@Nasser

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago
1 month, 3 weeks ago
@Nasser
2 months ago
@Nasser
3 months ago
@Nasser
3 months, 1 week ago
ኢሬቻ

ኢሬቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?

እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።

ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።

መውሊድ፣ ገና፣ ፋሲካ በዓል "ቢድዓህ" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ ነው "ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

3 months, 4 weeks ago
4 months, 1 week ago
***👍***ታላቅ የማንቂያ ሙሃደራ

👍ታላቅ የማንቂያ ሙሃደራ

🛖ይህ ቤት ሊፈርስ ነው

🎯የተከበረ ባል የሚያደርጉዎት 10 ነጥቦች

🗓መስከረም 1

ከአስር በኋላ

📌ኢማሙ አህመድ መስጅድ

⚠️ለወንዶች ብቻ

https://t.me/terbiyeh

4 months, 2 weeks ago
@Nasser
5 months ago
@Nasser
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana