፀም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲናገሩ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ በመደረጉ ያነሱት ጉዳይ ነው ብሏል።
"በግምት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ ሱቆች ዛሬ ዝግ ናቸው" ያለው አንድ ነጋዴ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር የተሳተፉባቸው የኮንትሮባንድ ምርቶች ወደ ገበያ ያለደረሰኝ እየተበተኑ ነጋዴውን ደረሰኝ ቁረጥ ማለት አግባብ አይደለም ብሏል።
የመርካቶ ነጋዴ የሱቅ መዝጋት አድማው "እስከ ስድት ቀን ሊቆይ ይችላል፣ እየተነጋገርን ነው" በማለት ተናግሯል።
መንግስት ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም የተገኘ ነጋዴ ንብረቶቹ ይወረሳሉ በሚል 'ሀሰተኛ መረጃ' አንዳንድ ባለንብረቶችና ነጋዴዎች ሱቃቸውን የመዝጋትና እቃዎችን የማሽሽ ሁኔታዎች አሉ ቢልም ነጋዴዎቹ የዛሬ ሳምንት ገደማ ይርጋ ሀይሌ የገበያ ማዕከል ደረሰኝ አልተቆረጠም በሚል ምክንያት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ደንብ አስከባሪዎች እንሰወሰዱባቸው ተናግረዋል።
የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር የለም - የመከላከያ ሚኒስቴር
በባሕርዳር የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር አለመኖሩን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷የኢፌዴሪ አየር ሃይል ካሉት "ቤዞች" አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድብ መሆኑን አንስቷል፡፡
በትናንትናው ዕለት በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ እንደነበርም አስታውሷል፡፡
ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡
ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ በረራ በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን÷ የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቅቋል ብሏል።
"የጠላት ሁለንተናዊ አቅምና የፕሮፖጋንዳ መስክ መክሰርና መከስከስ ካልሆነ በስተቀር የተከሰከሰ ሄሊኮፕተር የለም" ሲልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago