Ibnu Muhammedzeyn

Description
ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም
በፈቀደ መልኩ ትክክለኛው
ኢስላማዊ አስተምህሮት፦
① ከቁርኣን፣ ② ከሐዲሥ
√ በሰለፎች አረዳድ
እንድሁም
③ ከቀደምት እና በዘመኑ
ካሉ የሱናህዑለሞች
ንግግር ይቀርብበታል።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 years, 2 months ago
2 years, 2 months ago

سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ ، أشهد أن لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتُوبُ إِلَيْكَ

2 years, 2 months ago

ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?

አዎ ለቀብር ጨለማ !!
ለቂያማ ጭንቀት !!
በሲራጥ ለማለፍ !!
አላህ ፊት ቁመን ስንጠየቅ ላለው ጭንቀት !!
በጥቅሉ ከሞት በሗላ ላለው ሂወታችን ምን አዘጋጅተናል?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዐሰላ) እንድህ ይላል:-

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ }

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ » [ሐሽር (18)]

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Telegram

Ibnu Muhammedzeyn

ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም በፈቀደ መልኩ ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት፦ ① ከቁርኣን፣ ② ከሐዲሥ √ በሰለፎች አረዳድ እንድሁም ③ ከቀደምት እና በዘመኑ ካሉ የሱናህዑለሞች ንግግር ይቀርብበታል።

**ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?**
2 years, 2 months ago

የሱና ሰዎች መንገዳቸው ግልፅ ነው።

?በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ (ሐፊዞሁሏህ)
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/Muhammedsirage
t.me/Muhammedsirage

2 years, 2 months ago

? جديد التفريغات

? [ العقيدة الصحيحة وآثارها على الفرد والمجتمع ]

*?***لفضيلة الشيخ أ.د. صالح بن عبدالعزيز سندي - حفظه الله - أستاذ العقيدة بكلية الدعوة وأصول الدين بالجامعة الإسلامية بالمدينة النبوية

? تنبيه : الشيخ لم يراجع التفريغ

ا═•═?═•═ا
?فوائد أ.د. صالح سندي?
https://t.me/Drsalehs

2 years, 2 months ago

‏‌
‏يقول ابن الجوزي -رحمه الله- [أتطمع مع حب الوسادات في لحاق السادات]؟!

2 years, 2 months ago

በሐቅ ላይ ለመፅናት ሰበብ የሚሆንና ከጥመት ሰዎች የሚወረወሩ ሹብሀዎች እንዳያደናግሩን የሚረዳ ወሳኝ ቃዒዳ(መርሕ)

ማሳሰቢያ:- ((በተለይ ይህ መርህ ከስደት ወደሀገራቸው ለሚመለሱ ከእነርሱም ውስጥ በተለይ ወደገጠሩ የሀገራችን ክፍሎች ለሚመለሱ እህቶች እና ለተራው የሰለፊይ ክፍል ወሳኝ መርህ ነው። ከፅሁፌ መጨረሻ ላይ እሄን ያልኩበትን ምክኒያት አስቀምጣለሁ)) እሄን ወሳኝ ቃዒዳ አብረን እንመልከት

? ሹብሃ እንዳይበግርህ ሙብተዲዕ እንዳያምታታህ የባጢል ባለቤት ከያዝከው ሐቅ እንዳያዋልልህ ከፈለግክ እሄን ሸሪዓዊ መርህ በጥርስህ ነክሰህ ያዝ!!
ሁሌም በሒወትህ ውስጥ ተግባራዊ አድርገውም። የዛኔ ሹብሀ አይብግርህም በዐቂዳህም ሆነ በመንሀጅህ በጥቅሉ በሐቅ ላይ የባጢል ባለቤት በፍፅም ሹብሀ ሊጥሉብህ አይችሉም በአላህ ፍቃድ በዲን ላይ መገለባበጥም አታበዛም በሐቅ ላይ ፅናት ይኖረሃል።


እሄን ቃዒዳ እውቁ የተፍሲር ሊቅ የዚህ ዘመን ታላቅ ዓሊም (የኢብኑ ዑሠይሚን አስተማሪ የሆኑት) ዐብዱረሕማን አስ–ሲዕዲይ (ረሒመሁሏህ) የሚከተለውን የቁርአን አንቀፅ ሲያብራሩ እሄን ገራሚ ቃዒዳ እንድህ በማለት ያስቀምጣሉ:-
አላህ(ሱብሐነሁ ወተዓላ) እንድህ አለ:-

{ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ }

«ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡» [አል ዒምራን (60)]
ኢማሙ አስ–ሲዕዲይ እንድህ በማለት ያብራራሉ:-

«ጌታህ በእርሱ ከነገረህ በሆነ ነገር ጠርጣሪ አትሁን ማለት ነው።

በዚህና ቀጥሎ በሚመጣው አንቀፅ ውስጥ በጣም ትልቅ ለሆነች (ኢስላማዊ) መርሕ መረጃ አለ። እርሱም:- በዐቂዳም ይሁን በሌላ ጉዳይ ላይ ሐቅ በመሆኑ ላይ መረጃ የቆመበትና ባሪያ ቆርጦ ያመነበት (ማንኛውም የዲን) ጉዳይ ከእርሱ ተቃራኒ የሆነው ማንኛውም ነገር ባጢል ለመሆኑ ቁርጥ ተደርጎ ሊታመን ይገባል። በእርሱ(በባሪያ) ላይ የሚያመጧት ማንኛዋም ሹብሀ( ማምታቻ) ብልሹ (በመሆኗ ቁርጥ ተደርጎ ሊታመን ይገባል) ይህ ባሪያው ያን (ከባጢል ሰዎች) የመጣበትን ሹብሃ (ማምታቻ) መፍታት(መመለስ) ቻለም አልቻለም (ከሐቅ ውጭ ያለ ማንኛውም ነገር ባጢል በመሆኑ ቁርጥ አድርጎ ሊያምን ይገባዋል)
እሄን ሹበሀ(ማምታቻ) መመለስ አለመቻሉ (በመረጃ) ባወቀው (ሐቅ ላይ) ምንም አይነት ትችት ሊፈጥርበት አይገባም።
ምክኒያቱም ሐቅን የተቃረነ(የተኻለፈ) ማንኛውም ነገር ባጢል ነውና። አላህ እንድህ ይላል:-
{ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ }
«ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ» [ዩኑስ 32]

በዚች ሸሪዓዊ በሆነች መርህ (ምክኒያት) ፈላስፋዎች ከሚያመጡትና የመንጢቅ(የሎጂክ) ባለቤቶች ከሚያደራጁት ብዙ ችግሮች ከሰው ላይ ይፈታሉ።

قال الإمام المفسر العلامة عبدالرحمن السِّعدِّي في تفسير هذه الأية :-

{ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ } [ آل عمران 60]
ﺃﻱ: اﻟﺸﺎﻛﻴﻦ ﻓﻲ ﺷﻲء ﻣﻤﺎ ﺃﺧﺒﺮﻙ ﺑﻪ ﺭﺑﻚ، ﻭﻓﻲ ﻫﺬﻩ اﻵﻳﺔ ﻭﻣﺎ ﺑﻌﺪﻫﺎ ﺩﻟﻴﻞ ﻋﻠﻰ ﻗﺎﻋﺪﺓ ﺷﺮﻳﻔﺔ ﻭﻫﻮ ﺃﻥ ﻣﺎ ﻗﺎﻣﺖ اﻷﺩﻟﺔ ﻋﻠﻰ ﺃﻧﻪ ﺣﻖ ﻭﺟﺰﻡ ﺑﻪ اﻟﻌﺒﺪ ﻣﻦ ﻣﺴﺎﺋﻞ اﻟﻌﻘﺎﺋﺪ ﻭﻏﻴﺮﻫﺎ، ﻓﺈﻧﻪ ﻳﺠﺐ ﺃﻥ ﻳﺠﺰﻡ ﺑﺄﻥ ﻛﻞ ﻣﺎ ﻋﺎﺭﺿﻪ ﻓﻬﻮ ﺑﺎﻃﻞ، ﻭﻛﻞ ﺷﺒﻬﺔ ﺗﻮﺭﺩ ﻋﻠﻴﻪ ﻓﻬﻲ ﻓﺎﺳﺪﺓ، ﺳﻮاء ﻗﺪﺭ اﻟﻌﺒﺪ ﻋﻠﻰ ﺣﻠﻬﺎ ﺃﻡ ﻻ ﻓﻼ ﻳﻮﺟﺐ ﻟﻪ ﻋﺠﺰﻩ ﻋﻦ ﺣﻠﻬﺎ اﻟﻘﺪﺡ ﻓﻴﻤﺎ ﻋﻠﻤﻪ، ﻷﻥ ﻣﺎ ﺧﺎﻟﻒ اﻟﺤﻖ ﻓﻬﻮ ﺑﺎﻃﻞ ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ {ﻓﻤﺎﺫا ﺑﻌﺪ اﻟﺤﻖ ﺇﻻ اﻟﻀﻼﻝ}
ﻭﺑﻬﺬﻩ اﻟﻘﺎﻋﺪﺓ اﻟﺸﺮﻋﻴﺔ ﺗﻨﺤﻞ ﻋﻦ اﻹﻧﺴﺎﻥ ﺇﺷﻜﺎﻻﺕ ﻛﺜﻴﺮﺓ ﻳﻮﺭﺩﻫﺎ اﻟﻤﺘﻜﻠﻤﻮﻥ ﻭﻳﺮﺗﺒﻬﺎ اﻟﻤﻨﻄﻘﻴﻮﻥ، ﺇﻥ ﺣﻠﻬﺎ اﻹﻧﺴﺎﻥ ﻓﻬﻮ ﺗﺒﺮﻉ ﻣﻨﻪ، ﻭﺇﻻ ﻓﻮﻇﻴﻔﺘﻪ ﺃﻥ ﻳﺒﻴﻦ اﻟﺤﻖ ﺑﺄﺩﻟﺘﻪ ﻭﻳﺪﻋﻮ ﺇﻟﻴﻪ.. اهى


ከላይ ያሳለፍነው የሸይኽ ሲዕዲይ ተፍሲር ሀሳብ በአጭሩ ሲጨመቅ : «ሐቅን በመረጃ ካወቅክ ከባጢል ባለቤቶች የተለያዩ ሹብሀ ቢመጡብህ በያዝከው አቋም በፍፁም ልትጠራጠርም ሆነ ልትዋልል አይገባህም ምክኒያቱም ከሐቅ ውጭ ያለው ማንኛውም ነገር ባጢል ነው። አላህ እንድህ ይላል «ከእውነት በሗላ ጥመት እንጅ ሌላ ምን አለ» [ዩኑስ (32)] ከሐቅ ውጭ ያለ ማንኛውም ነገር አንተ መመለስ ቻልክም አልቻልክም ባጢል(ውድቅ) ነው። እንድሁም ለሚነሳው ባጢል ሁሉ መመለስ አለመቻልህ በየዝከው ሐቅ ላይ ምንም የሚፈጥረው ተፅእኖ አይኖርም» ማለት ነው።

እሄን ቃዒዳ በደንብ እንድንረዳ በምሳሌ እንመልከት
ለምሳሌ:-
አንተ አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ታምናለህ መረጃህም
{الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ}
«አል–ረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ፡፡»

የዚህ የቁርኣን አንቀፅ ትክክለኛውን ትርጉም በመረጃ ካወቅክ በዚህም መረጃ መሰረት አሏህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ታረጋገጥክ

ከዚህ በሗላ ሱፍይ፣አሻዒራ፣አህባሽና መሰል የቢዳዓ ባልተቤቶች የማታውቀውን ነገር እይዘበዘቡ እዚህኮ የተፈለገበት «መጃዝ ነው» ወይንም «ኢስተዋ ቢማዕና ኢስተውላ ነው ለዚህም መረጃችን ቀድኢስተዋ ቢሽሩን…» እያሉ ቢዘበዝቡብህና አንተ ደግሞ እሄን ከሸረሪት ቤት የደከመ መረጃ ለመመለስ እውቀቱ ቢያጥርህ በያዝከው አቋም በፍፁም አትጠራጠር የእነርሱም አቋም እውነት መስሉ በፍፁም አይታይህ ከላይ ባሳለፍነው መርህ መሰረት አንተ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን በመረጃ ካወቅክና ካረጋገጥክ ከእርሱ ውጭ ያለው ባጢል መሆኑን በእርግጠኝነት እወቅ።

ይህን እንደምሳሌ ነው የጠቀስኩት ሌሎችም በዐቂዳና በመንሀጅ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛቸውንም ማደናገሪያዎች በዚሁ መሰረት መመለስ ትችላለህ።

ይህ መርህ ወሳኝ መርህ ነው በተለይ ደግሞ አላህ የሐቅን ጎዳና ለመራቸው ግን ሰፊ እውቀት ለሌላቸው ወንድም እና እህቶች ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነው።

በተለይ ከላይ መግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት ወደውጭ ሀገር በስራ ምክኒያት ተሰደው ያላቸውን ክፍት ጊዜ በመጠቀም በሚዲያ ጠቃሚ የዲን ት/ቶችን በመከታተል ሐቁን ለተማሩ እህቶች በጣም አስፈላጊና ሆሌም ሊረሱት የማይገባ ወሳኝ መርህ ነው።

ስደተኛ እህቶችን የለየሁበት ምክኒያት:-
ብዙ እህቶች በስደት ሂወታቸው ትርፍ ጊዚያቸውን በመጠቀም በሚዲያ ጥሩ የሰለፊይ እውቀት ሲማሩ ቆይተው ወደሀገር ሲመለሱ በተለይ የገጠር አከባቢ ልጆች ከሆኑ የሱና ኡስታዞችና ዱዓቶች በአከባቢው ብዙም ላያገኙ ይችላሉ እንድሁም ካለው የኔትና የመብራት ችግር አልያም በቤተሰብ ጉዳይ ቢዚ በመሆን ከሚዲያም ይርቃሉ በዚህ ጊዜ ከቤተሰብም ይሁን ጎረቤት እንድሁም ከአከባቢ ሰዎች በተለይ በዝምድና ከሚቀርቧቸው ቅርብ ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ቢድዓ የተመረዙ አካሎች በያዙት የሰለፊያ አቋም ላይ ጧት ማታ ሹብሃ በመልቀቅ እራሳቸውን ዒልም ያላቸው በማስመሰል ከያዙት ሐቅ ለማስለቀቅ የሚፈታተኗቸው ብዞዎች ናቸው። ታዲያ የዛኔ ሹብሀቸውን የመመለሱ አቅም ባይኖራችሁም የሚያብራራላችሁ የሰለፊይ ኡስታዝ ባታገኙም በመረጃ በያዛችሁት አቋም በፍፁም አትጠራጠሩ ይልቁንም ከሐቅ በሗላ ጥመት እንጅ ምን አለ የሚለውን መርህ በመተግበር በአቋማችሁ ላይ ፅኑ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana