ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ውሸት ነው በይኝ፡፡
እንደሰው ተወድጄ ተከበሬ የኖርኩበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡ ከሰው ጋር ራሴን አላወዳድርም አልልሽም፡፡ ካልተወዳርኩ ደስታዬ ሀዘኔ ከየት ይመነጫል፡፡ ከሰው አነስኩ ይሉ የለ እናቶች እንኳን፡፡ ከሰው እንዳላንስ ተመክሬ ተዘክሬ ነው ከእናቴ ቤት የተሞሸረኩት ለዓለም የተዳርኩት፡፡
፡
፡
ያለንፅፅር ወደድኩህ ስትይኝ የደነገጥኩት ለዛም ነው፡፡ በምን አቅምሽ ቻልሽው፡፡ አለማወዳደርን አለማነፃፀርን፡፡ ወይስ Ego የሚሉትን ጣጣ እንደገላሽ እጣቢ ደፋሽው?
:
:
ውሸት ነው በይኝ፡፡ እኔን እየነካሽ የሰማሽው ሙዚቃ ምንድነው?
ትዝታ?
ገና መቼ ኖሬና፡፡
አንቺሆዬ?
እኔ ሆዬ የደረጃ ምረኮኛ የፉክክር ባርያ ነኝ፡፡
አምባሰል?
መብሰልሰል መቁሰል ....በነገር መብሰል፡፡
ባቲ?
እንደሆንኩ ታውቂያለሽ መዋቲ፡፡
.
.
ታዲያ ምን ሰማሽ ታዲያ ምን ነካሽና ወድሀለሁ አልሽ፡፡
ተይ አታስክሪኝ፡፡ የኖርኩበትን የእሽቅድምድም ሕይወት ፉርሽ አታርጊብኝ፡፡
እያፎካከርሽ ውደጅኝ፡፡
እያወዳደርሽ አልምጅኝ፡፡
፡
፡
አፈቅርሻለሁ
ከሁሉም አስበልጬ
እናፍቅሻለሁ
ከሁሉም መርጬ
እጠራሻለሁ
አንቺን ብቻ ውጬ፡፡
፡
፡
ያለውድድር ያለንፅፅር መውደድም መወደድም ዓለም አይችልበትም፡፡
አንቺ እንዴት
አልበም ወ ፌስቡክ
∞ ∞ ∞ ∞
በድሮ ዘመን fb ስላልነበር ሰዎች ፎቷቸውን ፖስት የሚያደርጉት አልበም ውስጥ ነበር ፤ ከዛም እንግዳ ሲመጣ ከለስላሳ መጠጥ ጋር ያቀርባሉ ፤ እንግዳውም "ይህንን ፎቶሽን እንዴት እንደወደድኩት!" ብሎ Like እና comment ያደርጋል ፤ የሆነ ሰው ቤቱ ሆኖ ስቅ ካለው mention ተደርጓል ማለት ነው ፤ እንግዳው የሚወደውን ፎቶ ከአልበም ውስጥ ካገኘ share ያደርጋል (ሰርቆ ይወስዳል) ፤ ፎቶ እየተሰረቀባቸው የሚቸገሩ ሰዎችም አልበሙን ቁም ሳጥን ውስጥ ቆልፈው only me ያደርጉት ነበር።ፎቶ አብሮ የተነሳው ሰውዬ ጋር ፀብ ከተፈጠረ ደግሞ block ይደረጋል ፎቶው ከሁለት ይቀደድና የሰውየው ምስል ያለበት ወደ ጋርቬጅ ይጣላል፣አልበም ውስጥ ፎቶ ካለው ጓደኛ ጋር ከተደባበሩ ደግሞ un follow ይደረጋል ፎቶው ላይ ሌላ ፎቶ ይደረባል።
ከግጥም ባሻገር የኔ አይታ 2
በመጀመርያው ክፍል ስለ ውበት ጥቂት ብያለው በዚኛው ክፍል ደሞ ስለወጣትነት ትንሽ ሀሳቤን(እይታዬን) ላካፍላችሁ።
ወጣትነት ልክ እሳት እንደያዘ የክርቢት እንጨት ይመስለኛል።የክርቢት እንጨት እሳትን የመያዝና እሱ እስኪያበቃለት ድረስ ማቆየት የያዘውንም እሳት ሌሎች ነገሮች ላይ ማጋባት ይችላል።ግን አንዳንዴ ሌሎች ላይ ማጋባቱ ይጠቅማል ወይም ይጎዳል ለምሳሌ የእንጨቱን እሳት ከሰል ለማንደድ ከተጠቀም ነው ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ልንሰራበት ምግብ ልናበስልበት ፣ውሀ ልናሞቅበትና ሌሎች ነገሮችን ልንሰራበት እንችላለን በተቃራኒው ያንኑ ክርቢት አላስፈላጊ ነገሮች ላይ እሳቱን ቢያጋባ እንደ መጋረጃና የኤሌትሪክ ገመዶች ያሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ቢያነድ ንብረት ሊያወድም ህይወት ሊያጠፋና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
አንድ ወጣትም ልክ እንደ ክርቢቱ ነው የዛ ወጣት እሳት ማለት በዕድሜው ተፈጥሮ ያደለው ጉልበት፣ጥንካሬ፣ችሎታ፣አቅም፣እውቀት ፣ተሰጥኦ፣ ቅልጥፍና የመሳሰሉት ናቸው። ይህ ወጣት ካስተዋለና መልካም ፍላጎት ካለው እራሱን ከወደደ ካከበረ እነዚህን እሳት የሆኑ የተፈጥሮ ስጦታዎቹን ጠቃሚ ነገሮች ላይ ይለኩሳል አልያ ደሞ ለራሱም ለሌሎችም ክብርና ፍቅር ከሌለው አላስፈላጊ ነገሮች ላይ ይለኩሳል።
እንዴት?ስንል .....
በመጀመርያ ማሰብ ያለብን በወጣትነት ምናደርጋቸው ነገሮች ወይም በህይወት እርሻ ላይ የምንዘራው ዘር ማምሻችንን(በእርጅናህ) እናጭዳለን ዋጋውን አንቀበላለን። በወጣትነት ጊዜህ ጠንክረህ ከሰራህ ለነፍስህም ለስጋህም መልካሙን ካደረክ የስኬትን መንገድ ጫፏን እንኳ ከያዝክ ማምሻህንም ሆነ በዛ እድሜህ የተሻለ ህይወት ለራስህ የመገንባት የመኖር እድልህ ከፍተኛ ነው።ይህ ማለት ያለህን እሳት ጠቃሚ ነገር ላይ ለኮስከው 👍💪ማለት ሲሆን በተገላቢጦሽ ደሞ በወጣትነት ጊዜህ ሱስ፣አላስፈላጊና ተራ ውሎ ፣ተራና ተስፋ ቢስ ጊዜያዊ ግንኙነቶችን ስታሳድድ ከከረምክ ሰው የዘራውን ያጭዳልና የመረጥከውን ህይወት ትኖራለህ መስራትና ጉልበትህን(እሳትህን) መጠቀም በነበረብህ ነገርና ሰዓት ላይ ስላልተጠቀምክ ድህነት ጌጥክ ቁጭትና ፀፀት ስንቅህ ሆነው ወደ ሞት ትጓዛለህ።😣😥 ምክንያቱም "ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው "በጊዜያችን የምንዘራው ነገር እንክርዳድ ይሁን ምርጡን ዘር ለይተን እንወቅ ልክ ክርቢቱ እንደሚያበቃለት አንተም ህይወትክ የሚያበቃበት ቀን አለና ።
እናስተውል እራሳችንን እንመርምር ምን ላይ ነው እሳታችንን እየለኮስን ያለነው የተሳሳተ ነገር ላይ ከሆነ ወደ ነበልባል ሳይቀየር አጥፍተን ሚጠቅመን ላይ እንለኩስ ስህተታችንን ለማስተካከል ዛሬ ተሰቶናል ከዚህ ቀን እንጀምር የተሰጠንን እንጠቀም ዛሬ የፈጣሪ ስጦታችን ነው ነገ ደሞ ተስፋችን ነው ነገ ብለው አቅደው ሞት የቀደማቸው ብዙ ናቸውና እንዳንቀደም
ስሚኝ ቆንጂት የቱ ጋር ነው እሳትሽን የለኮስሽው ?አንተስ ሸበላው?🥰
የገባችሁ👍
ያልገባችሁ 👎
ግራ የገባችሁ 🤷♀️ በመንካት ስሜታችሁን ግለፁ።😁
✍️የተክልዬዋ
3/8/2016
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm
መሄዷ ላይቀር እኔ እንዲህ መታገሌ
ላስቀራት ባልችል እንኳን ላዘገያት ነበር ሀሳቤ
ደቂቃም እድሜ ነው እንዲሉ
ጥቂት አብሪያት መሰንበት ብችል ብዬ....
Join eyalachu....gobez lij nat??
ልጅ በረከት ነው...
መንገድ ዳር ቁጭ ብላ እየለመነች የሚሰጥ የለም፣ ልጅ አሳቅፎኝ መሄዱ ይነሰኝ፣ ልጅ በረከት ነው ይባል የለ፣ ልጅ ስጦታስ ነው ይባል አልነበር ፣ እንደዛ ያልከው አሁን ከወዴት አለህ? ቸግሮኛል ፣ አንጀቴ ተጣብቋል ፣ ደረቅ ጡቷን እየጎተተ ሚያለቅሰውን ልጅ እያባበለች ፣ ከፈጣሪ ጋር ግብግብ በመያዝ ፣
ልጅ በረከት ነው ትለኝ አይደል እያለች ትቀጥላለች
ከጎኗ አንድ ሴት መታ ትቀመጣለች ፣ ያዘለችውን የሀያ አመት ልጅ እያወረደች ። ወገቧ በብዙ ጨርቅ ታስሯል። ላግዝሽ ይሆን አለቻት ክብድ ብሏት፣ አይይ ላም ቀንዷ ይከብዳታል ብለሽ ነው ፣ ምነው ምን ሆኖብሽ ነው? አለቻት ስቅጥጥ እያላት
መናገር አይችልም ፣ መስማት አይችልም ፣ አይንቀሳቀስም ፣ አለቻት ጭንቅላቱን እየዳበሰች ፣
ድንግጥ ብላ ካጠገቧ ያስቀመጠችዉን ልጅ እቅፍ አድርጋ እንባዋን እየዘረገፈች አይ እውነትም ልጅ በረከት ነው አለች...
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana