ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
✍️ዋጋሽ ከእግዚአብሔር ነው‼️ ክፍል ሁለት 2️⃣**
➫ስኬታችሁ ወደዚህ ዓለም የመጣችሁበትን #ዓላማ_መኖር እንጂ ባገኛችሁት ቦታ ሁሉ #መስሎ_መኖር አይደለም።
➫የምትኖሩለት ብቻ ሳይሆን የምትሞቱለት አላማ ከሌላችሁ ለዚህ አለም አስፈላጊ ሰዎች አይደላችሁም።
🔵 ሁሌ የሚያስፈልገን ጨዉ እንጂ ወርቅ አይደለም።
📌ወርቅ ሁሌም አያስፈልገንም ብለን ዋጋዉን አናረክሰዉም፥#ወርቅ_በጊዜዉና_በቦታዉ ሲሆን ነዉ #ዉድነቱን የምናዉቀዉ።
📌ሁሌ ስለሚያስፈልገን የጨዉን ዋጋ ዉድ አናደርገዉ፤ ለህይወት ማጠፈጫነት ካሉን ግብአቶች አንዱ ነዉ።
ሁሉም በቦታቸዉና በጊዜያቸዉ ዋጋቸዉን ይተምናሉ።
➫ወርቅን በእንጀራ እንደማትበሉት ሁሉ ጨዉንም ጌጥ አታደርጉትም።
አለ ቦታችሁ ስትገኙ ዋጋችሁን ሰዎች ያወርዱታል፣ አለ ጊዜያችሁም ከተገኛችሁ ቦታ አይኖራችሁም።
📌በትክክለኛዉ ጊዜና ቦታ ስትገኙ #ትክክለኛ_ክብር_ይሰጣችኃል።
“ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።”
— ዮሐንስ 6፥14
“ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን #አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥15-16
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
➻ዋጋሽ ከእግዚአብሔር ነው¶¶
ክፍል አንድ1️⃣**
🔵 በፍፁም ተሸናፊ ሆነሽ አትገኚ።
አንቺን ደካማ ያደረገሽ ጭንቅላትሽ ዉስጥ የተዘራዉ የአልችልም ባይነት ዘር እንጂ እንደማትቺ የሚገልፅ ቃል እግዚአብሔር አልነገረሽም።
📌#ራስሽን_ሁኚ፣ የተፈጠርሽበት አላማ ተረጂ፤ ህልምሽ ቤት፥ መኪና፥ ወርቅ፥ ዝና፥ መብለጭልጭና ፋሽን አይሁን ለምን እንደተፈጠርሽ የገባሽ ቀን ያለሽ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ዉድ መሆንሽ ይገባሻል።
➫እኩል ነኝ፣ ተራ አይደለሁም፥ እችላለሁ ስላልሽ ምንም አታመጪም ማን እንደሆንሽና ለምን እንደተፈጠርሽ እስካልገባሽ ድረስ ሴትን በተመለከተ የሚነገረዉ ሁሉ አንቺን አይገልጥም። ስለ አንቺ እግዚአብሔር ያለዉን እዉነት ብቻ ተረጂ፤ ሳትናገሪ ትሰሚያለሽ፥ ሳትፈልጊ ታገኚያለሽ።
📌 ዋጋሽን ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰዉም ከአለም #አትጠብቂ።
🔵 የህይወታችሁ ስኬት መሆን ያለበት ለተፈጠራችሁለት እውነት መኖር እንጂ በምታገኙት ዕድልና በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዘፈቅ አይደለም።
➫የሆናችሁትን ባለመሆን ማርፈድ ኪሳራ ያስከትላል።
📌የሆናችሁትን ሁኑና ነጋችሁን በበለጠ የተሻለ ለማድረግ ትጉ እንጂ ዛሬ ባገኛችሁት ስኬት አትሟሟቁ፥ በገጠማችሁም ችግር ተስፋ አትቁረጡ እላያችሁ ላይ ያለዉን አራግፉና ወደ ፊት ፍጠኑ።
✍የሆናችሁትን አለመሆን ያለሆናችሁትን እንድትሆኑና ከተፈጠራችሁበት ዓላማ ውጪ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል።
📌እግዚአብሔር ናችሁ ያላችሁን ጥሪ ትታችሁ ሰዎች ሁኑልን በሚሉአችሁ ተስባችሁ የኪሳራ ሳጥን ውስጥ እዳትገኙ ተጠንቀቁ።
➫ምክንያቱም ኢየሱስ የዓለም ቤዛ ለመሆን መጥቶ ንጉስ ሁንልን ብለውት ነበርና።.......
➻ይቀጥላል
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
**“..ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥8 (አዲሱ መ.ት)
✍️ሰይጣን እንዳለ እና እንደሚዋጋን ነፍስ ካወቅኩ ጊዜ ጀምሮ የማውቀው እውነት ቢሆንም ትናንት ማታ ግን ሰይጣን በእርግጥ እንዳለ አወቅኩ። መንፈሳዊ አካል ያላቸው መናፍስት Literally በዙራያችን አሉ። የተሸነፉ እና ስልጣን የሌላቸው አድርገን ስለሳልናቸው ብዙ ትዝ አይሉንም። እርግጥ ነው የተሸነፉ ቢሆንም አሁንም ችግር የመፍጠር አቅም አላቸው። ጌታ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ምን ያህል ለጨለማው ኃይላት ንቁ እንደነበሩ ማስተዋል ቀላል ይመስለኛል።
➻የሚታዩ ነገሮች ሁሉ ከማይታየው አለም የመጡ ናቸው። የማይታየው አለም ከሚታየው አለም በላይ real ነው። የማይታየው አለም ላይ በየሰከንዱ ሽርፍራፊ ብርቱ ጦርነት አለ። የማይታየው አለም ነገሮችን ወደሚታየው አለም ለመውለድ ምጥ ላይ ነው። ውግያችን ከስጋ ለባሽ ጋር አይደለም የተባለው ቃል በእርግጥ እውነት ነው። የጨለማው አለም ኃይላት ስልጣናት ገዢዎች አሉ።
🤲 ጸሎት ጸሎት ጸሎት‼️ ✍️Naum
♻️Share♻️Join♻️
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
**“እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፤ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤”
— 1ኛ ሳሙኤል 1፥28
ለሃና ሳሙኤል ከጣውንቷ ማስቆጣትና ብስጭት ያረፈችበት የፅኑ እንባዋ ፍሬ የፅሎቷ ውጤት በልቧ ጌታዋን በማውራቷ ብዛት እንደሰከረች ከተቆጠረችበት መንደር ስሟ የተቀየረበት ማስረሻዋ በሀዘኗኗ በጭንቀቷ ብዛት እንደ ምናምንቴ በታየችበት ስፍራ የስለቷ ደስታ በእግዚአብሔር የመታሰቧን ማሳያ ቢሆንም ከእግዚአብሔር የተቀበለችውንን ሳትሰስት የሰጥታዋለች ለእኔ ይሁነኝ ብላ ወደ ኋላ አልሸሸገችውም እናተዬ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ሳታስቀሩ ስጡት እሺ ከእሱ አትሸሸጉ አይ ካላችሁም ለራሳችሁ ጥቅም ሁሉ ታጣላችሁ‼️
✍️Samri Getu
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
**“ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?”
-- ኢዮብ 9፥4
አንዳንዴ በህይወታችን ከባድ በምንላቸው ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ፣ እምነታችን በገጠመን ፈተና ሲፈተንብን፣ እንደው ከእግዚኣብሔር ጋር ተሟግተን ተሟግተን ሊ'ረዳን ያልቻለ ሊመስለን ይችላል። ልክ ኢዮብ እንዳለው፦
“ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!”-ኢዮብ 6፥2
ኢዮብ ማንም የተረዳው ሳይመስለው ሲቀር ይህን👆 አለ። ያለበት ሀዘን እና ትካዜ በመመዘኛ ተመዝኖ በቁጥር መጠኑ ቢታወቅለት ተመኘ።
ክርስትናችን በእግዚኣብሔር ጠቢብነት እና በሃይሉ ታላቅነት ላይ ያልረጋ፣ እርግት ያላለ እና ያላረፈ እንዲሁም ያልተደላደለ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በብርቱ መፈተናችን የማይቀር ነው። በእግዚኣብሔር ሁሉን አዋቂነት፤ በእርሱ ሁሉን ቻይነት ላይ ስር የሰደደ መደላደል እንዲኖረን ዕለት ዕለት በፊቱ የበረታን እንድንሆን ጌታ ይርዳን!
ኢዮብ በስተመጨረሻ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው።”.. እንዳለ፣ በራሳችን ወይም በሰው ማስተዋል ላይ ተደግፈን ራሳችንን ሳናገኘው በፊት በእግዚኣብሔር ኃይል እና ማስተዋል ላይ መረጋጋት፣ መደላደል ይሁንልን። አሜን!
“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤”
ምሳሌ 3፥5
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨
👇👇👇ይቀላቀሉን👇👇👇**@jesusofscriptures@jesusofscriptures
በዘመናችን በጣም የምንወደው ፣ የምንሳሳለት፣ ባላጣነዉ ከእኛ ባይለየን ብለን የምናስበው ነገር ምንድነው .....? ያን የምንሳሳለትን ነገርስ እግዚአብሔር ይፈልገዉ ይሁን ..? ብቻ እርሱን ደስ ካለዉ ፤ ወዶ ስጡኝ ካለን ያንን የምንወደውን ነገር፤ በህይወታችን ርካሽ የሆነዉን ሳይሆን ዉድ ነገራችንን ለእግዚአብሔር መስጠት እና ማስገዛት ይሁንልን ።🙏*😭
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇*👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
"አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 63:16)
“ልክ እንደ ማርያም”
ሰላም😍 ሲስተርስ እንዴት ናችሁ?
³⁸ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።
…
⁴¹ ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤
⁴² የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።”
ሉቃስ 10 (አዲሱ መ.ት)
➻ከአንድ ጥያቄያችን ልጀምር ከመንገድ ወደ ቤታችሁ ለገባ እንግዳ ምን አይነት መስተንግዶ ታድርጉለታላችሁ? እንዴት ትቀበሉታላችሁ? የሚበላዉን ሰርታችሁ ታቀርቡለታላችሁ? ወይስ እሱ እጅ ላይ ያለው ይሻለኛል ብላችሁ እግሩ ስር ቁጭ ትላላችሁ?
➻ማርታ ከመንገድ ወደ ቤቷ የመጣው ኢየሱስ ምናልባት እርቦት ይሆናል ደግሞ ምትወደው ኢየሱስ ነው እና ቤቷ ሲመጣ ወደ ጓደዋ ገባች ልታሳረፈው ከዛ በምትሰራው ምግብ ልታጠግበው ፣ ልታስደስተው አሰበች ። እንደ አንድ ሰው ሚጠበቅባትን ነው ያደረገችው እኔ የገረመኝ የማርያም ነው ቤቷ ለመጣ ከመንገድ ለመጣ እንግዳ ልታስተናግደው ሲገባ እሷ ግን እግሩ ስር መቀመጥ መረጠች።እሷ ከምታቀርበው ይልቅ እሱ ላይ ያለውን መረጠች የማርያም ደንቆኛል እየሱስን እንዴት አይታው ነው?
➥በማርታና በማርያም መካከል ያለው ልዩነት ኢየሱስ ቤታቸው የመጣበትን ምክንያት የተረዱበት መንገድ ይመስለኛል። ለማርታ ኢየሱስ የቅርብ ሰው ከመንገድ ደክሞት መጥቶ እሷ በምትሰጠው ምግብም ምታስደስተው ነበር የመሰላት።
➥ለማርያም ግን ኢየሱስ እንደዛ አልነበረም ከሩጫ ይልቅ መቀመጧን፣ ከስራው ይልቅ ከእሷ ጋር ያለን ህብረት ፈልጎ ፣እንጀራ ሳይሆን ህይወት ሊሰጣት ፈልጎ እንደሆነ ገብቷት ነው የሆነ ነገር ከማቅረብ ይልቅ ኢየሱስ ጋር መቅረብን የመረጠችው።
➥ቤታችን የገባው ኢየሱስ ከእኛ አንዳች ነገረ ፈልጎ ሳይሆን ከኛ ጋር ህብረትን ለመመስረት ፈልጎ ነው። ስለዚህ አንድ ነገር ልበላችሁ ኢየሱስ ከሩጫችን በፊት እንድንቀመጥ ይፈልጋል ከእርሱ ጋር እንድንቆይ እንድንሰማው ይሻል።
➥ **አንድ ነገር ብያችሁ ልጨርስ ኢየሱስ በምናቀርብለት ሳይሆን በመቅረባችን ይደሰታል። አብዝተን መጠጋት ይሁንልን።ተባረኩ
✍️ሀና
▷ይ🀄️ላ🀄️ሉን◁
👇👇👇👇👇
✨@lebamsetministry123✨
✨@lebamsetministry123✨**
"ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ#ጌታ_ልብዋን_ከፈተላት።"
(የሐዋርያት ሥራ 16:14)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago