Ministry Tricks

Description
ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪወች የተከፈተ ቻናል!!!


You tube

https://youtube.com/@ministry_tricks?si=wz5tL7pnHHuQ82ws
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 23 hours ago

Last updated 2 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 6 days ago

3 months ago

ትምህርት የሚኖረው ለግማሽ ቀን ብቻ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ነገ በቀን 16/1/2017 ዓ.ም የደመራ በዓል ስለሚከበር በሁሉም የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት የሚኖረው ለግማሽ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ መልካም በዓል❗️****

@MINISTRY_TRICKS

3 months, 1 week ago
[***🏛***](https://t.me/Ministry_tricks)በ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት የሚጀመርባቸው **12 …

🏛በ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት የሚጀመርባቸው 12 የሙያ ዓይነቶች
👉እንጨት ስራ፣
👉ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣
👉 የማህበረሰብ ጤና፣
👉 ጋዜጠኝነት፣
👉ግብርናና የእንሰሳት እንክብካቤ፣
👉የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ዳንስ እንደሚገኙበት በሰነዱ ተመልክቷል። ትምህርት ቤቶች አርባውንም የትምህርት ዓይነቶች የግድ ከፍተው ያሰለጥናሉ ማለት እንዳልሆነና የሚከፈቱት የትምሕርት ዓይነቶች በተማሪዎቻቸው ፍላጎትና ዝንባሌ ላይ የተመሰረት እንደሚሆን መረጃው ይጠቁማል።

3 months, 1 week ago
[***📘***](https://t.me/Ministry_tricks)**ትምሕርት ሚንስቴር በ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ …

📘ትምሕርት ሚንስቴር በ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ትምሕርት ሥልጠና ሊጀምር ነው

ትምሕርት ሚንስቴር በመጪው 2017 ዓ.ም የትምሕርት ዘመን በመላው አገሪቱ ከ 11ኛ ክፍል ጀምሮ የቴክኒክና ሙያ ትምሕርት ሥልጠና መስጠት ሊጀምር ነው። ሰነዱ ላይ እንደተብራራው ለተማሪዎቹ በስምንት የትምህርት ክፍል ስር ካሉ አስራ ሁለት የትምህርት አይነቶች አንዱን መርጠው እንዲማሩ እንደሚደረግ ይገልጻል።

ሆኖም የየአካባቢዉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ፣ ትምህርት ቤቶች ያሉበት ቦታ፣ለሥልጠናዉ የሚያስፈልጉ ግብአት አቅርቦት ዉስንነት ሁሉንም የሙያ ዓይነቶች በሁሉም ትምህርት ቤቶች በአንድ ጊዜ ለመጀመር የማያስችል በመሆኑ፣ አጀማመሩን በተመለከተ አሰራር መዘርጋት እና በሂደት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዋዜማ የደረሳት ሰነድ ላይ ተመላክቷል። ትምህርቱን ለማስጀመር ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከክልል ክልል እንዲሁም ከትምህርት ቤት ትምህርት ቤት የሚለያይ በመሆኑ፣ እንደየአካባቢው ሁኔታ ሥልጠናው እንደሚሰጥም መመሪያው ያትታል።

በመሆኑም በቀላሉ ሊሟሉ የሚችሉትን የትምህርት ዓይነቶችን ግብዓት በማሟላት በቀጣዩ ዓመት ትምህርቱ እንደሚጀመር ከሚንስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በመጀመሪያው ዙር የሚመረጡ የሙያ አይነቶች በትምህርት ቤቱ በቀላሉ ለመጀመር የመማሪያ ቁሳቁሶችን ማግኘት፣ ወይም ማሟላት የሚቻልበት እና መምህራንን በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት እንደሚሆኑ፣በሁለተኛው ዙር የሚመረጡ የሙያ አይነቶች በትምህርት ቤቱ አንድ ዓመት የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና መምህራንን ለማሟላት ጊዜ የሚጠይቁ ሲሆኑ፣በሶስተኛው ዙር በአንድ ትምህርት ቤት ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችም ሆኑ መምህራን ለማሟላት ጊዜ እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ እንደሆኑ በሰነዱ ተብራርቷል።

በእያንዳንዱ ዙር በትምህርት ቤት ደረጃ የሚመረጡ እና ለተማሪዎች ለምርጫ የሚቀርቡ የሙያ ዓይነቶች ብዛት እንደትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ፍላጎት፣ ብዛት፣ የመማሪያ ቁሳቁሶች እና መምህራንን የመሟላት ሁኔታን ሊለያይ እንደሚችልም ዋዜማ ከሰነዱ ተመልክታለች።

በ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት የሚጀመርባቸው 12 የሙያ ዓይነቶች እንጨት ስራ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የማህበረሰብ ጤና፣ ጋዜጠኝነት፣ ግብርናና የእንሰሳት እንክብካቤ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ዳንስ እንደሚገኙበት በሰነዱ ተመልክቷል። ትምህርት ቤቶች አርባውንም የትምህርት ዓይነቶች የግድ ከፍተው ያሰለጥናሉ ማለት እንዳልሆነና የሚከፈቱት የትምሕርት ዓይነቶች በተማሪዎቻቸው ፍላጎትና ዝንባሌ ላይ የተመሰረት እንደሚሆን መረጃው ይጠቁማል።

የትምህርት ሚንስቴር፣የሥራና ክህሎት ሚንስቴር፣የክልል ትምህርት ቢሮ፣የዞን እና የክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያዎች፣የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ራሳቸው ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሳካት በየደረጃው ያለባቸውን ዝርዝር ኃላፊነትም ዋዜማ ከመመሪያ ተመልክታለች። በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት በልዩ ሁኔታ ድጋፍና ትብብር ሥልጠናውን መስጠት ለሚጀምሩ ትምህርት ቤቶች እንዲያደርጉ መመሪያ ያዛል።

መመሪያው እንደሚያትተው ትምህርት ሚንስቴር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ባስጠናው የፍኖተ ካርታ ጥናት መሠረት፣ አጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርቱ ሀገር በቀል እውቀት፣ የሙያና እና የግብረገብ ትምህርትን ያላካተተ መሆኑን አመላክቷል፡፡ በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን በአነስተኛ ደረጃ ለሥራ ብቁ ለማድረግ፣ እንዲሁም የተወሰኑትን ለከፍተኛ ትምህርት ለማብቃት ዓላማ የተቀረፀ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጨርሰው ወደ ሥራ ሲሰማሩ አይታይም ብሏል ሰነዱ፡፡

በዚህም ምክንያት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የሚጨርሱ ወጣቶች መሠረታዊ እውቀት የጨበጡ ነገር ግን ሥራ የማይፈጥሩ እና የተማሩ ሥራ አጦች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ሲል ያለፈውን የትምህርት ፖሊሲ ኮንኗል፡፡ ይህን ችግር በመሠረታዊነት ለመቅረፍና ሥራ ፈጣሪ ዜጐችን ለማፍራት እንዲቻል አዲሱን የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ማርቀቅ አስፈላጊ ሆኖ ተግኝቷል ተብሏል። #ዋዜማ

4 months, 3 weeks ago

የድሬዳዋ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት

የድሬዳዋ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡ ተማሪዎች ከታች ባለው ሊንክ አማካኝነት መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ውጤት ለመመልከት
https://www.gsix.diresrms.org/View_Result/get_result

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

for students grade 5-8??*??***@Ministry_tricks@Ministry_tricks

4 months, 3 weeks ago

#Update

ዌብሳይቱ በአሁኑ ሰዓት ለሁሉም ተማሪዎች በመስራት ላይ ይገኛል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት ?
https://oromia6.ministry.et/#result

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት ?
@emacs_ministry_result_qmt_bot

የ8ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት ?
https://oromia.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት ?
@emacs_ministry_result_qmt_bot

@MINISTRY_TRICKS@MINISTRY_TRICKS

4 months, 4 weeks ago

ኦሮሚያ - የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ይፋ ሆነ

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡ በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡ በክልሉ የገጠር አካባቢዎች ለተፈተኑ የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 48፣ ለሴቶች 45 ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 45 እና ለሴቶች 42 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የ6ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት https://oromia6.ministry.et/#result
የ6ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት @emacs_ministry_result_qmt_bot

የ8ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት https://oromia.ministry.et/#result
የ8ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት @emacs_ministry_result_qmt_bot

for students grade 5-8??*??***@Ministry_tricks@Ministry_tricks

5 months ago

**የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ - ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።

በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የማለፊያ ነጥብ ለወንድ ተማሪዎች 50%፣ ለሴት ተማሪዎች 47% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45% እንደሆነ ቢሮው አሳውቋል።

በዚህም በአስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከቀመጡ 9,085 ተማሪዎች መካከል 5,673 ተማሪዎች ወይም 62.43 በመቶዎቹ ማለፋቸውን ቢሮው ገልጿል።

ውጤት ለመመልከት ?https://www.geight.diresrms.org/View_Result/get_result for students grade 5-8????**@Ministry_tricks@Ministry_tricks

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 23 hours ago

Last updated 2 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 6 days ago