Apostolic Church of Bole Hermon Branch

Description
"፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤"
(ኦሪት ዘዳግም 6: 4)
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 6 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

1 month ago

? ማሳሰቢያ፦

? የበረከታችሁን ስፍራ አትልቀቁ

@ACEBoleHermon

1 month ago

በየስፍራው ሁሉ ላላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች!

የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችሁ ይሁን

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በሃድይኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን አቲ አቴቴሜ ደበሰንቶዮ (አንተ ያው አንተ ነህ አትለወጥም) የተሰኘ
የዝማሬ ስንዱቅ (Album) ሲያቀርብላችሁ በደስታ ነው።

ይህንን የዝማሬ አልበም በብዙ ድካም ያዘጋጀውን ዘማሪ አልባስጥሮስ ኤርሚያስ (ወንድሙ) እና በአልበሙ ዝግጅት በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ
እግዚአብሔር እንዲባርካቸው እየጸለይን ጌታችን ቢፈቅድ ብንኖር
አልበሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በአፖስቶሊክ ሶንግ መተግበርያ
ውስጥ ይለቀቃል።

በኢትዮጵያ ያላችሁ ተጠቃሚዎቻችን ዝማሬዎቹን ለማውረድ የምትጠቀሙበትን ኮድ በቴሌግራም ቦት t.me/ApostolicPayBot ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁ ደግሞ ክሬዲት ካርድ በመጠቀም አልበሙን ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን።

የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል

መስከረም 2017 ዓ.ም

@ACEBoleHermon

1 month, 1 week ago

? እንደገና ደግማችሁ ትስቃላችሁ!

“አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።”
ኢዮብ 8፥21
ሳራ በልብዋ ሳቅ ሳቀች። ሳራን ያሳቃት የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ነበር ። ያሳቃትም በመልአኩ በኩል "የዛሬ አመት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ" ተብሎ የተነገራት ቃል ስትሰማ ነበር።
ሳራ ግን ለምን ሳቀች?

በሴቶች የሚሆን ልማድ ከተቋረጠ ዘመን ያስቆጠረች ሴት ትወልጃለሽ ስትባል ለምን አትስቅ?

እግዚአብሔር  ግን ሊያስቃት ሳይሆን ሊያደርገው ነበር የተናገራት። እነሆም ሳራ  እንደሳቀችው ሳይሆን ጌታ እንደተናገረው ሆኖ በአመቱ ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም ይስሐቅ አለችው። በዚህ ጊዜም ሳራ ደግማ ሳቀች። የሳቀችው ግን እንደ  በፊቱ አይነት ሳቅ ሳይሆን ተደርጎላት የሳቀችው የደስታ ሳቅ ነበር።

"ሳራም ፀነሰች፥ እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት....ሳራም፡— እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል፡ አለች" ዘፍ 21:2_6

ጌታ እየሱስ የተስፋን ቃል በመሰዊያው ሲያመጣላችሁ "የማይመስል ነገር ያላችሁት" በአንደበታችሁ አሜን በልባችሁ ግን ባለማመን ምክንያት የሳቃችሁበት ሁሉ እንደሳራ ቀጣይ የእንደገና ሳቅ ከፊታችሁ አለ።

ባለማመን እንዳልሳቃችሁ ሁለተኛ ደግሞ ተቀብላችሁ ትስቃላችሁ። የማይመስል ያላችሁት እውን ሆኖ፣ አይሆንም ያላችሁት ሆኖ፣ ተደርጎላችሁ... ደግሞ በደስታ ትስቃላችሁ።

አይቀርም! እንደገና ትስቃላችሁ!!

@ACEBoleHermon

1 month, 1 week ago

ኧረ ስንት ጊዜ እንዲህ ብዬ አውቃለሁ
አለቀ የኔ ነገር መጨረሻዬ ነው
ኢየሱስ ግን አለ በዚህ አያበቃም
አይደመደምም ታሪክህ በድካም

ሀዘን ጨለማዬን ገፈፈው ጌታዬ
ምህረት ቸርነቱን አበዛልኝ በላዬ
የፈራሁትንም አለፍኩት በድል
ካየሁት የሚበልጥ አሳየኝ ክብር

ሞትን አሳልፎ ክብር አሳየኝ
ሀዘን አሳልፎ ክብር አሳየኝ
ለቅሶን አሳልፎ ሳቅን አሳየኝ
መጎናጸፊያዬን ቀየረው ምስጋና አለበሰኝ

ምስጋና ምስጋና ምስጋና ይኼው አለኝ
ምስጋና ምስጋና ለኢየሱስ ይኼው አለኝ

@ACEBoleHermon

1 month, 1 week ago

? በሚመጣው ዘመን!

- በሰማያዊው ስፍራ ባለ መንፈሳዊው በረከት ሁሉ ለመባረክ ስፍራችሁን አትልቀቁ!

• በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እደጉ

- ፊተኛውን ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚጠፋ ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ

- በአዕምሮአቹ መንፈስ ታደሱ

- ለእምነትም በሚሆን ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ፡፡

- ውሸትን አስወግዱ

- እርስ በእርሳችሁ ብልቶች ሁኑ

- እያንዳንዳቹ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ

- ተቆጡ ኃጢአት ግን አታድርጉ በቁጣቹ ላይ ፀሐይ አይግባ

- ለዲያብሎስ ፈንታ አትስጡ

- የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሰራ ይድከም ፡፡

- ለማነፅ የሚጠቅም ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ

- ለቤዛ ቀን የታተማችሁትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ፡፡

- መራርነት ንዴት ቁጣ ጩኃትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ይወገዱ፡፡

- እርስ በእርሳችሁም
ቸሮችና
ርኀሩኆች ሁኑ፡፡

▸ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ፡፡

-አንደ ልብ ሆኖ የመንፈስ አንድነትን መጠበቅ

- መለያየትን ከውስጣችን አስወግደን በአንድ ልብ ወደ ፀጋው ዙፋን ፊት በእምነት እና በአንድነት እንቅረብ

- በትምህርት ነፋስ ሳንፍገመገም ፣ በሚታየው ወጀብ ሳንቅበዘበዝ የእምነታችንን ራስ እና ፈፃሚውን ክርስቶስን ብቻ እየተመለከትን እንጓዝ

- መንፈሳችን ሳይቀዘቅዝ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው የተባለውን እያሰብን በፀሎት እየተጋን መኖር ምርጫ የሌለው ብቸኛ አማራጫችን ይሁን፡፡

• የሚለውን ተመልክተን፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን።
አሜን!!!

በሰማያዊ ስፍራ በሚገኝ ከሁሉ የሚበልጥ የተትረፈረፈውን የጸጋውን ባለጠግነት የምታዩበት ዘመን ይሁንላችሁ!!!

@ACEBoleHermon

1 month, 1 week ago

? ሳትመገብ እባቡን አታሸንፈውም!!

“ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።”
ራእይ 12፥14

በሚመጡ ዘመናት ሁሉ በአሸናፊነት የምንኖርበት ምስጢር!!!
የህይወት ስንቅ!!!

መልዕክቱን አድርሱ

@ACEBoleHermon

1 month, 2 weeks ago

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ፦

ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በህያው ጌታ ፊት ከምንለምነውና ከምናስበው በላይ እጅግ አብልጦ ለሚያደርገው ጌታ በቤተክርስቲያን በትውልዶች ሁሉ ከዘለዓለም እስከዘለአለም ክብር ይሁንለት!!!

በፊቱ በሰማያዊ ስፍራ በሰማያዊ በረከት ሁሉ የባረከን ሃይል የሰጠን ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ይባረክ!!

“ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።”
መዝ 45፥7
እንደሚል ቅዳሜ ለቅዱሳን ሁሉ አገልጋዮች ዘይት ቀብተን እንጸልያለን!!!

ከቅባቱ የተነሳ ቀንበሩ ይሰበራል የደስታ ዘይት በልባችሁ ይፈስሳል!!!

ለበረከት ሁኑ!!!!
ተነጋገሩ ሁላችሁም ተገኙ!!!

እሁድ በፍጻሜው በ 21 ኛው ቀን የተሻገረ ህዝብ የሚያነሳውን ከበሮ አንስተን ..........

“በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ......
ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።”
ዕዝራ 8፥21-23

የተለመነንን ጌታ በልዩ ምስጋናና አምልኮ!
"ሰምተኸኛልና መድሃኒትም ሆነህኛልና አመሰግንሃለሁ "

“ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።”
እያልን የአመቱን መስዋዕት እንሰዋለታለን!!

ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ይባረክ!!

@ACEBoleHermon

1 month, 2 weeks ago

" ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።"
ኢሳ40፥29-31

የመታደስ ስጦታ

“ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።”
2ኛ ቆሮ 9፥15

“አንዳንድ ጊዜ በተሰጠህ ዘመን ሁለተኛ እድል የማይሰጡ ሁኔታዎች ያጋጥሙሃል፤ ሁለተኛ እድል ካገኘህ ግን ችላ ሳትል ተጠቀምበት”

አንድ የቆሰለው ውጫዊ አካላችን በመድሃኒት ታገዘም አልታገዘ፣ በአስገራሚ ሁኔታ ወደነበረበት ሲመለስ፣ አንዳንዴም በጠነከረ ሁኔታ ራሱን አድሶና አቋቁሞ ማየታችን ሁል ጊዜ ሊያስገርመን የሚገባ ሂደትና ታላቅ መለኮታዊ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለሁሉ ሰው የተሰጠውን በመንፈሳዊውም ይሁን በምድራዊ ህይወት ኑሮ ያለውን የሁለተኛና የዳግም እድል እውነታ ማሳያ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ግን አይጠቀምበትም፡፡

ከዳግም እድል ውጪ ብዙዎቻችን ዛሬ የደረስንበት ደረጃ አልደረስንም፡፡ የተበላሸው እንደገና ሲታደስ፣ የደከመው እንደገና ሲበረታ፣ የጠፋው እንደገና ሲገኝ፣ ትቶን የሄደው እንደገና ሲመለስ … ለሁለተኛ እድል የመታደስን ስጦታ እንደተቸርን እናያለን፡፡ እንግዲህ የጥበብ ወሳኝነት እዚህ ጋር ነው ያለው፡፡ ጠቢባን ከእጃቸው አንድ የሄደውና የተጸጸቱበት ነገር እንደገና በእጃቸው የሚመለስበት ዕድል ከላይ ሲመጣ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በሚገባ ያውቁበታል፡፡

ምናልባት ለሰውነት ጤና ቀውስ ለሚሆን ልምምድ ራስህን ከማጋለጥህ የተነሳ የጤንነት ቀውስ ውስጥ ትሆናለህ፡፡ ምናልባትም፣ በመንፈሳዊ ህይወት ድካም፣ በህይወትህ ከሰራሃቸው የውሳኔ ስህተቶች የተነሳ ከላይኛውም ከታችኛውም መከናወን ጎድለህ ራስህን አግኝተኸው ሊሆን ይችላል፡፡ ካለብህ የባህሪይ ጉድለት የተነሳ የራስህ የሆኑትን ሰዎች ከአንተ አርቀሃቸው ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ
ከተዛባ አካሄድ የተነሳ ስራህን ወይም ስኬትህን አጥተህ ይሆናል፡፡ እነዚህና መሰል ሁኔታዎች የመታደስና ሁለተኛ እድልን የሚሰጡህ ጊዜ እንዳለ አትዘንጋ፡፡ አየህ፣ የብዙ ሰዎች ችግር ነገሮች መበላሸታቸው ሳይሆን፣ የተበላሹት ሁኔታዎች የሚታደሱበት ሁኔታ ሲቀርብላቸው ያንን ያለማየት ወይም አይተውት ያን ዕድል እንደገና የመጠቀም ተነሣሽነት ያለመኖሩ ነው፡፡

ሁሉም ነገር እንደገና ሊታደስ፣ ሕይወት ሊዘራ፣ ሊመለስና ሁለተኛ እድል ይዞልህ ሊመጣ እንደሚችል በማስታወስ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ እድሎች ሲመጡ ግን ለይቶ የማወቁና፣ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ የመሆኑ ሃላፊነት እኛው ጋር ነው ያለው፡፡ የመታደስና ሁለተኛ እድል የማግኘት እድል ለሁሉም ሰው የተሰጠ ነው፡፡ ያንን የማየትና የመጠቀም ትክክለኛው ምላሽ የሚሰጡት ብቻ ግን ይህንን ታላቅ የአምላክ ስጦታ እስከ ጥጉ ይጠቀሙበታል፡፡

አንዳንዶቹ የመታደስ እድሎች ራሳቸውን ወደአንተ የሚያቀርቡ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ አንተው በመንቀሳቀስ እውን ልታደርጋቸው የሚገቡህ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ይህ የሁለተኛ እድልና የመታደስ ስጦታ የአንተን ፍላጎትና ተሳትፎ የሚጠይቅ ከእግዚአብሔር የተሰጠህ አስገራሚ ስጦታ መሆኑን አውቀህ ተጠቀምበት !

@ACEBoleHermon

1 month, 3 weeks ago

? ማነከሴ በደጅ አያስቀረኝ

“ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ።”
ሐዋ 3፥8
"..እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ?"
1ኛ ነገሥ18፥21

@ACEBoleHermon

1 month, 3 weeks ago

? ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።
             በሚመጡት ዘመናት:-

*?* " ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት "
እንደሚል :- በዘመናችሁ መስዋእታችሁንና ቁርባናችሁን ሁሉ አስቦ ፍጻሜያችሁን በፊቱ ከሚሰበሰቡት ቅዱሳን ጋር ያድርግላችሁ!!

? እርሱ ባስቀመጠን ሰማያዊ ስፍራ በመገኘት በመገኘቱ ውስጥ ያለ ከሁሉ የሚበልጥ የጸጋው ባለጠግነት ለእናንተ ለትውልዳችሁም አትረፍርፎ ያፍስስላችሁ!!

? የከበረውን ከተዋረደው ትለዩ ዘንድ የአይን መከፈት ይሁንላችሁ!

? አመጽን የሚጠላ ጽድቅን የሚወድ ልብ   ይስጣችሁ!

? "ከፍ ካሉት በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ " ተብሎ እንደተፃፈ በህይወታችሁ ዘመን ሁሉ ከፍ ካሉባችሁ በላይ ከፍ ያድርጋችሁ! መግዛት ይሁንላችሁ !

? የቃሉም ብርሃን ዘውትር በልባችሁ ላይ ይብራ!!!

? የበረከት ዝናብ ይዝነብላችሁ!

? የእናንተ የሆነው ነገር ሁሉ ይለምልም የምድርን ፊት በሚሸፍን የጽድቅ ፍሬ ይሙላባችሁ!

? ምድረ በዳው ፍሬ ይስጣችሁ በርሃብ ዘመን በብዙ ማጨድ ይሁንላችሁ!

? ለብዙዎች መዳንና ለህይወታቸው መቀጠል ምክንያት  ያድርጋችሁ!!!

አሜን!! ይሁን!ይሁን!**@ACEBoleHermon

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 6 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago