ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ዛሬ ማታ በወንድማችን አብዱልከሪም ቤት የነበረን የላይቭ ፕሮግራም በመብራት ችግር ምክንያት ለሌላ ቀን ተራዝሟል። ኢንሻአላህ ቀኑን እናሳውቃለን።
ሙሉ ቁርኣን በአንድ ገፅ
"አምላክ" አይደለሁም ያለበት ቦታ!
አንዱ ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ፣ ህዝቡ ግን አላመነበትም። ስለዚህ ሰበሰባቸውና ዛሬ እኔ ነብይ መሆኔ በአደባባይ አረጋግጥላችዃለው አላቸው።
በል ማስረጃህን አቅርብ ሲሉት።
እሱ: እኔ በአሁን ሰአት በአዕምሮአቹ የምታስቡትን አውቃለው አላቸው።
ህዝቡ ማጉረምረም ጀመር ፣ በል ንገረንና እንመንህ አሉት።
እሱ፦ አሁን በዚህ ሰአት እያሰባቹ ያላችሁት ይህ ሰው ቀጣፊ ነው እያላቹ ነው አላቸው ይባላል።
እኛ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ" የሚል ስለራሱ የተናገረበት ንግግር መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የለም ብለን ስንጠይቅ መልሱ እንደሌለ የሚያውቁ ሰዎች የሚሰጡን ምላሽ፦
① አምላክነቱን ሊገልፅ አልመጣም ይላሉ
ሰው የሆነው ለእኛ ብሎ እስከሆነ ድረስ ፣ አምላክነቱን ለመግለፅ ምንድ ነው የሚያስፈራው? ምን እንዳይሆን ነው ሚስጢሩን የደበቀበት ምክንያት? ሞት ከሆነ እንደ እናንተ አስተምህሮ አልቀረለትም። ከግዜው በፊት እንዳይገሉት ፈርቶ ነው እንዳይባል "አምላክ ነው" ያለ ግዜው ቢገሉትም መነሳት ይችላል። ይህ ምላሽ አሳማኝ አይደለም።
② ነብያቶች ሲመጡ ነብይነታቸውን እንደሚገልፁ ሁሉ አምላክነቱን መግለፁ እና ማብራራቱ የሚጠበቅና ተገቢ ነው። ነብያቶቹን ግልፅ አድርጎ ራሱ ሲመጣ ግን "ተደብቆ " ለምን መጣ?
③ሌላኛው አምላክነቱን በግልፅ ለምን አልተናገረም? ተብለው ሲጠየቁ። "አምላክ አይደለሁም" ያለበትን ቦታ አምጡ አይደለሁም ካላለ ነው ማለት ነው የሚል አሲቂኝ መከራከሪያ ያመጣሉ።
እንዲያማ ከሆነ "አብርሀምም አምላክ አይደለሁም" ብሎ ቃል በቃል ስላልተናገረ አምላክ ነው ማለት ነው? ይሄ እጅና እግር የሌለው ሙግት ነው።
እናም እባካችሁ እንደ ሀሰተኛው "ነብይ ነኝ" ባይ የራሳችሁን መልስ ሳይሆን መሠረታዊ ሙግቱን ተከትላችሁ መልስ ስጡ!
ኢየሱስ "አምላክ ነው!" እና ሰሞነኛ ወሬው!
ስራ ሲቀዘቅዝበት ማስታወቂያ እንደሚያበዛ ነጋዴ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብሎ ለሙስሊሞች ለማስረዳት ክርስቲያኖች ሰበብ በተገኘ ቁጥር ሁሉ ይደክማሉ። ከዛሬ 20 አመት በፊት የተደረገ ጥናትን በማቅረብ ሰሞኑን በሙስሊሞች ላይ ሊሳለቁ ከርመዋል።
ጉዳዩን እንደ አዲስ በማራገብ "ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያሳይ የተቀረፀ ፅሁፍ ነብያችሁ ሙሐመድ ከመወለዱ በፊት እስራኤል ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል" በማለት ስሁት ሀተታ እየሰሩ ይገኛሉ። የስነ ቁፋሮ ባለሙያዎቹ እስራኤል ውስጥ በሚገኝ ሜጊዶ ወህኒ ቤት ላይ ባደረጉት ጥናት እስር ቤቱ ወለል ላይ በግሪክ ቋንቋ የተቀረፀ ፅሁፍ አግኝተዋል ¹
በዚህ ጥናት ወለል ላይ ሶስት ፁሁፎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም፦
The Gaianus Inscription - ወለሉ እንዲሰራ ክፍያ የፈፀመውን ወታደር ስም እና የሰራው ባለሞያ ስም
The Akeptous Inscription - አምላክ ወዳድ የሆነችው አኬፕቶስ አምላክ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህን ጠረፔዛ አቅርቧል - የሚል እና
The Women Inscription - ፕሪሚላ እና ሳይሪያካ እና ዶሮቲያ፣ እና በተጨማሪ ክረስቴን አስታውሱ - የሚል ፁሁፎች ተገኝተዋል።
ጥናቱ ያደረጉ ሰዎች በመጽሀፋቸው ሲያጠቃልሉ በገፅ 54 እንዲህ ይላሉ፦
“በከፋር ‘ኦትናይ’ የሚገኘው የክርስቲያን የጸሎት አዳራሽ መገኘቱ ከቆስጠንጢኖስ ዘመን በፊት በእስራኤል ምድር ክርስቲያን መገኘቱንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዋናነት በሥነ ጽሑፍ ምንጮች ሲዳሰስ በነበረበት ወቅት፣ በእስራኤል ምድር ለነበረው ክርስቲያን መገኘት ትልቅ ጠቀሜታ ያለው አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ ነው። በተጨማሪም የሕንፃው ጥናት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከአይሁድ እምነት ይልቅ አረማዊ የሆነ የክርስቲያን ማኅበረሰብ መኖሩን ያረጋግጣል”
ልብ በሉ! ይሄ ኢየሱስ ካረገ ከ200 አመታት በሗላ ነው!!! በዚያን ወቅት ታዲያ “ኢየሱስ አምላክ ነው” የሚል ፅሁፍ መገኘቱ ምን ያስገርማል ታዲያ? ይህ ጥናት ምን አዲስ ነገር ኖሮት ነው? ከ 1800 አመት በፊት በክርስትያኑ ዘንድ የሚታወቁ የቤተክርስቲያን አባቶች/Church Fathers/ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብለው መጻፋቸው የሚታወቅ ነው። ታዲያ ምኑ ይሄ ይገርማል?
ምናልባት ከኒቂያ ጉባኤ (325) ጋር ተያይዞ ከሆነ ወቀሳው በኒቂያ ጉባኤ ወልድ “አምላክነቱ” በድምፅ ብልጫ ከመፅደቁ በፊት በአርዮስ እና ተከታዮቹ የነበረ ሃሳብ መኖሩን ከመግለፅ ውጪ የተለየ ትርጉም አይሰጥም።
አርዮስ ብቸኛ አምላክ አብ ነው ወልድ ግን የተወለደ፤ መጀመሪያ ያልነበረ ነው ሲል ያምናል። አባት ልጁን እንደማይቀድመው ሁሉ ወልድም አብን አይቀድምም የሚለው ሙግት የአርዮስ ሙግት ነበር። ስለዚህ በዚህ ጉባዔ አሪዮስን ተሳስተሃል፤ ከመጀመሪያም ጀምሮ ነበረ ፤ ከአብም ጋር እኩል አምላክ እንጂ ሁለተኛ አምላክ አይደለም ብለው ነው በድምፅ ብልጫ ያፀደቁት።
እናም "ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ፅሁፍ በተገኘ ቁጥር ሙስሊሞች ላይ መሳላቁ ትርጉም አልባ የሆነና እናንተንም ትዝብት ውስጥ የሚከታችሁ ነው።
1- A CHRISTIAN PRAYER HALL OF THE THIRD CENTURY CE AT KEFAR ‘OTHNAY (LEGIO) Excavations at the Megiddo Prison 2005)
ክፍል ሁለት
ከአራት አመት በፊት 26 አይነት ቁርዓን ሙስሊሞች አላችሁ በሚል ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ክፍል አንድ
ዛሬ በምንም ጉዳይ ላይ ላወጋ አይደለም፤ ግን አንድ ወንድም ድንገት ችግር አገኘችውና ምናልባት እዚሁ ላላችኹ ጥቂት ሰዎች ጉዳዩን ባካፍላቹኹና የምንዳው ተቋዳሽ ብንኾን ብዬ አሰብኹ፡፡
ግልሰቡ የአላህ ፍላጎት ኾነና እናቱንና ኹለት ሴት ልጆቹን በተከታታይ በሞት አጣ፡፡ ቀጠለና ከገጠር የነበረው የአባቱ መሬት በቅርብ ዘመዱ ተነጠቀ፡፡ ለጠቀና እሱም በተለያዩ የጤና እንከኖች ተጎዳ፡፡ አኹን ላይ ደግሞ ችግሩን ለራሱ ብቻ ደብቆ ከሕይወት ጋር ግብግብ ላይ ነው፡፡ መንገድ ላይ ብቻውን እያወራ በምሽት አገኘኹት፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን አላውራው...
ኹላችንም የዚህ ምስኪን ልጅ ሕይወት ይመለከተናል ብዬ አስባለኹ፡፡ ቢቻልና ምስሉን በሚዲያ ለቀን ዕርዳታ ብናሰባስብለት በወደድኹ፤ ግን እሱ እምቢኝ አለ፡፡ በዚህ ልክ እንኳ ተጨኜው እንጂ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ለማንኛውም የምንችለውን ብናደርግና አንድን ሰው ወደ ሕይወት ብንመልስ ከአላህ ዘንድ እናገኘዋለን፡፡
وَمَا تُقَدِّمُوا لأنْفُسِكُمْ مِنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِنْدَ اللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا
የንግድ ባንክ ኣካውንት
1000370662553
ዓብዲ ሰዒድ
© Eliyah Mahmud
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana