ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ተከትሎ ፈተና የሬሚዲያል መግቢያ ነጥብ ገና ያልተገለጸ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
በዘንድሮ የምትምህርት ዘመን ግን ካለፉት ሁለት ዓመታት በቁጥር ያነሰ ተማሪ በሬሚዲያል ማካካሻ ትምህርት እንደሚካተት እና ቀስ በቀስም የሬሚዲያል የመቀበል አቅምን በማሳነስ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቆም ትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትናንትናው ዕለት መግለፃቸው ይታወሳል።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላቻንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 100 ፐርሰንት ተማሪዎችን ማሳለፍ ችሏል።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለተማሪዎች በሙሉ!!!
ለ MSc,MBA , Bsc, BA students from all discipline, !!!!
??????
ለማንኛውም
✍️Thesis MA/MSc
✍️Reaserch BA/BSc
✍️Proposal
✍️Title selection
✍️Research editing
✍️Power point preparation
✍ spss software training
✍️Term Paper
✍️Case Study
✍️Assignment any
✍️Article Review
✍️Data Analysis
✍️Seminar Paper
✍️Feasibility Study
✍️Business Plan
✍️Project
? በሚፈልጉት research area በፍጥነትና በጥራትበማስተማር/ ስልጠና መስጠትና በሚፈለገዉ ጊዜ አጠናቆ በመስራት ከማንም ልዪ ያደርገናል::
ፍጥነታችን መለያችን ነው
ለእገዛ??@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው?
ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልቷል፡፡
ቀደም ሲል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ እጣፈንታ እንደገጠመው መዘገባችን ይታወሳል፡፡
አብዛሃኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ችግር እንደገጠማቸው በዚህ ዘገባችን ስር ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡
ለማሳያነትም ድላ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረትና በምግብ ግብኣት ችግር ተማሪዎቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡
ዲላ ዩኒቨርስቲው በለጠፈው ማስታወቂያ እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት አስቆጥሯል ብሏል፡፡
ተማሪዎቼ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ አትክልት እንዲመገቡ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡
በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን ጠይቂያለሁ ያለው የድላ ዩኒቨርስቲ የአቅርቦት ሁኔታው እስከሚስተካከል በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል፡፡
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ‹‹ከፍተኛ የሙቀት መጠን ነዉ›› ሲል የዓለም ባንክ ገለጸ?
የዓለም ባንክ አደረግኩት ባለዉ ጥናት በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር ነዉ ብሏል፡፡
ከፈረንጆቹ 2003-2019 በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ወደ 2.5 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎችን ዳታ ሰብስቦ ያገኘዉ ዉጤት መሆኑን ነዉ ይፋ ያደረገዉ፡፡
በትምህርት ዓመቱ ለከፍተኛ ሙቀት የተዳረጉ በተለይ ደግሞ በፈተና ወቅት ከባድ ሙቀት የሚያገኛቸዉ ተማሪዎች ፤ቀዝቃዛ አየር ባለባቸዉ ስፍራዎች ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ሲወዳደር ዉጤታቸዉ በእጅጉ ቀንሶ ተገኝቷል ነዉ ያለዉ፡፡
እንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖ በተለይ በሰብ-ሰሃራ አፍሪካ አገራት ላይ የበረታ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለዉጡን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት አለመኖራቸዉ ሁኔታዉን እንደሚያባብሰዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
የጥናቱ መሰረታዊ ግኝት የሆነዉ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ሙቀት የሚስተናገድባቸዉ ቀናት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እንዲቀሩ የሚያደርግ መሆኑን ነዉ፡፡
ይህም በኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ላይ ወደ 2.28 በመቶ ዝቅ ያለ ዉጤት እንዲመዘገብ እንደሚያደርግ ነዉ፡፡
በጥናቱ ይፋ እንደሆነዉ ግልጽ የሆነ ምክንያት ባይቀመጥለትም ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በሙቀት መጨመሩ ምክንያት የፈተና ዉጤታቸዉ ዝቅ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩም ሴቶች በተሻለ መልኩ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ የሚገኙ እና ለትምህርታቸዉም ከፍተኛ ቦታ ያላቸዉ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡
አሁን ላይ በተለያዩ የአለማችን አገራት ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ የሙቀት መጨመር ምክንያት መሆኑን ማስረጃ አለን ሲሉ በዓለም ባንክ የሪሰርቸሮች ግሩፕ ዋና ተመራማሪ ፓትሪክ ቤህረር ተናግረዋል፡፡
ፓትሪክ ጨምረዉም ከፍተኛ ሙቀት ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በመምህራን የስራ እንቅስቃሴ ላይም የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል ነዉ ያሉት፡፡
ፖሊሲ አዉጪዎች ይህንን ጉዳይ በደንብ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ያሉት ተመራማሪዉ ፤በመማሪያ ክፍሎች ዉስጥ ያለዉን የሙቀት መጠን በማስተካከል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራን መፍጠር አለባቸዉ ብለዋል፡፡
የተሻለዉ አማራጭ እንደየአከባቢዉ የሚለያይ ቢሆንም ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሲሉ የሚጨምሩት ተመራማሪዉ ፤ይህም ተማሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ያልተጋለጡ አከባቢዎች ላይ እጅግ በተሻለ ሁኔታ መማር እንደሚችሉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በ2022 ዘ ጋርዲያን ይዞት በወጣዉ አንድ ጽሁፍ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር በጥራት እንዳናስብ በማድረግ ፣ የማሰላሰል እና የማመዛዘን ችሎታችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖረዉ ስህተት የመስራት ዕድላችንን ከፍ ያደርገዋል ሲል አስታዉቆ ነበር፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባር የ1ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የመጨረሻ ምዝገባ ቀን ዓርብ የካቲት 08/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።
ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምዝገባ ኦንደማይኖር ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago