STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Description
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

3 weeks ago
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
3 weeks ago
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
1 month ago

በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ‹‹ከፍተኛ የሙቀት መጠን ነዉ›› ሲል  የዓለም ባንክ ገለጸ🤔

የዓለም ባንክ አደረግኩት ባለዉ ጥናት በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር ነዉ ብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ 2003-2019 በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ወደ 2.5 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎችን ዳታ ሰብስቦ ያገኘዉ ዉጤት መሆኑን ነዉ ይፋ ያደረገዉ፡፡

በትምህርት ዓመቱ ለከፍተኛ ሙቀት የተዳረጉ በተለይ ደግሞ በፈተና ወቅት ከባድ ሙቀት የሚያገኛቸዉ ተማሪዎች ፤ቀዝቃዛ አየር ባለባቸዉ ስፍራዎች ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ሲወዳደር ዉጤታቸዉ በእጅጉ ቀንሶ ተገኝቷል ነዉ ያለዉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖ በተለይ በሰብ-ሰሃራ አፍሪካ አገራት ላይ የበረታ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለዉጡን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት አለመኖራቸዉ ሁኔታዉን እንደሚያባብሰዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የጥናቱ መሰረታዊ ግኝት የሆነዉ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ሙቀት የሚስተናገድባቸዉ ቀናት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እንዲቀሩ የሚያደርግ መሆኑን ነዉ፡፡

ይህም በኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ላይ ወደ 2.28 በመቶ ዝቅ ያለ ዉጤት እንዲመዘገብ እንደሚያደርግ ነዉ፡፡

በጥናቱ ይፋ እንደሆነዉ ግልጽ የሆነ ምክንያት ባይቀመጥለትም ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በሙቀት መጨመሩ ምክንያት የፈተና ዉጤታቸዉ ዝቅ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩም ሴቶች በተሻለ መልኩ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ የሚገኙ እና ለትምህርታቸዉም ከፍተኛ ቦታ ያላቸዉ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡

አሁን ላይ በተለያዩ የአለማችን አገራት ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ የሙቀት መጨመር ምክንያት መሆኑን ማስረጃ አለን ሲሉ በዓለም ባንክ የሪሰርቸሮች ግሩፕ ዋና ተመራማሪ ፓትሪክ ቤህረር ተናግረዋል፡፡

ፓትሪክ ጨምረዉም ከፍተኛ ሙቀት ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በመምህራን የስራ እንቅስቃሴ ላይም የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል ነዉ ያሉት፡፡

ፖሊሲ አዉጪዎች ይህንን ጉዳይ በደንብ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ያሉት ተመራማሪዉ ፤በመማሪያ ክፍሎች ዉስጥ ያለዉን የሙቀት መጠን በማስተካከል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራን መፍጠር አለባቸዉ ብለዋል፡፡

የተሻለዉ አማራጭ እንደየአከባቢዉ የሚለያይ ቢሆንም ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሲሉ የሚጨምሩት ተመራማሪዉ ፤ይህም ተማሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ያልተጋለጡ አከባቢዎች ላይ እጅግ በተሻለ ሁኔታ መማር እንደሚችሉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በ2022 ዘ ጋርዲያን ይዞት በወጣዉ አንድ ጽሁፍ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር በጥራት እንዳናስብ በማድረግ ፣ የማሰላሰል እና የማመዛዘን ችሎታችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖረዉ ስህተት የመስራት ዕድላችንን ከፍ ያደርገዋል ሲል አስታዉቆ ነበር፡፡

@NATIONALEXAMSRESULT

2 months, 2 weeks ago
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባር የ1ኛ ዓመት …

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባር የ1ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የመጨረሻ ምዝገባ ቀን ዓርብ የካቲት 08/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምዝገባ ኦንደማይኖር ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

2 months, 2 weeks ago

#repost

የመውጫ ፈተና ከረቡዕ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ፈታኝ መምህራን እና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ ፈተና መፈተኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተፈታኝ ተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከመተኛ ክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጅ ወይም ሲያስኮርጅ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ ከ15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

- የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው የሰበሰበው።

ለመላው ተፈታኞች መልካም ፈተና ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል !

(መልዕክቱ በባለፈው ዓመት የፈተና ወቅት የተዘጋጀ እና በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተለጠፈ ነው)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

2 months, 2 weeks ago

#ExitExam

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ከረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ቲክቫህ ፤ ከዩኒቨርሲቲዎች ያገኘው የተሻሻለ የፈተናው መርሀ ግብር ከላይ ባለው ፋይል አያይዞታል።

መርሀ ግብሩ እንደሚያሳየው ከሆነ በመጀመሪያው የፈተና ቀን የጤና ተማሪዎች ፈታናቸውን ይወስዳሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

2 months, 2 weeks ago
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
2 months, 2 weeks ago
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
2 months, 3 weeks ago

የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ቀን ጥር 30/2016 ዓ.ም)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

2 months, 3 weeks ago
**የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርቁ የሆኑት ዶ/ር መቅደስ …

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርቁ የሆኑት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ዶ/ር መቅደስ ከነርሰሪ እስከ 12ኛ ክፍል በአዲስ አበባ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ተምረዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ የህክምና ትምህርታቸውን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተከታተሉ ሲሆን የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰርተዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው በማስተማር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የህክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በጽንስና ማህጸን ትምህርት ክፍል ውስጥ የሠሩ ሲሆን የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነውም ሠርተዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን ላለፉት 18 ወራት በዓለም ጤና ድርጅት ዋና መ/ቤት ከፍተኛ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas