Feta Daily News

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад

1 week ago
**የጋዛ ህዝብ ቁጥር በ6 በመቶ ቀንሷል …

የጋዛ ህዝብ ቁጥር በ6 በመቶ ቀንሷል ተባለ

የጋዛ የህዝብ ቁጥር የቀነሰው የእስራኤል ሃማስ ጦርትን ተከትሎ ነው። የፍሊስጤም ስታተስቲክስ ቢሮ ከጦርቱ ወዲህ የጋዛ ህዝብ ቁጥር 160 ሺህ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል።

1 week ago
**በአሜሪካ አውሮፕላን ተጋጨ**

በአሜሪካ አውሮፕላን ተጋጨ

በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ከንግድ ህንጻ ጋር ተጋጭቶ የሁለት ሰዎች ህይወት መቀጠፉን እና 18 ሰዎች መጎዳታቸውን ባለስልጣናቱ አስታወቁ።

1 week, 2 days ago
**ሩሲያ በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ …

ሩሲያ በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ መላክ ማቆሟን አስታወቀች

የሩሲያው ጋዝፕሮም እና የዩክሬኑ ናፍቶጋዝ የተፈራረሙት የአምስት አመት ስምምነት በመጠናቀቁ ነው ሞስኮ በዩክሬን በኩል ነዳጅ መላክ ያቋረጠችው።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ "በእኛ ደም ቢሊየኖችን እንድታገኝ አንፈቅድም" በማለት ስምምነቱ እንደማይታደስ መናገራቸው ይታወሳል።

1 week, 2 days ago
**በሲዳማ ክልል በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ …

በሲዳማ ክልል በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

በሲዳማ ክልል በምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በገላና ወንዝ ድልድይ በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ትናንት በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ገልፀዋል።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰብና ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። የክልሉ መንግሥት ለሟቾቹ ቤተሰቦች አራት ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ሁላችንም ለሟቾቹ ቤተሰቦች ድጋፋችንን አጠናክረን ልንቀጥልና ልናጽናናቸው ይገባልም ብለዋል።

1 week, 3 days ago
Feta Daily News
3 months ago
**ሰሞኑን በተደረገዉ የነዳጅና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ …

ሰሞኑን በተደረገዉ የነዳጅና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ራይድ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት በመነሻ ያስከፍል በነበረዉ አገልግሎቱ ላይ የ 30 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።

የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ እና በቅርቡ የተደረገዉ የዉጪ ምንዛሪ ማሻሻያ ምክንያት መነሻ ከ ነበረዉ 100 ብር ከትላንት ጀምሮ 130 ብር መሆኑን የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራንድ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ በተለይ ለካፒታል ተናግረዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ የዋጋ ማሻሻያዉ በኪሎ ሜትር የ 1 ብር ጭማሪ መድረጉን ነዉ የተናገሩት ።

3 months ago
**የሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች 'በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና …

የሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች 'በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት' ዙርያ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ!

ቀጠናዊ ውጥረት ባየለበት ወቅት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ 'በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት' ዙርያ በአስመራ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ሁለቱ መሪዎች “በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዋነኝነት በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ያተኮረ ውይይት” በትናንትናው ዕለት ማድረጋቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል አስታውቀዋል።

መሪዎቹ “አስተማማኝ የመከላከያ እና የጸጥታ መዋቅርን ጨምሮ ጠንካራ እና ሉዓላዊ ተቋማትን መገንባት” አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል ተብሏል።

3 months ago
Feta Daily News
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад