Adebabay Media

Description
በወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ፤ ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። በFacebook/YouTube (@adebabaymedia) ይመልከቱን። www.adebabay.com
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago

የቤተ ክህነቱ እና የቤተ መንግሥቱ ፈተናዎች በ"የዖዛ ስብራት" መጽሐፍ ውስጥ || ውይይት ከመጽሐፉ ደራሲ ከመጋቤ ጥበብ ሳሙኤል ግዛው ጋራ

@followers Sami Gizaw Abel Gashe

======
የዛሬ ረቡዕ ዝግጅታችን ሰዓት
========
8 pm EST (በዲሲ ሰዓት)
5 pm PST (በካሊፎርኒያ ሰዓት)

1 month, 3 weeks ago

🔴 LIVE 🔴

1 month, 3 weeks ago

ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከዶ/ር ይርጋ ገላው ጋራ ጥሩ ውይይት ይኖረናል። የምትችሉ እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ። ዶ/ር ይርጋ ዓለም አቀፍ ሽልማት ያገኘ ገጣሚ፣ ተመራማሪና መምህር ነው::

4 months, 2 weeks ago

ቀብረዋቸዋል፡፡
እንደማጠቃለያ
በአጠቃላይ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም መጋቢት ፳፬ ቀን የፅንሰታቸውን፤ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የልደታቸውን፤ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት፤ ጥር ፬ ቀን የስባረ ዐፅማቸውን (እግራቸው የተሰበረበትን)፤ ግንቦት ፲፪ ቀን የፍልሰተ ዐፅማቸውን፤ ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች፡፡
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎታቸውን በረከታቸው፣
በመላው ሕዝበ ክርስቲያን አድሮ ይኑር፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ዋቤ መጻሕፍት
✍️ ገድለ ተክለ ሃይማኖት፡፡
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር፣ ነሐሴ ፳፬ ቀን፡፡
✍️ Encyplopedia of Aethiopica Vol.4
✍️ ኢትዮጵያዊው ሱራፌ

4 months, 2 weeks ago

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት (ነሐሴ ፳፬)
አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
=======
የጻድቁ አባታችን ሥዕሎች በኢትዮጵያ እና በቅብጣውያን (Copts) አሣሣል
=====

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዲስ ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ
++++
(በመ/ር ጌታቸው በቀለ)
ሐዲስ ሐዋርያ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍታቸው ነሐሴ ፳፬ ቀን በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
ሐዲስ ሐዋርያ
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን በቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ፲፭ ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፤ በ፳፪ ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ጌርሎስ (ቄርሎስ) ተቀብለዋል፡፡
በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን ሔዱ፡፡ በዚያች ዕለት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጦላቸው፤ ከአውሬ አዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደ ተመረጡ፤ አጋንንትን የማውጣት፣ ተአምራትን የማድረግ ሥልጣን እንደ ተሰጣቸው፤ ስማቸውም “ተክለ ሃይማኖት” እንደሚባል፤ ትርጓሜውም “ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ” ማለት እንደ ኾነ አበሠራቸው፡፡ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ” በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው ጻድቁ አባታችን በሀገራችን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ ብዙ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡
ደብረ ሊባኖስ
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በደብረ ሊባኖስ ገዳም (ደብረ አስቦ ዋሻ) በመግባትም ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን በግራ በአጠቃላይ ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾም፣ በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ በ፺፪ኛ ዓመታቸው ጥር ፬ ቀን አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታትም ፳፪ ናቸው፡፡ ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ያለ ምግብና ያለ ውኃ በትኅርምት ሌሊትና ቀን እንደ ምሰሶ ጸንተው በትጋት ለሰው ዘር ዅሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡
ቃል ኪዳን

ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ የሚያልፉበት ቀን ተቃረበ፡፡ በዚህ ጊዜ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደ እርሳቸው በመምጣት የሚያርፉበት ዕለት መድረሱን ነገራቸው፡፡ በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና

7 months, 1 week ago

በመምህራን አምላክ ተማጽነናል
+++++++++++++++
(ቀሲስ ስንታየሁ አባተ እንደጻፉት || Kesis Sintayehu Abate Reta )

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ መምህራን በጉባኤ ቤት ለደቀ መዛሙርት በልባቸው ስፋት በእምነታቸው ጽናት መሠረት ብቻ ሊነገር የሚገባውን ምሥጢረ ሥጋዌ በማኅበራዊ ሚዲያ መከራከርያ አድርገው ጎራ ከፍለው ሲከራከሩ ማየት ከመለመድም አልፎ ስጋት እየሆነ ነው።

አንድ ሰው የተማረውን ሁሉ ተማሪዎቹን ወይም ሰማዕያኑን ሳያገናዝብ ማስተማር ከጀመረ ፍጻሜው ለራሱም ለሚሰሙትም የከፋ ይኾናል። ክቡር መልአከ ሰላም ኃይለ ኢየሱስ ከበደ የሚባሉ ሊቅ ለአእንደዚህ ዓይነት መምህራን “ዐይን የሚያየውን መሬት ሁሉ እግር አይረግጥም። ዐይን ካየው የመሬት ክፍል እግር መርገጥ ያለበትን ልብ ይመርጥለታል። መምህርም የተማረውን ያወቀውን ሁሉ በአደባባይ ላገኘው ሁሉ አያስተምርም። የተማሪዎቹን መጽሐፉን የሚያነብቡ ምእመናንን የእምነት ዳራ ማወቅ አለበት። ያለበለዚያ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል” ይላሉ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቹና የረቀቀውን ምሥጢር መሸከም ላልቻሉተ “ወተት ጋትኋችሁ” ያለው መምህራን በራሳቸው የእውቀት ደረጃ ቆመው ሳይሆን በተማሪዎቻቸው ደረጃ ዝቅ ብለው በሂደት ወደ ልዕልና እንዲያደርሷቸው አርአያ ለመስጠት ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ “እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።” ያለው ተጽፎ በመልእክት የሚነገር እንዳለ ሁሉ ገፅ ለገፅ ተገናኝቶ በርጋታ የተማሪዎችን ደረጃ እየለኩ የሚነገር ስላለ ነው። 2ዮሐ 1፣12።

አንድ መምህር በአንድ ትልቅ የቤተ ክርስቲያናችን የነገረ መለኮት ኮሌጅ ሐዲሳትን ያስተምሩ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ የመጡት ከተለያዩ የሀገራችን ጠረፋማ አካባቢዎች ጭምር ነበር። የመጻሕፍት፣ የቅኔ፣ የድጓ፣ የአቋቋም የመሳሰሉ መምህራን ነበሩ። ገና ውዳሴ ማርያም ቁጥር ያልዘለቁ ደካሞችም ነበሩ። መምህሩ ለእነዚህ ሁሉ በአንድ ክፍል “ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ” እያሉ ትርጓሜውን ያወርዱት ጀመር።

በአጋጣሚ አንድ በመጻሕፍት መምህርነት ጥንቅቅ ያሉ ሊቅ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ተማሪዎቹን ሊጎበኙ ወደ ክፍሉ ገብተው መምህሩ የሚያወርዱትን የቀዳሚሁ ቃል ትርጓሜ ያዳምጣሉ። ተማሪዎቹን አይዟችሁ ብለው ያበረታቱና መምህሩን ወደ ውጪ ይዘዋቸው ይወጣሉ። ከዚያም በኃይለ ቃል “አንተ ጨካኝ ለመላእክት ሳይቀር የረቀቀውን ነገረ ቃልን እንዴት እንዲህ አድርገህ ገና ውዳሴ ማርያም እንኳ በቅጡ ማድረስ ላልቻሉ ደቀ መዛሙርት ታሸክማለህ? እያስተማርክ ሳይሆን እየሰበርኻቸው ነው” ብለው ገሠጿቸው። እንዴት ማስተማር እንዳለባቸውም በጥንቃቄ ነገሯቸው።

እባካችሁ በማኅበራዊ ሚዲያ ነገረ ሃይማኖትን የምታስተምሩ መምህራን ለሚሰሟችሁ፣ ለምንሰማችሁ፣ ለምናነባችሁ በመምህራን አምላክ ስም አስቡልን። መጽሐፍ “ከእናንተ መካከል ብዙዎች መምህራን አይሁኑ” ያለውንም እያሰባችሁ እስቲ አንዳንዴ ዝም በሉ። ለሁሉ ጊዜ አለው። ለሁሉ ስልት አለው። የተማረ ሁሉ አስተማሪ አይሆንም። የተማረ ሁሉ በማንኛውም ጊዜ አያስተምርም። እንደ እኔ ያሉ ደካሞችን በቃል እንዳታሰናክሉ የወፍጮውን ድንጋይ አስቡ።

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን።

7 months, 1 week ago

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ
ጉባኤ መግለጫ
++++++

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

  2. በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤

  3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

  4. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡

በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስመልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል።

  1. የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

  2. በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

  3. ረ ሰነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቡና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

  4. በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡

  5. ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

  6. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

  7. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana