ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ውርስ
~
ክፍል፡1
ውርስ በሙስሊሞች መካከል ግዴታ መሆኑ በቁርኣን እና በሱንና ተደንግጓል።
አሏህ እንዲህ ይላል፡-
« ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት (ንብረት) ድርሻ አላቸው፤ ለሴቶችም
ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ከእርሱ ካነሰው እና ከበዛው ድርሻ አላቸው፤ግዴታ የተደረገ ድርሻ (ተደርጓል።)» ቡኻሪ እና ሙስሊም
“አላህ በልጆቻችሁ (ውርስ በሚከተለው) ያዛችኋል። ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ
ብጤ አለው፤…” [አል ኒሳዕ፡ 11]
መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«የውርስ ድርሻን ለባለ ድርሻው አድርሱ። የተረፈው ከሁሉም በበለጠ በዝምድና ቅርብ ለሆነው ወንድ ነው።» ብለዋል።
በሌላ ዘገባም ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
“አሏህ በእርግጥ ለሁሉም ባለ ሐቅ ሐቁን ሰጥቶታል፤ ስለዚህ ለወራሽ ኑዛዜ
አይኖረውም።”
ነብዩ (ﷺ) የውርስ ህግጋቶችን አስመልክቶ ሰዎች እንዲማሩ አነሳስተዋል። በብዙ ሐዲሶቻቸውም ውስጥ ሰዎች እንዲማሩ ቀስቅሰዋል።
ነብዩ (ﷺ)፦
« የውርስ ህግጋቶችን ተማሩ፤ ሰዎችንም አስተምሩ፤ እርሱ የእውቀት ግማሽ ነውና፤
እርሱም ይረሳል፤ ከህዝቦቼ መጀመሪያ የምነጠቀውም እርሱ ነው።» ብለዋል።
ሱፍያን ኢብን ዑየይናህ አሏህ ይዘንላችውና
እንዲህ ብለዋል፡- “የእውቀት ግማሽ ነው
የተባለበት ምክንያት ሁሉም ሰዎች ስለሚፈተኑበት ነው።”
የውርስ ምክንያቶች፦
የውርስ ምክንያቶች ሶስት ናቸው።
እነሱም፦
- ዝምድና
- ጋብቻ (ንካሕ)
- ባሪያን ነጻ ማውጣት ናቸው።
ሀ. ዝምድና
ዝምድናን በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን። እነሱም፡አባት፣ እናት፣ አያት፣ ቅድመ አያት፣ እያለ በሁለቱም በኩል ርቆ የሚሄድ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ እያለ የሚወርድ ወንድም፣ የወንድም ልጅ፣ እህት የእህት ልጅ፣ … አጎት፣ የአጎት ልጆች፣… አክስት፣ የአክስት ልጆች፣ … እያለ የሚቀጥል።
ለ. ጋብቻ (ኒካህ)
ትክክለኛ የጋብቻ ህግ የተፈጸመበት የባልና ሚስት ትስስር ወይም ጥምረት ሲሆን፣ ጎጆ ባይወጡ እና የግብረ ስጋ ግንኙነት ባይፈጽሙም እንኳ ትክክለኛ ኒካህ ከተደረገ መወራረስ ይችላሉ።
አሏህ እንዲህ ይላል፡-
“ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት (ንብረት) ለእነርሱ ልጅ ባይኖራቸው ግማሹ አላችሁ፤…” (አል ኒሳእ፡ 12)
ሐ. ባሪያን ነጻ ማውጣት
አንድ ሰው አንድ ባሪያን ሴትም ይሁን ወንድ ነጻ ካወጣ እና ከባርነት ነጻ የተደረገው ሰው ወራሽ ከሌለው ለዋለለት ውለታ ሲባል ነጻ ያወጣው ሰውዬ ይወርሰዋል፤ ነጻ ያወጣው ሰውዬም ሞቶ ከሆነ የእርሱ ዐሰባዎች¹ ወንድ የሆኑት ብቻ ይወርሱታል።
ቡኻሪ፣ ነሳኢ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ
ነብዩ ﷺ፦
“ዝምድና (ከባርነት) ነጻ ላደረገ ሰው ነው።” ብለዋል።
ውርስን ክልክል የሚያደርጉ ነገሮች
ውርስን ክልክል የሚያደርጉ ነገሮች ስድስት ናቸው። እነሱም፦
- ኩፍር (ክህደት)
- ግድያ (ተወራሹን መግደል)
- ባሪያ መሆን
- ዝሙት (በዘሙት የተወለደ ልጅ እና በዝሙት የወለደ አባት አይወራረሱም)
- መረጋገም (ሊዓን)²
- ሙት ሆኖ የተወለደ ህጻን ናቸው።
₁_ ዐሰባህ፦ ማለት ብቻውን ሲሆን ያለውን ንብረት ጨርሶ (አጠቃሎ) መውረስ የሚችል ዘመድ ማለት ነው።
₂_ ሊዓን፡- ባል ሚስቱን ዝሙት ሰርታለች ብሎ ለሸሪዓ ፍርድ ቤት ይከሳል፤ ነገር ግን፣ ከእርሱ ውጪ ሌላ ምስክር አልተገኘም፤ ሚስት ውሸቱን ነው በማለት ክሱን ትቃወማለች፤ በዚህ ጊዜ ዳኛው ባልዬውን አራት ጊዜ “ወሏሂ እውነቴን ነው” ብሎ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ካደረገው በኃላ በአምስተኛው ለይ ውሸቴን ከሆነ የአሏህ እርግማን ይውረድብኝ ብሎ እንዲል ያደርገዋል፤ ሴትዬዋም በተራዋ በአሏህ ስም አራት ጊዜ ምላ ውሸቱን መሆኑን ካረጋገጠች ቡኃላ አምስተኛው ላይ ባሌ የተናገረው እውነቱን ከሆነ የአሏህ እርግማን በእኔ ላይ ይሁን በማለት ዝሙት ላለመስራትዋ በመሓላ ካረጋገጠች ቅጣቱ ይቀርላታል። ባልም ዋሸህ ተብሎ አይገረፍም።ከዝያም የሁለቱም ትዳር እንዲፈርስ ይደረጋል። ይህ መሃላቸው ሊዓን ይባላል።
Telegram
ፊቅህን ለማወቅ
ይህ ቻናል የፊቅህ ነጥቦችን ብቻ እያስተላለፍን የምንማማርበት ቻናል ነው፡፡
ስለምን እንማማር ከፊቅህ?
የዚህ ቤት ሰዎች ግን አላችሁ ? ወይስ ... ?
ከሶላት በኋላ የምንላቸው ዚክሮች
1- ሶስት ጊዜ ኢስቲጝፋር (አስተጝፊሩሏህ) ካሉ በዃላ እንዲህ ማለት፦ “ አሏሁመ አንተ ሠላም ወሚንከ ሰላም ተባረክተ ያ ዘል ጀላሊ ወል ኢክራም’’ [ሙስሊም]
ትርጉም ፦(አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ፡፡ ሰላምም ካንተ ነው፡፡ የክብርና የሞገስ ባለቤት የሆንከው ጌታ የተባረክ ነህ፡፡)
2- “ ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ፤ ላ ኢላሀ አልለላሁ ላ ነዕቡዱ ኢልላ ኢይያሁ፤ ለሁ-ንኒዕመቱ ወለሁ-ልፈድሉ፤ ወለሁ-ሥሠናኡ-ልሐሰን፤ ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ሙኸሊሲይነ ለሁ-ድዲይነ ወለው ከሪሀ-ልካፊሪዉን፡፡” [ሙስሊም]
ትርጉም ፦ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ ብጤ የለውም፡፡ ንግስናም ለርሱ ነው፡፡ ምስጋናም ለርሱ ነው፡፡ እርሱም በሁለም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ በርታትም ሆነ ነገሮችን መለወጥ በአላህ ካልሆነ በስተቀር የለም፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላን አናመልክም፡፡ ጸጋም ለእርሱ ነው፡፡ ችሮታም ለእርሱ ነው፡፡ መልካም ውዳሴም ለእርሱ ነው፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ከሐዲያን የሚጠሉ ቢሆንም ለእርሱ ቅን ታዛዦች ነን፡፡)
3- “ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪይከ ለሁ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር፤ አልላሁምመ ላ ማኒዐ ሊማ አዕጠይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕት ወላ የንፈዑ ዛል ጀድዲ ሚንከ-ልጀድ፡፡” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ትርጉም፦ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ ንግስናም ለእርሱ ነው፡፡ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ቻይ ነው- አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ከልካይ የለም፡፡ ለከለከልከውም ሰጪ የለም፡ ፡ ካንተ ችሮታ ይበልጥ የሌላ ችሮታ ፈጽሞ አይጠቅምም፡፡)
4- “ሱብሓነ-ልሏህ” (33) ጊዜ፡፡ “አልሐምዱሊልሏህ” (33) ጊዜ፡፡ “አልሏሁ አክበር” (33) ጊዜ፡፡ መቶ መሙያውን “ላ ኢሏሀ አልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ወሁወ ዓላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር ” አንድ ጊዜ ማለት፡፡[ሙስሊም]
5- “አላልሁምመ አዒንኒ ዐላ ዚክሪከ ወሹክሪከ ወሑስነ ዒባደቲክ፡፡
ትርጉም፦ (አላህ ሆይ! አንተን በማስተወስ፣ አንተን በማመስገን፣ ማመለክህን በማሳመር ላይ እርዳኝ፡፡) [አቡ ዳውድ እና ነሣኢይ]
6- “አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነ-ልቡኽሊ ወአዑዙ ቢከ ሚነ-ልጁብኒ፣ ወአዑዙ ቢከ አን ኡረድደ ኢላ አርዘሊ-ልዑሙሪ ወአዑዙ ቢከ ሚን ፊትነቲድዱንያ ወአዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢ-ልቀብር፡፡” [ቡኻሪይ]
ትርጉም፦ (አላህ ሆይ! ከንፉግነት ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈሪነትም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ወደእርጅና እድሜ ከመመለስም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከምድራዊው ሕይወት ፈተና ባንተም እጠበቃለሁ፡፡ ከቀብር ቅጣትም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡)
7- “ረብቢ ቂኒ ዓዛበክ የውም ተብዓሡ ዒባደክ”[ሙስሊም]
ትርጉም፦ (ጌታዬ ሆይ! ከቅጣትህ ጠብቀኝ ባሮችህን በምተሰበስብበት ቀን )
8- “ቁል ሁወሏሁ አሐድ” “ቁል አዑዙ ቢረብቢ-ልፈለቅ”ን እና “ቁል አዑዙ ቢረብቢ-ንናስ” መቅራት፡፡[አቡዳውድ]
° ከመጝሪብ እና ከሱብሂ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ ይደጋገማሉ።
9- “አየቱ-ልኩርሲይን” መቅራት
10- ከሱብሂ እና ከመግሪብ በኋላ አስር ጊዜ ይህን ማለት “ ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪይከ ለሁ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ዩህይ ወዩሚት ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።”[ቲርሚዚይ]
ትርጉም፦(ከአሏህ በስተቀር (በእውነትም የሚመለክ) ሌላ አምላክ የለም። ብቻውን ነው። ብጤ የለውም። ንግስናም ለእርሱ ነው። ምስጋናም ለርሱ ነው። ህያው ያደርጋል። ሙትም ያደረጋል። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።)
√ ከሶላት በኋላ ዚክር ስናደርግ ሌሎች ተፈጻሚ መሆን ያለባቸው ነገሮች
- ዚክሮችን በእጅ ማድረግና በቀኝ እጅ ማድረግ።
-እኚህን ዚክሮች ስናደርግ ቦታ ሳንቀይር ሶላት በሰገድንበት ቦታ ላይ ሊኾን ይገባል።
√ ከሶላት በኋላ የሚባሉት ዚክሮች ያላቸው ትሩፋት
- ግዴታዊ ከኾኑ ሶላቶች ኋላ ያሉት ዚክሮች በተገቢው መልኩ ማስገኘት እና በዚህ ተግባር ላይ ዘውታሪ መሆን በቀላሉ 55 የሚሆኑ ሱንናዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንዲገኝ ይረዳዋል።
- እኚህን ዚክሮች በማድረግ ዘውታሪ የኾነ ሶዶቃህ እንዳደረገ ይቆጠርለታል። መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል፦ “ እያንዳንዱ ተስቢሕ (ሱብሐነልሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተሕሚድ (አልሐምዱሊሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተህሊል (ላኢላሀ ኢልለሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ሰደቃህ ነው፡፡”[ሙስሊም]
- በእኚህ ተስቢሆች ላይ ዘውታሪ የኾነ ጀነት ውስጥ 500 ዛፎች ይተከሉለታል። መልእክተኛውﷺ ከእለታት አንድ ቀን አቡሑረይራ ዛፎችን እየተከለ ባለበት መንገድ አለፉና እንዲህ አሉት ፦ “ አንተ አቡ ሑረይራ ሆይ! ላንተ ከዚህ የተሻለ መትከልን ላመላክትህን? እርሱም አዎን! አለ። ነብዩምﷺ ሱብሐነልሏህ፣ አልሐምዱሊሏህ፣ አሏሁ አክበር በል። በየአንዳንዱ ተስቢሕ ጀነት ውስጥ አንድ ዛፍ ይተከልልሃል አሉት።” [ኢብን ማጃህ]
- በእርሱና በጀነት መካከል ሞት እንጂ ምንም የለም ተብሏል “አየተል ኩርሲይ”ን ከሶላት በዃላ ለቀራ ።
- ወንጀሉ የባህር አረፋ እንኳ ቢኾን ከላይ የተጠቀሱ ተስቢሆች(ዚክሮች)ን ያለ ወንጀሉ ይማርለታል ተብሏል።[ሶሂህ ሙስሊም]
- በእኚህ ዚክሮች ላይ ዘውታሪ የሆነ ከአኼራም ኾነ ከዱንያ ክስረት የተጠበቀ ነው።
- በፈርዱ ሶላት ላይ የተገኘውን ጉድለትና ክፍተት አሟይ ናቸው።
በሁለቱ ሱጁዶች መካከል የምንቀመጥበት አቀማመጥ ሁኔታን አስመልክቶ ሁለት አይነት ባህሪዎች ሲኖሩ ፦ የመጀመሪያው ኢፍቲራሽ ሲሰኝ ፣
ሁለተኛው ደግም ኢቅዓእ ይባላል።
ኢፍቲራሽ ማለት ፦ ቀኝ እግርን ቀጥ አድርጎ በማስቀመጥ ግራ እግርን አጥፎ የግራ እግር የውስጥ መዳፍ ላይ መቀመጫን ማስቀመጥ ነው።
ይህ አይነቱ የአቀማመጥ ሁኔታ በሁሉም የእውቀት ባለቤቶች ስምምነት የፀደቀ አቀማመጥ ነው።[ አልሙምቲዕ 3/126]
ኢቅዓእ ፦ ሁለቱንም እግሮቹን ቀጥ አድርጎ ጣቶችን ከምድር ጋር በማጠፍ በሁለቱ የእግር ተረከዞች ላይ መቀመጥ ነው ።
ይህ አይነቱን አቀማመጥን አስመልክቶ ከጧውስ የተዘገበው ሃዲስ የአቀማመጡን መደንገግ አመላካች ነው። ጧውስ እንዲህ ይላል፦
“ ለኢብን ዓባስ ስለ ኢቅዓእ ጠየቅነው ፤ እርሱም እንዲህ አለ ፦ እርሷ ሱንናህ ናት ! ። እኛም እንዲህ አልንው ፦ እኛ ይህን ተግባር (በእግሮች) ያለመረጋጋት አድርገን ነው ምንቆጥረው ? ኢብን ዓባስም እንዲህ አለ፦ ይህ የነብይህ ሱንና ነው ።’’
[ ሶሂህ ሙስሊም]
ኢማም አን-ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፦
እወቅ ! ኢቅዓእን አስመልክቶ ሁለት ሃዲሶች የተዘገቡ ሲኾን፤ በዚህ በላይኛው ሃዲስ ላይ ያየነው ሱንናህ መኾኑን የሚገቅስ ሲኾን ፤ በሌላ ሃዲስ ደግሞ ክልከላ መጥቶበታል። (ክልከላን የሚያመላክቱት) ሃዲሶች ባጠቃላይ ሰነዶቻቸው ደካሞች ናቸው ።[ ሸርህ ሙስሊም 5/19]
የእውቀት ባለቤቶች የኢቅዓእ አቀማመጥ አተረጓጎምን አስመልክቶ ብዙ ልዩነቶች ሲኖሯቸው ፤ ከነዚህ የታወቁትና ከልዩነቶች የፀዱት ሁለት ባህሪዎች እንዷሏት የሚጠቅሱት ናቸው።
አንደኛው ፦ የተጠላው አቀማመጥ ሲኾን
ሁለተኛው ፦ ሱንናህ የሆነው አቀማመጥ ነው ።
ሃሣቡን ለመረዳት ከታች የለጠፍኩትን ምስል ተመልከቱ !
ተህየተል መስጂድ
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦
‛‛ አንዳችሁ መስጂድ ከገባ ሁለት ረከዓዎችን ሳይሰግድ እንዳይቀመጥ ።’’
[ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ይህን እና ከዚህ ሃዲስ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ሃዲሶችን በመያዝ አንድ ሰው መስጂድ ሲገባ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓህ መስገድ ይኖርበታል። ተህየተል መስጂድ የሚለው ስያሜ በሃዲስ የተረጋገጠ ቃል ባይሆንም፤ ይህ ሶላት ፉቅሃዎች(የፊቅህ ሊቃውንት)ዘንድ ተህየተል መስጂድ በመባል ይጠራል።
የእውቀት ባለቤቶች በዚህች ሶላት ብያኔ ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖራቸው፤ አብዘሃኛዎቹ የፊቅህ ምሁራን ሱንና መሆኗን ይጠቅሳሉ። ሌሎች ደግሞ ግዴታ ነው ብለዋል። ያም ሆነ ይህ ሊተው የማይገባ ጥብቅ ሱንና ነው የሚለው አመዛኝ ነው።
- ተህየተል መስጂድ አንድ ሰው በየትኛውም ጊዜ(በተከለከሉ ጊዜያቶች ላይ ፣ ኹጥባ እየተደረገ፣ ትምህርት እየተሰጠ...) ወደ መስጂድ ሲገባና መቀመጥ ሲፈልግ የሚሰግዳት ሶላት ናት።
ነብዩ ﷺ የጁሙዓን ኹጥባ እያደረጉ ሳለ አንድ ሰው መስጂድ ገብቶ ሲቀመጥ ሁለት ረከዓህን እንዲሰግድ አዘውታል። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
- አንድ ሰው መስጂድ ገብቶ ሶላተል ጀናዛን ቢሰግደ ፣ ሰጅደተ ቲላዋ(የቁርአን ሱጁድን) ቢያደርግ ወይም የዊትር አንዱን ረከዓህ ቢሰግድ ተህየተል መስጂድ አስገኘ አይባልም ። ሃዲሱ ላይ ''ሁለት ረከዓህን ይስገድ'' ተብሏልና ከሁለት ረከዓህ ያነሠ ተህየተል መስጂድን አያብቃቃም።
- ነገር ግን አንድ ሰው መስጂድ ገብቶ የትኛውንም ትርፍ (ባለ ሁለት ረከዓህ) ሶላት ወይም ዋጂብ ሶላትን ከሰገደ ተህየተል መስጂድ መስገድ አይጠበቅበትም ።
- ተህየተል መስጂድ ብሎ ነይቶ የሚሰግደውም ራሱን የቻለ ሶላት የለውም። እንድ ትርፍ ሶላት ነይቶ አንድን ሶላት ከሰገደ ያብቃቃዋል።
YouTube
ዘካተል ፊጥር !
ዘካተል ፊጥር ምን ያህል ነው ሚወጣው ? ዘካተል ፊጥር በገንዘብ ይወጣልን ? ዘካተል ፊጥር ለማን ነው ሚሰጠው? መች ነው ሚሰጠው ? ... #ረመዳን #ዘካተል\_ፊጥር #ኢስላም #ዳዕዋ
ኢዕቲካፍ
|> ኢዕቲካፍ ማለት በቋንቋ ደረጃ፦ በአንድ መልካም ወይም መጥፎ ነገር ላይ መዘውተር እና ነፍስን በእርሱ ላይ መገደብ ማለት ነው።
|> እንደ ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ፦ አንድ ሰው በተነጠለ (መስፈርቱን በጠበቀ መልኩ) ወደ አሏህ መቃረብን ፈልጎ መስጂድ ላይ የሚያደርገው ማዘውተር "ዒዕቲካፍ" ይባላል።
ዒዕቲካፍ ብይኑ ሱንናህ ነው። ይህ ድርጊት ከረመዷን የመጨረሻ አስርቱ ቀናቶች ላይ ለይለተል ቀድር በመኖሯ ምክንያት ይበልጥ የጠነከረ ሱንናህ ይሆናል።
|> የዒዕቲካፍ የጊዜ ገደብ
አንድ ሰው ዒዕቲካፍን አደርጋለሁ ብሎ የተሣለ ከሆነ በተሣለበት ጊዜ መፈፀም ይኖርበታል። ከዛ ውጪ ባለው በተፈቀደው 'ልቅ' በሆነው የዒዕቲካፍ ድርጊት እስከዚህ ጊዜ የሚባል የጊዜ ገደብ የለውም። ሰለሆነም መስጂድ ላይ የተወሰነ ጊዜያትንም ቢያዘወትር ኢዕቲካፍ ይሰኛል።
|> የዒዕቲካፍ ማዕዘናት
- ኒያህ
- መስጂድ ውስጥ መዘውተር
- ዒዕቲካፍ አድራጊው መገኘት
- ዒዕቲካፍ የሚደረግበት ቦታ(መስጂድ) መሆን አለባቸው።
|> ዒዕቲካፍ ለማድረግ ፆመኛ መሆን መስፈርት ነውን?
በዚህ ነጥብ ላይ የእውቀት ባለቤቶች ልዩነት ሲኖራቸው ከፊሎች ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት አይሆንም ሲሉ ሌለኞቹ ደግሞ ፆምን መስፈርት አድርገዋል።
- ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ አንሁ
" በጃሂሊያ ዘመን በለሊቱ ክፍል መስጂደል ሃረም ላይ ዒዕቲካፍን ሊያደርግ ተስሎ ነብዩ ﷺ "ስለትህን ሙላ" ብለውታል። ቡኻሪይ እና ሙስሊም
-ይህንን ሃዲስ በመያዝ ፆም በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ስለማይኖር ዒዕቲካፍ ለሚባለው ድርጊት ፆም እንደመስፈርት አይወሰድም ብለዋል።
-ነብዩﷺ አስርቱን የመጀመሪያ የሸዋል ቀናቶች ዒዕቲካፍ አድርገው ነበር።[ቡኻሪ እና ሙስሊም]
ከነዚህ አስርት ቀናቶች መካከል አንዱ ዒድ ሲሆን በዒድ ፆም መፆም የተከለከለ ነው። ስለሆነም ይህ ሃዲስም የሚያመላክተው ለዒዕቲካፍ ፆም መስፈርት አለመሆኑ ነው። ብለዋል።
-ሌለኞቹ፦ ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ብላለች "ዒዕቲካፍ ለሚያደርግ አካል ሱንናው ፆመኛ መሆኑ ነው።" [አቡዳውድ]
-አንድ ሶሃብይ "ሱንናው እንዲህ ነው..." ካለ ይህ ንግግሩ ወደ ነብዩﷺ የተጠጋ ንግግር(የነብዩ ንግግር) ተደርጎ ይወሰዳል። ብለዋል።
-ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላል፦ አሏህ ዒዕቲካፍን ከፆም ጋር አቆራኝቶ እንጂ አልጠቀሰም፤ ነብዩም ከፆም ጋር እንጂ አልፈፀሙትም።
[ዛዱል መዓድ 2/87]
ቃዲ ዒያድ እንዲህ ይላል፦ "ይህ ንግግር የአብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤት ንግግር ሲሆን፤ አመዛኙና ትክክለኛውም እርሱ ነው።"[ነስቡራያህ 2/489] ሲል ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት መሆኑን አመዝኗል።
ይህን አቋም ኢብን ተይሚያህ፣ ጀሷስ[አህካሙል ቁርዓን1/245] እና ኢብን ዓብድል ሐዲይ ያመዘኑት አቋም ነው።
-ነብዩ የሸዋል የመጀመሪያ አስርት ቀናቶችን ዒዕቲካፍ አድርገዋል ለሚለው የሠጡት ምላሽ
ኢብን ዓብድል ሐዲይ እንዲህ ብለዋል፦
" ነብዩﷺ ያደረጉት ዒዕቲካፍ የመጀመሪያው የፊጥር ቀን (የዒድ ቀን) መሆኑን በግልፅ አልተጠቀሰም(ግልፅ አይደለም)። በሁለተኛው ቀን ሊሆንም ይችላል ዒዕቲካፍ ያደረጉት። እንደውም ይህ ነው ግልፅ ሆኖ ሚታየው።"
[ነስቡ ራያህ2/489]
|> የዒዕቲካፍ ቦታ
አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
[እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው፡፡]
ዒዕቲካፍ የሚደረግበት መስጂድ የጀመዓ ሶላት የሚደረግበት መስጂድ መሆኑ የተሻለ እና በላጭ ነው። ከፊሎች እንደ መስፈርት ጠቅሰውታል።
ኢብን ቁዳማህ እንዲህ ይላል፦
" ይህ እንደመስፈርት የተቀመጠው የጀመዓ ሶላት ዋጂብ(ግዴታ) በመሆኗ ነው። አንድ ሰው በጀመዓ ማይሰገድበት መስጂድ ዒዕቲካፍ በማድረጉ ሁለት ነገሮችን ያጣል፤ አንደኛው ግድ የሆነችውን የጀመዓ ሶላት መተው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መቆጠብ እየቻለ ካለበት መስጂድ ጀመዓ ሶላት ወደ ሚሰገድበት መስጂድ በመውጣት ዒዕቲካፍ ካደረገበት ቦታ መውጣትን ሊደጋግም ነው። ይህ ደግሞ ኢዕቲካፍን ያፈርሳል።"
[አል መጝኒ 3/187]
|> ኢዕቲካፍ አድራጊ መቼ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው(መስጂድ) ይገባል? መቼስ ኢዕቲካፉን ጨርሶ ይወጣል?
- አብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤቶች ኢዕቲካፍ አድራጊ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው የሚገባው ሃያኛው ቀን ፀሃይ ስትጠልቅ (የሃያ አንደኛው ለሊት መጀመሪያ ላይ) ነው። ከኢዕቲካፉ ቦታ የሚወጣው ደግሞ የመጨረሻው የረመዷን ቀን ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ብለዋል።
ሌለኞቹ ደግሞ፦
- ሃያ አንደኛው ንጋት ላይ ከፈጅር በኋላ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው ገብቶ የዒድ ንጋት ላይ ከኢዕቲካፍ ማድረጊያው ይወጣል። ብለዋል።
|> ኢዕቲካፍ አድራጊን የሚነጥሉ ስራዎች
የኢዕቲካፍ ዋና አላማው ነፍስን ወደ አሏህ በሚያቃርቡ ስራዎች ማሰር እና ማጠር ሲሆን፤ ኢዕቲካፍ በሚያደርግበት መስጂድ ውስጥ ባሉ መልካም ስራዎች[ሶላት፣ ዚክር፣ ቂርአት..] ሊሣተፍ ይገባል። ሌሎች የእውቀት ባለቤች ከመስጂድ ውጪ ያሉ አምልኮዎችን መስራት [የታመመን መጠየቅ፣ የሟችን ሬሳ መሸኘት ..] እንደሚችል ጠቁመዋል።
|> ኢዕቲካፍ አድራጊ ሊፈፅማቸው የተቻሉ ድርጊቶች
- ኢዕቲካፍ አድራጊ ለመፀዳዳት(ሽንት ቤት) መሄድ፣ የሚመገበውን ምግብ ሚያመጣለት ከሌለም ለማምጣት መውጣት ይችላል።
- ውዱእ ለማድረግ እና ገላን ለመታጠብ መውጣት
- ፀጉሩን ማበጠርም ሆነ መላጨት፣ ጥፍሩን መቁረጥ
- የተቻለ ከሆነ ለብቻው የሆነን ቦታ መስጂድ ውስጥ ማዘጋጀት
- ያለ እርሱ ሊከወኑ ማይችሉ ግድ የሆኑ የግዢ ወይም የሽያጭ ግብይቶችን መፈፀም
- ኢማም አን ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፦ " ኢዕቲካፍ አድራጊ ማግባትም ሆነ ሌላን መዳር ይችላል።
- ሽቶ መቀባት
- በአስገዳጅ ሁኔታ ለምስክርነት ከተፈለገ ከኢእቲካፉ ቦታ መውጣት
- ልጅ የምታጠባ እናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። ሃይድ ላይ ያለችም እንዲሁ(በነጥቡ ላይ የሃሣብ ልዩነት ያለው ቢሆንም) ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች።
|> ኢዕቲካፍን የሚያፈርሱ ተግባሮች
- 'አውቆ' ግንኙነት ማድረግ
- ረስቶ ከሆነ ኢዕቲካፉ አይበላሽም። ምንም የለበትም።
- የዘር ፈሳሽን ማውጣት
- ኢዕቲካፉን ለማቋረጥ ቁርጥ የሆነ ኒያን ማስገኘት...
ሱትራ ማለት አንድ ሰጋጅ ሶላቱን ሲሰግድ ሶላቱን ከሚያቋርጡ ነገሮች ለመከላከል ከፊትለፊቱ የሚያደርገው መከላከያ ነው።
- ሱትራ አንድ ሰጋጅ ከፊትለፊቱ በሚያደርገው
እንደ ግርግዳ፣ ዱላ ፣ ሰይፍ ወይም ማንኛውም ነገር ይገኛል(ቁርዓን ወይም ነጃሳ ነገር ሲቀር) ። የጎን ስፋቱ ይህን ያህል መሆን አለበት የሚል ገደብ የለውም።
- ከፍታውን በተመለከተ የፈረስ ኮርቻን የሚያክል ወይም አንድ መዳፍን የሚጠጋጋ ነው።
- ከሰጋጁ እና ከሱትራው መካከል የሚኖረው ክፍተት ሶስት ክርንን የሚቀራረብ ነው። ይህም ሰጋጁ ሱጁድ ማድረግ የሚችልበት ሁኔታ ላይ መሆኑ ነው። ወደ ሱትራ ይበልጥ መቅረቡም ይወደዳል።
- ሱትራ ኢማም ሆኖ ለሚያሰግድ እና ለብቻው ለሚሰግድም የተደነገገ ሱንናህ ነው። (ለፈርድ ሶላትም ይሁን ለሱንናህ ሶላት)
- የአሰጋጅ(ኢማም) ሱትራ መጠቀም ከኋላው ተከትለው ለሚሰግዱትም ጭምር ነው። ስለሆነም አስገዳጅ ሁኔታ ካጋጠመ ኢማምን ተከትለው በሚሰግዱ ሰጋጆች መሃከል ማለፍ ሶላትን አያቋርጥም ።
ሱትራን መጠቀም ብዙ ትሩፋት አለው ከእነኚህም፦
- ሱትራ ሶላትን መሉ በሆነ መልኩ ቆርጠው ሶላትን ከሚያፈርሱ ነገሮች(ሴት፣ አህያ እና ጥቁር ውሻ) ወይም ከፊል የሶላቱን ምንዳ ከሚያሳጡ መቋረጦች ይከላከላል።
- ሱትራ የሰጋጅን እይታ ይገድባል። በተለይ ሱትራው ወደ ጎን ሰፋ ያለ ከሆነ የሰጋጁ አይን ወደ ሱትራው እንዲሆን እና ወደሌሎች ነገሮች እይታው እንዳይሳብ ይረዳዋል።
- ሱትራን በመጠቀም የመልእክተኛውን ﷺ ድርጊት እና ትዕዛዝ ተግባራዊ ማድረግ እና መከተል ነውና ትልቅ ምንዳ አለው።
- ከሰጋጅ ፊትለፊት ማለፍ ትለቅ ወንጀል ነው። መልእክተኛው ﷺ ‛‛ ከሰጋጅ ፊት የሚሄድ ሰው ከሰጋጅ ፊት መሄድ ያለውን ወንጀል ቢያውቅ አርባን ቢቆም ይመርጥ ነበር ’’ ብለዋል።
Telegram
ፊቅህን ለማወቅ
ይህ ቻናል የፊቅህ ነጥቦችን ብቻ እያስተላለፍን የምንማማርበት ቻናል ነው፡፡
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana